በየመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016
የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች
👇👇👇👇👇
ንብረት ማፍራት እና መጠቀም አለም አቀፍ እውቅና ካላቸው ሰብዓዊ መብቶች አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያም የንብረት መብት ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት ጀምሮ በተለያዩ ፖሊሲዎች እና ህጎች ውስጥ ተካቶ ይገኛል። በህገ መንግስቱ አንቀፅ 40/1 ስር እንደተደነገገው ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የግል ንብረቱ ባለቤት መሆኑ/መሆኗ ይከበርለታል/ይከበርላታል። እንዲሁም በንዕስ አንቀፅ 7 ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ በመሬት ላይ ለሚገነባው ቋሚ ንብረት ወይም ለሚያደርገው ቋሚ መሻሻል ሙሉ መብት አለው። ቋሚ ንብረት ከሚባሉት ውስጥ ቤት አንዱ ነው። የቤት ባለቤት የሆነ ሰው ቤቱን ሊጠቀምበት ከሚችልባቸው ሁኔታዎች ውስጥ በኪራይ ለሌላ ሰው በማስተላለፍ የቤት ኪራይ ክፍያ በመግኘት ነው። ቤቱን የሚያከራይ ሰው ለራሱ ከኪራዩ መጠቀሙ እንዳለ ሆኖ ቤቱን በማከራየቱ ሌላ ሰው እንዲጠቀምበት የሚያደርግ ስለሆነ የቤት ኪራይ ጥቅሙ ለሁለቱም ወገን ማለት ለአከራይም ለተከራይም ይሆናል። የቤት ባለቤት የሆነ ሰው ቤቱን ሊያከራይ ከሚችልባቸው አገልግሎቶች ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት ማከራየት ይገኝበታል። በአከራይ እና በተከራይ መካከል የሚኖረው ግንኙነት በህግ የተደገፈ ሲሆን የሁለቱን ጥቅም የሚያስጠብቅ ይሆናል። በመሆኑም የመኖሪያ ቤት ኪራይን የሚቆጣጠር እና የሚያስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 ታውጆ በስራ ላይ እንዲውል ሆኗል።
በመሆኑም በዚህ አጭር የንቃተ ህግ ትምህርታዊ ፅሁፍ ስለ አዋጁ አስፈላጊነት እና የተፈፃሚነት ወሰን፣ ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እና ዋጋ፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ዘመን፣ ለአከራይ ስለሚሰጥ ማበረታቻ፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚታደስበት ሁኔታ፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ እና ሌሎች ጉዳዮች በወፍ በረር ይዳሰሳሉ።
• የቤት ኪራይ ውል ምንነት
በአዋጁ አንቀፅ 2(1) ስር እንደተደነገገው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ማለት ለመኖሪያነት የሚያገለግል አንድ ወይም ከአንድ በላይ ክፍሎችን የያዘ ቤትን ተከራይቶ በመጠቀም ለሚያገኘው አገልግሎት ለአከራይ ክፍያ እየፈፀመ የሚኖርበት የውል ግንኙነት ነው። ይህን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እና ዋጋ የሚቆጣጠር አካል በክልል እንደሚሰየም አዋጁ ያስቀምጣል።
• የአዋጁ አስፈላጊነት
በሀገራችን አሁን ባለው ሁኔታ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ እና በዜጎች ኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት አንገብጋቢ እና መሰረታዊ የመብት ጉዳይ እንደመሆኑ መንግስት የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሟላት እያደረገ ካለው ጥረት ጎን ለጎን እየናረ ያለውን የቤት ኪራይ ዋጋ የማህበረሰቡን አቅም ያገናዘበ እና ተመጣጣኝ እንዲሆን በከተሞች ያለውን የመኖሪያ ቤት ንረት በአግባቡ መቆጣጠርና ማስተዳደር በማስፈለጉ አዋጁን ማውጣት አስፈላጊ ሆኗል። በተጨማሪም የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር ግልፅነት፣ ተጠያቂነት ያለው እና የአከራዮችን እና ተከራዮችን ጥቅም እና መሰረታዊ መብቶች ሚዛን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊ በመሆኑ አዋጁ ወጥቷል።
• የአዋጁ የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ አዋጅ ተፈፃሚ የሚሆነው ተጠሪነታቸው ለክልል በሆኑ ከተሞች፣ በአዲስ አበባ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ላይ በሚፈፀም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ ሲሆን ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አዋጁ በሌሎች ከተሞች ላይ ተፈፃሚ ሊሆን ስለሚችልበት ሁኔታ ክልሎች ነባራዊ ሁኔታውን እያዩ እንደሚወስኑ አዋጁ ያስቀምጣል። በተጨማሪም አዋጁ ተፈፃሚ ከሚሆንበት ሁኔታ ውጪ ተፈፃሚ የማይሆንበት ሁኔታን የተመለከተ ሲሆን አዋጁ በሆቴል፣ ሪዞርት፣ የእንግዳ ማረፊያ እና ሌሎች በንግድ ፈቃድ መሰረት በሚከራዩ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን ተደንግጓል።
• ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እና ዋጋ
ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ውል በፅሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ እንዳለበት የአዋጁ አንቀፅ 4(1) የሚደነግግ ሲሆን የኪራይ ክፍያውም በባንክ ወይም በሌላ ህጋዊ በሆነ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ ብቻ የሚፈፀም ይሆናል። ተቆጣጣሪው አካል የማረጋገጥ እና የምዝገባ ስራውን ሲሰራ በክልሉ ሰነድን የማረጋገጥ ስልጣን ካለው አካል ጋር የሚሰራ ሲሆን ውሉ በፅሁፍ የመሆን መስፈርት፣ የማረጋገጥ እና የመመዝገብ ግዴታ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እድሳት ላይም ተፈፃሚ ይሆናል። አከራይ እና ተከራይ ውሉን በተፈራረሙ 30 ቀናት ውስጥ የማረጋገጥ እና እንዲመዘገብ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። በአዋጁ አንቀፅ 4(5) ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ያልተረጋገጠ እና ያልተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እንዳልተደረገ ይቆጠራል።
የማረጋገጥ እና የምዝገባ ግዴታን ያለመወጣት በአከራይ ወይም በተከራይ ላይ በተቆጣጣሪው አካል በሚወጣ መመሪያ የሚወሰን የገንዘብ ቅጣት የሚያስከትል ሲሆን የገንዘብ ቅጣቱ በማንኛውም ሁኔታ ባልተመዘገበው ውል ላይ ካለው የሶስት ወር ኪራይ ሊበልጥ አይችልም። በተጨማሪም አዋጁ ተቆጣጣሪው አካል የቤት ኪራይ ውል ሞዴል ማዘጋጀት እና የተቋሙ ድረ-ገፅ ጨምሮ በሌላ በማናቸውም መንገድ ለህዝቡ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ እንዳለበት ይደነግጋል።
ሌላው በአዋጁ የተካተተው ጉዳይ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ሲሆን የተመዘገበ የኪራይ ውል ላይ ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ የቤቱ የኪራይ ዋጋ እንደሆነ ተደርጎ እንደሚወሰድ ነው። ይህ እንደለ ሆኖ ተቆጣጣሪው አካል በአዋጁ መሰረት የወሰነው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ማሻሻያ መነሻ በማድረግ አከራይ የጨመረው የቤት ኪራይ ዋጋ የመኖሪያ ቤቱ ኪራይ ውል ላይ የተመለከተው የኪራይ ዋጋ አካል ተደርጎ ይወሰዳል። ውሉ በሚታደስበትም ሆነ በሚፈረምበት ወቅት በነባር ተከራይም ሆነ በአዲስ ተከራይ ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚቻለው ከላይ የተመለከተውን የቤቱ ኪራይ ዋጋ መነሻ አድርጎ በመውሰድ ነው።
በአዋጁ አንቀፅ 8(4) ስር እንደተደነገገው አከራይ ለነባር ተከራይ ወይም ለአዲስ ተከራይ በሚያከራየው የመኖሪያ ቤት ላይ ቀደሞ በነበረው ኪራይ ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪው አካል በአመት አንድ ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሬ መሰረት በማድረግ ነው። በዚሁ መሰረት የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ አንድ ለህዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ ዓመት የፀና ይሆናል።
አከራይ በአዋጁ መሰረት የቤት ኪራይ ውሉ የተመዘገበን የመኖሪያ ቤት ውል የውል ዘመኑ መጠናቀቅ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች ሳያከራየው ቆይቶ በኋላ ለኪራይ ሲያቀርበው የቤቱ የኪራይ ዋጋ የሚሆነው የቤቱ ኪራይ ሳይቋረጥ ቀጥሎ ቢሆን ኖሮ የሚኖረው የኪራይ ዋጋ ነው። አዋጁ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ወደኋላ ሁለት ዓመት በፊት የኪራይ ውሉ የተቋረጠ የመኖሪያ ቤት አዋጁ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ ለኪራይ ከቀረበ በአዋጁ መሰረት ሊጨመር የሚችለው የኪራይ ዋጋ እንደተጠበቀ ሆኖ ለመጨረሻ ጊዜ ሲከራይ በነበረው ዋጋ የሚከራይ ይሆናል።
የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የዋጋ ግመታ ሥርዓት በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ እስከሚወሰን ድረስ አዲስ የተገነባ ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ለኪራይ የቀረበ የመኖሪያ ቤት በሚከራይበት ጊዜ የቤቱ የኪራይ ዋጋ በአከራይና በተከራይ ስምምነት የሚወሰን ይሆናል።

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

Forwarded from አለሕግAleHig ️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ለልጁ ማሳደጊያ ላለመክፈል ሞቱን ያወጀው አሜሪካዊ እስርና የገንዘብ ቅጣት ይጠብቀዋል
የ39 አመቱ አሜሪካዊ ለልጁ ማሳደጊያ እንዲከፍል የተወሰነበትን ገንዘብ ከመስጠት ሞቱን ማወጅ መርጧል።
ጄሴ ኪፕ የተባለው የኬንታኪ ነዋሪ በካሊፎርኒያ ለምትኖር የቀድሞ ባለቤቱ 100 ሺህ ዶላር እንዲከፍል ተወስኖበታል፤ ለልጁ ማሳደጊያ የሚሆን።
ለቀድሞ ባለቤቴ ድንቡሎ ሳንቲም ከምሰጥ ይልቅ “ሞቼ ልገላገል” በሚልም ህልፈቱን በራሱ ያውጃል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3PUktWM

Forwarded from አለሕግ🔵AleHig
Council of Ministers Regulation No.543-2024.pdf
2.8 MB
የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አገልግሎት ለሚሰጣቸው የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ አገልግሎቶች የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያን ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሸከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አስተዳደር ስርዓትን በመዘርጋትየትራፊክ ፍሰቱን ለመቆጣጠር የሚያሽችል አዲስ ደንብ በቅርቡ ይፋ አድርጓል::
።።።።።።።።።።።።።
ደንብ ቁጥር 165 /2016 ተብሎ የተሰየመው ይህ ደንብ የተሸከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አስተዳደር ስርዓትን በመዘርጋት የትራፊክ ፍሰቱ እንዲስተካከል ና በዋናነት ደግሞ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ጠቀሜታ ያለው ነው፡፡
የዚህ ደንብ ዋና ዋና ድንጋጌዎች የተሸከርካሪ ማቆሚያ ክፍያ እንደሚያጠና እና ሲፈቅድ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ፣የተሸከርካሪ ማቆሚያ ቦታ ፍላጎትና አቅርቦት ጥናት አጥንቶ አማራጭ የመፍትሔ ሃሳቦችን እንደሚያቀርብ ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚተገብር፣ የፓርኪንግ ቦታዎች ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን እንደሚያረጋግጥና እንደሚቆጣጠር የማረጋገጥ ሃላፊነት ነው፡፡
በተጨማሪም ደንቡ የተሸከርካሪ ማቆሚያ አይነቶችን በመለየት በአይነታቸው መሰረት ለማስተዳደር እና ደረጃቸውን መሰረት በማድረግ የክፍያ አፈጻጸሙን የተሳለጠ ለማድረግ እና በተጨማሪም በግል የተሸከርካሪ ማቆሚያ ስፍራ ለሚያቀርቡ ባለሃብቶች በተቀመጠው አግባብ የሚያስተዳድሩበት እና ከመንግስት ጋር በአጋርነት የሚሰሩበት ሁኔታ ያመቻቸ ነው፡፡