Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
84K subscribers
2.42K photos
92 videos
2 files
305 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደንቢዶሎ በሳምንት ሶስት በረራዎችን ዛሬ በደማቅ ስነ-ስረአት መልሶ አስጀምሯል፡፡ይህ በረራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ የሚሰጠውን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት የማስፋፋት አንዱ አካል ነው።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የሀገር ውስጥ በረራዎን በምቾት ያድርጉ።
https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-expands-its-domestic-network-with-three-weekly-passenger-services-to-dembi-dollo-ethiopia
#ኢትዮጵያአየርመንገድ
ከበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል እንኳን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር በደህና መጡ! ቀጣይ መዳረሻዎ የት ነው? በምቾት ልናደርስዎ ሁሌም ዝግጁ ነን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ማሳሰቢያ

የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 1 (በተለምዶው የሀገር ውስጥ/Domestic Terminal) የማስፋፊያ እና የማዘመን ስራው ተጠናቅቆለት ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ የሀገር ውስጥ በረራ ለማድረግ ወደ ኤርፖርት የምትመጡ ክቡራን መንገደኞቻችን በቀጥታ ወደ ተርሚናል ቁጥር 1 ብቻ እንድትገቡ በትህትና እናሳውቃለን።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ለኢ-ኮሜርስ ሸቀጦች እንዲሁም ለፖስታ እና ጥቅል መልእክቶች የሎጂስቲክስ አገልግሎትን የሚያቀላጥፈው እና አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርገው ከኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የሚበረከተው የምስራች ይፋ ሊደረግ ሰዓታት ብቻ ቀሩት፡፡

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያካርጎእናሎጂስቲክስአገልግሎት
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ክቡር አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ እና የልዑክ ቡድናቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናው መስሪያ ቤት ተገኝተው ጉብኝት አደረጉ።
ክቡር አምባሳደሩና ልዑካኖቻቸው ከአየር መንገዳችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የአየር መንገዱ ማኔጅመንት አባላት ጋር ፍሬያማ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ስለ አጠቃላይ የአየር መንገዳችን የስራ እንቅስቃሴ እና የዕድገት ጉዞ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
ክቡር አምባሳደር ማሲንጋ ከልዑካኖቻቸው ጋር በመሆን በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ዘመናዊ የሆኑትን የተለያዩ የስራ ክፍሎቻችንን ጎብኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ዘመናዊ የመንገደኞች መቆያ ስፍራዎች ባልተሟሉባቸው በቀደሙት ግዜያት መንገደቾች በዚህ መልኩ በ DC-3 ሰፋፊ ክንፎች ስር በመሆን የቀትርን ፀሐይ ያሳልፉ ነበር።
#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