አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የአዲስ አበባ የህግ ምሩቃንን ያገለለው የስልጠና እና ስራ ዕድል
የኢትዮጵያ ፍትህ ስርዓት አዳዲስ የህግ ምሩቃንን በዳኝት እና በዐቃቤ ህግነት አሰልጥኖ የሚቀጥር ነው። የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ሰልጣኞች በቀጥታ የፍትህ ስርዓቱን ከመቀላቀላቸው በፊት የተግባር ልምምድ እንዲያገኙ ማስቻል ነው። 

የ አዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ተመራቂዎች  “በአዲስ አበባ የፍትህ አካላት የቅድመ ስራ ስልጠና ተቋም ባለመኖሩ ዓቃቤ ህግ ወይም ዳኛ ሆነው ለመሥራት መቸገራቸውን ይናገራሉ። ወደ ክልልሎች ሲሄዱም ስልጠና ለማግኘት የነዋሪነት መታወቂያና ቋንቋ እንደ ቅድመ ሁኔታ በመቀመጡ ስልጠናውን ማግኘት ሳይችሉ ይቀራሉ።
በተጨማሪም ከክልሉ ነዋሪ ውጪ እድሉን እንደማይሰጡና ቅድሚያ ለክልሎቹ ተመራቂዎች እንደሆነም ይነገራቸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ "አዲስ አበባ የራሷ የሆነ የፍትሕ አካላት ማሰልጠኛ ተቋም ባይኖራትም ከፌደራል የፍትህ እና የህግ ምርምር ተቋም በመቀናጀት ስልጠናው እየሰጠን መጥተናል፣ አሁንም እንሰጣለን። በመሆኑም ተቋም አለመኖሩ ችግር የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም” ባይ ናቸው። ከተማዋ የራሷ የሆነ የፍትህ አካላት የቅድመ ሥራ ማሰልጠኛ ተቋም እንዲኖራት እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ  የህግ ባለሙያ “አንድ የህግ ባለሙያ  ስልጠና ካልወሰደና በዓቃቤ ህግነት ወይም በዳኝነት ተቀጥሮ የመስራት አድሉ ጠባብ ነው ለዚህ ችግር መፍትሄው  አዲስ አበባ የራሷ የሆነ የህግ የቅድመ ስልጠና ማዕከል ማቋቋም ወይም እንኳን አዲስ አበባ የፌደራል መንግስት መቀመጫ እስከሆነች ድረስ ነዋሪዎቿ በፌደራል የፍትህ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ገብተው ስልጠናውን እንዲወስዱ ሊፈቀድላቸው ይገባል" ብለዋል።
አዲስ ዘይቤ
via #tikvahethmagazine
@lawsocieties
ቂሙን በፍየሎቹ ላይ የተወጣው ግለሰብ።

አንድ ግለሰብ ከወንድሙ ሚስት ጋር በመጣላቱ የተነሳ በፖሊስ ተይዞ ይታሰራል። ነገር ግን ግለሰቡ ለካ ለምን ታሰርኩ ብሎ ቂም በመያዝ በዋስ ከተፈታ በኋላ በመገስገስ ወደ ወንድሙ ሚስት ቤት ይሄዳል።

ሲደርስ ያጣታል፥ ይበሳጭና በሰፈር ውስጥ ታስረው ይግጡ የነበሩትን ንብረትነቱ ተጣላኋት ያላት የወንድም ሚስት የሆኑትን ሁለት ፍየሎች አርዶ ሄዷል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በሀረር ከተማ ሶፊ ወረዳ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መሆኑንና ግለሰቡም በድጋሚ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው አዛዥ ምክትል ኮማንደር መሀመድ ሳፊ ገልጸዋል።
#tikvahethmagazine
https://t.me/lawsocieties
#የሥራማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሥሩ ለሚገኙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ጀማሪ ባለሙያዎችን /Intern/ በኮንትራት ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

