አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ!

የ2012 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች #መግቢያ ቀናት እንደሚከተለው እንዲሆን ተወስኗል፦ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 22-23/2012 ዓ.ም እንዲሁም አዲስ ተማሪዎች ከመስከረም 28-29/2012 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል።

ምንጭ፦አስራት አፀደወይን የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት

የዩኒቨርሲቲ ጉዳዮችን ብቻ
ደንብ መተላለፍ በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#መግቢያ
በኢትዮጵያ ህግ ቅጣት ሊያስከትሉ የሚችሉ ድርጊቶችን ከክብደታቸው እና ከሚያስከትሉት ሀላፊነት አንፃር በወንጀል ህግ የሚያስቀጡ እና በደንብ መተላለፍ ህግ የሚያስቀጡ ብለን ልንከፍል እንችላለን፡፡ በደንብ መተላለፍ የሚያስቀጡ ድርጊቶች በኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ ሰባተኛ መፅሀፍ እና ስምንተኛ የተደነገጉ ሲሆን ቅጣትን የሚመለከቱ ደንቦች እና የህጉ ተፈጻሚነት ወሰን በወንጀል ህጉ ተካቶ ይገኛል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የደንብ መተላለፍ ምንነት እና ከወንጀል ሀላፊት በምን እንደሚለይ ፣ የደንብ መተላለፎች የሚያስከትሉት ቅጣት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ፡፡
የደንብ መተላለፍ ምንነት
አንድ ሰው ደንብ ተላልፏል የሚባለው ሥልጣን ያለው አካል ባወጣው ህግ የተመለከተውንና አንድ ነገር እንዳይፈፀም የሚያዘውን ወይም የሚከለክለውን ድንጋጌ የተላለፈ ወይም በወንጀል የማያስቀጣ ቀላል ጥፋት የፈፀመ ሲሆንና የዚህ ዓይነቱ ህግ መጣስ ወይም ቀላል ጥፋት በወንጀል ህጉ ከአንቀፅ 746 እስከ 775 በተመለከቱት ድንጋጌዎች የሚያስቀጣ ሲሆን ነው፡፡ በዚሁ መሰረት በወንጀል ህጉ የደንብ መተላለፍ ህግ ላይ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በቀር የነገሩን ዓይነት እንዲሁም የህጉን መንፈስና ግብ በመመልከት የወንጀል ህጉ ጠቅላላ ክፍል መሰረታዊ መርሆችና ደንቦች በደንብ መተላለፍ ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
የደንብ መተላለፍ አይነቶች
የደንብ መተላለፍ ህጉ በውስጡ የተለያዩ አይነት የደንብ መተላለፎችን የያዘ ሲሆን እነዚህ መተላለፎች በስራቸው ዝርዝር የጥፋት አይነቶችን ከሚያስከትሉት ቅጣት ጋር አካተው ይገኛሉ፡፡ የደንብ መተላለፍ አይነቶቹም በመንግስትና ህዝብ ጥቅም ላይ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ተግባሮች( ለምሳሌ ህጋዊ ገንዘብን አለመቀበል)፤ ወታደራዊ ግዴታዎችን መጣስ እና በመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም በፖሊስ ላይ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች፤ በመንግስት የስራ ግዴታዎች እና በመንግስት መስሪያ ቤት/ባለስልጣን/ ላይ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች(ለምሳሌ ሀቀኝነትን ማጓደል)፤ በሕዝብ ደኅንነት፣ሰላምና ተረጋግቶ መኖር ላይ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች(ለምሳሌ ሐሰተኛ የአደጋ ምልክት መስጠት)፤ በሕዝብ ጤና እና በፅዳት ጥበቃ ላይ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች( ለምሳሌ መርዛማና አደንዛዥ ንጥረ ነገሮችና መድሀኒቶች ለመቆጣጠር የወጣ ደንብ) እና በሰዎችና በንብረቶች ላይ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች ናቸው፡፡

ደንብ መተላለፍ ተፈፃሚ የሚሆንባቸው ጥፋቶች
በህጋዊነት መርህ እንደተመለከተው በደንብ መተላለፍ ህግ ወይም በሌላ ህግ የተደነገጉ ጥፋቶች ብቻ የሚያስቀጡ ሲሆን የሚያስቀጡትም በህጉ የተቀመጡትን ቅጣቶች ብቻ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የደንብ መተላለፍ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆኑት ለተፈፀመው ድርጊት የበለጠ ቅጣት የሚደነግጉ አንቀፆች በሌሉ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም አንድ ድርጊት የሚያስቀጣው በወንጀል ህግ ወይም በደንብ መተላለፍ ህግ በአንደኛው እንጂ በሁለቱም ሊሆን አይችልም፡፡ እንዲሁም የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሰራ መሆኑ መርህ በተመሳሳይ ለደንብ መተላለፍ ይሰራል፡፡ በመሆኑም የደንብ መተላለፍ ተግባሮች የሚያስቀጡት በተፈፀመበት ጊዜ ፀንተው ባሉት ድንገጌዎች መሰረት እንጂ ከድርጊቱ በኋላ የወጣን ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ እንዲፈፀም በማድረግ አይሆንም፡፡
በሌላ በኩል የደንብ መተላለፍ ተግባርን ለመፈፀም የሚደረጉ የመዘጋጀትና የሙከራ ድርጊቶች የማያስቀጡ ሲሆን ለደንብ መተላለፍ የሚደረግ ማነሳሳት፣አባሪነት እና ወንጀል ከፈፀመ በኋላ ወንጀል አድራጊውን መርዳት አያስቀጣም፡፡ ይህ ማለት የሚቀጣው ደንብ ተላላፊው ብቻ ነው ማለት ነው፡፡ እንዲሁም የህግ ሰውነት የተሰጠውን ሰው በአነሳሽነት ወይም በአባሪነት የማይቀጣ ሲሆን የድርጅቱ ሀላፊ ወይም ሰራተኛ የሚቀጣው በወንጀል ህጉ መሰረት በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ደንብን ወይም መመሪያን በዋና ደንብ ተላላፊነት በሚጥስበት ጊዜ ብቻ ነው፡፡

በተጨማሪም በወንጀል ህጉ አንቀጽ 743 እንደተደነገገው የማያስቀጡና ይቅርታ የሚሰጡ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነዚህም በህግ የታዘዙ ወይም የተፈቀዱ ድርጊቶች፣ የሞያ ስራ ግዴታ፣ የተጎጂው ፍቃድ ፣ ፍፁም የሆነ መገደድ፣አስፈላጊ ሁኔታ እና ህጋዊ መከላከልን የሚመለከቱ የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች ለደንብ መተላለፍም ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ ይሁንና ደንብ የተላለፈ ማንም ሰው ህግ አለማወቅን ወይም የማድረግ መብት አለ ብሎ መሳሳትን እንደመከላከያ ምክንያት አድርጎ ሊያቀርብ አይችልም፡፡

ለደንብ መተላለፍ ተፈፃሚነት ያላቸው ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎች

ለደንብ መተላለፍ መደበኛ የሆኑ የወንጀል ቅጣቶች ተፈፃሚ የማይሆኑ ስለሆነ ምንጊዜም ቢሆን ለወንጀሎቹ በተወሰኑት ፅኑ እስራት ወይም በቀላል እስራት አይቀጡም፡፡ ይህም የሚያመለክተው ደንብ መተላለፍ ከወንጀል የሚለየው በሚያስከትለው የተለየ ቅጣት እንደሆነ ነው፡፡ ስለሆነም የደንብ መተላለፍ ድርጊቶች በተፈፀሙ ጊዜ የሚወሰነው ነፃነትን የሚያሳጣ ቅጣት የማረፊያ ቤት እስራት እንጂ የማረሚያ ቤት እስራት አይሆንም፡፡ መደበኛ የማረፊያ ቤት እስራት የሚፈፀመው ከፍርድ ቤቶች ወይም ከፖሊስ ጣቢያዎች ጋር በተያያዙ ልዩ የመቆያ ቦታዎች ይሆናል ማለት ነው፡፡ እንዲሁም በማረፊያ ቤት እስራት ፈንታ የግዴታ ስራን ፍርድ ቤት ሊወስን የሚችልባቸውን ሁኔታዎች የደንብ መተላለፍ ህጉ ደንግጎ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በማናቸውም ጊዜ ቢሆን በማረፊያ ቤት እስራት እንዲቀጣ የተፈረደበት ሰው ወደ ጠባይ ማሻሻያ ወይም ማረሚያ ቤት እንዲላክ ፣በወንጀል ምክንያት ከተቀጡት እስረኞች ጋርም እንዲቀላቀል ማድረግ አይቻልም፡፡

በወንጀል ህጉ አንቀጽ 747 እና 768 እንደተደነገገው የደንብ መተላለፍ ድርጊቶች በተፈፀሙ ጊዜ የሚወሰነው ቅጣት እና የህጉ ልዩ ድንጋጌዎች የሚያስቀምጡት ከፍተኛ ቅጣት የማረፊያ ቤት እስራቱ የሚቆይበት ጊዜ ከአንድ ቀን እስከ ሶስት ወር ይሆናል( በደጋጋሚነት እና በመደራረብ ጊዜ ከሁለት ዓመት የማረፊያ ቤት እስራት አይበልጥም) ፡፡ በተጨማሪም ደንብ ተላላፊዎች ወታደሮች ወይም ወጣት ጥፋተኞች ሲሆኑ የሚፈፀመው የተለየ ቅጣት እንደተጠበቀ ሆኖ በደንብ መተላለፍ ረገድ የሚፈፀሙ ቅጣቶች በደንብ መተላለፍ ህግ በተደነገገው መሰረት ይሆናል፡፡ እንዲሁም ለህብረተሰቡ ሲባል የጥበቃ ወይም የሕክምና እርምጃዎች መወሰድ ሲኖርባቸው በተለየ ኃላፊ ሊሆኑ የማይችሉ ሰዎችን በሚመለከት ፍርድ ቤት አግባብነት ላለው የአስተዳደር ባለስልጣን ያሳውቃል፡፡

ሌላው በደንብ መተላለፍ ህጉ ለደንብ መተላለፍ ጥፋት የተቀመጠው ቅጣት የገንዘብ መቀጮ ቅጣት ነው፡፡ ይኸውም ጥፋተኛው ደጋጋሚ ካልሆነ ወይም የህጉ ልዩ ድንጋጌ የበለጠ ካልወሰነ በቀር በደንብ ተላላፊ ላይ የሚጣል መቀጮ ከአንድ ብር እስከ ሶስት መቶ ብር ለመድረስ የሚችል ሲሆን ጥፋቱ በተደጋገመ ጊዜ የሚደረገው የቅጣት ማክበጃ እንደተጠበቀ ሆኖ ተላላፊው ጣፋቱን የፈፀመው በአፍቅሮ ንዋይ እንደሆነ መቀጮው እስከ አምስት መቶ ብር ሊደርስ ይችላል፡፡ እንዲሁም ለተፈረደበት ሰው ቢያስፈልግም ከፋፍሎ በየጊዜው ዕዳውን እንዲከፍል በመፍቀድ ፍርድ ቤቱ እስከ ሶስት ወር ለመድረስ በሚችል የመክፈያ ጊዜ ሊወስንለት የሚችል ሲሆን ሁኔታዎች በቂ ምክንያት ያስገኙ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የመከፈያ ጊዜውን እስከ አንድ አመት ሊያራዝመው ይችላል፡፡...👇ይቀጥላል👇👇
#የማስረጃ_ዓይነቶች_እና_ማስረጃ_ስለማያስፈልጋቸው_ፍሬ_ነገሮች
#መግቢያ

የአንድን ፍሬ-ነገር መኖር ወይም አለመኖር ማረጋገጥ የሚቻለው ማስረጃ በማቅረብ ነው፡፡
ማስረጃ በሰው ምስክሮች፣ በዘገባ፣ በሰነድ፣ ተጨባጭነት ባላቸዉ ሊታዩና ሊዳሰሱ በሚችሉ ነገሮች እና በኤግዚቢት መልክ ሊቀርብ ይቻላል፡፡ አቀራረቡም በሕግ በተደነገገው መሰረት ነው፡፡ በክርክር ሂደት ማስረጃ የማያስፈልጋቸው ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ይህ ከፍሬ ነገሩ የተለየ ባህሪ ወይም የሚያከራክር ነገር ባለመኖሩ ምክንያት ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ የማይሆንባቸዉ ሁኔታዎች ስላሉ ነዉ፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ ስለ ማስረጃ ዓይነቶችና ማስረጃ ስለማያስፈልጋቸው ጉዳዮች እንመለከታለን፡፡
1. #የማስረጃ_ዓይነቶች
ማስረጃ የአንድን ፍሬ ነገር መኖር ወይም አለመኖር ለማረጋገጥ ወይም ለማስተባበል ከሚቻልባቸው ዘዴዎች እና ማስረዳት ከሚፈለገው ፍሬ ነገር ወይም መደምደሚያ ጋር ማስረጃው የሚኖረውን ግንኙነትን መሠረት በማድረግ በተለያዩ መንገዶች ከፋፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
 ፍሬ ነገርን ለማስረዳት ከምንጠቀምበት ዘዴ አንጻር፤
ሀ. የሰው ማስረጃ
ሰዎች በአካል ፍርድ ቤት ቀርበዉ ለችሎት መረጃ የሚሰጡበት መንገድ ሲሆን ፍሬ ነገሩን ለፍርድ ቤቱ የሚገልፁት በንግግር ወይም በምልክት ነው፡፡ ይህም የምስክርነት ቃል ይባላል፡፡ የሰው ማስረጃዎች ቀጥተኛ ምስክር፣ የአከባቢ ምስክርና የባለሞያ ምስክር ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ለ. የሰነድ ማስረጃ
ይህ የማስረጃ ዓይነት በላዩ ላይ የተፃፈበት፣ የተሳለበት ወይም ማናቸዉም ዓይነት ምልክት የተደረገበት ሲሆን ለምሳሌ ውሎች፣ ቼኮች፣ ለፖሊስ ወይም ለፍርድ ቤት የተሰጠ የዕምነት ቃል የተመዘገበበት፣ በጽሁፍ የተገለፀ የላብራቶሪ ወይም የህክምና ምርመራ ውጤት የሰነድ ማስረጃዎች ናቸው፡፡
ሐ. ገላጭ ማስረጃ
ይህ የማስረጃ ዓይነት ፍርድ ቤት እንዲያየውና ግንዘቤ እንዲወስድበት የሚቀርብ ማስረጃ ነው፡፡ ለምሳሌ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረት ወይም ወንጀል ለመፈፀም አገልግሎት ላይ የዋለ መሣሪያ በማስረጃነት ሲቀርብ ገላጭ ማስረጃ ይባላል፡፡
 ማስረዳት ከተፈለገው ፍሬ ነገር አንጻር፤
 ቀጥተኛ የሆነ ማስረጃ
ማስረጃ ቀጥተኛ ነዉ የሚባለው አንድን በጭብጥነት የተያዘ ፍሬ ነገር ወይም የተወሰደን መደምደሚያ ትክክለኛነት በቀጥታ ለማረጋገጥ ወይም ለማስተባበል የሚቀርብ ሲሆን ነዉ፡፡ ከዚህ አንፃር ምስክር ቀርቦ በጭብጥ የተያዘው ፍሬነገር መኖሩን ወይም አለመኖሩን ራሱ በስሜት ህዋሳቱ አማካኝነት በማየት፣ በማሽተት፣ በመቅመስ፣ በመስማት ወይም በመዳሰስ ያወቀ መሆኑን የሚመሰክር ሲሆን ቀጥተኛ ማስረጃ ይባላል፡፡ በሰነድ ማስረጃ በኩልም በማስረጃነት የቀረበው ሰነድ በጭብጥ የተያዘዉ ፍሬ ነገር መኖርን ወይም የተደረሰበት መደምደሚያ ትክክለኛ መሆኑን ሰነዱ ራሱ በቀጥታ ያረጋግጣል ወይም ያስተባብላል በሚል የቀረበ ከሆነ ቀጥተኛ ማስረጃ ይባላል፡፡ ለምሳሌ በቂ ስንቅ ሳይኖረው ቼክ ፈርሞ ሰጥቷል በሚል ገንዘብ እንዲከፍል በተከሳሽ ላይ ለቀረበ ክስ ከሳሽ ቼኩን በማስረጃነት ያቀረበ ቢሆን ተከሳሹ ስለመፈረም አለመፈረሙ እና ስለ ገንዘቡ ልክ ቼኩ በቀጥታ የሚናገር ስለሆነ ቀጥተኛ ማስረጃ ይባላል፡፡
 ቀጥተኛ ያልሆነ ማስረጃ
ማስረጃ ቀጥተኛ ያልሆነ ነዉ የሚባለው ከሁለት ሁኔታዎች አንፃር ነዉ፡- አንደኛዉ ማስረጃ ያስረዳል የተባለዉን ፍሬ ነገር ምንጭ ማስረጃዉ ራሱ በቀጥታ ያወቀዉ ሳይሆን ከሌላ ያገኘዉ ወይም የተረዳዉ ሲሆን ነዉ፡፡ ምስክር ሌላ ሰዉ የገለፀለት መሆኑን ጠቅሶ የሚመሰክር ሲሆን ቀጥተኛ ሳይሆን የስሚ ስሚ ማስረጃ (Hearsay Evidence) ይባላል፡፡ የስሚስሚ ማስረጃን ቀጥተኛ ያልሆነ የሚያሰኘዉ ማስረጃዉ ፍሬ ነገሩን የሚገልፀዉ ራሱ በቀጥታ እንዳወቀ ሳይሆን ከሌላ ሰዉ የሰማዉ ወይም ከሰነድ ያነበበዉ በመሆኑ ነዉ፡፡ በሰነድ ማስረጃም በኩል የስሚ ስሚ የሚያሰኘዉ ማስረጃ ሆኖ የቀረበዉ ሰነድ ላይ የተገለፀዉ ፍሬ ነገር አዉቃለሁ በሚል በሌላ ሰዉ የተዘጋጀ ሲሆን ነዉ፡፡
ሁለተኛዉ ቀጥተኛ ያልሆነ ማስረጃ ነዉ የሚባልበት ሁኔታ የሚያጋጥመዉ አካባቢያዊ ማስረጃ (Circumstantial Evidence) የቀረበ እንደሆነ ነዉ፡፡ አካባቢያዊ ማስረጃ በጭብጥ ስለተያዘዉ ፍሬ ነገር መኖር አለመኖር በቀጥታ አይነግረንም፡፡ ይልቁንም የተወሰኑ ፍሬ ነገሮችን መኖር ወይም አለመኖር በማረጋገጥ ከዚህ ተነስተን በጭብጥ የተያዘዉን ፍሬ ነገር በተመለከተ አንድ ዓይነት መደምደሚያ ላይ እንድንደርስ የሚያደርግ ነዉ፡፡
የማስረጃዉ ቀጥተኛ ወይም አካባቢያዊ መሆን አለመሆኑን መለየት በማስረጃ ምዘና ጊዜ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ፡፡
1. ማስረጃ ስለማያስፈልጋቸዉ ፍሬ ነገሮች
ከፍሬ ነገሮቹ የተለየ ባህሪ ወይም የሚያከራክር ነገር ባለመኖሩ ምክንያት ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ የማይሆንባቸዉ ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነሱም፡-
ሀ. ፍርድ ቤት ግንዛቤ ሊወስድባቸዉ የሚችሉ ወይም የሚገቡ ፍሬ ነገሮች፣ ለምሳሌ በአዋጅ ቁጥር 3/1987 መሠረት በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ላይ የወጡ ነገሮችን ፍርድ ቤቶች ሊቀበሏቸዉ እንደሚገባ ተደንግጓል፡፡ በነጋሪት ጋዜጣ ላይ የተገለፀ ፍሬ ነገር ለማረጋገጥ ሌላ ማስረጃ መቀበል አያስፈልግም፡፡ ጋዜጣዉን በመመልከት ብቻ ግንዛቤ ሊወሰድበት ይገባል፡፡
ለ. በፍርድ ቤት በሚደረግ የክርክር ሂደት በተከራካሪ ወገን የታመኑ ፍሬ ነገሮች፣
ሐ. ጠቅላላ እዉነታዎች (Universal Truth)፣
መ. የሕግ ግምቶች (Presumptions) ናቸዉ፡፡ ለምሳሌ በጋብቻ ውስጥ የተፀነሰ (የተወለደ) ልጅ አባቱ ባልየው እንደሆነ ህጉ ግምት ይወስዳል፡፡
በአጠቃላይ ግራ ቀኝ ተከራካሪ ወገኖች ያስረዱልናል የሚሏቸዉን ማስረጃዎች ወይም ማስረጃ ባይቀርብባቸዉም በሕግ መሠረት የሚወሰኑትን ለይቶ ለማቅረብ የማስረጃ ዓይነቶችን እና ማሰረጃ የማያስፈለጋቸዉን ፍሬነገሮች ማወቁ ተገቢ ነዉ፡፡
https://t.me/lawsocieties
ምንጭ፡- FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር (13/01/2015 E.C)