አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የእጅ ከፍንጅ ወንጀል በኢትዮጵያ ሕግ

👇👇👇👇👇👇👇👇
መግቢያ

ወንጀል የሰዉ ልጆች በህይወት ዘመናቸዉ ከሚያጋጥሟቸዉ ችግሮች መካከል አንዱ ነዉ::
ከብዙዎቹ ወንጀሎች መካከል አንዱ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ነዉ፡፡ ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረ ሰዉ በህግ አግባብ በፖሊስ የሚያዝ ሲሆን የሚያዘዉም በዋናነት በመያዣ በልዩ ሁኔታ ግን ያለመያዣ ነዉ፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርአት ህጉ መሠረት ፖሊስ ተጠርጣሪን ያለፍርድ ቤት መያዣ ትእዛዝ ሊይዝ እንደሚችል የሚያመለክቱት ድንጋጌዎች አንቀፅ 19፣20፣50 እና 51 ናቸው፡፡ ያለመያዣ ትእዛዝ መያዝ በፖሊስ ወይም በማንኛውም ሰው ሊፈፀም እንደሚችል የሥነ ሥርዓት ህጉ ያስቀምጣል፡፡
በዚህ መሠረት የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች ተፈፅመው ሲገኙ ፖሊስ ወይም ማንኛውም ሰው ተጠርጣሪውን መያዝ ይችላል፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ምንነትና በምርመራ ጊዜ ያለው ውጤት፣ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል በክስ ሂደት እና በፍርድ ሂደት ያላቸዉ እንድምታ የሚሉትን እንመለከታለን፡፡.....።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇ይቀጥላል
👆👆👆👆👆👆👆👆👆የቀጠለ

የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ምንነትና በምርመራ ጊዜ ያለው ውጤት

የእጅ ከፍንጅ ወንጀል የሚለው ቃል ትርጉም በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል የተዘጋጀዉ አማርኛ መዝገበ ቃላት አንድ ሰው ወንጀል በመፈፀም ላይ እንዳለ የመያዝ ሁኔታ ነዉ በማለት አስፍሮ ይገኛል፡፡ In flagrante delicto is a latin phrase defined as someone being caught during the act of crime...አንድ ሰው የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም ከተያዘ እጅ ከፍንጀ ወንጀል መሆኑን ይገልፃል፡ Black law dictionary እጅ ከፍንጅ ወንጀል ሲገልጽ፣Flagrant crimen-in Roman law a fresh or recent crime. This term designated the very act of its commission or while it was of recent occurrence. Flagrant delit –in French law a crime which is in actual process of perpetorration which has just been committed. ከነዚህ ሁለት ትርጉሞች የምንረዳዉ እጅ ከፍንጅ ወንጀል ማለት ወንጀሉ እየተፈጸመ ያለ ወይም እንደ ተፈጸመ ወዲያዉኑ ከሆነ ወይም ከተፈጸመበት ቅርብ ጊዜ እንደሆነ ይገልጻል:: በታይዋን ህግ መሰረት እጅ ከፍንጅ የሚባለዉ ወንጀሉን ሲፈጽም ከተያዘ ወይም እንደፈጸመ ወዲያዉኑ ከተያዘ በሚል ያስቀምጣል:: ከዚህም በተጨማሪ አንድ ሰዉ ከተሰረቀ ንብረት ጋር ከተገኘ ወይም ወንጀል ለመፈጸም ከሚያግዝ መሳርያ ጋር ከተያዘ ወይም ወንጀሉን ስለመፈጸሙ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ጋር ከተያዘ እጅ ከፍንጅ ወንጀል መሆኑን ይገልጻል::

የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ከተፈፀመ ከላይ ከተገለፁት የወንጀል አፈፃፀሞች በአንዱ ዓይነት ወንጀል ተፈፅሟል ማለት ነው:: የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች ከተፈፀሙ የወንጀል ምርመራ ይጀመራል:: በመቀጠልም ክስ እና ክርክር ይቀጥላል በመጨረሻ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡ ከዚህ በመቀጠል የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች አፈፃፀም በምርመራ ጊዜ፣ በክስ፣ በክርክር እና ውሳኔ ጊዜ ያለውን ሁኔታ ይገልፃል፡፡

አንድ ወንጀል በተፈፀመ ጊዜ ወንጀል አድራጊውን ለማወቅና ለፍርድ ለማቅረብ ምርመራ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ምርመራውም የሚጀመረው አግባብ ላለው አካል ይህ ድርጊት ሲገለፅ ነው፡፡ የወንጀል ምርመራ በሦስት መንገድ ሊጀመር ይችላል፡፡ አንደኛዉ ለሚመለከታው የፖሊስ አካል የሚቀርበው ጥቆማ ወንጀሉ በክስ (accusation) ከሆነ በማንኛው ሰው አማካይነት ሊሆን ይችላል:: ሁለተኛው መንገድ ደግሞ የግል ባህሪ ባላቸዉ ወንጀሎች ጉዳይ በግል ተበዳይ አቤቱታ ብቻ የወንጀል ምርመራ ይጀምራል፡፡ ሦስተኛዉ ፖሊስ በራሱ አነሳሽነት የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን ሲጠራጠር የሚጀምረዉ የምርመራ አይነት ነዉ:: የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች በምን ሁኔታ ምርመራ እንደሚጀመር ከመግለፅ አስቀድመን የእጅ ከፍንጅ ወንጀል በተመለከተ በ1954 ዓ.ም የወጣውን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ህግ የሰጠው ትርጉም ማየት አስፈላጊ ነው፡፡

በሥነ-ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 19(1) እና (2) መሰረት እጅ ከፍንጅ የሚባሉ ወንጀሎች
1. ወንጀል አድራጊው ወንጀሉን ሲሰራ የተያዘ ሲሆን ወይም ለመስራት ሲሞከር ወይም የወንጀሉን ስራ እንደፈፅመ ወዲያውኑ የተያዘ ሲሆን ነዉ፡፡
2. ወንጀል አድራጊው የወንጀሉን ስራ ከፈፀመ በኃላ ወዲያውኑ ሲሸሽ ምስክሮቹ ወይም ህዝቡ የተከታተሉት ወይም የህዝብ ጩኸትና እሪታ የተሰማ እንደሆነ ወንጀሉን እንደ እጅ ከፍንጅ መሰል ነዉ::

