አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የወንጀል ፍርድ ለፍትሐብሔር ጉዳይ ያለው #የማስረጃ_አግባብነት

👉በወንጀል  ጉዳይ  ተከሶ  ጥፋት  የሌለበት  መሆን  በራሱ  በተመሳሳይ ጉዳይ በፍትሐብሔር ከቀረበ ክስ ነፃ ለመውጣት እንደ በቂና የመጨረሻ መስፈርት እንደማይወሰድ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2149 ቢደነግግም ድንጋጌው የወንጀሉ ፍርድ ለተመሳሳይ የፍትሐብሔር ክርክር ያለውን የማስረጃ አግባብነት አይናገርም። በሰ/መ/ቁ. 43843 ቅጽ 10 (አመልካች ዶ/ር ተስፋነሽ በላይ እና ተጠሪ አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ መጋቢት 21 ቀን 2002 ዓ.ም.) የአመልካች ሾፌር ተጠሪ የመድን ሽፋን የሰጠውን መኪና ገጭቶ ጉዳት በማድረሱ ለባለመኪናው የተከፈለውን ካሳ እንዲመልስ ተጠሪ ያቀረበውን ጥያቄ የስር ፍርድ ቤቶች ተቀብለው አመልካችን ተጠያቂ ያደረጉት ሲሆን የሰበር ችሎትም ውሳኔያቸው በሰበር ችሎትም ፀድቋል።

👉መዝገቡ እንደሚያስረዳው የአመልካች ሾፌር የወንጀል ክስ ቀርቦበት በነጻ ወጥቷል። ሆኖም በፍትሐብሔር ክርክሩ ላይ ጥፋቱ የአመልካች ስለመሆኑ የትራፊክ ምርመራ ሪፖርት በማስረጃነት ቀርቧል። የስር ፍርድ ቤቶች አመልካችን ተጠያቂ ለማድረግ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2149 ከመጥቀስ ባለፈ የአመልካች ሾፌር ነጻ ሊባል የቻለበት ምክንያት እና በወንጀሉ ክርክር ላይ የትራፊክ ሪፖርት ስለመቅረቡ እንዲሁም በወንጀሉ ክስ ላይ የተገለጹት ፍሬ ነገሮች እና በትራፊክ ሪፖርቱ ላይ የተገለጹት ፍሬ ነገሮችን በግልጽ በመለየት የወንጀል ፍርዱን እንደ አንድ ማስረጃ ተጠቅመው መዝገቡን አልመረመሩም።

👉በአጠቃላይ በሰ/መ/ቁ. 43843 የተጠያቂነት እንጂ የማስረጃ ጥያቄ በወጉ አልታየም።
የሰበር ችሎት ይህን መሰረታዊ ነጥብ በመሳቱ የማስረጃ አግባብነትን በተጠያቂነት ተክቶታል። ይሄው አቋሙ በሌላ መዝገብ ላይም ተደግሟል። በሰ/መ/ቁ. 78414 ቅጽ 14 (አመልካች የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ እነ አቶ ቶላ መገርሣ ጥቅምት 07 ቀን 2005 ዓ.ም.) በወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ሰው በፍትሐብሔር ተጠያቂ መደረግ እንዳለበት አቋም ተይዟል።

👉በወንጀል ጉዳይ የተሰጠ ውሳኔ በዚያው ጉዳይ በፍትሐብሔር ክርክር አግባብነትና ብቃት የሚኖረው በወንጀል ክሱ ተከሳሹ ጥፋተኛ ተብሎ የተወሰነ ከሆነና ወደዚያ ድምዳሜ ለመድረስም በወንጀል ጉዳይ የተሰሙት ማስረጃዎች በፍትሐብሔሩ ጉዳይ ቀርበው የተሰሙ እንደሆነ ነው። በወንጀል እና በፍትሐብሔር ጉዳይ የተሰሙት ማስረጃዎች የተለያዩ ከሆነ እና በወንጀል ጉዳይ ክስ የቀረበበት ነጥብም ከፍትሐብሔሩ ክስ ጋር ግንኙነት የሌለው ከሆነ በወንጀል ክስ ተጠያቂ መሆን ሁልጊዜ በፍትሐብሄር ክስ ሀላፊነትን አያስከትልም። በዚህ መልኩ የሰበር ችሎት የተስተካከለ አቋም የያዘው በሰ/መ/ቁ. 46386 (አመልካች አቶ ሃይሉ ተስፋኡ እና ተጠሪ አቶ ብርሃነ መብራቱ ታህሣሥ 03 ቀን 2004 ዓ.ም ቅጽ 13) ነው።

#የማስረጃ_ህግ

credit to Abrham Yohannes
#Ale_Hig #Lawsocieties #Share #ሼር @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties