የሥራ ቦታ ዝውውርን ሠራተኛን ለማሰናበት በእጅአዙር መጠቀም /Constructive dismissal/
በአሠሪ እና ሠራተኛ ሕጉ መሠረት አሠሪው ሠራተኛውን ከቦታ ቦታ አዘዋውሮ የማሠራት ሥልጣኑ እስከ ምን ድረስ ነው? አሠሪ በቂ ምክንያት ሳይኖረው ሠራተኛውን ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ ማዘዋወር ይችላል? ሠራተኛው በአዲሱ የሥራ ቦታ ለመገኘት የማይችልበት በቂ ምክንያት ቢኖረው እና በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሪፖርት ሳያደርግ ቢቀር የሚኖረው ሕጋዊ ውጤት ምንድን ነው? በጉዳዩ የሰበር ችሎት አቋምስ ምን ይመስላል?
በኢትዮጵያ አሠሪና ሠራተኛ ሕግ እንዲሁም በሰበር ችሎት የተሰጡ አስገዳጅ ውሳኔዎች ለቀጣሪዎች የተለጠጠ ሠራተኛን የማስተዳደር ሥልጣን (Managerial prerogative) ይሰጣሉ፡፡ በመሆኑም አንዳንድ አሠሪዎች የሥራ ቦታ ዝውውርን እንደሁነኛ ሠራተኛን የመቅጫ መንገድ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡ አሠሪ የዓይንህ ቀለም አላማረኝም በማለት ሠራተኛውን ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ሲያዘዋውር ሠራተኛው ቅሬታ ቢኖረው እንኳን ወደተዘዋወረበት ቦታ ሔዶ ሥራ ከጀመረ በኋላ ክስ ማቅረብ ከመቻሉ በቀር ባለበት ቦታ ቅሬታውንም ይሁን ክሱን ማቅረብ አይችልም፡፡ የሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 37778፣ 38189 እና በሌሎች መዝገቦች በሰጠው ውሳኔ አንድ ሠራተኛ የዝውውርን ትእዛዝ ባለመቀበል ለአምስት ተከታታይ ቀናት አዲስ ወደተመደበበት የሥራ ቦታ ላይ ሪፖርት ካላደረገ እና ሥራውን ካልጀመረ በአሠሪና ሠራተኛ ሕጉ አንቀጽ 27 መሠረት ለሥራ ስንብት ምክንያት እንደሚሆን ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
የሰበር ችሎት በመ/ቁ 37778 (ቅጽ 8 ኅዳር 4 ቀን 2001) በአሠሪ በተደረገ የሥራ ዝውውር ቅሬታ አድሮብኛል በሚል ምክንያት ከሥራ መቅረት የሕግ ድጋፍ እንደሌለው ሲገልጽ በሰ/መ/ቁ 41623 (ቅጽ 8 መጋቢት 8 ቀን 2001) ላይ ደግሞ በአሠሪው ወደሌላ ቦታ ተዘዋውሮ እንዲሠራ የተደረገ ሠራተኛ ዝውውሩን በወቅቱ ሳይቃወም የተዘዋወረበት የሥራ ገበታ ላይ ለ 5 ተከታታይ ቀናት የቀረ እንደሆነ የሥራ ውሉን ለማቋረጥ በቂ ምክንያት እንደሆነ ያትታል፡፡
በሌላ በኩል ሠራተኛው ወደ ተዘዋወረበት ቦታ ተገኝቶ ሥራ መጀመር ሲገባው ይህን አለማድረጉ አሠሪው እርምጃ ከመውሰዱ በፊት የነገሩን ነባራዊ ሁኔታ ማየት ያለበት ስለመሆኑ ሰበር ችሎት በመ/ቁ 125004 ቅጽ 20 ላይ ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡ ችሎቱ ሠራተኛው በተዘዋወረበት ቅርንጫፍ ለመገኘት የሚፈጅበትን ጊዜ ግምት ውስጥ በማስገባት በተባለው ቀን መድረስ እንደማይችል ግምት በመውሰድ ስንብቱ ሕገወጥ ነው ብሏል፡፡
በዝውውር ምክንያት የሥራ ውል የመቋረጥ አግባብነት ጭብጥ ሆኖ በተያዘበት የሰ/መ/ቁ 238246 (አመልካች ወጋገን ባንክ አክሲዮን ማህበር እና ተጠሪ አቶ መንግሥቱ ካሣ መጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ያልታተመ) ችሎቱ በሰጠው ትንታኔ የሥራ ውሉ የተቋረጠበት አግባብ እና ሕጋዊ ውጤቱ እንደውሉ፣ የሥራው ዓይነት እና የሥራ ውሉ የተቋረጠበት ምክንያት የሚለያይ መሆኑን ያስረዳል፡፡
ስለሆነም በሥራ ውሉ የሥራ ቦታው አዲስ አበባ መሆኑ ከተገለጸ አሠሪ ከአዲስ አበባ ውጪ ወደ ሌላ ቦታ አዘዋውሮ ማሠራት አይችልም፡፡ (በአሠሪና ሠራተኛ ሕግ አንቀጽ 4/3 ማንኛውም የሥራ ውል የሥራውን ዓይነትና ቦታ መያዝ እንዳለበት ይገልጻል፡፡ ቦታው በውሉ አለመገለጹ የሚኖረው ውጤት አጠያያቂ ነው)
በሌላ በኩል በጥበቃነት የተቀጠረ አንድ ሠራተኛ ይሠራበት ከነበረው አዲስ አበባ አንስቶ ደሴ ላይ ማዘዋወር ሥራው ካለው ባህሪ አንጻር አዲስ በተመደበበት ቦታ በቀላሉ ሊተካ የሚችል በመሆኑ እና ሠራተኛውን ከማዘዋወር ይልቅ ሌላ ሠራተኛ መቅጠር የሚቀል በመሆኑ ዝውውሩ አግባብ አይሆንም፡፡
በሰ/መ/ቁ 238246 ላይ አሠሪው ሠራተኛውን አዘዋውሮ የማሠራት መብት ያለው መሆኑን ቢያስረዳም ሠራተኛው ወደተመደበበት ቦታ ለመሄድ የማይችልበትን ምክንያት በበቂ ሁኔታ ካስረዳ ስንብቱ ሕገወጥ እንደሚሆን ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም በዚህ ውሳኔ መሠረት ሠራተኛው ወደተመደበበት ቦታ መሄድ ያልቻለበትን በቂ ምክንያት በማስረጃ የማስረዳት ሸክም /burden of proof/ ያለበት ሲሆን ፍርድ ቤቱ ምክንያቱ በቂ ነው ብሎ ካመነ ዝውውሩን ሊያግድ ይችላል፡፡
በአብዛኛው የሥራ ቦታ ዝውውር የሚደረገው እንደ ጥበቃ ባሉ የሥራ ዘርፎች ሲሆን ሠራተኛውን ከሥራ ለማሰናበት እንደ legal loop hole በመሆን ሲያገለግል ይታያል፡፡ በአገራችን ያለው ዝቅተኛ የደመወዝ ምጣኔ እና በየዕለቱ የሚጨምረው ኑሮ ውድነት Stagflation የሚያስከትለው ጫና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ ወገኖች የራስ ምታት መሆኑ ቀጥሏል፡፡ ይባስ ብሎ በሥራ ቦታ ዝውውር ስም የሠራተኞቹ job security ጥያቄ ውስጥ መግባቱ አሳሳቢ ነው፡፡ አንድ ሠራተኛ ዝውውሩ ሕገወጥ ነው በማለት እየተከራከረ እያለ በተዘዋወርክበት ቦታ ሔደህ ክሰስ ማለት የሠራተኛውን ፍትሕ የማግኘት መብት በጥብቅ የሚጋፋ ነው፡፡ በመሆኑም የሰበር ችሎት በሰ/መ/ቁ 238246 የሰጠው ውሳኔ ተገቢ እና ቅጥ አጥቶ የነበረውን የአሠሪዎች የማስተዳደር ሥልጣን (Managerial prerogative) ልክ ያበጀለት ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡
#solomon Baye

#ጋብቻ
አሳስቢውን የጋብቻ ፍቺ ለመግታት ወደ ጋብቻ ከማምራት በፊት የጋብቻን መርህ ፣ ዓላማ ምንነት ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል ሲሉ የጋብቻ እና ቤተሰብ አማካሪ ባለሞያው ተናገሩ።
የጋብቻ እና ቤተሰብ አማካሪ አቶ ይመስገን ሞላ ትዳራቸውን ለማትረፍ ምክር ፈልገው የሚመጡ ቤተሰቦች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።
የጋብቻ እና ቤተሰብ አማካሪው ምን አሉ ?
" የችግሩ አይነት እየበዛ እየጨመረ መጥቷል። በዚህም ቢሯችን የምናስተናግደው እንኳን አብዛኛው ችግር ሲገጥማቸው ለምክር የሚመጡ ናቸው ለመገንባት ከሚመጡ ይልቅ።
በሀገራችን ምክንያት ተብለው የሚሰጡ አሉ፦
- የመጀመሪያው በወሲብ አለመጣጣም ይባለል ፣
- በገንዘብ እጥረት ይባለል አብዛኛው የሚፋታው ግን ገንዘብ ሲያገኝ ነው፣
- የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት / የጓደኛ ጠልቃ ገብነት ይባለል ይህም ቢሆን የግንኙነቱን ስስ መሆን ያሳያል፣
- የኮሚኒኬሽን ችግር ይባላል ፣
- አሁን እየጨመረ የመጣው የእምነት ጉዳይ ይነሳል በሁለቱ መካከል አለመተማመን አለ ምክንያት የሚባሉት እነዚህ ናቸው።
ለእኔ ግን ከዚህም በላይ ተጨማሪ ምክንያቶች አሉ ፦
- ያለን መንፈሳዊ እሴት መበላሸት አንድ ነገር ነው ፤
- በጾታዊ አክራሪነት የመጣው የወንድ እና የሴት ፆታ መገፋፋት ፣ አለመቀባበል በሁለቱ መካከል ያለው መተባበር ሳይሆን መፎካከር ስላለ፣ እንደ ባል እና ሚስት ሚናቸውን አለማወቃቸው ምክንያት ናቸው።
መጋባት ይፈልጋሉ ተዋደን ይሆናል ብለው መዋደድ ግን የጋብቻ መሰረት አይደለም ወይም ፍቅር ስላለ ጋብቻ መሰረት አያገኝም ውጤታማም አይሆንም። የጋብቻ መርህ አላማ፣ የጋብቻን ምንነት መረዳት ይጠይቃል። የነዚህ ሁሉ ድምር ውጤቶች ጋብቻ እንዳይፀና ቤተሰብ እንዲፈርስ ያደርጋል።
ወደ ጋብቻም ወደ ቤተሰብም የገቡ ሰዎች አስበው አይገቡበትም፤ ገብተው ምን እንደሚያደርጉ፣ ከመግባታቸው በፊት ምን መዘጋጀት እንዳለባቸው ስለማያውቁ ጋብቻው እንዳይዘልቅ ቤተሰብም እንዲፈርስ ዋነኛ ምክንያት ይሆናሉ። "
ባለሞያው ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ወደ ትዳር የሚገቡ #ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልጸው ከጋብቻ በፊት ስልጠና የመውሰድ ልምድም እያደገ ነው ብለዋል። ይህ ፍቺን ለመቀነስ ሚና እንዳለው ጠቁመው ከምንም በላይ ግን ቤተሰብ ልጆችን ሲያሳድግ አርያ መሆን አለበት ብለዋል።
ባለሞያው ፦
" ጋብቻ ብዙ ጊዜ እኛም ሀገር አይተን እንደሆነ ስመረቅ፣ ቤት ስገዛ ፣ስራ ስይዝ ብለው condition ያስቀምጣሉ ጋብቻ ግን Condition ሳይሆን Qualification ነው የሚጠይቀው። የበቃች ሚስት የበቃ ባል ለመሆን እራሱን አስቀድሞ ማዘጋጀት አለበት።
ለምሳሌ ፦ ባልነት ለበሰለ ወንድ ነው ኃላፊነት ለመሸከም ለበቃ ወንድ ነው ሚስትነትም እንደዛው ስለዚህ ከመዋደድ ያለፈ የመጋባት ምክንያትና ኃላፊነት የመወጣት አቅም ይጠይቃል። አንድ ወንድ ባል የሚሆነው ብስለቱና ብቃቱ ነው ወንድነቱ ብቻ ባል አያደርገውም። ስለዚህ ይህን ለማድረግ በግል እራስን መገንባት አለበት።