ስለሆነም በህጉ መሰረት አንድ ተጠርጣሪ አንድ ወንጀል ለመስራት ሲሞክር፣ ሲሰራ ወይም ከፈፀመ በኋላ በቦታው መያዙ እጅ ከፍንጅ መሆኑ ይገለፃል:: በህጉ ቁጥር 20 መሰረት ተመሳሳይ ሁኔታ ሲገለፅ አንድ ወንጀል የእጅ ከፍንጅ ተብሎ በቁጥር 19 መሰረት ሊጠቀስ የሚቻለው ወንጀሉ በተሰራበት ቦታ ወዲያውኑ ፖሊስ የተጠራ እንዲሆነ በተጨማሪ ወንጀሉ ሲሰራ ወይም እንደተፈፀመ ወንጀሉ ከተሰራበት ቦታ ላይ የድረሱልኝ እሪታ የተሰማ እንደሆነ ነው እንደ እጅ ከፍንጅ የሚቆጠረው:: ተጠርጣሪዉ ሲሸሽ በመከታተል የሕዝብ ጩኸት ከተሰማ፣ ወደ ቦታው ፖሊስ ወዲያውኑ ከተጠራ ወይም ተጠርጣሪውን ባይከታተሉውም በወንጀሉ ቦታ የይድረሱልኝ እሪታ የተሰማ እንደሆነ በተመሳሳይ ሀኔታ እንደ እጅ ከፍንጅ ወንጀል ይቆጠራል:: የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች አፈፃፀም ሆነ የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች መሰል ወይም ተመሳሳይ ሁኔታ አፈፃፀሞች በሕጉ ያለው ውጤት አንድ አይነት ነው:: ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ የወንጀል ምርመራ የሚጀምረው በግል ተበዳይ አቤቱታ ወይም በማናቸውም ሰው ጥቆማ ወይም ፖሊስ በራሱ በደረሰዉ ሁኔታ ቢሆንም የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ከተፈፀመ በዚህ ክፍል በተጠቀሰው ሕግ ቁጥር 21 መሰረት በቁጥር 19 እና 20 በተዘረዘሩት ወንጀሎች ማለትም እጅ ከፍንጅ እና እጅ ከፍንጅ መሰል ወይም ተመሳሳይ ወንጀሎች መሰረት ወንጀሉ የክስ አቤቱታ ሳይቀርብ ክስ ሊቀርብበት የማይችል ካልሆነ በቀር ክስ ወይም የክስ አቤታቱ እንዲቀርብበት አስፈላጊ ሳይሆን ክስ ማቅረብ ይቻላል:: እንደዚህ ያለው ሁኔታ በሚያጋጥምበት ጊዜ ፍርድ ቤት የሚሰጠው የመያዝ ትዕዛዝ ሳይኖር በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ- ሥርዓት ቁጥር 49 እና በተከታዩቹ ቁጥሮች መሰረት ወንጀለኛውን ለመያዝ ይቻላል:: በመሆኑም የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች በተፈፀሙ ጊዜ የግል አቤቱታ የማያስፈልጋቸዉ ከሆነ ምርመራ እና ተጠሪጣርን መያዝ በአንድ ላይ ይጀምራል:: ስለዚህም በግል አቤቱታ የሚቀርቡ ጉዳዩች በተበዳይ ፍላጎት ካልሆነ በስተቀር ወንጀለኛ ሊያዝ አይችልም:: ምክንያቱም ተበዳይ ጉዳዩ እንዲገለጽ ላይፈልግ ስለሚችል፣ ለኀብረተሰቡም ብዙ ጉዳት የሚያደርስ ባለመሆኑ ወንጀሉ በተፈፀመ ቦታ ወንጀለኛ መያዝ አስፈላጊ ባለመሆኑ ነው፡፡

በህጉ አንቀጽ 49 በተገለፀው መሰረት ማንም ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሊያዝ ወይም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ለማድረግ አይቻልም:: ሆኖም በህጉ አንቀጽ 50 በተገለፀው መሰረት ማንኛውም ሰው ወይም የፖሊስ ሰራዊት ባልደረባ በቁጥር 19 እና 20 በተመለከተው መሰረት ከሦስት ወር በማያንስ በቀላል እስራት ቅጣት የሚያስቀጣ የእጅ ከፍንጅ ወይም መሰል ወንጀል የፈፀመ እንደሆነ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወንጀል ሰሪውን ለመያዝ እንደሚቻል ገልጿል:: በመሆኑም በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ወንጀል ህግ ውስጥ በግልፅ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስቀጡ ወንጀሎች ተብለዉ የተጠቀሱ ለምሳሌ የእጅ እልፊት፣ ስድብ የመሳሰሉት እና በዚሁ በተጠቀሰው የወንጀል ህግ የወንጀል ቅጣት ከሦስት ወር በታች የሚያስቀጡ ከሆነ እጅ ከፍንጅ የተሰራ ወንጀል ቢሆንም ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዥ ወይም በሥነ ሥርዓት ህጉ 51 መሰረት በተሰጠው ስልጣን ካልሆነ ተጠሪጣሪን መያዝ አይቻልም፡፡ ሌላ በዚህ ክፍል ሊጠቀስ የሚገባው በህጉ መሰረት ከተጠቀሱት በግል አቤቱታ የማይቀርብና ከሦስት ወር በላይ የሚያስቀጣ ወንጀል ከሆነ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ወይም መሰል ወይም ተመሳሳይ ሁኔታ የፈፀመን ሰው ማንም ሰው በመያዝ ወደ አቅራቢያዉ ወደ አለው ፖሊስ ጣቢያ ማስረከብ ይቻላል:: በሌላ ሁኔታ ከፖሊስ ዉጭ በህግ የተጠረጠረን ሰዉ መያዝ አይቻልም፡፡
👇👇👇👇👇 ይቀጥላል
...... 👆👆👆👆👆👆👆👆የቀጠለ
በሌላ በኩል በሌሎች ህጎች የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች ሰርተው በህጉ በተለየ ሁኔታ የተቀመጠ ነገር ካልተሟላ በስተቀር ተጠርጣሪን መያዝ የማይቻልበት ሁኔታ አለ፡፡ ለምሳሌ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 54(6) እንደሚገልፀው ማንኛውም የሕዝብ ተወካዩች ምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈፀም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም:: በወንጀልም አይከሰስም፡፡ በዚሁ ህግ አንቀጽ 63(2) መሰረት ማንኛውም የፌዴሪሽኑ ምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈፅም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም:: በወንጀልም አይከሰስም፡፡ በእነዚህ ህግ መሰረት የየምክር ቤት ፈቃድ ተጠይቆ ዉሳኔ ሲሰጥ መያዣ ትዕዛዝ ማወጣት እና ማስረጃ በቂ ከሆነ ክስ መመስረት ብዙም ችግር የለም:: የወንጀል ደረጃ በተመለከተ ከባድ ወንጀል ነው ለማለት ምን መስፈርት መጠቀም አለብን የሚለው አከራካሪ ነው፡፡ የወንጀል ሕግ ስለወንጀል ደረጃዎች በግልፅ የሚናገረው ነገር የለም:: ሆኖም የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 106(1) ላይ ቀላል እስራት፣ ከባድነቱ መካከለኛ የሆነ ወንጀልን ባደረገና ጥፋተኛውም ለኅብረተሰቡ እጅግ አደገኛ መስሎ ባልታየ ጊዜ የሚወሰን የነፃነት ማሰጣት ቅጣት ነው:: በአንቀጽ 108(1) በተጠቀሰዉ መሰረት፣ የፅኑ እስራት ቅጣት የሚወሰነዉ ከባድ ወንጀል ባደረጉና በተለይም ለኅብረተሰቡ አደገኛ በሆኑ ወንጀለኞች ላይ ነው:: ከእነዚህ ከሁለት አንቀፆች የምንረዳው በወንጀል ሕግ ውስጥ በቀላል እስራት የሚያስቀጡት ወንጀሎች መካከለኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጡ የወንጀል አይነት ሲሆን በፅኑ እስራት የሚያስቀጡት ወንጀሎች በከባድ ደረጃ የሚቀመጡ የወንጀል አይነት ናቸው ማለት ነው:: በሌላ በኩል በአንቀጽ 103(1) ላይ እንደተገለፀው ከባድትነት የሌላቸውና በገንዘብ መቀጮ ወይም በግዴታ ስራ የሚያስቀጡ፣ ቀላል ደረጃ ያላቸዉ የወንጀል አይነቶች እንደ ቀላል ደረጃ ያላቸዉ የወንጀል አይነቶች እንደሆኑ መረዳት ይቻላል:: በመሆኑ በገንዘብ ወይም በግዴታ ስራ እንዲሰራ የሚደነግግ የወንጀል አይነት የፈፀመ ቀላል ደረጃ አይነት ወንጀል እንዲሁም በቀላል እና በፅኑ እስራት የሚያስቀጡ ወንጀሎች እንደ ቅደም ተከተላቸዉ በመካከለኛ እና በከባድ ደረጃ የሚቀመጡ ናቸው::

በመርህ ደረጃ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህጉ ቁጥር 32 በተጠቀሰው መሰረት ማንኛውም መርማሪ ፖሊስ ወይም የፖሊስ ሰራዊት ባልደረባ በፍርድ ቤት የተሰጠ የብርበራ ማዘዣ ካልያዘ በቀር መበርበር አይችልም:: ነገር ግን በልዬ ሁኔታ ያለብርበራ ማዘዣ መበርበር የሚፈቅድለት ፤ ወንጀለኛውን እጅ ከፍንጅ ሲከታተሉትና እቤት ውስጥ ሲገባ ወይም ወንጀል የሰራበትን ነገር እቤት ውስጥ ያስቀመጠ ሲሆን ነው፡፡ በተከሰሰበት ወንጀል ወይም ወንጀል ሰርቷል ተብሎ በተጠረጠረበት ነገር ማስረጃ የሚሆን በሰውነቱ ደብቋል የሚያሰኝ በቂ ምክንያት ካለ የተያዘውን ሰው መፈተሽ ይቻላል፡፡ እጅ ከፍንጅ ወይም መሰል ወንጀል እንደተፈፀመ በመከታተል ሰውነቱንም ሆነ ንብረቱ የተቀመጠበትን ቦታ መበርበር ይቻላል፡፡

የእጅ ከፍንጅ ወንጀል በክስ ሂደት ያለዉ እንድምታ
የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ በ109(1) በተገለፀው መሰረት ዐቃቤ ሕግ የፖሊስ ምርመራ መዝገብ በደረሰው በአስራ አምስት ቀን ጊዜ ውስጥ ውሳኔ መስጠት እንዳለበት ይገለፃል፡፡ ዐቃቤ ህግ ምርመራውን በቅርበት የሚከታተል በመሆኑ በሰዓታት ወይም በቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል:: የኢ.ፌዲ.ሪ የወንጀል ፍትህ ፖሊሲ መሰረት በማንኛውም የወንጀል ክስ ጉዳይ የተሟላ ማስረጃ እስከቀረበ ድረስ ማንኛዉም የወንጀል ክርክር በተቀላጠፈ ሥነ ሥርዓት ሊመራ ይችላል:: ምክንያቱም ሲገለፅ ማስረጃዎች ክሱን የማስረዳት ብቃታቸዉ ሳይቀንሱ በትኩሱ እንዲቀርቡ ለማድረግ፣ ከኤግዚቪይት ጋር ተያይዘው ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት እና የተጎጂ እና የተጠርጣሪ መብቶችን በአግባቡ ለማክበር በጊዜ ፍትህ ለመስጠት የሚስችል ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው፡፡ አሁን በተግባር የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች ችሎት እና መደበኛ ችሎቶች አሉ:: የእጅ ከፍንጅ የሚቀርቡ ጉዳዩች በፖሊሲ በግልፅ የመወሰን ስልጣን የዐቃቤ ሕግ እንደሆነ ይገለፃል፡፡ በዐቃቤ ሕግ በማስረጃ ይዘታቸዉ ውስብስብነት የሌላቸዉ የእጅ ከፍንጅ እና ለሌሎች ወንጀሎች በፈጣን ሥርዓት ማስከሄድ የተፈጣነ ፍትህ እንዲሰጥ ያደርጋል:: ይህንም ሲወስኑ የወንጀሉን አጠቃላይ ባሕሪይ የማስረጃዎችን ይዘትና ብቃት እንዲሁም የተጠርጣሪውንና የተጎጂውን ፍላጎት ግምት ዉስጥ ማስገባት ያስፈልጋል::

እጅ ከፍንጅ ወንጀሎች በፍርድ ሂደት ያለዉ እንድምታ
ዐቃቤ ሕግ ወደ እጅ ከፍንጅ ችሎት እንዲቀርብ አንድ ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ሲመራ በፍርድ ቤት እጅ ከፍንጅ ችሎት የሚከፈት መዝገብ በዕለቱ ወደ ችሎት ሄዶ ጉዳዩ ይታያል:: ነገር ግን በሌሎች መደበኛ ችሎቶች ቀጠሮ ተሰጥቶ ከዛም በኋላ በቀጠሮ ቀን ችሎት ይቀርባል:: እጅ ከፍንጅ ችሎት ከሌላው የሚለየው በዕለቱ ስራ መቀጠሉ ነው:: በላይ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ እጅ ከፍንጅ ችሎት የሚቀርቡት እጅ ከፍንጅ የተያዙት ተጠርጣሪዎች ብቻ ሳይሆን ማንኛውም የተሟላ ማስረጃ እና ተከሳሽ ያለበት መዝገብ እዚህ ችሎት ይቀርባል:: ሌላው ከመደበኛ ችሎት የሚለየው የተፋጠነ ስርዓት ከመሆኑ አኳያ ብዙ ጊዜ የዋስትና መብት እንደ አንድ ችግር ይታያል:: የዐቃቤ ህግ ምስክር ተሰምቶ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ መከላከያ ማስረጃ የለኝም ካለ ፍርድ ቤት ውሳኔ ወዲያዉኑ መስጠት ካልቻለ አንዳንድ ችሎት እንደሚያደርጉ ተከሳሽ በዋስ መለቀቅ አግባብ አይሆንም:: ምክንያቱም ውሳኔ መስጠት ብቻ የሚቀር በመሆኑ:: ከዚህ ውጭ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ችሎት ከሌሎች መደበኛ ችሎት ጋር አንድ አይነት ነዉ::
በአጠቃላይ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል በህግ የተደነገገ፣ ማሰረጀዉ የቅርብ የሆነ እና የወንጀል ምርመራዉ፣ የክስና የፍርድ ሂደቱ የተፋጠነ በመሆኑ በተሻለ ሆኔታ ፍትህን ለመስጠት የሚያስችል ነዉ፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 205827 ህዳር 27ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ አላማውን በማያሳካ መንገድ ተርጉሞታል በማለት አስገዳጅ ውሳኔ ሰጠ ።