በዚሁም መሠረት

- በህግ፣ በኮምፒውተር ሳይንስ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በኮምፒውተር ኢንጅነሪንግ፣ በሶሺዎሎጂ፣ ሶሻል ወርክ፣ በህዝብ አስተዳደር፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በሰው ኃብት አስተዳደር፣ በቢዝነስ ሊደርሺፕ፣ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በግዢ እና ንብረት አስተዳደር፣ በጋዜጠኝነት እና ስነጽሁፍ፣ በግራፊክስ ዲዛይን፣ በፖለቲካል ሳይንስ እና አለምአቀፍ ግንኙነት እንዲሁም ተያያዥ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው/ያላት

- አማካይ የመመረቂያ ውጤታቸው 3.5 እና ከዛ በላይ የሆነ፤

- ጥሩ የሆነ የአማርኛ እና የእንግሊዘኛ ቋንቋን ክህሎት (መናገር፣ መጻፍ እና ማንበብ) ያለው/ያላት፤

- የማይክሮሶፍት ኦፊስ (MS Word, Excel, Outlook, and PowerPoint) እውቀት እና በአግባቡ የመጠቀም ችሎታ ያላት/ ያለው፤

- የተቋሙን ደንብና መመሪያ የሚያከብር/ የምታከብር፤

- የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፤

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ቦርዱ ገልጿል።

ለመመዝገብ  https://forms.office.com/r/HvBrmNfKaX

* ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ

* ከአማርኛ በተጨማሪ ሌሎች የሀገር ውስጥ ቋንቋዎችን መናገር፣ መጻፍ እና ማንበብ የሚችሉ አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡
#tikvahethmagazine
የባለቤቱን እህት አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ . . .

በጉጂ ዞን ነገሌ ከተማ 03 ቀበሌ ውስጥ ታጀበ ከበበ የተባለው ግለሰብ የባለቤቱን ስራ መሄድ በመጠባበቅ ከ14 እስከ 16 ዓመት እድሜ ያላትን ታዳጊ በተደጋጋሚ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ይፈጽማል።

ከቀናት በኋላ የታዳጊዋ እህት ሁኔታዋን በመጠራጠር ደጋግማ ብትጠይም ምላሽ ታጣለች፡፡ ታዳጊዋ የደረሰባትን ሳትናገር  ከምትኖርበት አካባቢ ብትጠፋም ፖሊስ ባደረገዉ ብርቱ ፍለጋ ወደ መኖሪያ ቤቷ እንድትመለሰ ይደረጋል፡፡

በመቀጠልም ምን እንዳጋጠማት ስትጠየቅ በእህቷ ባለቤት በተደጋጋሚ የአስገድዶ መድፈር እንደተፈፀመባት እና ነፍሰ ጡር እንደሆነች ቃልዋን ለፖሊስ ታሳውቃለች፡፡

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየዉ የጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት በ15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ዉሳኔ አሳልፏል። (ለብስራት ሬድዮ)
#tikvahethmagazine
#ጥንቃቄ❗️

በመዲናዋ ስልክ እየደወሉ እና የተለያዩ የማጭበርበር ዘዴዎችን በመጠቀም  ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦች  በመኖራቸው ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል።

ግለሰቦቹ በተለያየ ስልክ በመደወል እንኳን ደስ አላችሁ ሎተሪ ደርሷችኋል ሲስተም እያስተካከልን ነው፣ የሞባይሎትን አቅም ከ4G ወደ 5G እየቀየርን ነው ፣ከሌሎች ባንኮች ጋር ኦንላይን ሲስተም እየጀመርን  ነው በሚሉ እና በሌሎች ማደናገሪያዎች በመጠቀም የተለያዩ የማጭበርበር ወንጀል እንደሚፈጽሙ ታውቋል።

አንዳንዶቹ የማጭበርበሪያ ስልቶች  ግለሰቦች እንዲያምኑ በኤቲም ገንዘብ ያወጡበት ትክክለኛ ቀን ተነግሯቸው የወንጀሉ ሰለባ እየሆኑ የሚገኙ ሲሆን የግለሰቦች የባንክ ሚስጥር የሚወጣበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ምርመራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ተብሏል።

