አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
👆የቀጠለ.... 👆👆👆👆👆👆👆
በተያያዘ ሁኔታ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ መቀጮው ያልተከፈለ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ሙሉውን ወይም ያልተከፈለውን ቀሪ መቀጮ ከሚያገኘው ገቢ ተቀናሽ በማድረግ ለመንግስት ገቢ ከማድረግ ጋራ ነፃነትን በሚቀንስ ወይም በማይቀንስ የግዴታ ሥራ እንዲለወጥ በማዘዝ በደንብ መተላለፍ ህጉ ጠቅላላ ድንጋጌዎች መሰረት የግዴታ ስራው የሚቆይበትን ጊዜ ይወስናል፡፡

በሌላ በኩል ከማረፊያ ቤት እስራት፣ ከግዴታ ስራ ወይም ከመቀጮ በተጨማሪ ፍርድ ቤት በቃል ወይም በፅሁፍ ጥፋተኛውን ሊያስጠነቅቀው፣ ሊወቅሰው፣ ሊገስፀው ወይም ተበዳዩን ይቅርታ እንዲጠይቅ ሊያደርገው ይችላል፡፡ እንዲሁም የጥንቃቄ እርምጃዎች ማለትም የመልካም ጠባይ ዋስትና፣ መውረስ እና ለመንግስት ገቢ ማድረግ፣ ድርጅቶችን መከልከል እና የስራ ፍቃድ ማገድ እና የግል ነፃነትን መከልከልና መቀነስ እንደ የጥንቃቄ እርምጃዎች የደንብ መተላለፍ በፈፀሙ ሰዎች ላይ ሊወሰኑ የሚችሉ እርምጃዎች ናቸው፡፡
ይሁንና ከመብት የመሻር ቅጣትን የተመለከቱ ማለትም ከህዝባዊ ወይም ከቤተዘመድ፣ የመንግሥት ሥራ ወይም የሙያ ሥራ ከመሥራት ወይም ከመሳሰሉት መብቶች መሻር እንዲሁም ወታደራዊ ማዕረግን ዝቅ ማድረግ ወይም ከመከላከያ ሰራዊት ባልደረባነት ማስወገድ በደንብ መተላለፍ ላይ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡ እንዲሁም በአመክሮ መለቀቅን የሚመለከቱ የወንጀል ህጉ ድንጋጌዎች ለማረፊያ ቤት እስራት ተፈፃሚ የማይሆኑ ሲሆን የደንብ መተላለፍ ቅጣቶች በወንጀል ህጉ ላይ በተደነገጉት ጠቅላላ ሁኔታዎች መሰረት በይቅርታ ወይም በምህረት ቀሪ እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል፡፡

የይርጋ ዘመንን በተመለከተ ማናቸውም ዓይነት የደንብ መተላለፍ ድርጊት ቢሆን ክስ ሳይቀርብበት አንድ ዓመት ካለፈ የተፈረደውም ቅጣት ተፈፃሚ ሳይሆን ሁለት ዓመት ካለፈ በይርጋ ይታገዳል፡፡ በሌላ በኩል ፍርድ ቤቶች የተከሳሹን ያለፈ ታሪክ ጠንቅቀው ማወቅ ይችሉ ዘንድ በደንብ መተላለፍ ረገድ የሚሰጡት የመጨረሻ ቅጣቶች የደንብ መተላለፍ ህግን ጠቅላላ ድንጋጌዎችን በወንጀለኞች መዝገብ ላይ እንዲመዘገብ ፍርድ ቤቱ ይወስናል፡፡

በአጠቃላይ የደንብ መተላለፍ ህግ በወንጀል ህጉ ውስጥ የደንብ መተላለፎችን እና የሚያስከትሉትን ቅጣቶች ያካተተ ቢሆንም በተጨማሪ ሌሎች ባለስልጣናት የሚያወጧቸው የደንብ መተላለፎች ለምሳሌ የትራፊክ ደንብ፣ የከተማ ደንብ ማስከበር( ለምሳሌ ህገ ወጥ ንግድ እና ግንባታ) በተደነገጉት የጥፋት አይነቶች እና ቅጣቶች ኃላፊነትን ያስከትላሉ ወይም ያስቀጣሉ፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
https://t.me/lawsocieties

https://t.me/AleHig
አእምሮ የሌለው ህዝብ ስርዓት የለውም፣
ስርዓት የሌለው ህዝብ የተደለደለ ኃይል የለውም‼️🔴
የኃይል ምንጭ ስርዓት ነው እንጂ፣ የሰራዊት ብዛት አይደለም‼️🔴

