አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የአድራሻ ለውጥ ስለማሳወቅ
******
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንፍስ ስልክ ላፍቶ ምድብ ችሎት የዳኝነት አገልግሎት ጀርመን አደባባይ ፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጀርባ እየሰጠ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንፍስ ስልክ ላፍቶ ምድብ ችሎት ከሚያዚያ 3/2014 ዓ.ም ጀምሮ የፍትህ ሚኒስቴር ባስገነባው እና ፍርድ ቤት በጋር በሚጠቀምበት መብራት ኃይል ለቡ ቫልኔሮ ፊት ለፊት በሚገኘው የተሻለ የስራ ከባቢ፣ በቂ የችሎት አዳራሾች፣ የአንድ መስኮት አገልግሎት ለተገልጋዮች ለመስጠት በሚያስችለው ህንጻ ላይ አገልግሎት መስጠት የምንጀምር መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ማህበረሰብ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
#አለ_ዜና
#አለ_ህግ #አለ_ልዩልዩ #አለ_ችሎት #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
የማይንቀሳቀስ ንብረት ውሎችን በተመለከተ የሰበር ውሳኔ -
#አለ_ህግ
1. የማይንቀሳቀስ ንብ የሚመለከቱ ውሎች በህግ ፊት የሚፀኑ እንዲሆኑ ሁለት መስፈርቶችን ሟሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የመጀመሪያው መስፈርት ውሉ በፁሁፍ መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው ውሉ በአዋዋይ ወይም በፍርድ ቤት መዝገብ ፊት መከናወኑ

2. የፍ/ብ/ህግ ቁ.1723(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በአዋዋይ ወይም በፍርድ ቤት ፊት እንዲደረግ የሚጠይቀው በተዋዋዮች መካከል በሕግ ፊት የሚፀና ውል እንዲኖር ለማድረግ ነው፡፡

3. የፍ/ ብ/ህ/ቁ/ 2878 የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ምዝገባ እንዲከናወን የሚጠይቀው ውሉ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ውጤት እንዲኖረው ለማድረግ ነው፡
"ስለ ውሎች በጠቅላላው" ምእራፍ ስር የሚገኘው የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 1723 እና “ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ" ስር የሚገኘው የፍ/ብ/ ህ/ቁ/ 2878 ድንጋጌዎች መካከል ልዩነት ቢኖርም በመካከላቸው ግልፅ የሆነ ግጭት የሆነ ግጭት የሌለ በመሆኑና የማይንቀሳቀስ ንብረትን ባለቤትነት ለማስተላለፍ ከሌሎች ውሎች የበለጠ ጥንቃቄና ጥበቃ ስለሚሻ አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት የሽያጭ ውልን የአፃፃፍ ፎርም በሚመለከት ገዢ ድንጋጌ መሆን ያለበት የተለየና ጥብቅ መስፈረት የሚያስቀምጠው የፍ/ ብ/ህ /ቁ/ 1723 ነው። የሰመ/ቁ/ 21448 ሚያዚያ 30/1999 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት።

#አለ_ትምህርት
#አለ_ህግ #አለ_ልዩልዩ #አለ_ችሎት #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
የሁከት ይወገድልኝ የሰበር ውሳኔዎች
#አለ_ህግ
1// ሰ/መ/ቁ.80241 ቅጽ 15፣

በፍ/ሕ/ቁ. 1149/1/ መሰረት የሁከት ይወገድልኝ ክስ መቅረብ የሚችለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻመ በሆነው ነገር በቀጥታ ወይም በጠባቂ ይዞታ ሲኖረው ነው። እንዲሁም የይዞታ ክስ የሚቀርበው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት በወቅቱ ለመያዝ ምንም ዓይነት መብት በሌለው ሰው ላይ ስለመሆኑም የድንጋጌው መንፈስ ያስረዳል። የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ አቅራቢ በማስረጃ ማረጋገጥ ያለበት ንብረቱ በይዞታው ስር የነበረና የሁከት ድርጊት ፈፃሚው ...

