አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ውርስ አጣሪ
#ነገረ #ፈጅ
@NegereFej
==================
• በሟች ንብረት ላይ መብት አለን የሚሉትን ወገኖችን ወይም ወራሾችን የመወሰን፣ የሟች ኑዛዜ መኖር አለመኖሩን የማረጋገጥና በኑዛዜው ተጠቃሚዎችን የመለየት፣ ውርሱን የማስተዳደር የውርሱን ተከፋይ ገንዘብ የመሰብሰብና እዳዎችን የመክፈል፣ የሟች ንብረት ማጣራትና ማፈላለግ እንዲሁም የኑዛዜ ስጦታዎችን የመክፈል ሥልጣን ያለውና እነዚህ ተግባራት እንዲያከናውን በወራሾች ወይም በፍርድ ቤት የሚሾም አጣሪ
ሰ/መ/ቁ. 45905 ቅጽ 11፣ ፍ/ህ/ቁ. 944፣ 946፣ 956፣ 960
የአጣሪው ስልጣን ወሰን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 956 እንደተደነገገው የአጣሪው ሥራ ሟቹ አንድ ኑዛዜ ትቶ እንደሆነ መፈለግና በመጨረሻ ውርሱ የሚደርሳቸው ሰዎች እነማን እንደሆኑ ማረጋገጥ፣ የውርሱን ሃብት ማስተዳደር፣ መክፈያቸው የደረሰውን የውርስ እዳዎች መክፈል እና ሟቹ በኑዛዜ ያደረጋቸውን ስጦታዎች መክፈልና የኑዛዜውን ቃል ለመፈፀም ማንኛቸውም ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎች ማድረግ ነው፡፡ እነዚህ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት በሚያከናውንበት ጊዜ ደግሞ በኑዛዜው የውርስ ንብረት መሆናቸው ተጠቅሶ የክፍፍል ስርአትም የተቀመጠላቸውና ወራሾች በሙሉ የተስማሙባቸው ንብረቶችና መክፈያቸው የደረሰው የውርስ እዳዎች ሲኖሩ በወራሾቹ ስምምነት መሰረት ንብረቶቹን ሊያከፋፍልና እዳዎችንም ሊከፍል ይችላል፡፡
@NegereFej
በኑዛዜው ላይ በተጠቀሱትና ባልተጠቀሱት ንብረቶች የውርስ ሃብት መሆን ያለመሆን ላይ ወራሾቹ ያልተስማሙና ክርክር ያነሱ ከሆነ ግን የአጣሪው ሥራና ሐላፊነት ወራሾች የተስማሙባቸውን ንብረቶች የውርስ ሃብት መሆናቸው መመዝገብ፣ ወራሾች ያልተስማሙባቸው ንብረቶችና እዳዎች ካሉ ደግሞ ማስረጃ በመሰማት ማስረጃው ምን እንደሚያስረዳ ሪፖርቱ ላይ በማስፈር እንዲያጣራ ላዘዘው ፍ/ቤት ማቅረብ እንጂ ንብረት አጣሪው ይህ ንብረት የውርስ ሐብት አይደለም የሚሉ ወራሾች ቢኖሩ ማስረጃ በመስማት የውርስ ሃብት መሆኑን ስለተገነዘብኩኝ ንብረቱ የውርስ ሃብት ነው በማለት ወስኛለሁ ወይም ደግሞ ማስረጃውን እንደተመለከትኩት ንብረቱ የውርስ ሐብት ያለመሆኑን ስላረጋገጥኩኝ የውርስ ሐብት አይደለም በማለት ወስኛለሁ ለማለት የሚያስችለው ሥልጣን የለውም፡፡
@NegereFej