ጉዳዩ የተነሳው ያረጋል ተገኘ የተባለ ተከሳሽ መስከረም 11/2012 ዓ/ም በአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ 1 ቱርክ ሽጉጥ ከመሰል 31 ጥይቶች ጋር ይዞ በመገኘቱ ዐቃቤ ህግ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 4(1) እና 22(2) ላይ የተመለከተውን ተላልፎ ጦር መሳሪያ ይዞ ተገኝቷል በሚል ክስ መስርቶበት የአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ፍ/ቤት ተከሳሸን ባመነው መሰረት ጥፍተኛ በማለት 2ወር ቀላል እስራትና 600ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ስለወሰነና ውሳኔ የአዊ/ብ/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ስላጸናው በተከሳሽ ይግባኝ ጠያቂነት የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ላይ የተመለከተውን የጊዜ ገደብ በመጥቀስ ተቆጣጣሪ ተቋሙ የጊዜ ገደብ አውጥቶ ምዝገባ ባልጀመረበት ሁኔታ ተከሳሽን ጥፋተኛ ብሎ መቅጣት ህጋዊ መሰረት የለውም በማለት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ በመሻሩ የአብክመ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ በማቅረቡ ነው ።
ይግባኝ የቀረበለት የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም ፦
1ኛ የአዋጁ አንቀጽ 23(2) ጊዜ ሰሌዳ ያስቀመጠ ቢሆንም ቅሉ በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ሆኖ ማነኛውም ግለሰብ ጦር መሳሪያ ይዞ ቢገኝ ከተጠያቂነት እንደሚድን አያስቀምጥም ።
2ኛ የአዋጁ መሰረታዊ አላማ የጦር መሳሪያን ወደ ህጋዊ ስርዓት አስገብቶ መቆጣጠር እንጅ በዚህ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ የጦር መሳሪያ ይዞ ለመገኘት ፈቃድ የሚሰጥ አይደለም ፤ የጊዜ ገደቡ የሚያገለግለው ጦር መሳሪያው በምዝገባ ሂደት ላይ እያለ ችግር እንዳያጋጥም እንጅ የአንድ አመት የመያዝ ፈቃድ የሚሰጥ ተደርጎ መተርጎም የለበትም ፤
ስለሆነም የጊዜ ገደብ መቀመጡ እስከ አንድ አመት ያለማንም ጠያቂነት የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመፍቀድ ታስቦ የተደነገገ አድርጎ መተርጎም የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የወጣውን አዋጅ አላማ የሚያሳካ ካልመሆኑም በተጨማሪ ተከሳሹ በሰጠው የእምነት ቃል መሰረት ጦር መሳሪያውን የያዘው ነባሩ አዋጅ በስራ ላይ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑ ያልተካደ በሆነበት ሁኔታ ተከሳሽን ከተጠያቂነት ነጻ ማድረግ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ አላማ ባልተገባ መንገድ በመተርጎም መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸም ነው በማለት የወረዳውንና የከፍተኛውን ፍ/ቤቶች ውሳኔ አጽንቶ የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሽሮታል ።
Please share it ( እባክዎ ያጋሩት)
በ ተስፍሽ ዐቢሲኒያ
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ኔሞ የሽናሻ_ታምሩ ዳኘው.pdf
305.2 KB
#4
#እኔም_የዕርቅ_ሀሳብ_አለኝ

''ኔሞ'' የሽናሻ ብሔረሰብ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት

አዘጋጅ: ታምሩ ዳኘው

" ኔሞ " ሽናሾች የሚመሩበት፣ የሚተዳደሩበት፣ እና ፍትህ የሚያገኙበት የህይወታቸው አንድ አካል ነው። የሺናሻ ብሄረሰብ በውስጡ ከ16 በላይ ንዑሳን ጎሳዎች ሲኖሩት እነዚህ ጎሳዎች ለኔሞ ስርዓት እንዲያመች ሆነው በሶስት ይከፈላሉ።

እነዚህም ጎሳዎች በብሄረሰቡ ባህል መሰረት “ሦስት ጉልቻ” ተብለው ይጠራሉ። ሦስቱ ጎሳዎች ዶዎ፣ ኢኖሮ፣ እና ኢንዲዎ ይባላሉ። ከእነዚህ ሶስቱ ጉልቻዎች አንዱ እንኳን ቢጎድል የኔሞ ስርዓትአይከወንም።

የቦሮ-ሽናሻ ብሄረሰብ ባህላዊ የፍርድ አሰጣጥ ሂደቶች አራት ደረጃዎች አሉት። እነዚህም፦

#ቡራ፦ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ የሚሰጥበት “ቡራ”በመባል ይታወቃል:: ቡራ አንድ ሽማግሌ ብቻውን ሆኖ የሚፈርድበት የቤተሰብ ባህላዊ ችሎት ነው።

#ኔማ፦ ሁለተኛ ደረጃ ፍርድ የሚሰጥበት የዳኝነት ክፍል”ኔማ” ይሰኛል። በዚህኛው ደረጃ ሦስት ሽማግሌዎች ግራናቀኝ አይተው ፍርድ ወይም ፍትህ ይሰጣሉ ተብሎ ይታመናል።

#ፄራ፦ ሶስተኛው የዳኝነት ክፍል ወይም ችሎት “ፄራ” ይባላል::ይህ ባህላዊ ችሎት የሚመራው በአንድ ባህላዊ ሹም ዳኛ ነው። በዚህ ክፍል ኔማ ችሎት መፍታት ያልቻለው ጉዳይ በጥልቀት ይታያል።

#ፋላ፦ ይህ በሺናሻ የመጨረሻ ወይም ከፍተኛ የዳኝነት አካል ነው፡፡

የሽናሾች ባህላዊ የኔሞ ስርዓት ዘመናዊውን ዳኝነት እጅጉን የማገዝ አቅም አለው። በአመክንዮአዊነቱ (ምክንያታዊነቱ) ዘመናዊ አስተሳሰብንና ፍትህን በሚዛናዊነት አስተናግዶህብረተሰቡ በሰላም ተሳስቦ መኖር እንዲችል አስተዋፅኦውወደር የሌለው በመሆኑ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ባህላዊ እሴት ነው።
ሙሉ ጹሑፉን ከላይ ተያይዟል
#tikvahethiopia
#አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties
የቤተሰብ ሕግ ሐተታ ዘምክንያት.pdf
840.6 KB
Full version here Above 👆👆👆👆👆
ምዕራፍ 1
ጠቅላላ ስለ ጋብቻ አፈፃፀም
አንቀጽ 14/

ልዩ ልዩ የጋብቻ አፈፃፀም ሥርዓቶች

ይህ ምዕራፍ በ1952 ዓ.ም. በወጣው የፍ/ብ/ሕግ ሁለተኛ መጽሐፍ ስለጋብቻ አፈፃፀም በምዕራፍ 3 የተመለከተው ሲሆን ሶስት ዓይነት ጋብቻ መኖሩን ይደነግጋል።


ጋብቻ የሚለው ቃል በአንድ በኩል ጋብቻ ውስጥ ለመግባት የሚደረገውን ሥርዓት (celebration/conclusion of marriage) የሚመለከት ሲሆን በሌላ በኩል ጥምረቱን ለመመስረት የሚከናወነው ሥርዓት ከተፈፀመ በኃላ ወይም ጋብቻ ለመመስረት የሚያስፈልጉ ሥርዓቶች ከተሟሉ በኃላ የሚመሰረተውን ግንኙነት ትብብሩን፣ትዳር የሚያመለከት ይሆናል።

ከዚህ በመነሳት በዚህ ሕግ ጋብቻ የሚለው ቃል የአፈፃፀም ሥርዓቱን የሚያመለክት ሲሆን በሶስት ዓይነት ሥርዓቶች ሊፈፀም ይችላል፡፡ በመሆኑም በፍ/ብሔር ቁጥር /577-580/ ያሉት ድንጋጌዎች ጋብቻ ሊመሰረትባቸው የሚችሉ የአፈፃፀም ሥርዓቶችን የሚያመለክት በመሆኑ ከአንቀጽ /14/ ባሉት ድንጋጌዎች የአገላለጽና የቃላት ለውጥ ተደርጓል። ብሔራዊ” የሚለው ቃል በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገመንግስት ከተሰጠው ትርጓሜና አጠቃቀም አኳያ ብሔራዊ ጋብቻ የሚለው አገለላጽ አግባብነት የሌለው ሆኖ በመገኘቱ በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈፀም ጋብቻ በሚል ርዕስና አጠቃቀም እንዲተካ ተደርጓል።

በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 34/4/ በተደነገገው መሠረት በባህልም ሆነ በሀይማኖት ሥርዓት የሚፈፀሙ ጋብቻዎች በክብር መዝገብ ሹም ፊት ከሚፊፀመው ጋብቻ ጋር በእኩል ደረጃ የሚታዩ መሆናቸውን ለማመልከት ልዩነት በሚፈጥሩ አገላለጾች ላይ ለውጥ የተደረገ ሲሆን የሶስቱም ዓይነት ጋብቻ አፈፃፀም ሥርዓት ግልጽ በሆነ አነጋገር ሰፍሯል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties #lawsocieties
👍👍👍 የቀብድ ሕጋዊ ውጤት 🙏🙏🙏
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1. ቀብድ ሻጭና ገዥ በተነጋገሩበት ጉዳይ ላይ ውል መፈፀማቸውን እርግጠኛ ሲሆኑ የሚቀባበሉት ገንዘብ በመሆኑ ይህን ማድረጋቸው ገንዘቡን ለመቀባበላቸው ብቻ ሳይሆን ውሉን ለመዋዋላቸውም ማስተባበያ የማይቀርብበት ማስረጃ መሆኑን የፍትሃ ብሔር ሕግ ቁ 1883 ይደነግጋል።

ገዥና ሻጭ አንድን ቤት ሲሻሻጡ በፍትሃ ብሔር ሕግ 1723(1) ሥር የተመለከተውን ፎርም ባያሟሉም ሻጭ ለዚሁ የሽያጭ ውል ማስፈፀሚያ ቀብድ መቀበሉ ከተረጋገጠ በማያከራክር ሁኔታ ውሉ መደረጉን ያረጋግጣል። አንድ ውል የህጉን ፎርም ካላሟላ በሕግ ፊት የማይፀና ይሆናል ነገር ግን በልዩ ሁኔታ የቀብድ ገንዘብ ክፍያ ካለ ውሉ የሕጉን ፎርም ያላሟላ ቢሆንም የቤት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ የማያከራክር ማረጋገጫ ስለሆነ ውሉ የፀና ይሆናል።

(የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ መዝገብ/ቁ 56794 ቅፅ 12)

የተከፈለው ክፍያ ግን ቀብድ መሆኑ በውሉ ላይ ካልተገለፀ በቀር ቀብድ ነው ተብሎ ሻጭ አጠፌታውን እንዲከፍል የማያስገድድ ከመሆኑ በላይ ውሉ መኖሩንም ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም።

2. የቀብድ ክፍያ መኖሩ የውሉን መኖር የሚያረጋግጥ ብቁ ማስረጃ ቢሆንም ተዋዋይ ወገኖች ውሉን ለማፍረስ ተቃራኒ ስምምነት ካላደረጉ በቀር ቀብድ ተቀባዩ የተቀበለውን ገንዘብ እጥፍ አድርጎ በመመለስ፥ ቀብድ ሰጪው ደግሞ ይህንኑ የሰጠውን ገንዘብ ለተቀባዩ በመልቀቅ ያለሌላ ተጨማሪ ሁኔታ ውሉን የማፍረስና በመካከላቸው የተመሰረተውን ግዴታ ለማስቀረት መብት አላቸው። ይህም አሰራር በቀብድ የታሰረ ውል ከሌሎች ውሎች የሚለይበት ልዩ ባህሪ ነው። (የፍትሃ ብሔር ሕግ ቁ. 1885)

ፍርድ ቤቶችም በተዋዋይ ወገኖች መካከል ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ሻጩ የቀብዱን አጠፌታ ከፍሎ ውሉን በማፍረስ የሸጠው ቤት እንዲመለስለት ከጠየቀ መወሰን የሚገባቸውና ተገዶ እንዲፈፅምም ማድረግ የሌለባቸው መሆኑ ግልፅ ነው።

የተደረገው ውል ሊፈፀም የማይችል (impossible)፣ ወደ ገዥ ሊተላለፍ የማይችል እና ሕገ ወጥ (unlawful) ከሆነ ግን ውሉ ፈርሶ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት ከሚመላለሱ በቀር ሻጭም እጥፉን እንዲመልስና ገዢም የከፈለውን እንዲለቅ የሚጣልባቸው ግዴታ የለም።

3. ውሉ በአግባቡ ከተፈፀመ እና ለ ቀብዱ ገንዘብ ዕጣ ፋንታ በተዋዋዬቹ መሀል የተደረገ ሌላ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ የቃብድ ሂሳቡ ከጠቅላላው የሽያጭ ዋጋ ላይ የሚታሰብ ወይም እንዲመለስ የሚደረግ ይሆናል።
(የፍትሃ ብሔር ሕግ ቁ. 1884)
via Tax and custom law blog
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ይህ የ #አለ_ህግ የቴሌግራም ቻናል እና ግሩፕ ጠቅሞኛል ካላቻሁ ሌሎችም ተጠቃሚ እንዲሆኑ #Share ሼር ያድጉላቸው።
ወደ ግሩፑ
#add ያድጓቸው።

#አለ_ህግ #AleHig

@Lawsocieties

@AleHig

https://t.me/lawsocieties

https://t.me/AleHig
የጉምሩክ (የመጨረሻ ረቂቅ) ደንብ. 2014.pdf
13.7 MB
በአገራችንን የወጪና የገቢ ንግድ ሥርዓት ከሚመሩ ሕጎች መካከል የጉምሩክ መጋዘን አስተዳደርን እና የጉምሩክ አስተላላፊዎችን በሚመለከት የወጡ ደንቦች ይገኙበታል፡፡ እነዚህን ደንቦች በአንድ በማጠቃለል ዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ጋር የሚጣጣም፣ በአገራችን እያደገ የመጣውን የማምረቻ ኢንዱስትሪ ልማት የሚደግፍ እንዲሁም ሕጋዊ ንግድን እና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ፣ በስራ ላይ ካለው የጉምሩክ አዋጅ ጋር የሚጣጣም ደንብ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤትም በረቂቅ ደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ከዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

ምንጭ ፡- Hima Xpress
#አለ_ህግ #AleHig @Lawsocieties
Our Court - Give your verdict!
___
Mr. A took a 11,750 ETB loan from Mr. B and promised to return the loan amount with interest (23,500 ETB). This agreement was made in written form and signed by both parties. After a year, Mr. A paid back only the initial loan amount, and Mr. B asked Mr. A to pay the interest as indicated in the loan contract. Mr. B said he is not bound to pay the interest but only the loan amount.

👨‍⚖🧑‍⚖‍ If you were a judge for this case what would be your judgment, "Is Mr. A bound to pay an interest that is equal with the loan amount based on the written loan contract?"

Give your verdict! 👇👇👇👇👇
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
Our Court - Give your verdict!
___________________________
Anonymous Poll
67%
Yes ☑️
33%
No 👎
አዲስ ለተወለደ ህፃን ልጅ ስም የማውጣት መብት፤ የእናት ወይስ የአባት?

የሕግ ባለሙያዎች ወግ
በአቤል ልዑልሰገድ አበበ


ከሰሞኑ በአንድ ጠበቆች፣ ዳኞች፣ ዓቃቢያነ ሕግች፣ የሕግ ምሁራን እና የሴቶች መብት አቀንቃኞች የተገኙበት የሴቶች እኩልነት እና ሰብዓዊ መብቶች በሚል ርእስ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝቼ ሳለሁ፤ አንዲት ተሳታፊ ጠበቂት ሃሳቧን ስታጋራ ለህፃን ስያሜ የመስጠት መብት የወላጆች የጋራ መብት ነው ብላ በደፈናው ተናግራ ስትጨርስ የውይይቱ መሪ ይህን ሀሳብ በሕግ የተደነገገ መብት ነው ብላ ስትደግም ከተሳታፊዎች ጉርምምታ ሲበዛ ለምን አላጠራውም በሚል፤ ይህንን ንግግሯን የሚደግፍ የሕግ ማዕቀፍ ካለ በሚል ጥያቄ አቅርቤላት ነበር፡፡ አወያዪዋም የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ እና ሕገ-መንግሥቱ ይደነግጋል በማለት ምላሽ ስትሰጥ፤ በዚህ ነጥብ ላይ የጦፈ ክርክር ይነሳል፡፡

በአንድ ወገን ይህንን ስያሜ የመስጠት ቅድሚያ መብት የሚደነግገው የፍትሐብሔር ሕጉ ነው እንዲሁም በቤተሰብ ሕጉ በግልፅ የተደነገገ አንቀጽ የለም በሚል ሲቃወሙ፤ በሌላ ፀንፍ አወያዩዋን ጨምሮ ሌሎች ተሳታፊዎች ደግሞ የሴቶች እኩልነት በሕገ-መንግሥቱ ስለተደነገገ እና በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ስር ቤተሰብን በጋራ የማስተዳደር ኃላፊነት በጋራ መሆን አለበት በሚለው አንቀጽ ስር ይወድቃል በማለት ተከራከሩ፡፡ በመጨረሻም ከስምምነት መድረስ ሲያቅተን ጭብጥ ቀይረን ውይይቱን ቀጠልን፤ ነገር ግን እንደ አንድ የሕግ ባለሙያ ጉዳዩን የበለጠ ልመረምር ይገባል ብዬ ይህንን ዕልባት ያላገኘ ነጥብ ወደ ማውቃቸው የሕግ ምሁራን ወስጄ ሀሳባቸውን ስጠይቅ እዚህም ሁለት ጎራ የያዘ ምላሽ አገኘሁ፡፡ በዚህም የተነሳ ይህንን ነጥብ የበለጠ ለማጥራት ከሕግ ማዕቀፎቹ፣ ከመሰረታዊ የሕግ ፍልስፍና መርሆች እና ከፆታ እኩልነት አንጻር ለመመርመር ወደድኩ፡፡ ምንም እንኳ በውይይቱ አንዱን ጎራ ይዤ ስከራከር የነበረ ቢሆንም ለዚህ ፅሁፍ አላማ ሲባል ገለልተኛ ሆኜ የሁለቱንም ገራ ክርክር አካትቼ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2033-choice-of-first-name-in-ethiopia
#አለ_ህግ #AleHig

@Lawsocieties

@AleHig

https://t.me/lawsocieties

https://t.me/AleHig
ለህግ ት/ት Exit Exam ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው ይቅለላችሁ፣
እንደልፋታችሁ መልካም የማስተዋል ጊዜ።
#አለ_ህግ
#Daily_Tip
የአላማ ሰው መሆን!


'ምንም ነገር መጀመር ያለብህ ቀድመህ በአይምሮህ ስትጨርሰው ነው' የሚባል ሀሳብ አለ።
ብዙ ነገር ጀምረህ ያቆምከው ወይ መሀል ላይ ግራ የሚገባህ አቅም አንሶህ ወይ ሰነፍ ስለሆንክ አይደለም አላማህን ስለማታውቀው ነው! ወይ ደግሞ አላማህን ብታውቀውም እቅድ የለህም።

ሰውነትክን ከማሰራትክ በፊት አእምሮክ መጨረሻውን መዳረሻውን ማየት አለበት እንዴት ወዴት ከማን ጋር የሚለውብ በሀሳብክ ጨርስ።
Via - Social media
#Ethiopian Business Daily
Abortion should be Legal or Illegal?
Anonymous Poll
29%
Legal
71%
Illegal
#ህጉ ምን ይላል?
#የዉል ስምምነት የሚጸናባቸዉ ነጥቦች
በእዉቁ የህግ መዝገበ ቃላት ብላክስ ሎዉ ላይ “ዉል ማለት በሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በመካከላቸዉ አንድን ድርጊት ለማድረግ ወይንም ላለማድርግ በመስማማት ግዴታ የሚፈጥሩበት መንገድ ነዉ” ሲል ትርጉም ይሰጠዋል፡፡ እንዲሁም በፍትሐ ብሔር ህጋችን አንቀፅ 1675 ላይ “ዉል ማለት ንብረታቸዉን የሚመለከቱ ግዴታዎችን ለማቋቋም ወይም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ባላቸዉ ተወዳዳሪ ግንኙነት በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መሀል የሚደረግ ስምምነት ነዉ” በማለት ትርጉም ሰጥቶታል፡፡

የዉል ስምምነት ከሌሎች ስምምነቶች የሚለየዉ ለአፈፀሙ ከበስተጀርባዉ የሕግ ድጋፍ ያለዉ ስምምነት መሆኑ ነዉ፡፡ ይህም ማለት ተዋዋይ ወገኖች የተስማሙበትን ነገር እንደ ስምምነታቸዉ ባይፈፅሙ ያልፈፀሙትን ነገር በህግ ተገደዉ እንዲፈፅሙ ይደረጋሉ፡፡ ይህም የሚያሳየን ዉል በተስማሚዎቹ አካላት መካከል እንደ ህግ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን ነዉ፡፡
👇👇👇👇👇የቀጠለ👇👇👇👇

ዉል በተወያይ ወገኖች መካከል ህጋዊ ዉጤት እንዲኖረዉ አስቀድሞ የዉል አመሰራረቱ ህጋዊ መስፈርቱን ማሟላት አለበት፡፡ በፍትሐብሔር ህጋችን አንቀፅ 1678 ላይ በግልፅ እንደተቀመጠዉ የሚፀና ዉል ነዉ ለማለት መሟላት ያለባቸዉን ሁኔታዎች አስቀምጧል እነሱም፡-

1ኛ. ዉል የሚፈፀመዉ ተዋዋዮቹ ለመዋዋል በሕግ 'ችሎታ ባላቸዉ ሰዎች መካከል መሆኑ ሲሆን ይህም የተዋዋዮች ዕድሜ ከ18 ዓመት በላይ መሆን እና የአእምሮ ጤንነት ነዉ።

2ኛ• ፈቃድ (Consent) ፡- ተዋዋዩ ፈቃዱን የሰጠው ወዶና ፈቅዶ በማያሻማ ሁኔታ መሆን ይኖርበታል። ይህ ማለትም በመታለል/በማታለል የተፈጸመ ውል ዋጋ አይሰጠውም።

3ኛ• የውሉ ዋና ጉዳይ በሕግ የሚፈጸም መሆን አለበት፡- ይህም ማለት እንድን ውል ለመዋዋል ከህግና ከሞራል የሚቃረን መሆን የለበትም፡፡ ለምሳሌ ከህግ አንፃር ባዶ መሬት መሸጥ አይቻልም ስለዚህ የባዶ መሬት ሽያጭ ውል ቢደረግም በፍርድ ቤት ውድቅ ነው።

4ኛ• የውል አቀራረጽ ወይም ፎርም ነው፡- ይህም ማለት ለምሳሌ ለማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ሁለት ምስክሮች መኖራቸው፣ በውል አዋዋይ ፊት ዉሉ መረጋገጡ ነዉ።
via DARA
#አለ_ህግ #AleHig

@Lawsocieties

@AleHig

https://t.me/lawsocieties

https://t.me/AleHig
የከፍተኛ_ባለሙያዎች_ምዘናና_ማረጋገጫ_አፈፃፀም_ረቂቅ_መመሪያ.pdf
1 MB
በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ግንቦት 2014 ዓ.ም በኮንስትራክሽን ዘርፍ የከፍተኛ ባለሙያዎች ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ አፈፃፀም ላይ የወጣ ረቂቅ መመሪያ
ደንብ መተላለፍ በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#መግቢያ
በኢትዮጵያ ህግ ቅጣት ሊያስከትሉ የሚችሉ ድርጊቶችን ከክብደታቸው እና ከሚያስከትሉት ሀላፊነት አንፃር በወንጀል ህግ የሚያስቀጡ እና በደንብ መተላለፍ ህግ የሚያስቀጡ ብለን ልንከፍል እንችላለን፡፡ በደንብ መተላለፍ የሚያስቀጡ ድርጊቶች በኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ ሰባተኛ መፅሀፍ እና ስምንተኛ የተደነገጉ ሲሆን ቅጣትን የሚመለከቱ ደንቦች እና የህጉ ተፈጻሚነት ወሰን በወንጀል ህጉ ተካቶ ይገኛል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የደንብ መተላለፍ ምንነት እና ከወንጀል ሀላፊት በምን እንደሚለይ ፣ የደንብ መተላለፎች የሚያስከትሉት ቅጣት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ፡፡
የደንብ መተላለፍ ምንነት
አንድ ሰው ደንብ ተላልፏል የሚባለው ሥልጣን ያለው አካል ባወጣው ህግ የተመለከተውንና አንድ ነገር እንዳይፈፀም የሚያዘውን ወይም የሚከለክለውን ድንጋጌ የተላለፈ ወይም በወንጀል የማያስቀጣ ቀላል ጥፋት የፈፀመ ሲሆንና የዚህ ዓይነቱ ህግ መጣስ ወይም ቀላል ጥፋት በወንጀል ህጉ ከአንቀፅ 746 እስከ 775 በተመለከቱት ድንጋጌዎች የሚያስቀጣ ሲሆን ነው፡፡ በዚሁ መሰረት በወንጀል ህጉ የደንብ መተላለፍ ህግ ላይ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በቀር የነገሩን ዓይነት እንዲሁም የህጉን መንፈስና ግብ በመመልከት የወንጀል ህጉ ጠቅላላ ክፍል መሰረታዊ መርሆችና ደንቦች በደንብ መተላለፍ ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
የደንብ መተላለፍ አይነቶች
የደንብ መተላለፍ ህጉ በውስጡ የተለያዩ አይነት የደንብ መተላለፎችን የያዘ ሲሆን እነዚህ መተላለፎች በስራቸው ዝርዝር የጥፋት አይነቶችን ከሚያስከትሉት ቅጣት ጋር አካተው ይገኛሉ፡፡ የደንብ መተላለፍ አይነቶቹም በመንግስትና ህዝብ ጥቅም ላይ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ተግባሮች( ለምሳሌ ህጋዊ ገንዘብን አለመቀበል)፤ ወታደራዊ ግዴታዎችን መጣስ እና በመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም በፖሊስ ላይ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች፤ በመንግስት የስራ ግዴታዎች እና በመንግስት መስሪያ ቤት/ባለስልጣን/ ላይ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች(ለምሳሌ ሀቀኝነትን ማጓደል)፤ በሕዝብ ደኅንነት፣ሰላምና ተረጋግቶ መኖር ላይ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች(ለምሳሌ ሐሰተኛ የአደጋ ምልክት መስጠት)፤ በሕዝብ ጤና እና በፅዳት ጥበቃ ላይ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች( ለምሳሌ መርዛማና አደንዛዥ ንጥረ ነገሮችና መድሀኒቶች ለመቆጣጠር የወጣ ደንብ) እና በሰዎችና በንብረቶች ላይ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች ናቸው፡፡

ደንብ መተላለፍ ተፈፃሚ የሚሆንባቸው ጥፋቶች
በህጋዊነት መርህ እንደተመለከተው በደንብ መተላለፍ ህግ ወይም በሌላ ህግ የተደነገጉ ጥፋቶች ብቻ የሚያስቀጡ ሲሆን የሚያስቀጡትም በህጉ የተቀመጡትን ቅጣቶች ብቻ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የደንብ መተላለፍ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆኑት ለተፈፀመው ድርጊት የበለጠ ቅጣት የሚደነግጉ አንቀፆች በሌሉ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም አንድ ድርጊት የሚያስቀጣው በወንጀል ህግ ወይም በደንብ መተላለፍ ህግ በአንደኛው እንጂ በሁለቱም ሊሆን አይችልም፡፡ እንዲሁም የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሰራ መሆኑ መርህ በተመሳሳይ ለደንብ መተላለፍ ይሰራል፡፡ በመሆኑም የደንብ መተላለፍ ተግባሮች የሚያስቀጡት በተፈፀመበት ጊዜ ፀንተው ባሉት ድንገጌዎች መሰረት እንጂ ከድርጊቱ በኋላ የወጣን ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ እንዲፈፀም በማድረግ አይሆንም፡፡
በሌላ በኩል የደንብ መተላለፍ ተግባርን ለመፈፀም የሚደረጉ የመዘጋጀትና የሙከራ ድርጊቶች የማያስቀጡ ሲሆን ለደንብ መተላለፍ የሚደረግ ማነሳሳት፣አባሪነት እና ወንጀል ከፈፀመ በኋላ ወንጀል አድራጊውን መርዳት አያስቀጣም፡፡ ይህ ማለት የሚቀጣው ደንብ ተላላፊው ብቻ ነው ማለት ነው፡፡ እንዲሁም የህግ ሰውነት የተሰጠውን ሰው በአነሳሽነት ወይም በአባሪነት የማይቀጣ ሲሆን የድርጅቱ ሀላፊ ወይም ሰራተኛ የሚቀጣው በወንጀል ህጉ መሰረት በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ደንብን ወይም መመሪያን በዋና ደንብ ተላላፊነት በሚጥስበት ጊዜ ብቻ ነው፡፡

በተጨማሪም በወንጀል ህጉ አንቀጽ 743 እንደተደነገገው የማያስቀጡና ይቅርታ የሚሰጡ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነዚህም በህግ የታዘዙ ወይም የተፈቀዱ ድርጊቶች፣ የሞያ ስራ ግዴታ፣ የተጎጂው ፍቃድ ፣ ፍፁም የሆነ መገደድ፣አስፈላጊ ሁኔታ እና ህጋዊ መከላከልን የሚመለከቱ የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች ለደንብ መተላለፍም ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ ይሁንና ደንብ የተላለፈ ማንም ሰው ህግ አለማወቅን ወይም የማድረግ መብት አለ ብሎ መሳሳትን እንደመከላከያ ምክንያት አድርጎ ሊያቀርብ አይችልም፡፡

ለደንብ መተላለፍ ተፈፃሚነት ያላቸው ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎች

ለደንብ መተላለፍ መደበኛ የሆኑ የወንጀል ቅጣቶች ተፈፃሚ የማይሆኑ ስለሆነ ምንጊዜም ቢሆን ለወንጀሎቹ በተወሰኑት ፅኑ እስራት ወይም በቀላል እስራት አይቀጡም፡፡ ይህም የሚያመለክተው ደንብ መተላለፍ ከወንጀል የሚለየው በሚያስከትለው የተለየ ቅጣት እንደሆነ ነው፡፡ ስለሆነም የደንብ መተላለፍ ድርጊቶች በተፈፀሙ ጊዜ የሚወሰነው ነፃነትን የሚያሳጣ ቅጣት የማረፊያ ቤት እስራት እንጂ የማረሚያ ቤት እስራት አይሆንም፡፡ መደበኛ የማረፊያ ቤት እስራት የሚፈፀመው ከፍርድ ቤቶች ወይም ከፖሊስ ጣቢያዎች ጋር በተያያዙ ልዩ የመቆያ ቦታዎች ይሆናል ማለት ነው፡፡ እንዲሁም በማረፊያ ቤት እስራት ፈንታ የግዴታ ስራን ፍርድ ቤት ሊወስን የሚችልባቸውን ሁኔታዎች የደንብ መተላለፍ ህጉ ደንግጎ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በማናቸውም ጊዜ ቢሆን በማረፊያ ቤት እስራት እንዲቀጣ የተፈረደበት ሰው ወደ ጠባይ ማሻሻያ ወይም ማረሚያ ቤት እንዲላክ ፣በወንጀል ምክንያት ከተቀጡት እስረኞች ጋርም እንዲቀላቀል ማድረግ አይቻልም፡፡

በወንጀል ህጉ አንቀጽ 747 እና 768 እንደተደነገገው የደንብ መተላለፍ ድርጊቶች በተፈፀሙ ጊዜ የሚወሰነው ቅጣት እና የህጉ ልዩ ድንጋጌዎች የሚያስቀምጡት ከፍተኛ ቅጣት የማረፊያ ቤት እስራቱ የሚቆይበት ጊዜ ከአንድ ቀን እስከ ሶስት ወር ይሆናል( በደጋጋሚነት እና በመደራረብ ጊዜ ከሁለት ዓመት የማረፊያ ቤት እስራት አይበልጥም) ፡፡ በተጨማሪም ደንብ ተላላፊዎች ወታደሮች ወይም ወጣት ጥፋተኞች ሲሆኑ የሚፈፀመው የተለየ ቅጣት እንደተጠበቀ ሆኖ በደንብ መተላለፍ ረገድ የሚፈፀሙ ቅጣቶች በደንብ መተላለፍ ህግ በተደነገገው መሰረት ይሆናል፡፡ እንዲሁም ለህብረተሰቡ ሲባል የጥበቃ ወይም የሕክምና እርምጃዎች መወሰድ ሲኖርባቸው በተለየ ኃላፊ ሊሆኑ የማይችሉ ሰዎችን በሚመለከት ፍርድ ቤት አግባብነት ላለው የአስተዳደር ባለስልጣን ያሳውቃል፡፡

ሌላው በደንብ መተላለፍ ህጉ ለደንብ መተላለፍ ጥፋት የተቀመጠው ቅጣት የገንዘብ መቀጮ ቅጣት ነው፡፡ ይኸውም ጥፋተኛው ደጋጋሚ ካልሆነ ወይም የህጉ ልዩ ድንጋጌ የበለጠ ካልወሰነ በቀር በደንብ ተላላፊ ላይ የሚጣል መቀጮ ከአንድ ብር እስከ ሶስት መቶ ብር ለመድረስ የሚችል ሲሆን ጥፋቱ በተደጋገመ ጊዜ የሚደረገው የቅጣት ማክበጃ እንደተጠበቀ ሆኖ ተላላፊው ጣፋቱን የፈፀመው በአፍቅሮ ንዋይ እንደሆነ መቀጮው እስከ አምስት መቶ ብር ሊደርስ ይችላል፡፡ እንዲሁም ለተፈረደበት ሰው ቢያስፈልግም ከፋፍሎ በየጊዜው ዕዳውን እንዲከፍል በመፍቀድ ፍርድ ቤቱ እስከ ሶስት ወር ለመድረስ በሚችል የመክፈያ ጊዜ ሊወስንለት የሚችል ሲሆን ሁኔታዎች በቂ ምክንያት ያስገኙ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የመከፈያ ጊዜውን እስከ አንድ አመት ሊያራዝመው ይችላል፡፡...👇ይቀጥላል👇👇