የኃይል ተግባር በመጠቀም ወይም በሚስጢር ንብረቱን የወሰደበት መሆኑን ነው፡፡ ሁከት ተፈጥሯል የሚባለው ባለይዞታ የሆነው ሰው በይዞታው ስር በሚገኘው ንብረት እንዳይገለገልበ ሌላ ሰው ጣልቃ ገብቶበት መሰናክል ሲፈጥርበት ወይም ረብሻ ሲፈጥርበት ነው።

2// ሰ/መ/ቁ. 38228 ቅጽ 9 የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ ከሳሹ ማስረዳት ያለበት ባለቤትነት ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዳለው ሳይሆን ክስ ያቀረበበት ንብረት ህጋዊ ባለይዞታ መሆኑ በሌላ አነጋገር ሁከት የተፈጠረበትን ነገር በእጁ አድርጎ በእውነት ሲያዝበት እንደነበር ነው።
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ልዩልዩ #አለ_ችሎት #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መጀመሪያ ራስህን ከእሳት ስታወጣ ከአንተ በኋላ ያለውን ትዉልድ ነፃ ታወጣለህ። አብሬ ልሙት ካልክ ግን አለምን ታጠፋታለህ።
የአመለካከት፣የህይወት ክህሎትና የስኬት መንገድ መጀመሪያ ራስን ለማዳን ከተለመደው አሰራርና አስተሳሰብ ራስን ማዉጣት ነው። የተፈጠርነው በአላማና በምክንያት እንጂ ባጋጣሚ አይደለምና።

ስለዚህ ራስህን ከመጥፎ ልማድ ፣ ከመጥፎ አመለካከት ፣ ከመጥፎ አስተሳሰብ ፣ ከመጥፎ የህይወት ዘይቤ ፣ ከከሳሽነት ፣ ከአማራሪነት፣ ከሰበብ ፣ ከስንፍና ፣ ከዘረኝነት......ነፃ አዉጣ።
ያኔ ታሪክህ ይቀየራል ለብዙዎችም ትተርፋለህ።

መልካም ቀን


ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 2035(2)..................... 🙏

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ልዩልዩ #አለ_ችሎት #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Current Jobs at Bunna Insurance S.C

1: Driver II
2: Legal Aid
3: Marketing officer

📌ሰለ ሰራው ሙሉ መረጃ ለማየት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ👇👇
👉Read Detail:- https://bit.ly/3wPDO2G
በፅሁፍ ያልተደረገ የሥራ ዉልን በሚመለከት
#አለ_ህግ
በመርህ ደረጃ በህግ በተለየ አኳኋን ካልተደነገገ በቀር የሥራ ዉል የተለየ ፎርም እንደማያስፈልገዉ ከአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ አንቀጽ.(5) መረዳት ይቻላል። በአዋጁ አንቀጽ.(7) ንዑስ አንቀጽ(1) መሰረት የሥራ ዉል በጽሑፍ ያልተደረገ ከሆነ አሠሪዉ እና ሰራተኛዉ በቃል የዉል ስምምነት ባደረጉ በአስራ አምስት ቀናት ዉስጥ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ.(6) መሰረት የሚከተሉትን ዝርዝር ሁኔታዎች የያዘ የጹሑፍ መግለጫ አሠሪዉ ፈርሞ ለሠራተኛዉ መስጠት እናዳለበት ተመላክቷል እነሱም፡

የአሠሪዉን ስምና አድራሻ፣
የሠራተኛዉን ስምና እድሜ፤አድራሻና፤የሥራ ካርድ ቁጥር ካለ፣
የሥራዉ ዓይነትና ቦታ፣
ለሥራ ሚከፈለዉን የደመወዝ መጠን፤የስሌቱ ዘዴ፤ የአከፋፈሉ ሁኔታና ጊዜ፣
ዉሉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ፣
የተዋዋዮች ፊርማ።
ሠራተኛዉ የጽሑፍ መግለጫዉ በደረሰዉ በ15 ቀናት ዉስጥ በሙሉም ሆነ በከፊል ካልታቃወመ መግለጫዉ በአሠሪዉና በሠራተኛዉ መካከል የተደረገ የሥራ-ዉል እንደሚቆጠር ከአዋጁ አንቀጽ.(7) ንዑስ አንቀጽ(2) መገንዘብ ይቻላል። ነገር ግን ከአዋጁ አንቀጽ.8 በግልጽ መረዳት እንደሚቻለዉ ከላይ የተዘረዘሩት ሁኔታዎች አለመሟላት ሠራተኛዉ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጁ የሚያገኛቸዉን መብቶች የሚያሳጣ ዉጤት አይኖረዉም።
እያጋራችሁ
#አለ_ችሎት #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
ውልን 'ስላለመፈም"
የፍትሐብሔር ህግ አንቀጽ 1771 የውል አለመፈጸም ስለሚያስከትለው ነገር

(፩) ከተዋዮቹ ፡ አንዱ " የውል ፡ ግዴታ ያልፈጸመ ፡ እንደሆነ ' ሌላው ወገን ፡ እንደ · ነገሩ አጋጣሚ ሁኔታ ውሉን ' እንዲፈጽምለት · ሊጠይቅ፡ ይችላል ! ይህም ፡ ባይሆን የውሉን ' መፍረስ ' ራሱ ፡ ሊጠይቅ ፡ ወይም ሊገልጽ ፡ ይችላል "
በሌላ በኩል ደግሞ የውሉ አለመፈጸም ጕዳይ ጉዳት ስላደረሰበት የጉዳት ኪሣራ እንዲከፈለው ለመጠየቅ መብት ይኖረዋል "
1772-የማስጠንቀቅ አስፈላጊነት።
እንደ ' ውሉ ' ሳይፈጸምልኝ ቀርቷል በማለት፡ ክርክር፡ለማቅረብ የሚፈልገው ' አንደኛው ' ወገን ፡ ተዋዋይ የተዋዋለው ሰው ግዴታውን እንዲፈጽ ምለት ለማድረግ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ሊሰጠው ያስፈልጋል "

1773 ማስጠንቀቂያ የሚደረግበት' ሥርዐትና' ( ፎርም ) ' ዘመን "

(5) የማስጠንቀቂያ ፡ መስጠት ' ጕዳይ ፡ የሚደረገው ፡ ይህን ፡ እንድትፈጽም ፡ የሚል፡ እንደ፡ መጨረሻ ትእዛዝ፡ በሆነ ማስታወቂያ ወይም በሌላ አድራጎት የባለገንዘቡን አሳብ መግለጫ በሆነ ዐይነት የሚቀርብ የውሉን ፍጻሜ ለማግኘት የሚደረግ ተግባር ነው።
#አለ_ችሎት #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Lawyer at Black Infinity Solution Consultancy S.C
#አለ_ህግ #አለ_ስራ
Company: Black Infinity Solution Consultancy S.C
Location: Ethiopia
State: Addis Ababa Jobs
Job type: Full-Time
Job category: Black Infinity Solution Consultancy

Job Requirement
Academic qualification: LLB in law
Minimum experience: 0 years
Salary:  Birr 6,000
Location: Addis Ababa

Method of Application

Submit your CV, copies of relevant documents and Application to :
Megenagna – around Lem Hotel; Amare Abraham building 12th floor, Addis Ababa;
Phone number: – +251965082791
Closing Date : 5 April. 2022
#አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
።።።።።።።።። የወሊድ ፈቃድ ።።።።።
#አለ_ህግ
አዲሱ የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አዋጅ ነፍሰጡር ለሆነች ሠራተኛ ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ አሠሪው ከደመወዝ ጋር ፈቃድ ይሰጣታል፤ ሆኖም ሠራተኛዋ ከምርመራ በኋላ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ አለባት፡፡

ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ከመውለዷ በፊት ሐኪም እንድታርፍ ካዘዘ አሠሪው ከክፍያ ጋር እረፍት ይሰጣታል፡፡

ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት የ 30 (ሰላሳ) ተከታታይ ቀናት የቅድመ-ወሊድ ፈቃድ ፣ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ ለ 90 (ዘጠና) ተከታታይ ቀናት የድህረ-ወሊድ ፈቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጣታል፡፡
ሠራተኛዋ ከመውለዷ በፊት የወሰደችው የ 30 (ሰላሳ) የሥራ ቀናት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ካልወለደች እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ከላይ በቁጥር ሁለት ስር በተመለከተው መሠረት እረፍት ልታገኝ ትችላለች፡፡
የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 88 መሰረት
የ 30 (ሰላሳ) የሥራ ቀናት የቅድመ-ወሊድ ፈቃዷ ሳያልቅ ከወለደች 90 (ዘጠና) የሥራ ቀናት የድህረ-ወሊድ ፈቃዷ ይጀምራል ማለት ነው፡፡
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Top 10 countries with the worst education system in Africa.
በአፍሪካ የከፋ የትምህርት ስርዓት ያላቸው 10 ምርጥ ሀገራት።

5. Ethiopia (0.622 EDI) Worst education system in Africa
Ethiopia brings us to number 5 with a 0.622 EDI - barely nudging out Eritrea by 0.001 and an ALR of 39%; the 5th lowest in the world. With some of the lowest educational statistics in the world, the system in Ethiopia looks bleak for the country's schoolchildren. -

With a Gross Enrollment Ratio of 5.5%, the situation would seem almost hopeless but a recent World Bank publication states that the WB's Board of Executive Directors has "approved major financing for Ethiopia to transform the quality of its teaching and learning for more than 21 million children in primary and secondary schools". The project will receive US $550 million of investment towards their goal of increasing educational quality in the country. Hopefully the project is successful and Ethiopia can find its way out of the bottom rungs of international education rankings.
#አለ_ህግ
በአፍሪካ የስከፊ የትምህርት ስርዓት ካላቸው 10 ምርጥ ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ 5ኛ በመሆን (0.622 EDI) በአፍሪካ የከፋ የትምህርት ሥርዓት ያላት አገር ሆናለች።
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
ሕግን አለማወቅ

ዜጎች ማወቅ ከሚጠበቅባቸው የህግ ፍልስፍናዎች ውስጥ የመጀመሪያው የሚተዳደሩበትን ህግ ማወቅ ግዴታቸው መሆኑ ሲሆን ፡ ይህ ፍልስፍና በሰው ልጆች ታሪክ አስቀድሞ የተፈጠረው ግንዛቤ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለረጅም ጊዜ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ባህል እንደሆነ ተቆጥሯ ፡፡
በዚህም መሰረት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 81 በህግ ላይ ስለመሳሳትና ህግን ስላለማወቅ በሚል ርዕስ ይህንን መርህ አስመልክቶ የሚከተለውን ደንግጓል ፡፡
( ህግን አለማወቅ ወይም በህግ ላይ መሳሳት መከላከያ ሊሆን አይችልም )፡፡

ከዚህ ድንጋጌ እንደምንረዳው ህግን አለማወቅ ከጥፋተኝነት አያድንም ፡፡ ስለሆነም አንድ የወጣን ህግ አላውቅም በማለት ከቅጣት ለመዳን ስለማይቻል ሰዎች የህግ እውቀታቸውን ለማዳበር ጥረት ማድረግ የግድ ያስፈልጋቸዋል ፡፡
በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የትኛውም ህግ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚጸና መሆኑን የወጣው አዋጅ እራሱ ያውጃል ፡፡ ስለሆነም ህግን ማወቅ ያለባቸው የህግ አስፈፃሚዎች ብቻ ሳይሆኑ እያንዳንዱ ሰው ህግን የማወቅ ግዴታ የተጣለበት ሲሆን ፡ መንግስት በበኩሉ ያወጣውን ህግ ለህዝብ የማሳወቅ ስራውን በአግባቡ የመወጣት ኃላፊነቱን መወጣቱን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል ፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ሰዎች አንድን የወጣን ህግ ባለማወቃቸው ምክንያት ለሚፈጽሙት ጥፋት ህጉን አላውቅም ነበር በማለት መከላለያ ሊያቀርቡ እና ከቅጣት ነጻ ሊወጡ አይችሉምና ፡፡
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
United Beverages Share Company በሚከተለው የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Position:-Legal Assistant

🔷ትምህርት ዓይነት እና ደረጃ:-

Educational Qualification: LLB Degree

Experience Level: 0-2 years (Junior Level)

🇪🇹 የስራ ቦታ:- Addiss Ababa
🧭የምዝገባ ጊዜ /Deadline/: እስከ ሚያዚያ2/2014 ዓ.ም
🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://jobs.amazonethiopia.com/job/legal-assistant/
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
አለ_ህግን ለወዳጅ ዘመድዎ እና ለጓደኛዎ አጋርተዋል
አሁኑኑ ሼር ያድርጉት እና ውለታ ይዋሉ።

#አለ_Share..... #Share #Ale_Law #አለ_ስራ #አለ_ችሎት #አለ_ጠበቃ
አለ_ህግ፣ #አለ_ህግ አማካሪ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ክሶች፣ የውል ፎርሞች፤ የህግ መፅሐፍቶች 🔴ሁሉም ሕጎች በአንድ🔴 All in one, for All.
አለ_ህግ፣ መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው። contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.com
https://t.me/lawsocieties
።።።።።።።። ቀብድ የሕግ ውጤቱ ።።።።
#አለ_ህግ #Ale_Lawsocieties
ለዘመናት በተገለገልንበት በኢትዮጵያ ፍትሃብሄር ሕግ ስለ ቀብድ ጠለቅ ያለ ወይም ግልፅ የሆነ ትርጉም የለም።
ነገር ግን Blacks law dictionary ስለ ቃብድ ትርጉም ያስቀምጠዋል"
ቀብድ ማለት ሊሸጥ ወይም ሊተላለፍ የታሰበውን የእቃውንው ወይም የሸቀጡን የተወሰነ ያህል ክፍል ቅድመ ክፍያ ማለት ሲሆን አላማውም ዉል በሚፈፀምበት ጊዜ ገዥው ለመዋዋል ፍቃደኛ መሆኑን እና እንደ ማረጋገጫ የሚያገለግል ነው ይላል"
በአገራችን በኩል ደግሞ የመጀመሪያው ሕጋዊ ውጤት ተዋዋይ ወገኖች እንደ ውላቸው ውሉ ሲፈፀም ሻጩ ሁለት አይነት አማራጭ ይኖሩታል አንደኛው ቀብዱን በማቆየት ቀሪውን ገንዘብ ከሻጩ መቀበል አልያም ቀብዱን በመመለስ ሙሉ ክፍያውን መጠየቅ ይችላል በሚል ፍ/ሕ/ቁ 1884 ይደነግጋል ሀገራችን የተለመደው አሰራር ግን የመጀመሪያው ቀብዱን ከራሱ አቆይቶ ቀሪውን ገንዘብ መጠየቅ ነው በዚህ ሁኔታ ቀብዱ ለመጨረሻው ክፍያ እንደ ተቀናሽ ገንዘብ/down payment/ ይቆጠራል❗️❗️

በፍታብሔር ሕጋችን ስለ ቀብድ ለየት ያለው ውጤት ደግሞ ውሉ ሳይፈፀም በሚቀርበት ጊዜ ቀብድ መኖሩ ተዋዋይ ወገኖች ዉሉን በግላቸው (Unilateraly) እንዲያቋርጡ (termination) ይጠቅማል።
ነገር ግን ይህን ውል የሚሠርዘው ገዥው በሆነ ግዜ ቀድሞ የከፈለው ቀብድ ተመላሽ አይሆንለትም ነገር ግን ውሉን የሚሠርዘው አካል ሻጩ በሆነ ግዜ ቀድሞ በዉሉ የተቀበለውን የቀብድ መጠን እጥፍ (Double) ዋጋ ለገዥው ወይም ለቀብድ ከፋዩ መመለስ እንዳለበት የፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 1885 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2 ይደነግጋሉ።
ነገር ግን እነዚህ ህጎች ተፈፃሚ የሚሆኑት ሌላ ከዚህ የተለየ የውል ስምምነት ሳይኖር ሲቀር ብቻ ነው።
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
ሳይበርና የሳይበር ጥቃት ወንጀል ምንነት እንዲሁም ከአለማቀፍ እና ከሀገራችን የህግ ማዕቀፍ አኳያ እንዴት ይታያል የቅጣት ገደቡስ ምን ያህል ነው?

ከሳይበር ወንጀል ምንነት እንዲሁም ከአለማቀፍ እና ከሀገራችን የህግ ማዕቀፍ አኳያ እንዴት ይታያል የቅጣት ገደቡስ ምን ያህል ነው? የሚለውን በፍትህ ሚኒስቴር የንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ከሆኑት ከአቶ ዮሐንስ ግርማ ጋር ቆይታ አድርገን ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተውናል እንደሚከተለው ይቀርባል፡-
ሳይበር ለሚለው ቃል የተለያዩ መዝገበ ቃላት በሰጡት ትርጉም ኮምፒዩተር እና የኮምፒዩተር ኔትዎርክ ማለት ነው ሲሉ አቶ ዮሐንስ ስለሳይበር ምንነት ላነሳንላቸው ጥያቄ ምላሽ ይሰጣሉ በተለምዶ ይላሉ አቶ ዮሐንስ ሳይበርና ኮምፒዩተር የሚሉትን ቃላት ባለሙያዎች በተለዋዋጭነት ሲጠቀሙባቸው ይስተዋላል ለዚህ አጭር ጽሁፍ አላማም የሳይበር ወንጀል ማለት የኮምፕዩተር ወንጀል ማለት ነው ብለዋል፡፡
የሳይበር ጥቃት በሳይበር ክልል የሚፈጸም ወንጀል ሲሆን የሳይበር ክልል ማለት ትስስር ያለው አለማቀፍ ኔትዎርክ ማለት ነው የሳይበር ጥቃት ኮምፒዩተር፣ የኮምፒዩተር ስርአት ወይም የኮምፒዩተር ኔትዎርክን ያለባለቤቱ ፍቃድ ማግኘት ሲሆን አላማውም ጉዳት ማድረስ ነው፤የሚያደርሰውም ጉዳትም ብልሽት፣ ማዛባት፣ ማስወገድ ወይም ኮምፒዩተሩን በመለወጥ ማጥፋት ወይም ማገድ ሲሆን በስርአት ውስጥ ያለ መረጃን ማዛባት ወይም መስረቅንም ይጨምራል ይላሉ ፡፡
 የሳይበር ጥቃት አድራሾች እነማን ናቸው? ስንል ከተል አድርገን ላነሳንላቸው ጥያቄ
የሳይበር ጥቃት የማጥቃት እስትራቴጂ ባለው በማንኛውም ሰው ወይም ቡድን ከየትኛውም ቦታ ሊሰነዘርይ ይችላል ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ጥቃቱን የሚፈጽሙ ሰዎች የሳይበር ወንጀለኞች ወይም በተለምዶ ሃከሮች ተብለው ይታወቃሉ ብለዋል፤ የሳይበር ጥቃት አድራሾች በመንግስታት በሚደገፉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልሂቃን ቡድኖች እና መንግስትን የሚቃወሙ ሰዎች የሚፈጽሙት ነው ያሉት ዐቃቤ ህጉ የመስኩ ባለሞያዎችም nation-state attackers እና hacktivists ሲሉ ይጠሯቸዋል፡፡በሌላ በኩል ከራሱ ከውስጥ ድርጅቱ ሰራተኞች በኩል የሚፈጸም የሳይበር ጥቃትም አለ፡፡ በሀገራት መካከል በሚኖር ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባትን ምክንያት በማድረግ እንደዋነኛ ማጥቂያ መሳሪያ ወይም ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖ ለማሳደር በማሰብ እንዱ ሀገር በሌላው ሀገር መንግሰት ላይ የሚፈጽሙት የሳይበር ጥቃት አይነት የሳይበር ጦርነት (Cyberwarfare) ይባላልም ብለዋል፡፡ በአለማችን አሉ አቶ ዮሐንስ አሁናዊ የሀገራት ግንኘነትም እንዲህ አይነት ሹክቻዎች እንዳሉ ይታወቃል ሲሉ በቴክኖሎጂው በኩል ያለውን ሁኔታ ይዳስሳሉ።