ወላጆች ልጆቻቸውን ለራሳቸው ጥሩ ልጅ፣ ለዛ ቤት ደግሞ ጥሩ ባልና ሚስት እንዲሆኑ፤ ሲወልዱ ጥሩ አባት እና እናት እንዲሆኑ ሞዴል መሆን አለባቸው።
አሁን የሚታየው የጋብቻ መፍረስ፣ የፍቺው ብዛት፣ የልጆች መጎዳት ትላንት ያልተሰራው ስራ መዘዝ ነው። ነገም እንደዚያ ይቀጥል ከተባለ ዛሬ እያንዳንዳችን የራሳችንን ቤት ጠብቀን ልጆቻችንን ለጋብቻ ማብቃት (የራሳችንን ጋብቻ በመጠበቅ)፣ ልጆቻችን እንዲሰለጥኑ ማድረግ ጋብቻን አውቀው እንዲኖሩ ማድረግ መፍትሄ ነው " ብለዋል።
ፁሁፍ በቲክቫህ ቤተሰብ አባላት።
Credit፦ ቪኦኤ (አስማማው አየነው)
@tikvahethiopia

Public Information Noble (PIN) is an NGO/CSO that works to promote the right to access information.
They have a website at [pinngo.org](https://www.pinngo.org) where you can find more information about their work. In addition, they have a presence on various social media platforms such as Facebook, Twitter, Telegram, YouTube, LinkedIn, and TikTok.
You can find their official Facebook page at
[facebook.com/PublicInformationNoble](https://www.facebook.com/PublicInformationNoble?mibextid=ZbWKwL),
their Twitter handle at
[@PINNGO_org](https://twitter.com/PINNGO_org?t=xKZd2ejDdUIKvS4bkrdZ5A&s=09),
their Telegram channel at
[t.me/PublicInformationNoble](https://t.me/PublicInformationNoble),
their YouTube channel at
[youtube.com/@PublicinformationNoblePIN](https://youtube.com/@PublicinformationNoblePIN?si=xVQQAoiVF-nqw1dN),
and their TikTok account at
[vm.tiktok.com/ZMjNEvekB/](https://vm.tiktok.com/ZMjNEvekB/).
You can also reach out to them via email at support@pinngo.org or info@pinngo.org.

Facebook
Log in to Facebook
Log in to Facebook to start sharing and connecting with your friends, family and people you know.
