አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ቤት ወይም ህንጻ በማከራየት የሚገኝ ገቢ


ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢን በተመለከተ ቤት ወይም ህንጻ በማከራየት የሚገኝ ጠቅላላ ገቢ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-

1. የኪራይ ዋጋ ጭማሪን ወይም ተመሳሳይ ክፍያዎችን ጨምሮ በኪራይ ወሉ መሠረት ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ የሚያገኘው ማናቸውም የገንዘብ መጠን፣
2. በኪራይ ውሉ መሠረት ተከራይ አከራዩን በመወከል በግብር ዓመቱ ለሌሎች የሚከፍላቸው ክፍያዎች፣
3. በቤቱ ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ማስተካከያ ይሆን ዘንድ ግብር ከፋዩ የያዘውና በግብር ዓመቱ ያልተጠቀመበት ለግብር ከፋዩ ገቢ የተደረገው ማናቸውም ቦንድ፣ ዋስትና ወይም ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን፣
4. ለግብር ከፋዩ ከሚከፈለው ኪራይ በተጨማሪ በኪራይ ውል መሠረት ተከራይ ራሱ ለቤቱ እድሳት ወይም ማሻሻያ የሚያወጣው ገንዘብ፣
5. ግብር ከፋዩ ቤቱን ያከራየው ከዕቃዎች ጋር በሚሆንበት ጊዜ ያገኘው ጠቅላላ ገቢ ከዕቃዎቹ የተገኘውን የኪራይ ገቢም ያጠቃልላል፡፡
#አለሕግ #Alehig
Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴
#አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍11👌1
ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች መድረክ የጋራ የአቋም መግለጫ

1. በኤፌዲሪ ሕገ-መንግስት መሠረት የዳኝነት ስልጣን በፌዴራልና በክልል ደረጃ ለሚገኙ ፍርድቤቶች የተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሠረት በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ ነፃና ገለልተኛ ሆነው በህገ- መንግስት የተቋቋሙ ፍርድ ቤቶች የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ ፍትህ እንዲሰፍን እና ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ የማይተካ ሚና አላቸው፡፡ እነዚህን ሕገ-መንግስታዊ ኃላፊነታቸውን በውጤታማነት መወጣት እንዲችሉ ቅንጅታዊና ወጥ አሰራርን መዘርጋት እንደሚያስፈልግ ይታመናል፡፡

2. በዚህ መሠረት በአዋጅ 1231/2013 ሀገር አቅፍ የህግ ተርጓሚዎች መድረክ በህግ እውቅና አግኝቶ የተቋቋመ ሲሆን ይህም በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ፍርድ ቤቶች የተሰጣቸውን የዳኝነት ስልጣንና ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ለዜጎች አለኝታ የሆነ እና ተአማኒነትን ያተረፈ የዳኝነት አካል ለመገንባት ይረዳቸዋል፡፡

3. እኛም ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች መድረክ አባላት በዳኝነት የለውጥ ፍኖተ ካርታ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ዙሪያ መጋቢት 27/2016 ዓ.ም ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡
ይቀጥላል ከላይ የተያያዘውን ያንብቡት ......... 👆👆👆👆👆

#አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍53
የጋብቻ ምዝገባ-ግለሰባዊ ጥቅሞች

ጋብቻ ለመከሰቱ ህጋዊ ማስረጃ በመሆን

ጋብቻዉ ህጋዊ መሆኑን ለማረጋገጥ፣

የተጋቢዎቹን ዝምድና እና ግንኙነት ለማረጋገጥ፣

የጋብቻ ውጤት ለሆኑት ህፃናት በቤተሰብነት የመጠበቅ ህጋዊ መብትን ለማረጋገጥ፣

ህጋዊ ወራሽነትን ለማረጋገጥ፣

ለቤተሰብ ድጎማ ለመንግስት ጥያቄ ለማቅረብ፣

ከተጋቢዎች አንዳቸው ቢሞቱ ቋሚው የኢንሹራንስ ጥያቄን ለማቅረብ፣

ጋብቻ በሚፈርስበት ጊዜ የልጆችን አስተዳደግ ለመወሰን፣

ወደ ውጪ ሃገር ለመጓጓዝ ፓስፖርት የማግኘት ፈቃድን ለማቅረብ፣

የልጆችን ህጋዊነት ለማረጋገጥ፣

የራስን ልጆች ህጋዊነት ለመመስረት እንዲሁም ከሌላ የተወለዱትን ለማስመዝገብ፣

የዜግነት ቅያሬን ለመጠየቅ፣

ጋብቻዉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ቦታ በማሳወቅ ህጋዊ መረጃ በመሆን፣

Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!

በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/alehig

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.com
👍11