 የሳይበር ክልልን መቆጣጠር እና ማስተዳደር የማን ድርሻ ነው? ስንልም ጠየቅናቸው
የሳይበር ክልልን መቆጣጠር እና ማስተዳደር ከህግ ተቋማት በተጨማሪ የሌሎች አካላት ተሳትፎ ይፈልጋል፡፡ ይሄውም ለኢንተርኔት መፈጠር እና መስፋፋት መሪ ሚና የተጫወቱ እና አገልግሎጭ ሰጪ ተቋማት ማለትም እንደ google, facebook, IPadress,የኢንተርኔት እስታንዳርድ እና ፕሮቶኮል አዘጋጆች፣ ሲቪል ማህበራት (Internet society) እና የመሳሰሉት የዘርፉ ቁልፍ ተዋናይ አካላት ዘርፉን በማስተዳደር እና ከሳይበር ጥቃት ከመከላከል አኳያ ከመንግስታት የህግ አስተዳደር በተጨማሪነት ጉልህ ሚና አላቸው ሲሉ መልሰውልናል፡፡

 የሳይበር ጥቃት ኢላማ እነማናቸው?
የሳየበር ጥቃት ኢላማዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እና እንደ ጥቃት አድራሾቹ ፍላጎት ይለያያሉ ሲሉ ዐቃቤ ህጉ ብዙውን ጊዜ እንደሚጠቀሰው የንግድ ተቋማት፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የጤና ተቋማት እና የጠበቆች መረጃዎች እና የደህንነት ተቋማት ዋነኛ የሀከሮች ኢላማ ናቸው ብለዋል፡፡ የጥቃት አድራሾቹ ዋነኛ ፍላጎትም የገንዘብ ጥቀም ማግኘት፣ ጥብቅ የሆኑ የግል መረጃዎችን ማግኘት፣ ስም ማጥፋት፣ ዝናማግኘት፣ በቀል፣ ሀገራዊ ቀውስ ማስከተል፣ የፈጠራ መብትን መንጠቅና የመሳሰሉት ይገኙባቸዋል ሲሉ እነዚህን ጥቃት ለመከላከል በመረጃ እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ ጥልቅ የሆነ የሳይበር ጥቃት መከላከያ፤ ፖሊሲ እና ይሄንኑ ለማስፈጸም የሚችል የሰው ሀይል እና እውቀት መገንባትና መጠቀም ያስፈልጋልም ሲሉ ይጠቁማሉ፡፡
 የሳይበር ወንጀል አለማቀፍ የህግ ማእቀፍ ምን ይላል? ብለን ላቀረብነውም ጥያቄ
በአለም አቀፍ ደረጃ የኮምፒዩተር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እስካሁን ወጥ የሆ ህግ የሌለ መሆኑን አውስተው በአውሮፓ ህብረት ደረጃ ግን በ2004 የወጣው የቡዳፔስቱ የሳይበር ወንጀል ላይ የተፈረመው ስምምነት ተጠቃሽ ህግ ሲሆን በአፍሪካ ደረጃም በህብረቱ በረቂቅ ደረጃ ያለው የሳይበር ደህንነት እና የግለሰብ ዳታ ለመጠበቅ የወጣውን ስምምነት በጉዳዩ ላይ ተጠቃሽ ክፍለ አህጉራዊ ህግጋት ናቸው ብለውናል፡፡ሌሎች የቀጠናው ስምምነቶች አሉ የቡዳቤስቱ ስምምነት 55 አገራት