የሥራ ቦታ ዝውውርን ሠራተኛን ለማሰናበት በእጅአዙር መጠቀም /Constructive dismissal/
በአሠሪ እና ሠራተኛ ሕጉ መሠረት አሠሪው ሠራተኛውን ከቦታ ቦታ አዘዋውሮ የማሠራት ሥልጣኑ እስከ ምን ድረስ ነው? አሠሪ በቂ ምክንያት ሳይኖረው ሠራተኛውን ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ ማዘዋወር ይችላል? ሠራተኛው በአዲሱ የሥራ ቦታ ለመገኘት የማይችልበት በቂ ምክንያት ቢኖረው እና በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሪፖርት ሳያደርግ ቢቀር የሚኖረው ሕጋዊ ውጤት ምንድን ነው? በጉዳዩ የሰበር ችሎት አቋምስ ምን ይመስላል?
በኢትዮጵያ አሠሪና ሠራተኛ ሕግ እንዲሁም በሰበር ችሎት የተሰጡ አስገዳጅ ውሳኔዎች ለቀጣሪዎች የተለጠጠ ሠራተኛን የማስተዳደር ሥልጣን (Managerial prerogative) ይሰጣሉ፡፡ በመሆኑም አንዳንድ አሠሪዎች የሥራ ቦታ ዝውውርን እንደሁነኛ ሠራተኛን የመቅጫ መንገድ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡ አሠሪ የዓይንህ ቀለም አላማረኝም በማለት ሠራተኛውን ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ሲያዘዋውር ሠራተኛው ቅሬታ ቢኖረው እንኳን ወደተዘዋወረበት ቦታ ሔዶ ሥራ ከጀመረ በኋላ ክስ ማቅረብ ከመቻሉ በቀር ባለበት ቦታ ቅሬታውንም ይሁን ክሱን ማቅረብ አይችልም፡፡ የሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 37778፣ 38189 እና በሌሎች መዝገቦች በሰጠው ውሳኔ አንድ ሠራተኛ የዝውውርን ትእዛዝ ባለመቀበል ለአምስት ተከታታይ ቀናት አዲስ ወደተመደበበት የሥራ ቦታ ላይ ሪፖርት ካላደረገ እና ሥራውን ካልጀመረ በአሠሪና ሠራተኛ ሕጉ አንቀጽ 27 መሠረት ለሥራ ስንብት ምክንያት እንደሚሆን ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
የሰበር ችሎት በመ/ቁ 37778 (ቅጽ 8 ኅዳር 4 ቀን 2001) በአሠሪ በተደረገ የሥራ ዝውውር ቅሬታ አድሮብኛል በሚል ምክንያት ከሥራ መቅረት የሕግ ድጋፍ እንደሌለው ሲገልጽ በሰ/መ/ቁ 41623 (ቅጽ 8 መጋቢት 8 ቀን 2001) ላይ ደግሞ በአሠሪው ወደሌላ ቦታ ተዘዋውሮ እንዲሠራ የተደረገ ሠራተኛ ዝውውሩን በወቅቱ ሳይቃወም የተዘዋወረበት የሥራ ገበታ ላይ ለ 5 ተከታታይ ቀናት የቀረ እንደሆነ የሥራ ውሉን ለማቋረጥ በቂ ምክንያት እንደሆነ ያትታል፡፡
በሌላ በኩል ሠራተኛው ወደ ተዘዋወረበት ቦታ ተገኝቶ ሥራ መጀመር ሲገባው ይህን አለማድረጉ አሠሪው እርምጃ ከመውሰዱ በፊት የነገሩን ነባራዊ ሁኔታ ማየት ያለበት ስለመሆኑ ሰበር ችሎት በመ/ቁ 125004 ቅጽ 20 ላይ ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡ ችሎቱ ሠራተኛው በተዘዋወረበት ቅርንጫፍ ለመገኘት የሚፈጅበትን ጊዜ ግምት ውስጥ በማስገባት በተባለው ቀን መድረስ እንደማይችል ግምት በመውሰድ ስንብቱ ሕገወጥ ነው ብሏል፡፡
በዝውውር ምክንያት የሥራ ውል የመቋረጥ አግባብነት ጭብጥ ሆኖ በተያዘበት የሰ/መ/ቁ 238246 (አመልካች ወጋገን ባንክ አክሲዮን ማህበር እና ተጠሪ አቶ መንግሥቱ ካሣ መጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ያልታተመ) ችሎቱ በሰጠው ትንታኔ የሥራ ውሉ የተቋረጠበት አግባብ እና ሕጋዊ ውጤቱ እንደውሉ፣ የሥራው ዓይነት እና የሥራ ውሉ የተቋረጠበት ምክንያት የሚለያይ መሆኑን ያስረዳል፡፡
ስለሆነም በሥራ ውሉ የሥራ ቦታው አዲስ አበባ መሆኑ ከተገለጸ አሠሪ ከአዲስ አበባ ውጪ ወደ ሌላ ቦታ አዘዋውሮ ማሠራት አይችልም፡፡ (በአሠሪና ሠራተኛ ሕግ አንቀጽ 4/3 ማንኛውም የሥራ ውል የሥራውን ዓይነትና ቦታ መያዝ እንዳለበት ይገልጻል፡፡ ቦታው በውሉ አለመገለጹ የሚኖረው ውጤት አጠያያቂ ነው)
በሌላ በኩል በጥበቃነት የተቀጠረ አንድ ሠራተኛ ይሠራበት ከነበረው አዲስ አበባ አንስቶ ደሴ ላይ ማዘዋወር ሥራው ካለው ባህሪ አንጻር አዲስ በተመደበበት ቦታ በቀላሉ ሊተካ የሚችል በመሆኑ እና ሠራተኛውን ከማዘዋወር ይልቅ ሌላ ሠራተኛ መቅጠር የሚቀል በመሆኑ ዝውውሩ አግባብ አይሆንም፡፡
በሰ/መ/ቁ 238246 ላይ አሠሪው ሠራተኛውን አዘዋውሮ የማሠራት መብት ያለው መሆኑን ቢያስረዳም ሠራተኛው ወደተመደበበት ቦታ ለመሄድ የማይችልበትን ምክንያት በበቂ ሁኔታ ካስረዳ ስንብቱ ሕገወጥ እንደሚሆን ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም በዚህ ውሳኔ መሠረት ሠራተኛው ወደተመደበበት ቦታ መሄድ ያልቻለበትን በቂ ምክንያት በማስረጃ የማስረዳት ሸክም /burden of proof/ ያለበት ሲሆን ፍርድ ቤቱ ምክንያቱ በቂ ነው ብሎ ካመነ ዝውውሩን ሊያግድ ይችላል፡፡
በአብዛኛው የሥራ ቦታ ዝውውር የሚደረገው እንደ ጥበቃ ባሉ የሥራ ዘርፎች ሲሆን ሠራተኛውን ከሥራ ለማሰናበት እንደ legal loop hole በመሆን ሲያገለግል ይታያል፡፡ በአገራችን ያለው ዝቅተኛ የደመወዝ ምጣኔ እና በየዕለቱ የሚጨምረው ኑሮ ውድነት Stagflation የሚያስከትለው ጫና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ ወገኖች የራስ ምታት መሆኑ ቀጥሏል፡፡ ይባስ ብሎ በሥራ ቦታ ዝውውር ስም የሠራተኞቹ job security ጥያቄ ውስጥ መግባቱ አሳሳቢ ነው፡፡ አንድ ሠራተኛ ዝውውሩ ሕገወጥ ነው በማለት እየተከራከረ እያለ በተዘዋወርክበት ቦታ ሔደህ ክሰስ ማለት የሠራተኛውን ፍትሕ የማግኘት መብት በጥብቅ የሚጋፋ ነው፡፡ በመሆኑም የሰበር ችሎት በሰ/መ/ቁ 238246 የሰጠው ውሳኔ ተገቢ እና ቅጥ አጥቶ የነበረውን የአሠሪዎች የማስተዳደር ሥልጣን (Managerial prerogative) ልክ ያበጀለት ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡
#solomon Baye