ከወጪ መጋራት ጋር ተያይዞ የአሰሪዎች ግዴታ
ማንኛውም አሰሪ፡-
1. የቀጠራቸውን ተጠቃሚዎች ዝርዝር ለባለሥልጣኑ ወይም ለሚመወክለው የማስታወቅ
2. በገንዘብ ለመክፈል ግዴታ ከገቡ ተጠቃሚዎች የሚፈለግባቸውን እዳ የሚያሳይ ማስረጃ ከተጠቃሚዎቹ በመቀበልና ስለ ትክክለኛነቱ ከሚኒስቴሩ በማረጋገጥ በየወሩ ከጥቅል ደመወዛቸው ቢያንስ 10% እየቀነሰ ከእያንዳንዱ ወር መጨረሻ አንስቶ ባሉት ሰላሳ ቀናት ውስጥ ለሚኒስቴሩ ወይም ለሚወክለው የመክፈል
3. ተጠቃሚዎች ከተቋሙ የተሰጣቸውንና የሚፈለግባቸውን እዳ የሚያሳየውን ማስረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ ካልሆኑ የጥቅል ደመወዛቸው አንድ ሶስተኛ እየቀነሰ ለሚኒስቴሩ ወይም ለሚወክለው ገቢ የማድረግ፣
4. ገንዘብ በመክፈልም ሆነ አገልግሎት በመስጠት እዳቸውን ከፍለው ያጠናቀቁ ተጠቃሚዎችን ዝርዝር ክፍያው በተጠናቀቀበት ወር ለሚኒስቴሩ ወይም ለሚወክለው የማሳወቅ
5. አገልግሎት በመስጠት እንደሚከፍሉ ተገልጾ የተመደቡለትን ተጠቃሚዎች ተገቢውን ክትትል በማድረግ ማሰራትና አገልግሎት ካቋረጡ ሙሉ ለሙሉ ማቋረጣቸውን በማረጋገጥ ወዲያውኑ ለሚኒስቴሩ፣ ለትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም ለመደባቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የማሳወቅ ግዴታ አለበት ፡፡

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ መግለጫ
=========================
NBE’ Monetary Policy Explanation (Amh. Version)
#Ale_Hig #Lawsocieties #Share #ሼር @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አዲስ አበባ
የፍትህ ሚኒስቴር ክበቶች የግብር አከፋፈል ጋር በተያያዘ የሂሳብ መዝገብ እንዲይቡ በሕግ የሚሄዱ የደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዮች በተመለከተ መ, 03/12/2015 በቁጥር ማንን ገና በተግራ ደብዳቤ ጠበቆቹ ግብር የሚከፈልበትን ገቢ ለማስገኘት ያወጣቸው አስፈላጊ ወጪዎች በተተኛነት እንዲያበላቸው ሆቴ የግብር ግዴታቸውን እንዲወጡ ያስተላለፈው መመሪያ ከጠበቆች የግብር አከፋፈል ጋር በተያያዘ የሚሉ አብዛኞቹን ችግሮች የሚፈታ መሆኑን ሆኖም መመሪያው በቅርቡ የተላለፊ በመሆኑ የ15 ዓም የግብር መክፈያ ወቅት ጠበቆቹ ለሥራቸው ያወጧቸውን ወጪዎች ወደኋላ ተመልስው የሂሳብ መዝገብ ለማደራጀት የማይችሉ በመሆኑ ለ2016 የግብር ዓመት በተላለፈው መመሪያ መሠረት የግብር አከፋፈሉ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ጠበቆቹ የዚህ ዓመት የግብር ግዴታቸውን በቀደመው አስራር መሠረት እንዲስተናገዱ ነሐሴ 25 ቀን 2015 በቁጥር /ሚ/1156 በተፃፈ ደብዳቤ ያቀረበውን ጥያቄ ይመለከታል።
የደረጃ "ሀ" እና የደረጃ "ለ" ግብር ከፋይ ጠበቆች የሚያወጡት የነዳጅ ወጪ እና ሌሎች መሰል ወጪዎችን በተመለከተ ወረው ግቢውን ለማመንጨት የወጣ ወጪ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ የንግድ ፈቃድ ወይም የተሽከርካሪ ታርጋ ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ክግምት ውስጥ ሳይገባ በማስረጃ ተረጋግጦ በሚቀርበው መሠረት እሚያስገኘው ገቢ አኳያ ያልተጋነነ እና ተመጣጣኝ መሆኑ እየተረገጠ ወሬው በተቀናሽነት እንዲያዝ ሆኖ የሚጠበቅባቸውን ግብር እንዲከፍሉ ሊደረግ የሚገባ መሆኑን ከዚህ በላይ ቀንና ቁጥሩ በተገለፀው ደብዳቤ በተላለፈ መመሪያ የተመለከተ መሆኑ ይታወቃል።
ሆኖም በሠንጠረዥ | ሥር ተመድቦ የሚከፈለውን የገቢ ግብር የመክፈል ግዴታ ያለባቸው የደረጃ ሀ እና የደረጃ "ለ" ግብር ከፋይ ጠበቆች እና ሌሎች መሰል እንደኢንሹራንስ ብሮከርስ ያሉ ግብር ከፋዮች ለትክክለኛ ግብር አወሳሰንና አከፋፈል የሚረዱ አግባብነት ያላቸውን የሂሳብ መዝገቦች በመያዝ የግብር ግዴታቸውን ሲወጡ የሚገባ ሲሆንም ለበርካታ ዓመታት በቁርጥ ግብር ሲስተናገዱ የነበረ በመሆኑ ወደኋላ ተመልሰው ተገቢውን የሃሳብ መዝገብ በማቅረብ በተላለፈው መመሪያ መሠረት የ2015 ዓ.ም የግብር ግዴታቸውን ሊወጡ እንደማይችሉ መገንዘብ የተቻለ በመሆኑ ለችግሩ መፍትሔ መስጠት ተገቢ መሆኑ ታምኖበታል።
ስለዚህ የግብር አከፋፈሉ ለሚቀጥሉት የግብር ዓመታት በተላለፈው መመሪያ መሠረት ተግባራዊ የሚደረግ መሆነ እንዲሁም ግብር ከፋዮቹ ይህንኑ ተገንዝበው የግብር ግዴታቸውን በተላለፈው መመሪያ መሠረት ሊወጡ የሚገባ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የሚጠበቅባቸውን የሃሳብ መዝገብ ያላቀረቡ የደረጃ "ሀ" እና የደረጃ "ለ" ግብር ክፋይ ጠበቆች እና ኢንሹራንስ ብርክርስ የሂሳብ መዝገብ ባለመያዝ በሕጉ መሠረት እየተቀጡ ለመጨረሻ ጊዜ ለዚህ የግብር ዓመት በመመሪያ ቁጥር 138/2010 የሂሳብ መዝገብ ያልያዙ ግብር ከፋዮች በሚስተናገዱበት የቁርጥ ወጪ ሰንጠረዥ መሠረት እንዲስተናገዱ እንዲደረግ የተወሰነ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ገንዘብ ሚኒስቴር
በኢዮብ ተካልኝ (ዶር ሚኒስትር ዴኤታ)

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

✅የወንጀል ፍርድ ለፍትሐብሔር ጉዳይ ያለው #የማስረጃ_አግባብነት
👉በወንጀል ጉዳይ ተከሶ ጥፋት የሌለበት መሆን በራሱ በተመሳሳይ ጉዳይ በፍትሐብሔር ከቀረበ ክስ ነፃ ለመውጣት እንደ በቂና የመጨረሻ መስፈርት እንደማይወሰድ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2149 ቢደነግግም ድንጋጌው የወንጀሉ ፍርድ ለተመሳሳይ የፍትሐብሔር ክርክር ያለውን የማስረጃ አግባብነት አይናገርም። በሰ/መ/ቁ. 43843 ቅጽ 10 (አመልካች ዶ/ር ተስፋነሽ በላይ እና ተጠሪ አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ መጋቢት 21 ቀን 2002 ዓ.ም.) የአመልካች ሾፌር ተጠሪ የመድን ሽፋን የሰጠውን መኪና ገጭቶ ጉዳት በማድረሱ ለባለመኪናው የተከፈለውን ካሳ እንዲመልስ ተጠሪ ያቀረበውን ጥያቄ የስር ፍርድ ቤቶች ተቀብለው አመልካችን ተጠያቂ ያደረጉት ሲሆን የሰበር ችሎትም ውሳኔያቸው በሰበር ችሎትም ፀድቋል።
👉መዝገቡ እንደሚያስረዳው የአመልካች ሾፌር የወንጀል ክስ ቀርቦበት በነጻ ወጥቷል። ሆኖም በፍትሐብሔር ክርክሩ ላይ ጥፋቱ የአመልካች ስለመሆኑ የትራፊክ ምርመራ ሪፖርት በማስረጃነት ቀርቧል። የስር ፍርድ ቤቶች አመልካችን ተጠያቂ ለማድረግ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2149 ከመጥቀስ ባለፈ የአመልካች ሾፌር ነጻ ሊባል የቻለበት ምክንያት እና በወንጀሉ ክርክር ላይ የትራፊክ ሪፖርት ስለመቅረቡ እንዲሁም በወንጀሉ ክስ ላይ የተገለጹት ፍሬ ነገሮች እና በትራፊክ ሪፖርቱ ላይ የተገለጹት ፍሬ ነገሮችን በግልጽ በመለየት የወንጀል ፍርዱን እንደ አንድ ማስረጃ ተጠቅመው መዝገቡን አልመረመሩም።
👉በአጠቃላይ በሰ/መ/ቁ. 43843 የተጠያቂነት እንጂ የማስረጃ ጥያቄ በወጉ አልታየም።
የሰበር ችሎት ይህን መሰረታዊ ነጥብ በመሳቱ የማስረጃ አግባብነትን በተጠያቂነት ተክቶታል። ይሄው አቋሙ በሌላ መዝገብ ላይም ተደግሟል። በሰ/መ/ቁ. 78414 ቅጽ 14 (አመልካች የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ እነ አቶ ቶላ መገርሣ ጥቅምት 07 ቀን 2005 ዓ.ም.) በወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ሰው በፍትሐብሔር ተጠያቂ መደረግ እንዳለበት አቋም ተይዟል።
👉በወንጀል ጉዳይ የተሰጠ ውሳኔ በዚያው ጉዳይ በፍትሐብሔር ክርክር አግባብነትና ብቃት የሚኖረው በወንጀል ክሱ ተከሳሹ ጥፋተኛ ተብሎ የተወሰነ ከሆነና ወደዚያ ድምዳሜ ለመድረስም በወንጀል ጉዳይ የተሰሙት ማስረጃዎች በፍትሐብሔሩ ጉዳይ ቀርበው የተሰሙ እንደሆነ ነው። በወንጀል እና በፍትሐብሔር ጉዳይ የተሰሙት ማስረጃዎች የተለያዩ ከሆነ እና በወንጀል ጉዳይ ክስ የቀረበበት ነጥብም ከፍትሐብሔሩ ክስ ጋር ግንኙነት የሌለው ከሆነ በወንጀል ክስ ተጠያቂ መሆን ሁልጊዜ በፍትሐብሄር ክስ ሀላፊነትን አያስከትልም። በዚህ መልኩ የሰበር ችሎት የተስተካከለ አቋም የያዘው በሰ/መ/ቁ. 46386 (አመልካች አቶ ሃይሉ ተስፋኡ እና ተጠሪ አቶ ብርሃነ መብራቱ ታህሣሥ 03 ቀን 2004 ዓ.ም ቅጽ 13) ነው።
#የማስረጃ_ህግ
credit to Abrham Yohannes

ከቀናት በፊት በሰ/መ/ቁ. 230023 በሰበር ችሎት የተሰጠውን የህግ ትርጉም post ውሳኔው በርካታ የህግ ባለሞያዎችን ያስደነግጣል: የመነጋገሪያ ርዕስ ይሆናል የሚል ግምት ነበረኝ።
አሁንም በጣም ላሳጥረውና የውሳኔውን ይዘት በድጋሚ ልግለፀው።
የሰበር ችሎት De Facto Divorce በተመለከተ የሰጠው የህግ ትርጉም በፌዴሬሽን ምክር ቤት መስከረም 27 ቀን 2012 በተሰጠ ውሳኔ ተሽሯል።
በሰ/መ/ቁ. 230023 ውሳኔ መሰረት የም/ቤቱ ውሳኔ ከ 2012 ዓ/ም በፊት ለተደረገ De Facto Divorce ተፈጻሚነት የለውም። ተፈጻሚነቱ ከ2012 ዓ/ም በኋላ ለተደረገ De Facto Divorce ነው።
ውሳኔው 4 ለ 1 በሆነ አብላጫ ድምፅ ነው የተሰጠው።
በእኔ እምነት ይህ ውሳኔ the most absird cassation decision. ችሎቱ ከም/ቤቱ ጋር እልህ የተጋባ ነው የሚመስለው።
#አብርሃም ዩሃንስ

የመከላከያ ማስፈቀጃ
በአጭር ስነ ስርዓት ታይቶ እንዲወሰን ክስ በሚቀርብበት ጊዜ ተከሳሹ ክሱን ለመከላከል እንዲፈቀድለት የሚያቀርበው አቤቱታ
በአጭር ሥነ ሥርዓት እንዲታይ በሚቀርብ ክስ አመራር ሥርዓት ተከሳሽ ለመከላከል እንዲፈቀድለት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት በፍ/ቤቱ አግኝቶ የተጠየቀውን ገንዘብ ላለመክፈል በቂ ምክንያት መሆን አለመሆኑ የሚታወቀው ፍ/ቤቱ ከአጭር ሥነ ሥርዓት ወደ መደበኛ የክርክር ሥነ ሥርዓት ውስጥ በመግባት ግራ ቀኙን በአግባቡ በማስረጃ ካከራከረ በኋላ ነው፡፡
የፈቃድ ጥያቄ ደረጃ ላይ የቼክ ባሕርይ ሳይሆን መታየት ያለበት ተከሳሽ ለመከላከል እንዲፈቀድለት ያቀረበው ምክንያት ፈቃድ የሚያሰጥ መሆን አለመሆኑን ነው፡፡ የፍሬ ነገር ክርክር ከፈቃድ በኋላ የሚታይ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 43315 ያልታተመ፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 284-286
#ethiolawtips

የኢትዮጵያ ሕጎችና የሰበር ውሳኔዎች ዳታቤዝ
ሰላም!
የአቢሲኒያሎው የሕግና የሰበር መረጃ ቋት አዳዲስ አዋጆችና ደንቦችን አካትቶ ተሻሽሏል። ሕጎችን አዋጆችን እና ደንቦችን ሲፈልጉ የሕጉን ቁጥር ብቻ በማስገባት ወይም የሰበር ውሳኔውን ቁጥር በማስገባት ማውረድና መጠቀም ይችላሉ።
ይህ የጎግል አይነት የመፈለጊያ ዘዴ ሲሆን የሚፈልጉት ሕግ ቁጥሩን ለምሳሌ 1234 ወይም የሕጉን ስያሜ አንድ ቃል ለምሳሌ ፍርድ ቤት ብለው በመጻፍ በአጭሩ ማግኘት ይችላሉ።
በዚህ የሕግና የሰበር ውሳኔዎች ቋት፦
1. የሚፈልጉትን ማናቸውንም ሕግ ወይም የሰበር ውሳኔ መፈለጊያ ውስጥ በተየባችሁ (ታይፕ ባደረጋችሁ) በአንድ ሰከንድ ውስጥ ያገኛሉ፤
2. የአንድን ሕግ ሁኔታ ማለትም ይሻር፣ ይሻሻል ወይም ተፈፃሚ ይሁን አይሁን እዛው መረጃውን ያገኛሉ፤
3. የሰበር ውሳኔዎችን በመዝገብ ቁጥራቸው ወይም በተከራካሪ ወገኖች ስም ብቻ ሳይሆን በክርክሩ ወይም ውሳኔው ውስጥ በተጠቀሰው አዋጅ ወይም ሕግ አንቀጽ ፈልገው ማግኘት ይችላሉ።
ይህንን ቋት ራሱን በቻለ አንድ መረጃ ውስጥ የከተትን ሲሆን በአቢሲኒያሎው ድረገጽ laws የሚለውን መስፈንጠሪያ በመጫን ወይም www.pocketlaw.abyssinialaw.com በሚለው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ።