Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
84K subscribers
2.42K photos
92 videos
2 files
305 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ለኢ-ኮሜርስ ሸቀጦች እንዲሁም ለፖስታ እና ጥቅል መልእክቶች የሎጂስቲክስ አገልግሎትን የሚያቀላጥፈው እና አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርገው ከኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የሚበረከተው የምስራች ይፋ ሊደረግ ሰዓታት ብቻ ቀሩት፡፡

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያካርጎእናሎጂስቲክስአገልግሎት
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አዲሱን በአፍሪካ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን እና 55 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መዋዕለ-ንዋይ ያፈሰሰበትን ዘመናዊ የኢኮሜርስ መሰረተ ልማት በደማቅ ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡ የዚህ በልዩ ሁኔታ ለኢኮሜርስ ሸቀጦች እንዲሁም ለፖስታ እና ጥቅል መልእክቶች የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ ወደ ስራ የሚገባው መሰረተ-ልማት የአፍሪካን የኢኮሜርስ ኢንደስትሪ ዕድገት ከማፋጠኑም ባሻገር አዲስ አበባን በአፍሪካ ብሎም በዓለም የድንብር ተሻጋሪ ኢኮሜርስ ማዕከል የሚያደርግ ነው፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያካርጎእናሎጂስቲክስአገልግሎት