ሰ/መ/ቁ. 23322 ቅጽ 7፣ ፍ/ህ/ቁ. 956
የዳኝነት ስልጣን የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶች የወራሽነት የምስክር ወረቀት ከመስጠት በስተቀር ውርስ እንዱጣራ አጣሪ የመሾም የስረ ነገር ሥልጣን የላቸውም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 52530 ቅጽ 11፣ ሰ/መ/ቁ. 35657 ቅጽ 9፣ የተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 41/ለ/ሸ/፣ አዋጅ ቁጥር 408/96
https://t.me/NegereFej
@NegereFej
@NegereFej
የኢትዮጵያ ሚዲያዎችን አራተኛ መንግሥት የማይሆኑበት ምክንያት በጥቂቱ ለመዳሰስ እንሞክራለን ።
#ከመሪው ጋር የመጣበቅ እንጂ ራሳቸውን ችለው ለመቆም ፍላጎት የሚያሳዩ አይደለም ።ለመሆንም ተነሳሽነቱ የላቸውም ።
#ደላላ ወይም ጥቅሙ ላይ የሚያተኩር ነጋዴ ናቸው ።
#ቀን ቀበሌ ሰርተው ማታ ዜና አንባቢ ናቸው።
#አንዷን ኢትዮጵያ አራት ኢትዮጵያ ለማድረግ የሚሰሩ ናቸው ።
#ወቅታዊ /አሳሳቢ የመወያያ አጀንዳ ከአድማጭ/ተመልካች ጋር በቀጥታ ውይይት ሲያደርጉ ወሳኝ ሃሳብ ሲነሳ ፤አድማጫችን አጠገብዎ ሬዲዮ አለ፣ኔትወርክ ይቆራረጣል መደማመጥ አልቻልንም መልሰው ይደውሉልን ብለው ከአየር ያስወጣሉ።
#ሚዲያው ላይ በርካታ ሳሙኤል ዘሚካኤሎች አሉ።
#አንድ የቲቪ/የሬዲዮ ፕሮግራሞች ሳይጨመሩ ተቀንሰው 40 ጊዜ የሚቀባበሉት ሆኗል ።
#ጥያቄ ጠይቀን ሽልማት እንሸልማለን/ሽልማት ሸልመናል የሚሉት ውሸት እማ አሁን አሁንማ ሕዝቡ ባኖባቸዋል።
#ሚዲያው ላይ ያሉት ጥቂት ለሙያው መሥዋዕት ነት የሚከፍሉ ቢኖሩም አብዛኞቹ እንኳን ለጋዜጠኝነት ለእድር ጥሩምባ ነፊ አይመጥኑም
#ሚዲያው ተቀበል ሲባል የሚቀበል አዝማሪ ነው።ቀሀስ፣ደርግ፣ወያኔ፣ብልፅግና
#በተለይ የግል ሚዲያ የሚባሉት ሚዲያ ላይ ያሉት የጋዜጠኝነት ሙያ እውቀት የሌላቸው በዘመድ አዝማድ የተሞላ እና በተለይ ሴቶቹ በhost አድራጊ ስም ባ* ጭ* ቂ* ለማሳየት የተሰየሙ ይመስላሉ።ሲቀጠሩም የተቀጠሩት በዚህ ሁኔታ ነው።የተወሰኑትን የጋዜጠኝነት ኮርስ ውሰዱ ብለን መክረናቸው ነበር።አሁን ላይ ተሳዳቢ ናቸው።ስልካቸው ላይ ስንደውል አያነሱም።የት እንደሚደርሱ እናያለን ።መጨረሻቸውን ያሳየን
የቀረው ይቆየን
Ethio Journalist
https://t.me/NegereFej
Negere Feg
#ነገረ #ፈጅ
የሞባይል ሚስጥራዊ አገልግሎቶች
========================
1ኛ. ሞባይሉ ዉስጥ ያለዉን ስልክ ቁጥር ለማግኘት፡-*111#
2ኛ. የሞባይል የተሰራበት ዘመንና ባትሪን ለማወቅ፡-*#*#4636#*#*
3ኛ. የሞባይል ሚስጥረ ቁጥር/IMEI/ serial No፡-*#06#
4ኛ. የሞባይሉ ዋና መስገብ ሰርቨስ ለማገኝት፡-*#0*#
5ኛ.የሞባይል ኮሜር መረጃ ለመግኘት፡-*#*#34971539#*#*

6ኛ. ሞባይሉ ላይ ሙል ፋይል ለማግኛት፡-*#*#273282*255*663282*#*#*
7ኛ. የሞባይሉ ዋይለስ LAN/ ለማየት፡-*#*#232339#*#*
8ኛ. ሞባይልን አገልግሎት ለማስጀመር፡-*#*#197
328640#*#*
9ኛ. የሞባይልን ግልጽ ማብራት ለማየት፡-*#*#0842#*#*
10ኛ. የሞባይልን የእስክር መያዥ ለማየት፡-*#*#2664#*#*

11ኛ.የሞባይልኑ ቫይቭረሽን ለማየት፡-*#*#0842#*#*
12ኛ.የሞባይሉን ኤፍት ሶፍትወሩን ለማየት፡-*#*#1111#*#*
13ኛ. የሞባይሉን ሶፍትወር እና ሃርድወር መረጃ ለማየት፡-*#125080*369#
14ኛ. የሞባይሉን ኮንፍግረሽንና ዳያጎሽትክ ለማየት፡-*#9090#
15ኛ. የሞባይሉን ሴታፕና ድሞድ(Dump Modef) ለማያት፡-*#9900#

16ኛ. የሞባይሉን ሜኑ(HSDPA/HSUPA:- *#301279#
17ኛ. የሞባይሎን ዩስፕ(USB) ለማየት፡-*#872564#
18ኛ. የሞባይሎን ጽፈት ለማየት፡- *#7465625#
19ኛ. የሞባይሉን ዳታ መረጃ ወደ መጀመሪያ ምሪት ለመሜልስ፡- *#*#7780#*#*
20ኛ. የሞባይሉን ወደ ፈብርካ ምርት ለመሜልስ፡-*2767*3855#
21ኛ. የሞባይሎን Motorola droids ለማግኘት፡-##776426

ምንጭ ፣ ምርጥ መጣጥፎች
#Share #Share
https://t.me/NegereFej
Negere Fej
#ነገረ #ፈጅ
 ሰብአዊ መብትን የሚያከብር መሆኑ፡- አሳልፎ የመስጠት ጥያቄ የቀረበለት አገር የቀረበለትን ጥያቄ በመቀበል ወይም በመከልከል ለሚሰጠው ውሳኔ የሚያገናዝባቸው ልዩ ልዩ መነሻዎች እንደሚኖሩ የሚጠበቅ ሲሆን በተለይ ተላልፎ የሚሰጠው ሰው የሰብአዊ መብት ጥሰት በተለይም ተላልፎ ከተሰጠ በኋላ ለአካላዊ ድብደባና ወ.ዘ.ተ ቅጣቶች የማይጋለጥ መሆኑን፣ በፍርድ ሂደትም ቢሆን ሊጠበቁለት የሚገቡ መሰረታዊ የሂደት መብቶች የሚጠበቁለት መሆኑን ማረጋገጥ የሚጠበቅበት ይሆናል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ተፈላጊው ሰው የተፈለገበት መነሻ ዘሩን፣ ሀይማኖቱን፣ ዜግነቱን፣ ብሔሩን፣ የፖለቲካ አስተያየቱን ወይም ማሕበረሰባዊ መደቡን መሰረት ያደረገ ከሆነ ጥያቄው ውድቅ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡ ስለሆነም የትብብር ጥያቄ በእነዚህ ላይ ተመስርቶ ያልቀረበ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡
 የተጠያቂውን አገር ሕግ ያገናዘበ መሆን፡- አሳልፎ የመስጠት ጉዳይ በዋናነት የሚወሰነው ትብብር በተጠየቀው አገር ሕግ እና ለጉዳዩ ተፈጻሚነት ባላቸው ስምምነቶች መሰረት ነው፡፡ በተለይ ግን አንዳንዶቹ ጉዳዮች ብዙውን ጊዜ የሚወሰኑት ትብብር በተጠየቀው አገር ሕግ መሰረት በመሆኑ የተጠያቂው አገር ሕግ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚደነግገውን ማወቅ ለውጤታማ ተላልፎ የመሰጠት ሂደት በጣም አስፈላጊና መሰረታዊ ነው፡፡ ይልቁንም ትብብር ጠያቂው አገርና ትብብር በተጠየቀው አገር የሚከተሉት የሕግ ሥርዓት (Legal System) የተለያየ ከሆነ የሕግ አሰራራቸው ይበልጥ የመራራቅ ዝንባሌ የሚኖረው በመሆኑ ከዚህ አንጻር የአገሩን ሕግ መገንዘብ አስፈላጊነቱ ከፍተኛ ነው፡፡ በተጠያቂው አገር ሕግ ውስጥ መገናዘብ ከሚገባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ከአሳልፎ መስጠት ጉዳይ አንጻር መገናዘባቸው ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው የሚከተሉት ናቸው፡-
• አሳልፎ የመስጠት ጥያቄ ሊከለከል የሚችልባቸው መነሻዎችን ማወቅ፤
• ተፈላጊው ሰው ተላልፎ እስኪሰጥ ድረስ በእስር ሊቆይ ስለሚችልበት ሁኔታ ወይም እንዳይጠፋ ሆኖ ስለሚቆይበት ሁኔታ ማወቅ፤
• አሳልፎ የመስጠት ጥያቄው ከሚቀርብበት ጊዜ ጀምሮ ተላልፎ እንዲሰጥ በመፍቀድ ወይም በመከልከል ውሳኔ እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ ያለው ቆይታ ወይም ጊዜ ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ፤
ለውጤታማ የአሳልፎ መስጠት ጥያቄና ሂደት አስፈላጊና መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡

 የገደብ መርሕን (rule of specialty) ማክበር፡- የገደብ መርሕ የሚባለው የተፈለገው ሰው በተላልፎ ይሰጠኝ ጥያቄ በግልጽ ተጠቅሶ ከተመለከተው የወንጀል ጉዳይ ውጭ በሌላ ወንጀል በትብብር ጠያቂ አገር እንዳይጠየቅና እንዳይከሰሰ እንዲሁም ያለ አሳልፋ ሰጭዋ አገር ፍቃድ ለሌላ ሦሥተኛ አገር ተላልፎ እንዳይሰጥ የሚከለከል መርሕ ሲሆን ለዚህም ትብብር ጠያቂው አገር በምታቀርበው የአሳልፎ ይሰጠኝ ጥያቄ ውስጥ ይህን መርሕ እንደምታከብር ማረጋገጫ መስጠት ይኖርባታል፡፡ ከዚህ ባሻገር የአሳልፎ ይሰጠኝ ጥያቄው በውስጡ ከሚይዘው የተላልፎ ይሰጠኙን የተመለከተ ዝርዝር ባሻገር እንደአስፈላጊነቱ መሟላት ያለባቸውን የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ወይም ፍርድ ወ.ዘ.ተ. ሰነዶች፣ ከጥያቄው ጋር አብሮ ማቅረብ ይገባል፡፡

አሳልፎ መስጠትን በተመለከተ ከላይ የተነሱት ጉዳዮች እንደተጠበቁ ሆነው በዚህ ሂደት ውስጥ በተለይ ከፍተኛ ሚና ያላቸው አካላት እንደአገሩ ሁኔታ ልዩነት ቢኖርም ማዕከላዊ ባለስልጣን ሆኖ የሚሰራ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወይም ፍትሕ ሚኒስቴር፣ የፍርድ ቤቶች፣ ፖሊስና ማረሚያ ቤቶች ሚና ተጠቃሽ ነው፡፡ አሳልፎ የመስጠት ጉዳይን በተመለከተ የመወሰን ስልጣን እንደአገሩ ሁኔታ በአስፈጻሚው አካል ወይም በፍርድ ቤት ሊወሰን የሚችል ሲሆን አገራችንን በተመለከተ የአሳልፎ መስጠት ጉዳዮችን ጨምሮ በወንጀል ጉዳዮች ዓለም ዓቀፍ ትብብርን የማድረግ ስልጣን በአዋጅ ቁጥር 943/2008 መሰረት ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተሰጠ ነው፡፡ ሆኖም ጉዳዮቹን ከመወሰን አንጻር ተፈጻሚነት ያለው ሕግ የተሟላና በበቂ ሁኔታ ግልጽ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ ነው፤ ለዚህም ወደፊት እንደሚጸድቅ የሚጠበቀው የወንጀል ስነ ስርአትና የማስረጃ ሕግ በረቂቁ የያዘው ጉዳይ ወሳኝነት የሚኖረው ይሆናል፡፡

በአገራችን ሁኔታ የአሳልፎ መስጠት ጥያቄ ሊቀርብ የሚገባው በአዋጁ መሰረት ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሲሆን አገራችን ለሌሎች አገራት የምታቀርበው የአሳልፎ መስጠት ጥያቄ የሚቀርበውም በዚሁ አካል አማካኝነት ነው፡፡ ይሁን እንጂ የአሳልፎ መስጠት ትብብር ስኬታማ እንዲሆን የሌሎች ባለድርሻ አካላት ማለትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢሚግሬሽን፣ ፍርድ ቤቶች፣ የብሔራዊ ኢንተርፖል፣ የፖሊስና ማረሚያ ቤት ተቋማት ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡
የኢፌዲሪ ጠቅላ አቃቤ ህግ
https://t.me/NegereFej
Negere Feg
#ነገረ #ፈጅ