ሠበር በ7 ዳኞች የተሰጠ ውሳኔ ።።።።።።።።።**።።።።።።።።።።።።።።።።።።። https://t.me/lawsocieties ።።።።።።።።።።።**።።።።።።።።።።።።።።።።።ሠሰ/መ/ቁ. 190307 ( ያልታተመ) ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ምየአ/አ/ክትማ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት በፍርድ ቤት ክርክር በማድረግ የከተማዉ ነዋሪዎችን/የህዝብና የመንግስትን መብትና ጥቅም ለማስከበር ያለዉመብት/ስልጣን ተመሳሳይ መብትና ጥቅምን ለማስከበር ስልጣንና ኃላፊነት ባለዉ ሌላ የከተማዉ አስተዳደር አካል ክርክር ተደርጎበት ዉሳኔ ያረፈበት ጉዳይ በድጋሚ እንዲታይ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የመቃወም አቤቱታ ለማቅረብ ያስችለዋል ወይ?ሦስተኛ ወገን በክርክሩ ተሳታፊ ካልሆነ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ፍትሐዊ ዉሳኔ ለመስጠት የማይችል ዓይነት (indispensable party) ከሆነ በፍርድ ቤቱ አነሳሽነት ወይም መብት ባለዉ ሰዉ አቤቱታ አቅራቢነት፣ እንዲሁም ዉጤቱ መብቴን ሊነካ ይችላል በሚል ወገን (interested party) አቤቱታ አቅራቢነት ሦስተኛ ወገን በተጀመረ ክርክር ተሳታፊ የሚሆንበትን ሥርዓት የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ ይዘረጋል (አንቀጽ 40 እና 41 ይመለከቷል)፡፡ ዓላማዉም የጉዳዩ አመራር ፍትሐዊ እንዲሆንና በሥርዓት እንዲከናወን ለማስቻል ሲባል ነዉ ተብሎ ይታመናል፡፡ ይሁንናበተለያዩ ምክንያቶች ከላይ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት ክርክሩ በሂደት ላይ እያለ በክርክሩ ተሳታፊ ሆኖ መብቱን ማስከበር ይችል የነበረ ሰዉ ተሳታፊ ባልሆነበት መብቱን የሚነካ ዉሳኔ ሊሰጥ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ ስለሆነም በፍርድ ቤት ወይም በህግ የዳኝነት ስልጣን ባለዉ አካል በተሰጠ ዉሳኔ መብቴ ተነክቷል የሚል ሦስተኛ ወገን አቤቱታዉን በማቅረብ ዉሳኔዉን በመቃወም መብቱን ሊያስከብር የሚችልበትን ሥርዓት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 ላይ ተመልክቷል ።በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የሚቀርብ አቤቱታ የክርክሩ ተሳታፊ ባልሆነበት በተደረገ ክርክር የተሰጠ ዉሳኔ መብቱን የሚነካበት ሦስተኛ ወገን የመቃወም አቤቱታዉን አቅርቦ የክርክሩ ተሳታፊ በመሆን ተከራክሮ መብቱን ማስከበር እንዲችል ታስቦ የተዘረጋ ነዉ፡፡ በመሆኑም አቃቤ ህግ ወኪል ሆኖ ሊከራከር የሚችልበት መብትና ጥቅም ክርክር በማድረግ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ለማስከበር ስልጣን ባለዉ ጉዳዩ በሚመለከተዉ መስሪያ ቤት ክርክር ቀርቦበት ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ አቃቤ ህግ ዉሳኔዉን በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት ሊቃወም የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የለም፡፡የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 37502 (ቅጽ 8 ላይ እንደታተመዉ) የሰጠዉ የህግ ትርጉም ተለዉጧል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ዐቃቤ ህግ ቢሮ (በየደረጃዉ ያሉ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤቶችን ይጨምራል) ወኪል ሆኖ ክርክር በማቅረብ የነዋሪዉን መብትና ጥቅም እንዲያስከብር በአስፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 5 ስልጣን የተሰጠዉ ቢሆንም፣ ይህ ስልጣኑ ብቻዉን ተመሳሳይ መብትና ጥቅምን ለማስከበር ስልጣን ያለዉ የሚመለከተዉ የከተማዉ አስተዳደር አካል የክርክሩ ተሳታፊ በሆነበት ታይቶ ዉሳኔ የተሰጠበትን ጉዳይ መሠረት አድርጎ እንደገና ክርክር ለማድረግ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የመቃወም አቤቱታ እንዲያቀርብ ምክንያት አይሆንም፡፡
#ዳንኤል ፍቃዱ
#ዳንኤል ፍቃዱ
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶች
***
✒* ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ በተወሰኑ የፍትሐ ብሔር እና የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።
✒* የመጀመሪያውን ማሻሻያ ያደረገው አዋጅ ቁጥር 65/89 ነው።
✒* ይህ አዋጅ በፍ/ሕ/ቁ 2851 እና 3ዐ6ዐ ላይ ማሻሻያ አድርጎባቸዋል።
✒* ማሻሻያው የሚመለከተው ባንክ በመያዣ የተያዙ ንብረቶች አሻሻጥ ሥርዓትን ነው።
✒* ባንክ በመያዣ የያዘውን ንብረት ወደ ፍ/ቤት መምጣት ሳያስፈልገው ራሱ እንዲሸጥ።
✒* የሚያደርገ ስምምነት ሕጋዊ ውጤት እንዲኖረው ተደርጓል።
✒ * አዋጅ ቁጥር 97/9ዐ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን አዋጅ ሽሮታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለባንክ በመያዣ የተሰጠ የንግድ መደብርን በተመለከተ አዋጅ ቁጥር 98/98 በቀድሞው የንግድ ሕጉ ላይ ማሻሻያ አድርጓል።
✒* እነዚህ አዋጆች ባንክ በመያዣ የያዛቸውን ንብረቶች ራሱ የውል ጊዜው ተጠናቆ ብድር ካልተመለሰ እንዲሸጥ የሚያደርገውን ስምምነት ህጋዊነት ይቀበላሉ።
✒* አዋጆቹ ከመውጣታቸው በፊት እና በኋላ በመያዣ በተሰጡ ንብረቶች ላይ ልዩነት አድርገዋል።
✒* አዋጆቹ ከመውጣታቸው በፊት ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ ባንኩ የተዋዋዮቹ ስምምነት ሳያስፈልገው ንብረቶቹን ራሱ ለመሸጥ ህጉ መብት ሰጥቶታል።
✒* አዋጆቹ ከወጡ በኋላ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ ራሱ ለመሸጥ ግን ስምምነት ያስፈልገዋል።
✒* ባንኩ ንብረቶቹን ራሱ ለመሸጥ ስምምነት ካላደረገ የፍትሐብሔር ህጉ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ።
✒* በአሻሻጥ ሥርዓቱ ላይ ከተደረገው ለውጥ በቀር የፍትሐብሔር ህጉ ሆነ የንግድ ህጉ ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል።
✒* በአዲሱ የንግድ ሕግ በአንቀጽ 654 ሥር የተቀመጡ ድንጋጌዎች ንግድ ባንኮች በአዋጁ የተሰጠንን መብት የሚሸረሽር ነው በሚል ቅሬታ እያቀረቡበት ነው ።
📌* በዚህ አንቀጽ ሥር የተቀመጠው መሠረታዊ ድንዳጌ፣ ‹‹…የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ፣ የንብረት ዋስትና ያላቸውን፣ የቅድሚያ መብት ያላቸውን፣ እንዲሁም ባለሀብትነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የተደረጉ የሽያጭ ውሎች ያሏቸው ገንዘብ ጠያቂዎችን ጨምሮ፣ በማናቸውም ገንዘብ ጠያቂዎች ክፍያ ለማስፈጸም በተናጠል የሚደረጉ ክርክሮች፣ በሙሉ ባለ ዕዳው ወይም በመልሶ የማደራጀት ኃላፊው በተናጠል ክፍያ ለማስፈጸም የሚደረጉ ክርክሮች እንዲቋረጡላቸው ጥያቄ ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው በመጠባበቂያ ጊዜው ወቅት በሕግ ተቋርጠው ይቆያሉ፤›› የሚል ነው፡፡
📌* በዚህ የአዲሱ ህግ ድንጋጌ እና በጠቅላላው ምዕራፍ 3 ላይ የተካተቱ ድንጋጌዎች መሰረት አንድ ተበዳሪ ያለበት ብድር ተበላሽቷል ( bad debit) ሆኗል ከመባሉ አስቀድሞ ብድሩን ሊከፍል የሚችልበት አማራጭ እድል ይሰጠዋል።
📌* ይህም በብዙዎች ኢ- ህገመንግስታዊ እና ኢ-ፍትሃዊ ነው ተብሎ ከተረቀቀበት ጊዜ አንስቶ ሲተች የነበረውን አዋጅ ቁ. 90/97 እና አዋጅ ቁጥር 98/98 የማሻሻል የህግ ውጤት ስላላቸው የንግድ ህጉ አካሄድ ይበል እሚባል ነው ።
💼#ዳንኤል ፍቃዱ (ጠበቃና የህግ አማካሪ)
https://t.me/lawsocieties

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የተከሰተው በአንድም በሌላም በተለያየ መንገድ ተፅዕኖ የፈጠሩ ኢትዮጵያውያን የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ሕግ እውቀት ተደራሽነት አሳሳቢ መሆኑን በግልጽ ያሳዬ ነው።
ሕግ እና ስርዓት አክብሮ መስራት ለእራስ ነው።
ማንኛውም ሰው ያለ ፈቃዱ መቅረጽ አይቻልም፣ በተለይም የአንድን ተቋም አሰራር እና ደንብ አክብሮ አገልግሎት ማግኘት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።
ሕግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!
ስለሆነም የሰሞኑ #የጆን #ዳንኤል ጉዳይ ከሕግ እና ከተከበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሰራር እና ስርዓት ያፈነገጠ ስሜታዊነት የበዛበት ከንቱ ጩኸትና መብትና ግዴታችንን የት እና እንዴት እንዲሁም መቼ እንጠቀማለን፣ እንጠይቃለን የሚሉትን ጥያቄዎች ያልመለሰ ሆኖ አግኝተነዋል።
በጊዜው የነበረው የአየር ሁኔታ ለመብረር አመች አይደለም ተብሎ በባለሙያዎች በረራውን ሲሰረዝ ለግለሰቡም/#ጆን_ዳንኤል ደህንነት አየር መንገዱ የስራ ግዴታ እና ሀላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል።
AleHig አለሕግ ከዛሬ ጀምሮ ለማንኛውም ለሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና ተጠቃሚዎች ነፃ አማራጭ የሕግ እውቀት እንሰጣለን።
መብትና ግዴታችንን የት እና እንዴት እንዲሁም መቼ እንጠይቃለን፣ እንጠይቃለን ከሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም አንፃር።
#አለሕግ
ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍ/ሕ/ቁ 2035(2)
ለመሰረታዊ የሕግ እውቀት በቴሌግራም
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/lawsocieties
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE
Legal Information🔵
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/
#Share 👈👈👈👈