ስርዓት ከሌለው ሰፊ መንግስት ይልቅ *በህግ* የምትኖር ትንሽ ከተማ ሞያ ትሰራለች‼️🔴

ገብረህይወት ባይከዳኝ
Via #አለ_ህግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
ሰሞኑን "ፊያስ" በተባለ አድራሻው በማይታወቅ የኦላይን ማጭበርበሪያ ዘዴ ብዙዎች በየዋህነት ገንዘባቸውን ተበልተዋል። ይህ ትምህርት ሊሆነን ይገባል። አሁንም በኦላይን እያጭበረበሩ የሚገኙ ስላሉ ጥንቃቄ አድርጉ።

የአማራ ባንክ ተመርቆ እንደተከፈተ ያልተከፈተ የቴሌግራም ቻናል የለም። እነዚህ በአማራ ባንክ ስም የተከፈቱ የቴሌግራም ቻናሎች የመኖሪያ ቤት ሽልማት ይሰጣል ከዛ በፊት ግን ለ50 ወይንም ለ60 ሰው ሼር አድርጉ ይላሉ። ይህን መረጃ አምኖ ሼር የማያደርግ የለም።ለእነሱ የራሳቸውን የቴሌግራም ተከታይ ለማሳደግ የፕሮሞሽን ሥራ እየሰሩነው። አለፍ ሲልም ለሌላ ወንጀል ይጠቀሙበታል።

ለጎደኞቻችሁ ሼር የምታደርጉ ሰዎች ፍፁም ውሸት መሆኑን ልታውቁት ይገባል።
ፊደል የቆጠረ ሰው እንዲህ በአለ ነገር በቀላሉ መሸወድ የለበትም። ትክክለኛውን ገፅ ለማግኘት ይሄን ያህል የሚከብድ አይደለም። ወይንም በውስጥ መስመር መረጃውን ብትልኩ አጣርተን ትክክል መሆኑንና አለመሆኑን ማወቅ እንችላለን።
ከውጭ አገር አሜሪካ ሳይቀር ለእኔም አሰልቺ ማስታወቂያዎች በግል ደርሰውኛል።

ለማንኛውም አማራ ባንክ ምንም አይነት የቤት ሆነ የመኪና ሽልማት ማስታወቂያ አላወጣም እውነት ቢሆን እንኳን እንደሌሎቹ ባንኮች በቴሌቪዥን የምታዩት ነው የሚሆነው።

ትክክለኛው የአማራ ባንክ ቴሌግራም ይሄኛው ነው!!!

Telegram: https://t.me/Amhara_Banksc

የአማራ ባንክ የፌስቡክ ገፅ ይሄ ነው።
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1

ትክክለኛ የዐማራ ባንክ የቲዊተር አድራሻ ይሄ ነው። https://twitter.com/Amharabanksc
እስካሁን በአጭበርባሪዎች ተሸውዳችሁ ለ60 ሰው ያሰራጫችሁ ሰዎች ይሄን ትክክለኛው መረጃ ለ100 ሰው ብታሳውቁ አትጎዱም። ለወደፊቱ ጥንቃቄ አድርጉ!!!

በሌሎችም የሪል እስቴት ስሞች፣ ድርጅቶች እና ታዋቂ ባለሀብቶች ስም የተከፈቱ የተለያየ አጓጊ ሽልማት አለው ሼር አድርጉ የሚሉ ብዙ የሀሰት የቴሌግራም ቻናሎች አሉ።

ጥንቃቄ ይጠብቅሃል ማስተዋል ይጋርድሀል።

እኛ ተሸውደን እና ተታለን ሰዎችን እዲታለሉና እንዲሸወዱ መንገድ አንክፈት።

#share ሼር በማድረግ እውነትን አጋልጡ

Via #አለ_ህግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 2035(2)
Ignorance of the law is no excuse.
civil code article 2035(2)
@lawsocieties @AleHig
አለሕግAleHig ️
https://t.me/lawsocieties https://t.me/AleHig
በትክክል !!!
ዳኛ ከፈጣሪ በታች ውሳኔ ሰጪ አካል ነው ፣ የዳኝነት ስራውንም በተቢው ጥንቃቄ መስራት ይጠበቅበታል ፣ ከጣፍም እሱንም ሆነ ተመልካቹን ሊያሰተምር የሚችል ህጋዊ መሰረት ያለው ቅጣት ሊቀጣ ይገበዋል ።
ነገር ነገር ግን ምክኒያት እየፈለጉ በግለሰብ ጥላቻ የፍትህ መዋቅሩን ( ሌሎችንም መልካም አጋጣሚዎች ) በመጠቅም ዳኛውን እና የዳኝነት ስርዓቱን ማወክ ህዝብን ማወክ ወይም ማስቸገር ነው የሚሆነው !!!
ሰለሆነም የህዝብን ሰላማዊና የተረጋጋ እንቅስቃሴ ለመጠበቅ ካሰፈለገ ለዳኛው ሳይሆን የዳኝነት አገልግሎቱ ለሚያስፈልገው ህዝብ ሲባል የህግ ጥበቃ እንዲደረግለት ማድረግ አንዱ መፍትሔ ነው !!!
ወርቁ መኮነን
Our Court - Give your verdict!
_______
When a customer returned to collect his property that was to be serviced by a technician and discovered that it was lost, he filed criminal charges for dishonesty against the technician. The technician asserted that he hadn't committed any crime and should instead be held liable for the value of the lost property by the Civil Law.
👨‍⚖🧑‍⚖‍ If you were a judge for this case what would be your judgment, "Is the act a crime?"
Answer here below👇👇👇👇👇
If you were a judge for this case what would be your judgment,
"Is the act a crime?"
Anonymous Poll
43%
Yes, it's a crime
57%
No, it's not a crime
ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ሥራ የሚደረግ የሥራ ውል
የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156 መሠረት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሁኔታዎች የሥራ ውል ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ሥራ ሊደረግ ይችላል፤
🔹ሠራተኛው የተቀጠረበት የተወሰነ ሥራ እስከሚያልቅበት ጊዜ ድረስ፤
🔹በፈቃድ በሕመም ወይም በሌላ ማናቸውም ምክንያት ለጊዜው ቀሪ የሆነ ሠራተኛን ለመተካት፤
🔹የሥራ ብዛት በሚያጋጥምበት ጊዜ ሥራን ለማቃለል፤
🔹በሕይወት ላይ አደጋ ወይም በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል አጣዳፊ ሥራዎችን ለመሥራት፣ 🔹በድርጅቱ ሥራ፣ ዕቃ፣ ሕንፃ ወይም ፋብሪካ ላይ የደረሰውን ጉድለትና ብልሽት ለማደስ፤
🔹አልፎ አልፎ የሚሰራ ሥራ ማለትም ሥራው የአንድ አሠሪ ቋሚ ሥራ ሆኖ እየተቋረጠ ሥራው በሚኖርበት ጊዜ ብቻ የሚሠራ ሥራ ለመሥራት፤
🔹የወቅት ሥራ ለመሥራት ማለትም የአንድ አሠሪ ቋሚ ሥራ ሆኖ በየዓመቱ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ በተለመደው ጊዜ እየተደጋገመ የሚሰራ ሥራ ለመሥራት፤
🔹አንዳንድ ጊዜ የሚሰራ ሥራ ማለትም ለአንድ አሠሪ ቋሚ ሥራ ያልሆነ በሚያስፈልግበት ጊዜ ብቻ የሚሰራ ሥራ ለመሥራት፤
🔹ላልተወሰነ ጊዜ የሥራ ውል በተደረገበት የሥራ መደብ ላይ ሠራተኛ በድንገት ለዘለቄታው በመለየቱ ለጊዜው ሥራ ለማሰራት፤
🔹በድርጅት መዋቅር ጥናት እና በጥናቱ አፈጻጸም መካከል ባለው ጊዜ የሚፈጠርን ክፍት የሥራ መደብ ለማሟላት ለጊዜው የሚፈጸም ቅጥር፡፡
🔹ለተወሰነ ጊዜ የሚደረግ የሥራ ውል ከ 45 የሥራ ቀናት ላልበለጠ ጊዜና ለአንድ ጊዜ ብቻ መሆን አለበት፡፡
By lawyer Tsegaye Demeke
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም በወጣው አንቀጽ 39 (1) (ሸ) መሠረት አንድ ሰራተኛ በገዛ ፈቃዱ ሲለቅ የስራ ስንብት ክፍያ ለማግኘት ቢያንስ አምስት ዓመት በአሠሪው ዘንድ የሥራ አገልግሎት ሊኖረው ይገባል።
Addis Abeba laws ቅፅ 1.pdf
3.7 MB
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተጠቃለሉ ህጎች…