ወንጀሉ በልዩ ልዩ የአፈፃፀም ስልቶች እየተፈፀመ ከመሆኑም ባሻገር ስልክ በመንጠቅና ቴክኒካል የሆኑ ዘዴዎችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ አካውንት ወደ ቴሌ ብር በማስተላለፍ ወንጀሉ እየተፈፀመ ይገኛል፡፡

ህብረተሰቡ የማያውቋቸው የስልክ ጥሪዎች እና የጹሁፍ መልዕክቶች ሲደርሷቸው ተገቢውን ማጣራት ማድረግ እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
#tikvahethmagazine
https://t.me/lawsocieties
የወንድሙን ልጆች በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ

በጎፋ ዞን ኡባ ደብረ ፀሀይ ወረዳ ጋዶላ ጎዱማ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ አሳሼ አታረ መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ረቡዕ ዕለት በግምት ከቀኑ 11 ሰዓት አከባቢ በእርሻ ማሳዬ የሚገኘውን አትክልት በበግ አስበልተዋል በሚል የወንድሙን ልጆች ገድሏል።

የክስ መዝገቡ ተከሳሽ የስድስትና የስምንት ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ሁለት የወንድሙን ልጆች አባብሎ ወደ ቤቱ ካስገባ በኋላ በስለት ወግቶና ቆራርጦ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎና በማዳበሪያ ጠቅልሎ ሽንት ቤት ውስጥ መጣሉን ያስረዳል።

ወንጀሉን የፈጸመው ግለሰብም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። የጎፋ ዞን አቃቤ ህግም የወንጀል ህግ አንቀፅ 539(1)ሀ/ድንጋጌን በመጥቀስ ክስ መስርቶበት በማስረጃ በመረጋገጡ ግለሰቡ ላይ የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ውሳኔ መተላለፉን ከደቡብ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#tikvahethmagazine
የ2 ልጆቿን አባት በመጥረቢያ በመምታት የግድያ ወንጀል የፈጸመችው ግለሰብ በ21 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣች።

በተደጋጋሚ ይሰድበኛል በሚል በባለቤቷ ላይ ቂም በመያዝ እንቅልፍ የተኛበትን አጋጣሚ በመጠቀም በመጥረቢያ ጭንቅላቱን ደጋማ በመምታት ህይወቱ እንዲያልፍ ግለሰብ በ21 ዓመት ፅኑ አስራት እንድትቀጣ ፈርዶባታል።

ከበቡሽ አለሙ የተባለችው ግለሰብ የሁለት ልጆቿ አባት በሆነው ባለቤቷ ላይ የግድያ ወንጀሉን የፈፀመችው መጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ/ም በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው 58 መዝናኛ ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ፖሊስ ግለሰቧን በቁጥጥር ስር አውሎ መዝገብ ካደራጀ እና በአቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰረት ካደረገ በኋላ ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ የከባድ ውንብድና እና ግድያ ወንጀል ችሎት በ21 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ የወሰነባት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
#tikvahethmagazine
https://t.me/lawsocieties
በፍትህ ሚኒስቴር የሚሰጡ አገልግሎቶች በብሄራዊ መታወቂያ ብቻ እንዲሰጡ ሊደረግ ነው ተባለ።

በፍትህ ሚኒስቴር የሚሰጡ አገልግሎቶች በብሄራዊ መታወቂያ ብቻ እንዲሆኑ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የፍትሕ ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህ መሰረት እያንዳንዱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በስሩ ያሉ ሰራተኞችና ተገልጋዮች አገልግሎቱ ሙሉ ለሙሉ ወደትግበራ ከመግባቱ በፊት ብሄራዊ መታወቂያ ለማግኘት እንዲመዘገቡ እና በእጃቸው እንዲያስገቡ አቅጣጫ መሰጠቱን መ/ቤቱ አመላክቷል፡፡

የብሄራዊ መታወቂያ ለማግኘት የት መመዝገብ ይቻላል?

ለብሄራዊ መታወቂያው በተመረጡ ባንኮች ፣በገቢዎች ሚኒስቴር፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ስር በሚገኘው የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ፣በዋናው ፖስታ ቤት ፣አራት ኪሎ ቤተ-መንግስት መግቢያ ፓላስ ፓርኪንግ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ አገልግሎቱ ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

የፍትሕ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች ፣ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚያገኙ ጠበቆች እና ሌሌችም የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም አገልግሎት ፈልገው ወደተቋሙ የሚመጡ ግለሰቦች ለብሄራዊ መታወቂያ በመመዝገብ የካርድ ህትመትን በመያዝ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ተቋሙ አሳስቧል።
#TikvahethMagazine
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
🔴

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ፈቃድ መስጠት እንደሚጀመር ገለፀ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከየካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ፈቃድ መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ ከተቋቋመ ጊዜ አንስቶ ራሱን በማደራጀት የሕግ ማዕቀፍ ሲያዘጋጅ መቆየቱን የገለፁ ሲሆን አሁን ላይ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ በማዘጋጀት ወደ ሥራ መግባቱን ገልፀዋል።

በዚህ መሰረትም በዘርፉ ሥራ ላይ የሚገኙ አካላት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ መመዝገብ እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን ባለስልጣኑ 15 አዳዲስ ፈቃዶች መስጠት እንደሚጀምር ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ መስጠት እንደሚጀመርም የተገለፀ ሲሆን የመንግስት የልማት ድርጅቶችም በዚህ ማዕቀፍ ለመካተት ዝግጅት ማድረጋቸውን ተመላክቷል።

ሶስት ትላልቅ የውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮች መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እንደተሰጣቸውም ነው የተገለፀው።
#TikvahethMagazine
https://t.me/lawsocieties
አዲሱ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበር ረቂቅ አዋጅ . . .

ላለፉት 49 ዓመታት በሥራ ላይ የቆየው የሕዝብ በዓላትን እና የእረፍት ቀንን ለመወሰን የወጣ አዋጅ በአዲስ ሊተካ ረቂቅ መዘጋጀቱ ሲገለፅ ፓርላማው መጋቢት ወር ላይ ወደ ሥራ ሲመለስ ይመለከታቸዋል ተብሎ ከሚጠበቁ አዋጆች መካከል ይህ ረቂቅ አዋጅ የሚገኝበት መሆኑ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ያለው በደርግ መንግሥት የወጣው አዋጅ 13 የሕዝብ እና ሃይማኖታዊ በዓላትን በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበሩ የደነገገ ሲሆን ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ በዚህ አዋጅ ውስጥ የድል ቀን ላይ ብቻ ማሻሻያ በማድረግ ይሄንን አዋጅ መተግበር መቀጠሉና አሁን በሥራ ላይ ባለው አዋጅ እና በአተገባበሩ ላይ ክፍተቶች እንዳሉት ተጠቁሟል።

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ያመጣቸው ለውጦች ምንድናቸው?

- አዲሱ ረቂቅ አዋጅ፤ ከቀድሞው አዋጅ የሚለየው ዋነኛ ጉዳይ የበዓላት አከባበርን በተመለከተ ዝርዝር ሁኔታዎችን የያዘ ሲሆን ረቂቅ አዋጁ የሕዝብ በዓላትን “ተከብረው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት” ፣ “ታስበው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት” እና “ሃይማኖታዊ በዓላት” ሲል ይከፋፍላቸዋል።

- ተከብረው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት መደበኛ ሥራ ዝግ የሚሆንባቸው ቀናት እንደሆነ ረቂቁ ላይ የሰፈረ ሲሆን እነዚህም የዘመን መለወጫ፣ የአድዋ ድል፣ የላብአደሮች ቀን እና የአርበኞች (የድል) ቀን ናቸው።

- ሥራ ሳይዘጋ ታስበው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት 2የሰማዕታት ቀን እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን መሆናቸው ሲገለፅ ወደ ም/ቤቱ የተላከው ረቂቅ ላይ በሃይማኖታዊ በዓልነት የተቀመጡት አምስት የክርስትና እንዲሁም ሦስት የእስልምና እምነት በዓላት ሲሆኑ ከዚህ ቀደም ከነበረው ዝርዝር ውስጥ የተደረገ ለውጥ የለም ተብሏል።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛ ነው
#TikvahethMagazine
20 ፓኬት ሲጋራ በእንጀራ ውስጥ ደብቆ ተጠርጣሪ ለመጠየቅ የሄደው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አንበሳ ጋራዥ ጀርባ ወደሚገኘው የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ስንቅ ለማቀበል በሚመስል መልኩ በያዘው ሳህን ውስጥ ወደ ተጠርጣሪ ማቆያ ቤት ሲጋራ ለማስገባት የሞከረው ግልሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

በፖሊስ መምሪያው የተጠርጣሪ ማረፊያ ቤት አካባቢ የፍተሻ እና የማረጋገጥ ስራ የሚሰሩ የፖሊስ አባላት በወቅቱ ግለሰቡ ምግብ አስመስሎ የያዘውን ሳህን እንዲከፍት አድርገው ሲመለከቱ 20 ፓኬት ሲጋራ ከላይ በእንጀራ ተሸፍኖ ማግኘታቸው ተገልጿል።

በወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ጣቢያ የተጠርጣሪ ማቆያ ቤት ለሚገኙ ሰዎች ሲጋራ ማስገባት የተከለከለ ሲሆን፤ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በወጣው ደንብ ቁጥር 299/2006 ላይ በተደነገገው መሰረት ትምባሆን በማንኛውም ህዝብ በሚሰበሰብበት ወይም በሚገለገልበት ቦታ ማጨስ ክልክል እንደሆነ ተደንግጎ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
#TikvahethMagazine
የትዳር አጋሩን የተለያየ የሰውነት ክፍል በቢላዋ በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ተከሳሽ በፅኑ አስራት ተቀጣ

ከሌላ ወንድ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለሽ በሚል ምክንያት የትዳር አጋሩን በቢላዋ ጭቅላቷን፣ አንገቷን፣ ፊቷን፣ የግራ ክንዷንና ጣቷን፣ ደረቷንና ጀርባዋን በመውጋት የገደለው ግለሰብ በፅኑ እስራት መቀጣቱን የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ስሜነህ ግርማ በለጠ የተባለው ተከሳሽ ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 2፡20 ሲሆን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስኮ ሰፈረ ወርቅ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው የትዳር አጋሩ የሆነችው ሟች ማህሌት ፍቃዱ ላይ ወንጀሉን የፈፀመ መሆኑ ተገልጿል።

ግልሰቡ ይህንን በማድረጉ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ የቆየ ሲሆን ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ ባለማቅረቡና የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ምክንያት ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ነው በማለት ተከሳሽ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል።
#TikvahethMagazine
#አለሕግ #Alehig
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
አካል ጉዳተኞችን የተመለከተ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊወጣ መሆኑ ተሰማ

አካል ጉዳተኞች መብታቸው እንዲጠበቅ ለመብታቸው መጠበቅም ምላሽ የሚሰጥ ተፈጻሚነቱን የሚከታተል ባለቤት ያለው አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊወጣ መሆኑን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞችን መብት ምላሽ የሚሰጥ ጥቅል አዋጅ የላትም የተባለ ሲሆን ያን ለማድረግ የአካል ጉዳተኞች ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ወደ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መላኩ ተገልጿል።

ይህ የአካል ጉዳተኞች አዋጅ ፥ ያሉትን ህጎች ተከታትሎ የሚያስፈፅም፣ ካልተፈፀሙም ተጠያቂ የሚሆን ተቋም እንዲኖር ለማስቻል ፣ የህግ ክፍቶችም እንዲስተካከሉ ያደርጋል ተብሏል። አዋጁ ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ተልኮ አስፈላጊ አስተያየት ከተሰጡበት በኋላ ወደ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መላኩ ነው የተገለፀው።
#TikvahethMagazine
ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!

ምንም ውሳኔ ከመወሰንዎ በፊት አማራጭ የሕግ እውቀት ያግኙ::
    0920666595

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig?si=BQvQV6OdOb6G8WI1

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
#update: " የ5 አመት ህፃን የደፈረው ግለሰብ ላይ ክስ መስርታ #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ ያስደረገችው ዐቃቤ ህግ ከስራ ታግዳለች " የቤንሻንጉል ክልል ፍትህ ቢሮ

በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ የ5 ዓመት ህፃን ልጅ ላይ በተፈፀመ የመድፈር ወንጀል የወንበራ ወረዳ ዐቃቤ ህግ በወንጀል ፈፃሚዉ ላይ ክስ መስርቶ ክርክር ከተደረገበት በኋላ የወንበራ ወረዳ ፍ/ቤት ጥፋተኛ የተባለዉን ግለሰብ #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ይታወሳል።

የቤንሻጉል ክልል ፍትህ ቢሮ የቅጣት ዉሳኔዉ ከተፈፀመዉ ወንጀል አንፃር አስተማሪነቱ አጠያያቂ እንደሆነና ለቅጣቱ ማነስ እንደ ምክንያትነት የሚጠቀሰዉ የክሱ አመሰራረት ክፍተት መሆኑን መገንዘቡን ገልጿል።

እናም የፍትህ ቢሮው የታችኛዉን መዋቅር ባሳተፈ መልኩ ዉጤታማ ስራ ሰርቶ የማስተካከያና የእርምት እርምጃ እስከሚሰጥ ድረስ ክሱን የመሰረቱት የወንበራ ወረዳ ዐቃቤ ህግ የሆኑት ወ/ሪት ዘወትር አበበ ቡሩሶ ከመጋቢት 20/2016 ዓ/ም ጀምሮ ከስራ ታግደው የሚሰጠዉን ዉሳኔ እንዲጠባበቁ ተወስኗል።

ምንም እንኳን ዐቃቤ ህግ በተሰጠዉ ዉሳኔ ይግባኝ የጠየቀ ቢሆንም ለተፈፀመዉ ወንጀል ተገቢዉን ዉሳኔ ከማሰጠት አኳያ በክስ አመሰራረቱ ላይ የተፈጠረዉን ክፍተት በጥናት ላይ ተመስርቶ በማረም ተገቢ እና ተመጣጣኝ ዉሳኔ ለማሰጠት እንደሚሰራም የፍትህ ቢሮው ገልጿል።
#TikvahethMagazine
ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!

ምንም ውሳኔ ከመወሰንዎ በፊት አማራጭ የሕግ እውቀት ያግኙ::
    0920666595

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig?si=BQvQV6OdOb6G8WI1
የጋዜጠኞች መብት እንዳይጣስ የሚከራከር የህግ ባለሙያዎች ቡድን ሊቋቋም ነው

የሚዲያ ተቋማት እና ጋዜጠኞች ስራቸውን በመስራታቸው ብቻ የሚደርስባቸውን ችግር ለመፍታት የህግ የባለሙያዎች ቡድን እየተቋቋመ መሆኑን ኢትዮኤፍ ኤም ዘግቧል።

የህግ ባለሙያዎቹ ቡድን የተለያዩ ጋዜጠኛውን የሚጎዱ ህጎች ላይ በመከራከር ጋዜጠኛውን መብቱን የማስጠብቅ ስራ የሚሰራ መሆኑን በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ዋና ዳይሬክተር አቶ መሱድ ገበየው መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ይህ የህግ ባለሙያዎች ቡድን 'መላ' የሚል ስያሜ እንደተሰጠው ሲገለፅ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን እንዲሁም የጋዜጠኞችን መብት ለማስጠበቅ ይስራል ነው የተባለው።

#TikvahethMagazine

አማራጭ የሕግ እውቀት
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
በአዲስ አበባ ከተማ በ2016 በጀት ዓመት 38 ሺህ 239 ጋብቻ እና 8 ሺህ 949 ፊቺ መመዝገቡ ተገልጿል።

በዚሁ በጀት ዓመት 765 ሺህ 272 የነዋሪነት መታወቂያ የተሰጠ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 715 ሺህ 138ቱ የዲጂታል መታወቂያ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ከልደት ጋር ተያይዞም ከዚህ ቀደም በ40 የጤና ተቋማት ላይ ብቻ ይሰጥ የነበረው ምዝገባ አሁን ላይ በ73 ጤና ተቋማት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ተብሏል፡፡ (AMN) #tikvahethmagazine
#AddisAbaba
#NewsUpdate: የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2017 ዓ/ም የዳኝነት የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በ6 ኪሎ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተካሂዷል።

ፍርድ ቤቶች ከነሀሴ 1/ 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መከረም 30/ 2017 ዓ/ም ለሁለት ወራት በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩ ሲሆን ዛሬ ጥቅምት 1 በይፋ መከፈታቸው ተበስሯል።
#tikvahethmagazine
Telegram
https://t.me/AleHig

Telegram_Group
https://t.me/AleHig_Group

Facebook Page
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

LinkedIn
https://www.linkedin.com/company/alehig/

YouTube
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

TikTok
https://www.tiktok.com/@alehigofficial

Instagram https://www.instagram.com/alehigofficial

Twitter /X
https://x.com/AlehigOfficial?t=yFRauAZ7v70Je2MEPIGGsQ&s=09

official website
https://www.alehig.com

#LegalAwareness #AleHig #LegalUpdates #AccessToJustice
#እንድታውቁት 📣❗️🆕

የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለስልጣን በሽያጭ የተሽከርካሪ ስም ዝውውር ለማድረግ ሊሟሉ እሚገባቸው ጉዳዮች ብሎ የሚከተሉትን ነጥቦች አስቀምጧል።

በዚህም በሽያጭ የተሽከርካሪ ስም ዝውውር ለማድረግ፦

1. በተሽከርካሪው ላይ የተላለፈ ማንኛውም ዓይነት እዳ እና እገዳ እንዲሁም ቀረጥ ያለበት ከሆነ የስምምነት ደብዳቤ መኖሩን ማረጋገጥ፣

2. ኮድ 01 እና ኮድ 03 ከሆነ ከገቢዎች የግብር ክሊራንስ መቅረቡን

3. የዘመኑን ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ/ቦሎ፤ ያደረገ መሆኑን፤

4. የጸደቀ የውልና ማስረጃ ሰነድና የስም ዝውውር 2% የከፈለበት ማስረጃ መኖሩን፣

5. የንግድ ተሽከርካሪ ከሆነ አንዱ የግምት ውጤት ለሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ይላካል፤ ሁለተኛውን የግምት ውጤት ሁለቱ ተዋዋዮች ውል መፈፀም የሚችሉ ለመሆኑ በሸኚ ደብዳቤ ለሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተላከበት ሰነድ፤

6. የቤት ተሸከርካሪ ከሆነ የግምት ውጤቱን በቀጥታ ሰሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ የተላከበት ሰነድ፤

7 . የገዢ ሁለት ፎቶ ግራፍ

8. የስም ዝውውርና የአገልግሎት ለውጥ የሚያደርግ ከሆነ ተሸከርካሪው በድጋሚ ለቴክኒክ ምርመራ ብቃት ማረጋገጫ ሲቀርብ እገልግሎቱ ይሰጣል ሲል አስቀምጧል።

በተጨማሪም ቢሮው በዚሁ መረጃው ላይ በሰጠው ማሳሰቢያ፦

1. የሚገዙት ተሽከርካሪ የሻንሲና ምተር ቁጥር ትክክለኛነት የማረጋገጥ፣

2. የተሚገዙት ተሽከርካሪ ሊብሬና ተሽከርካሪ ስለያዙ እና ዉክልና ስለተሰጦት ብቻ ሀጋዊ ተሽከርካሪ ማለት ስላልሆነ የሚገዙት ተሽከርካሪ በተመዘገበበት ቅ/ጽ/ቤት ትክክለኛነቱ መረጋገጥ አለበት ሲል ገልጿል።
#tikvahethmagazine
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp📱 #+251920666595
Telegram📱 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM