አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#Suicide #Abrham_Duressa

ዛሬ የደረሰን መረጃ ልባችንን ሰብሮታል

ነገሩ እንዲህ ነው #አብርሃም_ዱሬሳ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት የመውጫ ፈተና ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል ነበር እናም ፈተናውን ማክሰኞ፣ረቡዕ እና ሀሙስ በሰላም ተፈትኖ የመጨረሻው የፈተና ዕለት ማለትም አርብ የመፈተኛ ኮዱን ረስቶ ወደ ስድስት ኪሎ FB ኮሌጅ ይሄዳል ካለ መፈተኛ ኮዱ መግባት ስለማይችል ወደ ቤቱ ሽሮ ሜዳ ተመልሶ የመፈተኛ ኮዱን ይዞ ሲመጣ የመፈተኛ ሰዓት አልፏል ይባላል ፤ ፈተናው 3፡30 የሚጀመር ሲሆን #አብርሃም ግን 3፡40 ይደርሳል። ሱፐርቫይዘሩ መግባት እንደማይችል ሲነግረው ስላረፈደበት ምክንያት ሊያስረዳ ይሞክራል ተማሪ #አብርሃም_ዱሬሳም በተለያየ መንገድ ይማፀናል #አይነ_ስውር መሆኑን ታሳቢ አድርገው እንዲተባበሩት ቢለምንም ፈተናውን እንዲወስድ ግን አልፈቀዱለትም ።

ፈተናውን መፈተን ባለመቻሉ ሲያለቅስ ፥ ሲበሳጭ ይውላል ምሽት ላይ ወደ ቤቱ በመግባት በራሱ ላይ የወሰደው እርምጃ ህይወቱን እንዳሳጣው የቻናላችን ቤተሰብ የሆነ የ#አብርሃም_ዱሬሳ ጓደኛ የነገረን ሲሆን ተማሪ #አብርሃም_ዱሬሳ ፈተናውን ባለመውሰዱ እጅግ ተበሳጭቶ ሲያለቅስ ይውልና ምሽት ላይ ቤቱን ዘግቶ በራሱ ላይ ጋዝ አርከፍክፎ ከፍተኛ ቃጠሎ እንደደረሰበትና በኋላም ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ተወስዶ ቃጠሎው ከፍተኛ ስለነበር ህይወቱ እንዳለፈ ከጓደኛው ሰምተናል።

📌ጉዳዩን ለማጣራት ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደውለን ነበር ተማሪው የመጨረሻውን ፈተና እንዳልወሰደና ሲያለቅስም እንደነበረ አረጋግጠውልን ከግቢ ውጭ ስለተፈጠረው ጉዳይ ግን መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

📌ጉዳዩን ለማጣራት ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ለመደወል እየሞከርን ሲሆን ምላሻቸውን የምናሳውቅ ይሆናል።
#Suicide

🧿የተማሪ አብርሃም ዱሬሳ ጓደኛ ስለ ጉዳዩ ዝርዝር መረጃውን ነግሮናል ያድምጡ

📌ወንድማችን የላከልንን ፎቶ አስፈላጊ መስሎ ስላልተሰማን እኛው ጋር አስቀርተነዋል።

via Amharic tutorial class
በፍርድ ቤት 'የራስ አነሳሽነት' የሚሰጥ ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ እና የመሰማት መብት
#አብርሃም ዮሐንስ

በወንጀል ጉዳይ በተለይ ደሞ በፍትሐብሔር ክርክር ወቅት ፍርድ ቤት በራሱ አነሳሽነት ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ የመስጠት ሰፊ ስልጣን አለው። ጥቂት ምሳሌ መጥቀስ ቢያስፈልግ አቤቱታ እንዲሻሻል: ተጨማሪ ማስረጃ እንዲቀርብ ትዕዛዝ መስጠት፤ የስረ-ነገር ስልጣኑ ላይ ብይን መስጠት እንዲሁም የመብት መቅረት በጊዜ ገደብ ሲወሰን በመብቱ አለመኖር ላይ ውሳኔ መስጠት /ለምሳሌ አሰሪው የሚከራከርበት የስንብት ምክንያት ድርጊቱ መፈፀሙን አሰሪው ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ ሲታሰብ አንድ ወር ካለፈው/ የአሰሪው የማሰናበት መብት ቀሪ ይሆናል። ይህ ከይርጋ የተለየ እንደመሆኑ በፍርድ ቤቱ በራሱ ሊነሳ ይችላል። ከጊዜ ገደብ ጋር በተያያዘ የሰ/መ/ቁ 17361 ቅፅ 10 ይመለከቷል/

የራስ አነሳሸነት ለፍርድ ቤቱ አስገዳጅ ነው ወይስ 'የእንደፈቀደ' /discretionary/ ስልጣን የሚለው ጥያቄ መሰረታዊና አከራካሪ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሌላ ይበልጥ መሰረታዊ ጉዳይ ጥያቄ ሆኖ ሲነሳ አይታይም።

በራስ አነሳሽነት የሚሰጥ ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ መሰረታዊና እና ህገ-መንግስታዊ ከሆነው የመሰማት መብት አንጻር አሉታዊ እንደምታው በሚገባ አልተፈተሸም።

በምሳሌነት የስረ-ነገር ስልጣንን እንመልከት።
በተግባር እንደሚታየው ብሎም በስነ-ስርዓት ህጉ እና በሰበር ትርጉም ጭምር ድጋፍ ያገኘው አቋም አንድ ፍርድ ቤት የሰረ-ስልጣን ከሌለው በተከራካሪ ወገኖች ባይነሳም በራሱ አነሳሽነት መዝገቡን መዝጋት ይኖርበታል።
ግን በራስ አነሳሽነት ሲባል ምን ማለት ነው? በራስ አነሳሽነት የሚያስገነዝበው ፍርድ ቤቱ ነጥቡን መጀመሪያ በክርክር ወቅት ማንሳት አለበት ማለት ነው። የሚያነሳው ደግሞ ለተከራካሪ ወገኖች ነው። በዚሁ መሰረት ተከራካሪ ወገኖች በተነሳው ነጥብ ላይ ያላቸውን የህግ ክርክር ብሎም ማስረጃ ማቅረብ ወይም ማሰማት አስፈላጊ ከሆነ ማስረጃቸውን ሊያሰሙ ይገባል። የመሰማት መብት በግራ ቀኙ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ፍርድ የሚያነሳውንም ነጥብ ይጨምራል።

በራስ አነሳሽነት ማለት ተከራካሪ ወገኖች ሳያውቁትና ሳይሰሙ በድንገት እና በድብቅ የሚሰጥ ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ ማለት አይደለም። ፍርድ ቤት የስረ-ነገር ስልጣኑን የሚወስነው በግምት ሳይሆን በተረጋገጡ አግባብነት ያላቸው ፍሬ ነገሮችና በህጉ ትርጓሜ ላይ በመመስረት ነው። በፍሬ ነገር /ማስረጃ/ እና የህግ ትርጉም በሚመለከት ጉዳይ ተከራካሪ ወገኖች የመሰማት መብት አላቸው።

ነገሩን እንደሚከተለው እንመልከተው።
የስረ-ነገር ስልጣን መቃወሚያ በተከራካሪ ከተነሳ ተቃራኒው ወገን የመሰማት መብት ካለው ፍርድ ቤት ስላነሳው ብቻ ይህን መብቱን የሚያጣበት አንዳችም የህግ መሰረት የለም።
በተጨማሪም ተካራካሪዎችን ያላሳተፈ 'የራስ አነሳሽነት' ለስህተት የመጋለጡ ዕድል በጣም ሰፊ ነው።

እንበልና በመኪና አደጋ የተነሳ ከውል ውጭ ሀላፊነት ክስ ሲቀርብ ተከሳሽ በመልሱ ላይ የጠቀሰው አድራሻ ተከራካሪዎች የተለያየ ክልል ነዋሪዎች መሆናቸውን ይጠቁማል። ሆኖም ተከሳሽ የጠቀሰው ቤተሰቡ የሚኖርበትን አድራሻ እንጂ መደበኛ የንግድ ስራውን የሚያከናውነውና አብዛኛውን ጊዜ የሚኖረው አደጋው በደረሰበት ክልል ነው። ተከሳሽ የስረ-ነገር ስልጣን አላነሳም። ከሳሽም በዚህ ነጥብ ላይ ማስተባበያ አላቀርበም። ካሁን አሁን ፍርድ ቤት በራሱ አነሳሽነት የስረ-ነገር ስልጣኑን በዚህ ላይ ተመስርቶ ብይን ሊሰጥ ይችላል በሚል ስሌት ማስተባበያ እንዲያቀርብም አይጠበቅበትም። ፍርድ ቤት በራሱ የሚያነሳቸው ነጥቦች በርካታ እንደመሆናቸው የትኛውም የህግ ባለሞያ ሁሉንም ከወዲሁ ሊያውቃቸው ሆነ ሊገምታቸው አይችልም።

ፍርድ ቤት በራስ አነሳሽነት የስረ-ነገር ስልጣኑን የመወሰን ሀሳብ ካለው ማድረግ ያለበት ተከራካሪ ወገኖች የተለያየ ክልል ነዋሪዎች መሆናቸውን እንደ ምክንያት ይዞ በራሱ ጊዜ መዝገቡ መዝጋት አይደለም። መጀመሪያ ከስልጣን ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤቱ የስረ-ነገር ስልጣኑን ለመወሰን የተከራካሪ ወገኖች አድራሻ መጣራት እንዳለበት ለተከራካሪ ወገኖች በመንገር በዚህ ረገድ የህግ ክርክር ካላቸው በተጨማሪም ክርከራቸውን የሚደግፍ ማስረጃ ካላቸው እንዲያቀርቡ ዕድል መስጠት አለበት። ይህ ሲሆን ነው ተከሳሽ የንግድ ስራውና አብዛኛውን ጊዜ የሚኖረው አደጋው በደረሰበት ክልል መሆኑን ከሳሽ ማስተባበያ ማቅረብ የሚችለው። በተጨማሪም አንድ ሰው የንግድ እና የቤተሰብ መኖሪያ ስፍራው የተለያየ ከሆነ ለስረ-ነገር ስልጣን አወሳሰን የየትኛው ክልል ነዋሪ ነው? የሚለው የህግ ጭብጥ ግራ ቀኙ ሊከራከሩበት ይገባል።

በአጠቃላይ 'በራስ አነሳሽነት' ማለት ፍርድ ቤት በራሱ ጊዜ የሚያነሳው ሆኖም ባነሳው ነጥብ ላይ ግራ ቀኙ የመሰማት መብታቸው ተጠብቆ ከተከራከሩ በኋላ የሚሰጥ ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ ማለት እንጂ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ሳያውቁት ፍሬ ነገሩን በራሱ ገምቶ፣ የህጉን ትርጉም ለብቻው አውጥቶ አውርዶ መጨረሻ ላይ ድንገት የሚሰጠው ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ ማለት አይደለም።
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ከቀናት በፊት በሰ/መ/ቁ. 230023 በሰበር ችሎት የተሰጠውን የህግ ትርጉም post ውሳኔው በርካታ የህግ ባለሞያዎችን ያስደነግጣል: የመነጋገሪያ ርዕስ ይሆናል የሚል ግምት ነበረኝ።
አሁንም በጣም ላሳጥረውና የውሳኔውን ይዘት በድጋሚ ልግለፀው።

የሰበር ችሎት De Facto Divorce በተመለከተ የሰጠው የህግ ትርጉም በፌዴሬሽን ምክር ቤት መስከረም 27 ቀን 2012 በተሰጠ ውሳኔ ተሽሯል።
በሰ/መ/ቁ. 230023 ውሳኔ መሰረት የም/ቤቱ ውሳኔ ከ 2012 ዓ/ም በፊት ለተደረገ De Facto Divorce ተፈጻሚነት የለውም። ተፈጻሚነቱ ከ2012 ዓ/ም በኋላ ለተደረገ De Facto Divorce ነው።
ውሳኔው 4 ለ 1 በሆነ አብላጫ ድምፅ ነው የተሰጠው።
በእኔ እምነት ይህ ውሳኔ the most absird cassation decision. ችሎቱ ከም/ቤቱ ጋር እልህ የተጋባ ነው የሚመስለው።

#አብርሃም ዩሃንስ