አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና በአክስዮን ማኅበር መካከል ያላቸዉ መሰረታዊ አንድነት እና ልዩነት
1. አባልነት/Membership: -
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለማቋቋም የሚያስፈልጉ ሁለት/2/ ሰዎች ብቻ ሲሆኑ አክሲዮን ማኅበር ደግሞ ለመጀመር ቢያንስ አምስት/5/ አባላት ያስፈልጋሉ ፡፡
በአክሲዮን ማህበር ውስጥ በከፍተኛው የአባላት ብዛት ላይ ገደብ የለም ፡፡ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ቢበዛ 50 አባላት ብቻ ሊኖሩት ይችላል ፡፡
2. ዳይሬክተሮች/ Directors፡ -
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአንድ ወይም በብዙ ሥራ አስኪያጆች የሚተዳደር ሲሆን አክሲዮን ማኅበሩ ደግሞ አነስተኛ ቁጥራቸው ሦስት በሚሆኑ ዳይሬክተሮች የሚተዳደር ነው ፡፡
3. ፕሮስፔስተስ/ Prospectus: -
አንድ አክሲዮን ማኅበር ለአክሲዮኖቹና ለዕዳ ወረቀቶቹ ደንበኝነት እንዲመዘገብ ህዝቡን መጋበዝ ይችላሉ ፣ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ካፒታሉን ለማሳደግ ወደ ሕዝብ መሄድ አይችልም ፡፡
4. አነስተኛ ምዝገባ /Minimum subscription:-
በአክሲዮን ኩባንያ ውስጥ ሁሉም ካፒታል መፈረም አለባቸው እና ከምዝገባ በፊት የካፒታልው 25% መከፈል አለበት። ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሙሉ በሙሉ በተከፈለ ካፒታል ይመዘገባል ፡፡
5. የማህበሩ ዋና ገንዘብ / capital፡-
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ዋና ገንዘብ ከ15,000 ብር በታች መሆን አይችልም፡፡ በአክሲዮን ኩባንያ ደግሞ መነሻ ካፒታሉ ከ50,000 ብር በታች መሆን አይችልም፡፡
6. የተገደበ ሀላፊነት/Limited liability: -
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሆነ በአክስዮን ማህበር በማህበሩ ባዋጡት/ባላቸዉ ድርሻ ልክ ብቻ ሀላፊነት አላቸዉ፡፡ ማህበርተኞቹም ለማህበሩ ግዴታዎች አላፊ የሚሆኑት ባላቸዉ ድርሻ ልክ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም በተገደበው የኃላፊነት ደንብ መሠረት የኩባንያው አበዳሪዎች በድርጅቱ በራሱ ንብረት ላይ ብቻ የይገባኛል ጥያቄ ለማቅረብ የተገደቡ ሲሆን የድርጅቱ ባለአክሲዮኖች በግል በያዙት ንብረት ላይ ምንም ዓይነት የይገባኛል ጥያቄ የላቸውም ፡፡
7. የህግ ስዉነት/Legal personality፡-
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርም ሆነ አክስዮን ማህበር የራሳቸዉ የሕግ ሰዉነት ያላቸዉ ሲሆን በስማቸዉ የመክሰስ ሆነ የመከሰስ እንዲሁም ማንኛዉንም ስራ የመስራን ሰፊ መብት ተጎናፀፈዋል፡፡
8. የአክስዮኖችን ማስተላለፍን በተመለከተ/Transferable shares፡-
አክስዮን ማህበር ምንም እንኳን በማኅበሩ አንቀጾች ውስጥ የአክሲዮን ነፃ ዝውውርን መገደብ ቢቻልም (አንቀጽ. 333 (1) የአክሲዮን ኩባንያ አጠቃላይ መርሆዎች በነፃነት የሚተላለፉ በመሆናቸው በአክሲዮን ገበያ ሊሸጡ ወይም ሊገዙ ይችላሉ ፡፡ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአባላቱ መካከል በነፃነት የሚተላለፉ ሲሆን ለሌሎች ግን እንደ አክስዮን ማህበር እንደፈለጉ በነፃነት የሚተላለፍ አይደለም ምክንያቱም ሲመሰረትም ቤተሰባዊ እና ቅርርብን መሰረት ተደርጎ የሚመሰረት ማህበር በመሆኑ ነው፡፡
☞ሰናይ ጊዜ
© Yilkal
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
የአክስዮን ማህበር መመስረት የሚያስገኙ ጥቅሞች፡-
የአባላቱ ሀላፊነት የተወሰነ መሆኑ፤
የአክስዮን አባላቱ ቢሞቱም በወራሾች በቀላሉ መቀጠል ስለሚችል የማይሞት መሆኑ፤
አክስዮን ማህበር ትልቅ ካፒታል የሚጠይቅ ስለሆነ ግዙፍ ኢንተርፐራይዞች እንዲኖሩ ማድረግ መቻሉ፤
ጠንካራ የገንዘብ አቅም መኖሩ፤
ድርሻዉ በቀላሉ የሚተላለፍበት እና የአባላትም ቁጥር የሚቀያየር መሆኑ፤
ቦንድ/የብድር ሰነድ/መሸጥ የሚችል መሆኑ፤
የተለያየ የአስተዳደር አካላት ማለትም የዳይሬክቶሮች ቦርድ፤ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ እና የዉጪ ኦዲተር ያሉት መሆኑ፤
የመስፋፋት እድል መኖሩ፤
የተበተነ አደጋ መኖሩ/Diffused risk/
ከ50 በላይ አባላት ያሉት ማቋቋም ሲፈለግ፤
መዋጮ ከህዝብ መሰብሰብ መቻሉ ማለትም ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለማቋቋም የአክስዮን ሽያጭ ማስታወቂያ ለህዝብ አስነግሮ ካፒታል መሰብሰብ አይችልም ፡፡ በመሆኑም ብዙ ገንዘብ በሚጠይቁ ዘርፎች ለመሰማራት ካፒታልን ከህዝብ መሰብሰብ የሚያስችል ስለሆነ አክስዮን ማህበር ተመራጭ ያደርገዋል፡፡
ለሶስተኛ ወገኖች የበለጠ አስተማማኝ እና ተቋማዊ ቅርፅ የያዘ መሆኑ፤ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አሰራሩ ቀላል፤ በህግ የሚደረግበት ቁጥጥር የላላ፤ የአስተዳደር ስርዓቱ በአንፃራዊነት የማያስተማምን ስለሆነ 3ኛ ወገኖችን ብዙ አያስተማምንም፡፡ በተቃራኒዉ አክስዮን ማህበር አሰራሩ ዉስብስብ፤ዝርዝር የህግ ቁጥጥር ያለበት፤ አስተዳደሩ በብዙ አካላት የተደራጀ ስለሆነ ለአባላትም ሆነ ከአክስዮኑ ጋር ግኑኙነት የሚፈጥ የ3ኛ ወገኖች መብት ለማስጠበቅ አስተማማኝ ነው፡፡
አንዳንድ የስራ ዘርፎች በህግ በግልጽ በአክስዮን ማህበር ብቻ የሚሰሩ መሆናቸዉ፤ ምሳሌ ባንክ እና ኢንሹራንስ ስራ በሀላፊነቱ የጠወሰነ የግል ማህበራት የማይሰራ መሆኑ፤
ስለሆነም የአክስዮን ማህበር ከላይ ባየናቸዉ ባህሪያት ያሉት ከአባላቱ የተለየ ሀላፊነት ያለበት ራሱን የቻለ የህግ ሰዉነት ያለዉ ድርጅት መሆኑ ተመራጭ የሚያደርገዉ ቢሆንም የራሱ ሆነ ድክመቶች ያሉት ሲሆን እንደሚከተለዉ እናያለን፡፡
የአክስዮን ማህበር መመስረት ያሉት ጉዳቶች፡-
አክስዮን ማህበር ለመመስረት ዉስብስብ እና አስቸጋሪ ስነ ስርዓት መጠየቁ፤
በምስረታ ሂደት የተለያዩ ባለሙያዎች አስፈላጊ መሆናቸዉ ምሳሌ መመስረቻ ፁሁፍን እና መተዳሪያ ደንቡን ለማዘጋጀት የህግ ባለሙያ ማስፈለጉ፤ በአይነት የሚደረገዉን መዋጮ ለመወሰን የሂሳብ ሰራተኛ እና ማህንዲስ አስፈላጊ መሆኑ በምስረታ ሂደትን ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑ፤
በቀጥታ የንብረቱ ባለቤት ያለመሆን፤
የዉሳኔ መዘግየት መኖሩ ምክንያቱም በእያንዳንዱ ወሳኝ ጉዳይ ላይ የጠቅላላ አባላትን እና የተለያዩ አካላትን ዉሳኔን የሚያስፈልግ መሆኑ፤
በጥቂት እጅ የወደቀ እና የተንኮል አስተዳደር የመፈጠር እድሉ ሰፊ ነው ምክንያቱም ባላክስዮኖቹ በየሀገሩ የተበታተኑ እና የማይተዋወቁ በመሆናቸዉ በቀላሉ ለመቆጣጠር እና መብታቸዉን በተደራጀ መልኩ ለማስከበር ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌ፡- የባንክ አባሎች የማይተዋዉ ብዙ ቁጥር ያለቸዉ በመሆኑ ቦርድ እና ስራ አስኪያጆችን በየቀኑ ለመቆጣጠር ያስቸግራል፡፡
ሚስጢር ያለመጠበቅ ችግር

ሰናይ ጊዜ 👏
YilkalG.
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
የቤት ብድር የሚሰጡ ባንኮች
#አለ_ህግ
ብሄራዊ ባንክ ሞርጌጅ ባንኮች ለማቋቋም የሚያስችል ደንብ እያረቀቀ እንደሆነ ሪፖርተር አስነብቧል። መንግሥት ለልዩ ዓላማ ለሚቋቋሙ ባንኮች ራሱን የቻለ ደንብ እንዲያዘጋጅ የፋይናንስ ዘርፉ ሲወተውት የቆዩ ሲሆን፣ በቅርቡ ግን ብሄራዊ ባንክ ኮሚቴ አቋቁሞ ለሞርጌጅ ባንክ ማቋቋሚያ ልዩ ደንብ ማዘጋጀት መጀመሩን አንድ የባንኩ ከፍተኛ ኃላፊ ተናግረዋል። ሞርጌጅ ባንክ በባሕሪው የተለየ እና ለደንበኞቹ የሚሰጠው ብድር የረጅም ጊዜ በመሆኑ፣ ለመደበኛ ባንኮች ከሚውሉት መስፈርቶች ቀለል ያሉ መስፈርቶች ሊዘጋጁለት እንደሚገባ የዘርፉ ባለሙያዎች ጠቁመዋል። ከአምና ጀምሮ ጎህ ባንክ ብቻ የሞርጌጅ ብድር እየሰጠ እንደሆነ የገለጠው ዘገባው፣ ብሄራዊ ባንክ ግን ባንኩን የሚያውቀው እንደ ማንኛውም ንግድ ባንክ እንደሆነ አውስቷል።
ዋዜማ ሬዲዬ
የተሻሻለው የፌደራል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀፅ 5(2)
=======/////======= #አለ_ህግ
የክልል ጉዳይ ሆኖ በክልል ፍ/ቤቶች እየታዬ ባለ ክርክር ስልጣንን የሚቀይር ተከራካሪ ወገን ወደ ክርክሩ ቢገባ ክርክሩ የት ይቀጥላል?
~~~~
ጉዳዩ የክልል ጉዳይ ሆኖ ክርክር እየቀጠለ ባለበት ጊዜ ስልጣኑን የሚቀይር የሌላ ክልል ነዋሪ የሆነ ተከራካሪ ወገን ወይም የኢንሹራንስ ተቋም ወደ ክርክሩ ሲገባ ጉዳዩ የፌደራል ፍ/ቤቶች ስልጣን ይሆናል ወይስ አይሆንም? የክልል ፍ/ ቤቶች ስልጣናቸውን ያጣሉ ወይስ አያጡም? ጉዳዩን የያዘው ፍርድ ቤትስ መዝገቡን ስልጣን ላለው ያስተላልፍ ወይስ ይዝጋው? የሚሉት ጉዳዬች በቀድሞው አዋጅ ቁጥር 25/88 ድንጋጌዎችእና ከፍ/ስ/ስ/ህጉ ድንጋጌዎች አንፃር አከራካሪ መሆኑ ይታወቃል። የተሻሻለው አዋጅ ለዚህ ምላሽ በሚሰጥ መልኩ የተቀመጠ ነው።
~~~
በመርህ ደረጃ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልሎች የሆኑ ሰዎች ወይም በፌደራል የተመዘገበ የኢንሹራንስ ተቋም ተከራካሪ የሆኑበት የፍትሀብሄር ክርክር ጉዳይ ላይ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን ያላቸው ሲሆን በልዩ ሁኔታ ግን የክልል ጉዳይ ሆኖ በክልል ፍርድ ቤቶች በመታየት ላይ እያለ የሌላ ክልል ነዋሪ ወይም የኢንሹራንስ ተቋም በየትኛውም የክርክር ደረጃ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 40(2), 41,43, 358ና 418ንም ጨምሮ ወደ ክርክሩ ቢገባ ጉዳዩ በጀመረበት አግባብ የክልል ጉዳይ ሆኖ ከሚቀጥል ውጭ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን ነው በሚል ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት የሚተላለፍ አይሆንም።
(via voice of justice)
Live stream started
H. R. 6600 01951.pdf
924.9 KB
Share 'H. R. 6600 01951.pdf'
Live stream finished (1 hour)
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
የቼክ ክፍያ ይቁም ትዕዛዝ (Stop Payment Order) የሚሰጠው መቼ እና እንዴት ነው?

በገዙ አየለ መንግሥቱ

በዚህ ጽሑፍ የሚከተሉት ቁም ነገሮች ያገኛሉ
የቼክ ክፍያ ባንክ አልፈጽምም ሊል የሚችለው መቼ ነው
የቼክ ክፍያ ይቁም ትዕዛዝ መስጠት የሚቻልበት መንገድ
የቼክ ክፍያ ይቁም ትዕዛዝ ከብሔራዊ ባንክ መመሪያ አንጻር
የቼክ ሂሳብ እንቅስቃሴን በተመለከተ

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/1800-stop-payment-order
።።።።።።። ይግባኝ ማስፈቀጃ ====
• በህጉ የተቀመጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ

አንድ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈበት ምክንያት በቂ መሆኑን ሲረዳ ይግባኙ እንዲቅርብ ሊፈቅድ እንደሚገባ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 326/1/ ስር ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ፍ/ቤቱ የቀረበለት ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑን በአግባቡ ሊመረምረው ይገባል፡፡ በእርግጥ በቂ ምክንያት የሚባሉት ነገሮች ሕጉ ዘርዝሮ ያላስቀመጣቸው በመሆኑ ለመወሰን አስቸጋሪ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም የምክንያቱ በቂ መሆን አለመሆን በእያንዳንዱ ጉዳይ ከሚቀርቡ ፍሬ ነገሮች ጋር ተገናዝበው ሊመዘኑ ይገባል፡፡

ሰ/መ/ቁ. 38145 ቅጽ 8፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 326/1/

በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ መሠረት ለአንድ ፍርድ ቤት መዝገብ ሹም የተሰጠው ሥልጣን ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ማለፍ አለማለፉን በመመልከት ይግባኝ መዝገቡ እንዲከፈት ማድረግ ሲሆን ይግባኙ ጊዜውን ጠብቆ ያልቀረበ ከሆነ ማመልከቻውን መመለስ፣ ማመልከቻው የተመለሰበት ወገን የይግባኝ ጊዜው ያለፈበት ሕጋዊ ምክንያት ካለው ማስፈቀጃ አቤቱታውን በማቅረብ ይኸው ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድለት ራሱን የቻለ አቤቱታ አቅርቦና ይህ መዝገብ ተከፍቶ ጉዳዩ ለችሎት ቀርቦ ችሎቱ የይግባኝ ማስፈቀጃውን በመመርመር በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 መሠረት ተገቢ ነው ያለውን ትእዛዝ የሚሰጥበት ነው፡፡

የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 ድንጋጌዎች ጋር አንድ ላይ ሲነበቡ የመዝገብ ቤት ሹም ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለችሎት እንዲቀርብ የመፍቀድ ስልጣን የሌለው መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን ፋይሉ ተከፍቶ ቀርቦ ከሆነም ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ ይግባኙ የቀረበው ጊዜው ከአለፈ በኋላ ነው በማለት መዝገቡን ከመዝጋት የሚከለክለው አይደለም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 61843 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 324-326
ማሳሰቢያ አለ_ህግ #law #societies
ሁሉንም የ #አለ_ህግ አባላት የሚያሳትፍ ቀጠሮ፣ ሁሌም እሁድ እሁድ የቀጥታ (Live stream) የድምፅ ውይይት ይኖረናል።
#የህግ ጉዳይ የመወያያ እርዕስ አስቀድማችሁ እንዳትመርጡ እናሳስባለን።
ምክንያቱም፣ ከወዲሁ ተዘጋጅተው ለውይይቱ እንዲመጡና ፍሬአማ ሀሳቦችን እንድናገኝ ይረዳናል።
1. የመወያያ አጀንዳ ይምረጡ
2. ተዘጋጅተው የውይይቱ ተሳታፊ ይሁኑ
3. Share and add ማድረግን አትርሱ
#Ale_Lawsocieties
#አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties

@lawsocieties
#Embassy of Canada#

▪️Position - Common Services Officer (Contracts and Procurement)
▪️Salary - 712,866 ETB per annum
▪️Location - Addis Ababa
▪️Education - Bachelor’s degree in a related field (i.e. business administration) from a recognized university with 3 years of experience
▪️Find More Details Here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3J0kHFr

▪️Deadline - Apr 08/2022

How to Apply

Applications will only be considered when received through our portal.  Link for this job poster – https://staffing-les.international.gc.ca/en/careers/common-services-officer-contracts-and-procurement-addis-64049-en


#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
የዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በፍርድ ቤቶች
*
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በህብረተሰቡ ዘንድ የህግ ግንዛቤን ለማስጨበጥ በሁለት የተከፈለ ስራ ተሰርቷል፡፡ አንዱ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በፍርድ ቤት የሚሰጠውን የዳኝነት አገልግሎት መሰረት በማድረግ ሂደቱን እና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚያስገነዝብ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሲሆን ሁለተኛው ደግም በተማሪዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር፡፡ በተለይም የዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ የተግባር ልምምድ (internship program) እና በዳኞች ቅርብ ክትትል፣ ምክርና አቅጣጫ ጠቋሚነት የአመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት የማዳበር (Mentorship) ፐሮግራም ተቀርጾ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ የዚህ ፕሮግራም ፋይዳን የሚዳስስ አጭር ቪዲዮ እንዲህ ቀርቧል፡፡
https://m.youtube.com/watch?v=HD-jNaksHg4

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties