አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በአ/አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች የሪፎርም ስራዎች ለህግ ባለሙያዎች፣ ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት  የተዘጋጀ መጠይቅ
  ይህ መጠይቅ የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የሪፎርም ስራዎች ቡድን ሲሆን ዓላማውም በፍ/ቤቱ እየተሰሩ ለሚገኙ የለውጥ ስራዎች የግብዐት ማሰባሰቢያነት ነው፡፡  መጠይቁንም በመረጡት የአማርኛ ወይም የእንግሊዝኛ ቋንቋዎች በመጠቀም መሙላት ይችላሉ፡፡ በመጠይቁም የሚሰጡት መረጃ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ይህ መጠይቅ የተዘጋጀውም የፍ/ቤቱ ሰራተኞች ላልሆኑ የህግ ባለሙያዎችና ተገልጋይ ማህበረሰብ ክፍሎች ብቻ ነው፡፡

ስለምላሽዎ እናመሰግናለን፡፡
👇👇👇👇👇👇

https://docs.google.com/forms/d/1qAqaRe8KKT5ggJIRE_byTEyf5ZIqnDPb5RkpTpbMoWw/edit

👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
ምክር ቤቱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ
---------------------
(ዜና ፓርላማ)፣ መጋቢት 24፣ 2016 ዓ.ም፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 19ኛ መደበኛ ስብሰባ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ በምክር ቤቱ አሰራርና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 መሰረት ለቋሚ ኪሚቴ ሳይመራ ወደ ሁለተኛ ንባብ እንዲሸጋገር የድጋፍ ሞሽን ቀርቦ የጸደቀ ነው፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ረቂቅ አዋጁን አስመልክተው ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡

መንግስት የመኖሪያ ቤት አቅርቦትንና ፍላጎት ለሟሟላት እያደረገ ካለው ጥረት በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ከተሞች የሚስተዋለውን ያልተረጋጋና ፍትሀዊ ያልሆነ የቤት ኪራይ ዋጋ የማህበረሰቡን አቅም ያገናዘበ፣ ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታን መሰረት ያደረገ እንዲሆን፣ የአከራይ እና የተከራይን መብት በፍትሀዊነት የሚያስጠብቅ ረቂቅ አዋጅ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ክብርት ጫልቱ ሳኒ ረቂቅ አዋጁን በሚመለከት ለምክር ቤቱ አባላት ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን፤ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የመንግስት ሰራተኞችና የከተማ ነዋሪዎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ስለመሆኑ ጠቁመዋል፡፡

አዋጁ የመኖሪያ ቤቶችን ብቻ የሚመለከት ሲሆን የንግድ ቤቶችን በሚመለከት በሂደት የሚታይ ስለመሆኑም ሚንስትሯ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ቀደም ሲል የነበረው አሰራር መንግስት በዘርፉ ማግኘት የነበረበትን ገቢ አለማግኘቱና ይህ አዋጅ ይህንን ችግር በመቅረፍ የከተሞችን ገቢ ማሳደግ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

ዜጎች ከሚያገኙት ገቢ ከ25 እስከ 30 በመቶ በላይ ለቤት ኪራይ ማዋል እንደማይጠበቅባቸው ወ/ሮ ጫልቱ ጠቁመው፤ አንድ ተከራይ ለሁለት ዓመት ያክል ያለምንም ጭማሪ በተከራየው ቤት ውስጥ ተረጋግቶ የመኖር መብት የሚሰጠው አዋጅ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የፍትህ ሚንስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በበኩላቸው አዋጁ የአከራዩን እና የተከራዩን መብት በማጣጣም የሚያስከብር ስለመሆኑ ጠቁመው፤ በሁለቱ መካከል አለመግባባት ካለ በተቆጣጣሪው አካል በሚደረግ አስተዳደራዊ ፍትህ የሚቀረፍ እንጂ በቀጥታ ጉዳዩ በፍድ ቤት እንደማይታይ ገልጸዋል፡፡

አዋጁ የመኖሪያ ቤት ችግር በስፋት በሚስተዋልባቸው ከተሞች ተግባራዊ የሚደረግ ስለመሆኑና ዝርዝር አፈጻጸሙ ግን ለከተማ መስተዳድሮችና ለክልሎች እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት የረቂቅ አዋጁን አስፈላጊነት እና አፈጻጸሙ ላይ በትኩረት ሊታይ ይገባል ያሉትን አስተያየት ያቀረቡ ሲሆን፤ መንግስት የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች ነው ብለዋል፡፡

በአዋጁ አፈጻጸም ላይ ክፍተት እንዳይፈጠርና የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳይኖር ሚንስቴር መስርያ ቤቱም ሆነ ጉዳዩ የሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ክትትልና ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ አባላቱ አሳስበዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ በሶስት ድምጸ ተአቅቦ አዋጅ ቁጥር 1320/2016 ሆኖ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡
HPR

👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
FB_IMG_1712081330192.jpg
81 KB
አዲሱ አዋጅ “ስለ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል” ዘመን ምን ዝርዝር ይዟል?
ዛሬ በፓርላማ በጸደቀው “የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ” ከተዘረዘሩ ድንጋጌዎች ውስጥ፤ “የመኖሪያ ቤት የኪራይ ውል ዘመንን” የሚመለከቱት የሚጠቀሱ ናቸው። “የመኖሪያ ቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም” ሲል የደነገገው አዋጁ፤ ይህ የተደረገበትን ዋነኛ ምክንያት በማብራሪያው ላይ አስፍሯል።

“የአዋጁ ዓላማ የመኖሪያ ቤት ኪራይ የተረጋጋ እንዲሆን ለማድረግ በመሆኑ፤ [ውሉ] ከሁለት ዓመት ያነሰ ቢሆን አከራዩ ውሉን ለማደስ ፍቃደኛ ላይሆን ስለሚችል፤ ተከራይ በየጊዜው በቀጣይ ስለሚከራየው ቤት በመጨነቅ የተረጋጋ ህይወት እንዳይመራ ያደርገዋል” ሲል የአዋጁ ማብራሪያ አትቷል። “ከሁለት ዓመት ያለፈ ዘመን ይኑረው ቢባል ደግሞ የአከራይን መብት እንዳይጫን፤ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የውል ዘመኑ ከሁለት ዓመት ያላነሰ ጊዜ እንዲሆን” መደረጉን የአዋጁ ማብራሪያ አስገንዝቧል።

“አዋጁ ከመውጣቱ በፊት ከሁለት ዓመት በታች የተደረጉ የቤት ኪራይ ውሎች ላይ ይህንን አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ ፍትሐዊ ስለማይሆን፤ በውላቸው ላይ ያጸደቁት ቤት ኪራይ የውል ዘመን ተቀባይነት እንዲያገኝ ተደርጓል” ሲል ማብራሪያው አክሏል። ከዚህ በተጨማሪ የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ፤ የአንድ ቤት ባለቤትነት “በውርስ፣ በሽያጭ፣ በዕዳ ወይም በሌላ ማናቸውም ህጋዊ ምክንያት” ለሌላ ወገን ከተላለፈ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ ሊቋረጥ የሚችለው “ቤቱ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ የሚቆጠር የ6 ወር ማስጠንቀቂያ ለተከራይ በመስጠት ቤቱን እንዲለቅ ማድረግ እንደሚቻል ማብራሪያው” ደንግጓል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
ዝርዝሩን ከታች ከተያያዘው ምስላዊ መረጃ ይመልከቱ
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
📌 We are hiring Junior Associate for one of our clients

📌 Zero Year of experience

📌 Bachelor Degree in Law

📌 Female candidates are highly encouraged

📌 To APPLY: Send your CV to jobs@thetalentfirm.cpm with subject line " Junior Associate"
ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ግብር የሚከፈልበት የኪራይ ገቢ የሚባለው በግብር ዓመቱ ግብር ከፋዩ ቤት በማከራየት ካገኘው ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ላይ ለግብር ከፋዩ የተፈቀደው ጠቅላላ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ የሚቀረው ገቢ ላይ ነው፡፡

የተከራይ አከራዮች

• የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ያገኘው ግብር የሚከፈልበት ገቢ ነው የሚባለው የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ከተቀበለው ጠቅላላ የኪራይ ገቢ ላይ ለዋናው አከራይ የሚከፍለው ኪራይ እንዲሁም ገቢውን ለማግኘት ያወጣቸው ሌሎች ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ የሚቀረው ገንዘብ ነው፡፡
• ተከራይ የተከራየውን ቤት መልሶ እንዲያከራይ የሚፈቅድ የቤት ባለቤት ተከራዩ ግብሩን ሳይከፍል ቢቀር ስለእርሱ ሆኖ ግብሩን የመክፈል ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡

Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴
#አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
የኢት/ ፌደራል ጠበቆች ማህበር አዘጋጅቶ የሚያሰራጨውን የስራ/አባልነት መታወቂያ የመረጃ ማደራጀት ተግባራትን አጠቃሎ ለፌደራል ጠበቆችና የህግ አማካሪዎች ማሰራጨቱን ቀጥሎአል
***

የኢት/ ፌደራል ጠበቆች
ማህበር እስከእሁን ድረስ ከ 2160(ሁለት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ) በላይ ለሚሆኑ የፌደራል ጠበቆችና የህግ አማካሪዎችን ከሁሉም ክልሎች መረጃዎቻቸውን በማሰባሰብና በማደራጀት ደረጃውን የጠበቀ መታወቂያ ማሰራጨቱ የሚታወስ ነው::

በዚህም አስቀድሞ ባሳወቀው መሰረት የመታወቂያ ህትመት በዝርዝሩ መሰረት ከፒያሳ ከፍ ብሎ አራዳ ከፍተኛ ፍ/ቤት የፍትህ አካላት ህንፃ 9ኛ ፎቅ በሚገኘው በማህበሩ ዋና መ/ቤት ቀርባችሁ እንድትወስዱ የተለጠፈ የስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው::

መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር

መጋቢት 26 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