#update ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ከፍትሕ አካል አባላት ጋር እየተወያዩ ነው።
በውይይቱ ላይ ከ3 ሺህ በላይ ዳኞች፣ ዐቃብያነ ሕግ፣ ጠበቆችና የፍትሕ ዘርፍ አመራሮች መሳተፋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተገኝ መረጃ ያመላክታል።
በውይይት መድረኩ በፍትሕ ሥርዓቱ ለውጥና የማሻሻያ ሥራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ምክክር የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል።
@lawsocieties @lawsocieties

#Update
.
የ2014አም መውጫ ፈተና አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግንቦት ወር መጨረሻ እንደሚሰጥ ይታመናል።ከዚህ በፊት በፃፍኩት ፅሁፍ ላይም ተፈታኞች መዘናጋት እንደሌለባችሁና ጥናታችሁን በአግባቡ ልታጠኑ እንደሚገባ አሳውቄ ነበር።በግል መስመር እጅግ በጣም ብዙ ተፈታኞች በእርግጥም ፈተናው ግንቦት ወር ላይ ይሰጣል ወይ እያላችሁኝ ነው።እኔም በተደጋጋሚ እንደምገልፀው አድስ ነገር እስካልተፈጠረ ድረስና ባለድርሻ አካላቱ ተራዝሟል እስካላሉ ድረስ ሳትዘናጉ ጥናታችሁን ተከታተሉ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታም ፈተናው ግንቦት ወር እንደሚሰጥ እናምናለን ብለዋል የELSA ፕሬዝደንትና የኮንሰርቲየሙ ዋና ፀሃፊ።
.
.
#Ahmed.M

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትን ሹመት ያጸደቀው፤ በሶስት ድምፅ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።
Photo Credit : ኤፍ ቢ ሲ

ወይዘሮ አበባ እምቢአለ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።
ምክር ቤቱ የወይዘሮ አበባ እምቢአለን ሹመት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
ወ/ሮ አበባ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኛነት ፣ የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግነት፣ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኛነት አገልግለዋል።
አቶ ቴዎድሮስ ምህረት (ፕሬዜዳንት) እና ወ/ሮ አበባ እምቢአለ (ምክትል ፕሬዜዳንት) በጉባኤው ፊት ቀርበው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል።
#tikvahethiopia

በፎፌክስ ትሬዲንግ ስም የሚያታልሉ ግለሰቦችንና ቡድኖችን በህግ ተጠያቂ ማድረግ እንደሚቻል ተገለፀ።
በፎሬክስ ትሬዲንግ የኦንላይን ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን" የሚል የፌስቡክና የቴሌግራም ማስታወቂያ በሚያስነግሩ የተደራጁ ቡድኖች የተጭበረበሩ ሰዎችን አስመልክቶ ቲክቫህ ተከታታይ ዘገባ መስራቱ ይታወሳል።
ጉዳዩን አስመልክቶ የሚመለከተውን አካል ያነጋገርን ሲሆን ፥ በዚህ ጉዳይ ወንጀል ተፈፅሞብኛል የሚሉ ግለሰቦች የሚያቀርቡትን ጥቆማና መረጃ ተከትሎ ከህግ አካላት እና ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ጉዳዩን እንደሚያጣሩ የኢትዮጵያ ፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የህዝብ ግንኙነትና የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለ አሰፋ ለቲክቫህ ገልፀዋል።
አቶ እንዳለ በፎሬክስ ትሬዲንግ የማጭበርበር ድርጊት ጉዳይ እስካሁን ጥቆማ ለመስሪያ ቤቱ እንዳልደረሰ የገለፁ ሲሆን "ወንጀል ተፈፅሞብኛል" የሚሉ ሰዎች በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ምርመራ ክፍል ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው በማሳሰብ ፥ በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤት በኩል የሚፈለገው እገዛ ለፖሊስ እንደሚሰጥ አስረድተዋል።
ይህን መሰል የማታለል ድርጊት በህግ እንዴት ይታያል?
ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ያናገርናቸው ጠበቃ እና የህግ አማካሪ እንዲሁም በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት አቶ እሱባለው አማረ የወንጀል ድርጊቱ ፈርጀ ብዙ የህግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ገልፀዋል።
ጠበቃ እና የህግ አማካሪው አቶ እሱባለው ድርጊቱ በንብረት መብት (property right) ላይ ከሚፈፀም ወንጀል ጋር እንደሚያዝ ያስረዱ ሲሆን በዋናነት በንብረት ላይ ሊፈፀም ከሚችሉ ወንጀሎች ተብለው በወንጀል ህጋችን ከተጠቀሱት መሃከል በ"አታላይነት" ወንጀል እንደሚያስጠይቅ ለቲክቫህ ገልፀዋል።
"አታላይነት" በወንጀል ህጉ ከአንቀፅ 692 ጀምሮ ሽፋን እንደተሰጠው የገለፁት የህግ መምህሩ ፥ "ማታለልን ያካተቱ ወንጀሎች" በሚል ንዑስ ስር ያለ የዚህ ድንጋጌ ንዑስ አንቀፅ 1 "ማንም ሰው የማይገባ ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ አሳሳች የሆኑ ነገሮችን በመናገር፣ የራሱን ማንነት ወይም ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለጽ የሚገባውን ነገር በመደበቅ ወይም የሌላውን ሰው የተሳሳተ እምነት ወይም ግምት በመጠቀም፣ በማድረግም ሆነ ባለማድረግ ሌላውን ሰው አታልሎ የራሱን ወይም የሶስተኛ ወገንን የንብረት ጥቅም የሚጎዳ አድራጎት እንዲፈፀም ያደረገ እንደሆነ የአታላይነት ወንጀል እንደተፈፀመ ያስቀምጣል" ሲሉ አስረድተዋል።
ይህ የወንጀል ድርጊት በቀላል እስራት ወይም
እንደነገሩ ከባድነት ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት እና የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለ አሰፋ በፎሬክስ ስም የማታለል ወንጀል ተፈፅሞብኛል የሚሉ ሰዎች ወይም በጉዳዩ ላይ አጠራጣሪ ነገሮችን የተመለከቱ ግለሰቦች ፖሊስ ጋር ከመሄድ ባሻገር ለተቋሙ በስልክ ቁጥር +251-11-812-8261 ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉ በማስረዳት ፥ ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር ክትትል እንደሚደረግ ገልፀዋል።
በኦላይን የሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመጠቆም @tikvahmagbot ይጠቀሙ።
በጉዳዩ ላይ ለመወያየት https://t.me/tikvahforum/22079 ላይ ሀሳቦትን ያካፍሉን።
👋 @TikvahethMagazine

#update
" ዓቃቢ ህግ በፍርድ ቤቱ በኩል ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ ይግባኝ በመጠየቅ ክሱ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል እንዲታይ ተደርጓል" - የወምበራ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት
" ይህንን የፍርድ ዉሳኔ የሰጠዉ ዳኛ ከስራና ከደመወዝ ታግዶ እንዲቆይና ጉዳዩ በኮሚቴ ተጣርቶ እንዲቀርብ ትእዛዝ ተሰጥቷል " - የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት
በወምበራ ወረዳ ፍ/ቤት ከዚህ ቀደም ስሙ ያልተጠቀሰው ' ተክለአብ ገለታ ' የተባለው ተከሳሽ የ5 አመት ህጻን ልጅ በመድፈር ወንጀል ተከስሶ #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ይታወሳል።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የወረዳው ፍርድ ቤት ያስተላለፈው ውሳኔ አግባብ አለመሆኑንና አስተማሪነቱን ባለመቀበል ዓቃቢ ህግ በፍርድ ቤቱ በኩል ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ #ይግባኝ መጠየቁን የወምበራ ወረዳ ፍትህ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ አመንቴ ገልፀዋል።
ጉዳዩን አስመልክተው ለወረዳው ኮሚዩኒኬሽን ማብራሪያ የሰጡት የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ የወረዳው ፍርድ ቤት ባስተላለፈው የቅጣት ውሳኔ ከተፈፀመው ወንጀል ጋር ተመጣጣኝና አስተማሪ ባለመሆኑ ይግባኝ ተጠይቆ ክሱ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል እየታየ መሆኑን አስረድተዋል።
ይህንን ተከትሎ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የመዝገቡን የክስ ሂደት ማጣራትና ማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ወደ መተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ኮሚቴ በመላክ ጉዳዩ በአስቸኳይ እንዲጣራ ኮሚቴ መላኩን አሳውቋል።
ጠቅላይ ፍ/ቤቱ " ይህንን የፍርድ ዉሳኔ የሰጠዉ ዳኛ ከስራና ከደመወዝ ታግዶ እንዲቆይና በኮሚቴዉ ጉዳዩ ተጣርቶ ሲቀርብ ቀጣይ በዲስፕሊን ታይቶ በክልሉ ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ተገቢውን የእርምት እርምጃ ይወሰዳል " ብሏል።
የተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ቅጣት ማነስ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በመተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ እየታየ መሆኑን ያረጋገጠው የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሚሰጠውን ዉሳኔ በቀጣይ መረጃዉን ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከወምበራ ኮሚኒኬሽን እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እንዳገኘው ያሳውቃል።
@TikvahethMagazine

#update: " የ5 አመት ህፃን የደፈረው ግለሰብ ላይ ክስ መስርታ #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ ያስደረገችው ዐቃቤ ህግ ከስራ ታግዳለች " የቤንሻንጉል ክልል ፍትህ ቢሮ
በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ የ5 ዓመት ህፃን ልጅ ላይ በተፈፀመ የመድፈር ወንጀል የወንበራ ወረዳ ዐቃቤ ህግ በወንጀል ፈፃሚዉ ላይ ክስ መስርቶ ክርክር ከተደረገበት በኋላ የወንበራ ወረዳ ፍ/ቤት ጥፋተኛ የተባለዉን ግለሰብ #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ይታወሳል።
የቤንሻጉል ክልል ፍትህ ቢሮ የቅጣት ዉሳኔዉ ከተፈፀመዉ ወንጀል አንፃር አስተማሪነቱ አጠያያቂ እንደሆነና ለቅጣቱ ማነስ እንደ ምክንያትነት የሚጠቀሰዉ የክሱ አመሰራረት ክፍተት መሆኑን መገንዘቡን ገልጿል።
እናም የፍትህ ቢሮው የታችኛዉን መዋቅር ባሳተፈ መልኩ ዉጤታማ ስራ ሰርቶ የማስተካከያና የእርምት እርምጃ እስከሚሰጥ ድረስ ክሱን የመሰረቱት የወንበራ ወረዳ ዐቃቤ ህግ የሆኑት ወ/ሪት ዘወትር አበበ ቡሩሶ ከመጋቢት 20/2016 ዓ/ም ጀምሮ ከስራ ታግደው የሚሰጠዉን ዉሳኔ እንዲጠባበቁ ተወስኗል።
ምንም እንኳን ዐቃቤ ህግ በተሰጠዉ ዉሳኔ ይግባኝ የጠየቀ ቢሆንም ለተፈፀመዉ ወንጀል ተገቢዉን ዉሳኔ ከማሰጠት አኳያ በክስ አመሰራረቱ ላይ የተፈጠረዉን ክፍተት በጥናት ላይ ተመስርቶ በማረም ተገቢ እና ተመጣጣኝ ዉሳኔ ለማሰጠት እንደሚሰራም የፍትህ ቢሮው ገልጿል።
#TikvahethMagazine
ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
ምንም ውሳኔ ከመወሰንዎ በፊት አማራጭ የሕግ እውቀት ያግኙ::
0920666595
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig?si=BQvQV6OdOb6G8WI1

በግደያ ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በፅኑ እስራት መቀጣቱን ፖሊስ አሳወቀ‼️
*
የአሶሳ ዩንቨርሲቲ ተማሪ የሆነችውን ግለሰብ በጩቤ ሶስት ቦታ በጀርባዋ በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ (18) አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የአሶሳ ከተማ አስ/ር ወረዳ አንድ ፖሊስ አስታወቀ።
በዕለተ ዕሮብ ግንቦት 9/2016 ዓ/ም በግምት ከጧቱ 2፡45 ሰዓት አከባቢ ተከሳሽ አቶ ዩሀንስ መርጋ ኢተቻ የተባለው ግለሰብ የሴት ጓደኛው የሆነችው ተማሪ ደራርቱ ለሜሳ የተባለችው ላይ ጭካኔ በተሞላበት የግድያ ወንጀል በመፈፀሙ ተከሳሽ በፈፀመው ሰው በመግደል ወንጀል ተከሷል።
መርማሪ ፖሊስ እና ዐቃቢ ህግ በጋራ በመሆን ተጠርጣሪው ላይ ክስ መስርተው ምርመራ በማጣራት የወንጀል ድርጊቱን የሚያስረዱ የሰው ማስረጃና የህክምና ማስረጃ በማስደገፍ ለሚመለከተው ፍ/ቤት ልኳል።
የክስ መዝገቡ የደረሰው የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍ/ቤትም መዝገቡን ሲመርምር ከቆየ በኃላ የኢ/ፌ /ድ/ሪ .የወንጀል ህግ አንቀጽ 539(1ሀ) ስር የተመለከተውን መተላለፉ ካረጋገጠ በኃላ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ በመሆኑ በቀን 15/9/2016 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት እሱንም ያርማል ማህበረሰቡንም ያስተምራል በማለት በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንድቀጣ ዉሳኔ አስተላልፎል።
[መረጃውን አሶሳ ዩንቨርሲቲ ከአሶሳ ከተማ ወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤትን ዋቢ በማድረግ የዘገበው ነው]