የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚያደርገውን የኤርባስ A350-1000 ትዕዛዝ ከኤርባስ አውሮፕላን አምራች ካምፓኒ ጋር ተፈራረመ። አየር መንገዳችን ከዚህ በፊት 22 ኤርባስ A350-900 በማዘዝ 16ቱን ተረክቦ በማብረር ላይ ሲሆን ከተቀሩት የኤርባስ A350-900 አውሮፕላን ትዕዛዞች አራቱ ወደ ኤርባስ A350-1000 እንዲቀየሩ ስምምነት ተደርጓል። ይህ ስምምነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000ን አገልግሎት ላይ የሚያውል የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር መንገድ ያደርገዋል። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ። https://bit.ly/3BiEJei
👍85👏15❤11🤩11
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪየሽን አካዳሚ ሰልጥነው ብቁ የአቪየሽን ባለሙያ ይሁኑ።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአካዳሚው ድረ ገጽ እና ፌስቡክ ገፅ ያግኙ።
http://www.ethiopianairlines.com/eaa
https://www.facebook.com/EthiopianAviation
#የኢትዮጵያአቪዬሽንአካዳሚ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአካዳሚው ድረ ገጽ እና ፌስቡክ ገፅ ያግኙ።
http://www.ethiopianairlines.com/eaa
https://www.facebook.com/EthiopianAviation
#የኢትዮጵያአቪዬሽንአካዳሚ
👍52❤14🥰3👏3
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ- ግብር አንድ መቶ ሺህ ችግኞችን ለመትከል የያዘውን እቅድ ለመተግበር የአየር መንገዳችን አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት የመጀመሪያውን ዙር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በዛሬው እለት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አካሂዷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሰል ተግባራትን በሰራተኞቹ፣ በማኔጅመንት አባላት እንዲሁም በመንገደኞቹ ስም ሲያከናውን የቆየ ሲሆን ፣ ይህ ተግባር አየር መንገዱ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ከሚወጣባቸው መንገዶች አንዱ ነው ። በቀጣይ ዙሮችም በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ተመሳሳይ የችግኝ ተከላ መርሐ- ግብሮችን በተከታታይ ያካሂዳል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አረንጓዴአሻራ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አረንጓዴአሻራ
👍55❤31🥰7🤩3
የአስደናቂ የተፈጥሮ ገጽታ ባለቤት የሆነችውን ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያን ይጎብኙ ! ትኬትዎን በድረ-ገፃችን ወይም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን ይግዙ ፤ እንዲሁም ቪዛዎትን በኦንላይን አገልግሎት ያግኙ ።
https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app
https://www.evisa.gov.et
#ውብኢትዮጵያ #ምድረቀደምት
https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app
https://www.evisa.gov.et
#ውብኢትዮጵያ #ምድረቀደምት
👍56❤32🤩5👏3