ያጸደቁት ሲሆን ሰፋ ያለ እና በጉዳዩ ላይ አባል አገራት ሊከተሉአቸው የሚገቡ አሰራሮችን የዘረዘረ ሲሆን ከአውሮፓ ህብርት አባል ሀገራት ውጭ ያሉ ከ130 የሚበልጡ አገራት በመቀበል እየተገበሩት ይገኛል ብለዋል በአለማቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ ህግ ባይኖርም አብዛኛው የአለም አገራት የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል በማሰብ የኮምፒዩተር ወንጀልን በህግ ስርአታቸው አካተው ይገኛሉ፡፡
 የሳይበር ወንጀል በኢትዮጵያ ህግ ስርአት ምን ይመስላል?
ሀገራችን ዘግይታ ቢሆንም የሳይበር ጥቃትን በወንጀልነት ከደነገጉ ሀገራት መካከል የገባች ሲሆን ይሄንኑ የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል በሀገር ደረጃ የተደነገጉ ህግጋትን ስንመለከት የሳይበር ጥቃት በህጋችን የኮምፒዩተር ወንጀል ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተደነገገውም በ1996 ዓ.ም.ተሻሽሎ በወጣው የወንጀል ህግ ሲሆን ይሄውም ከአንቀጽ 706 እስከ 711 ተደንግጎ ይገኛል ሲሉ ያመላክታሉ ነገር ግን ይህ ድንጋጌ ብቻውን በየግዜው እየተወሳሰበ የመጣውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የወንጀል ተጋላጭነት በበቂ ሁኔታ ለመቆጣጠር ባለማስቻሉ በአዲስ መልክ እራሱን ችሎ በአዋጅ እንዲሸፈን ለማድረግ በማሰብ በኮምፒዩተር ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 958/2008 በዝርዝር ተደንግጎ ወጥቷል ያሉ ሲሆን አሁን በስራ ላይ ያለው ይሄው ህግ ነው ብለዋል፡፡

የኮምፒዩተር ወንጀል አይነቶች እና የሚስከትሉት ተጠያቂነት ምንድን ነው?

በአዋጁ አንቀጽ 2 መሰረት የኮምፒውተር ወይም የኮምፒዩተር ሥርዓት ማለት በሶፍትዌር እና ማይክሮቺፕ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የዳታ ፕሮሰሲንግ፣ ክምችት፣ ትንተና፣ ስርጭት፣ ግንኙነት ወይም ሌሎች ሂሳባዊ ወይም አመክንዮአዊ ተግባራትን የሚያከናውን ማንኛውም መሳሪያ ሲሆን የመሳሪያው ተገጣሚ አካልንም ይጨምራል ያሉት አቶ ዮሐንስ የኮምፒዩተር ወንጀልም ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚፈጸም ወንጀል ነው ይላሉ፡፡ በዚሁም መሰረት ወንጀሉ

1. በኮምፒዩተር እና የኮምፒዩተር ስርአት ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚፈጸም(attacking the computer itself እና
2. የኮምፒዩተር ስርአትን ሌላ ወንጀል ለመፈጸም በመጠቀም (using computer and computer system as a instrument of crime)
በሚል የተደነገገ ሲሆን ከነዚህ ወንጀሎች ከፊሎቹን ስናይ የመጀመሪያው ወንጀል ህገ-ወጥ ደራሽነት(አንቀጽ3) ሲሆን ይሄውም ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ስርዓት፣ የኮምፒዩተር ዳታ ወይም ኔትዎርክ ደራሽነት በከፊልም ሆነ በሙሉ ማግኘት ነው ብለዋል ሌላኛው ወንጀል አሉ አቶ ዮሐንስ ህገ-ወጥ ጠለፋ (አንቀጽ 4) ሲሆን እሱም ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ ይፋዊ ያልሆነን የኮምፒዩተር ዳታ ወይም የዳታ ፕሮሰሲንግ አገልግሎት መጥለፍ ነው፡፡ መጥለፍ ማለትም በኮሙኒኬሽን ሂደት ላይ ያለን የኮምፒዩተር ዳታ ወይም የዳታ ፕሮሰሲንግ አገልግሎት መከታተል፣ መቅዳት፣ ማዳመጥ፣ መውሰድ፣ ማየት፣ መቆጣጠር ወይም መሰል ድርጊት መፈጸም ነው ብለው በተመሳሰይ ሁኔታ ሌሎች ዝርዝር ወንጀሎችም በህጉ የተዘረዘሩ መሆኑን ከታች ያሉትን ሀሳቦች አንስተውልና እነሱም ባጭሩ፡-
 በኮምፒዩተር ሥርዓት ላይ ጣልቃ መግባት(አንቀጽ-5)
 በኮምፒዩተር ዳታ ላይ ጉዳት ማድረስ( አንቀት 6)
 ከኮምፒዩተር መሣሪያ ና ዳታ አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ወንጀሎች(አንቀጽ 7)
 የኮምፒዩተር ዳታን ወደ ሐሰት መለወጥ (አንቀጽ 9)
 በኮምፒዩተር አማካኝነት የሚፈፀም የማታለል ወንጀል( አንቀጽ 10)እና
 የኤሌክትሮኒክ ማንነት ስርቆት(አንቀት11) ከፊሎቹ ናቸው፡፡

🔴ስለ ቅጣት ገደብ
በመጨረሻም ለዐቃቤ ሕጉ የቅጣጥ ገደቡ ምን ይመስላል ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄ የኮምፒዩተር ወንጀል የሚያስከትለው ቅጣት በአዋጁ መሰረት እንደየ ወንጀሎቹ ክብደት ከ3 አመት በማይበልጥ ቀላል አስራት እስከ 25 አመት በሚደርስ ከባድ እስራት እና ከብር አስር ሺ እስከ ብር ሁለት መቶ ሺ በሚደርስ መቀጮ የሚያስቀጡ ናቸው ያሉን ሲሆን ነገር ግን ወንጀሎቹ የተፈጸሙት፡-
 ለወታደራዊ ጥቅም ወይም ለዓለምአቀፍ ግንኙነት ሲባል በሚመለከተው አካል ጥብቅ ምስጢር ተብሎ በተሰየመ የኮምፒዩተር ዳታ ወይም ዳታው በሚገኝበት የኮምፒዩተር ሥርዓት ወይም ኔትዎርክ ላይ ከሆነ፤ወይም
 አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት ሀገሪቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ በምትገኝበት ወቅት ከሆነ፤
 በሕግ የሰውነት መብት ለተሰጠው ተቋም አገልግሎት ብቻ በሚውል የኮምፒዩተር ሥርዓት ላይ እና በቁልፍ መሠረተ ልማት ላይ ከሆነ ጉዳቱ ከፍ ስለሚል ቅጣቱም በዛው ልክ እስከ 25 ዓመት ከባድ የዕስራት ጣሪያ ድረስ ከፍ ብሎ የሚወሰን ይሆናል ብለዋል፡፡

አያይዘውም በአዋጁ አንቀጽ 19 መሰረት የኮምፒዩተር ሥርዓት አማካይነት የሚፈፀም ማናቸውም ዓይነት ወንጀል በልዩ ሕጎች ወይም በወንጀል ሕግ የሚያስቀጣ ሌላ ወንጀል አስከትሎ እንደሆነ፤ ለዚሁ ወንጀል ተገቢነት ያለው ድንጋጌ በተደራቢነት ተፈፃሚ ይሆናል ሲሉ ይህ ማለት በኮምፒዩተር ስርአቱ በመጠቀም የተፈጸመው ወንጀል በወንጀል ህጉ በሌላ ውንጀልም የሚያስጠይቅ ከሆነ በሁለቱም ህጎች ድንጋጌዎች ይቀጣል ማለት ነው ሲሉ ስለቀጣት ገደቡ ግልጽ ማብራሪያ ሰጥጠውናል፡፡

እኛም ከሳይበርና የሳይበር ጥቃት ወንጀል ምንነት እንዲሁም ከአለማቀፍ እና ከሀገራችን የህግ ማዕቀፍ አኳያ አጠቃላይ ይዘት አቶ ዮሐንስ ለሰጡን ማብራሪያ እያመሰገን በቀጣይ በሌላ ፕሮግራም አስክንገኛኝ መልካም ጊዜ ተመኘን፡፡
የኢ.ፌ.ድ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties