አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በሕግ አስከባሪ አካላት ያለአግባብ ጉዳት የደረሰበት ሰው ምን መፍትሔ አለው? /የሕግ ጉዳይ/

አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ወይም ሹም (ፖሊስን ይጨምራል) የሥራ ጥፋት ፈጽሞ በሰው ላይ ጉዳት ካደረሰ መንግሥት ካሳ የመክፈል ግዴታ አለበት።(የፍሕቁ 2126 /2/)። ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ወይም ሹም የሚፈጽመው ጥፋት ደግሞ የሥራ ጥፋት ነው ተብሎ ይገመታል።(የፍሕቁ 2127 /3/)። ስለዚህ ፖሊስ ወንጀል ለመፈጸሙ ምክንያታዊ ጥርጣሬ ሳይኖረው ሰው ቢይዝ፣ ፍርድ ቤት ሳይፈቅድለት ከ48 ሰዓት በላይ ሰው በእስር ቢያቆይ፣ ወይም በእስረኞች ላይ ድብደባ ቢፈጽም የሥራ ጥፋት ነው ማለት ነው። ለዚህ የፖሊስ ጥፋት መንግሥት ማለትም የፖሊስ ተቋም ፍትሐብሔራዊ ሀላፊነት ይኖርበታል ማለት ነው። ለተጎጂዎች ካሳ ለመክፈል ይገደዳል። ይህ በተግባር ሲሠራበት ባይታይም ሕጉ የሚለው ይህንን ነው።

በተመሳሳይ ዐቃቤ ሕግም ማስረጃ ወይም ሕግ ሳይኖር ሰው ያለአግባብ ቢከስ የሥራ ጥፋት ነው። ስለዚህ መሥሪያ ቤቱ ካሳ ለመክፈል ይገደዳል። ነገርግን ፖሊስ ካሰባሰበው ማስረጃ አንጻር ዐቃቤሕግ በበቂ ምክንያት ከከሰሰ እና ተከሳሹ ተከላክሎ ቢወጣ በፖሊስም ሆነ ዐቃቤ ሕግ በኩል የተፈጸመ ሙያዊ ጥፋት አለ ለማለት አይቻልም። በተግባር ብዙም ባይሠራበትም ሕጉ ይሄው ነው።

ሌላው ሠራተኛው ወይም ሹሙ የሥራ ሳይሆን የግል ጥፋት የፈጸመ እንደሆነ በፍሕቁ 2126 /3/ መሠረት መንግሥት ከሀላፊነት ነጻ ቢሆንም ሹሙ ወይም ሠራተኛው ግን ለግል ጥፋቱ ከመጠየቅ ከለላ የሚሰጠው ሕግ የለም። ስለዚህ አንደኛ ነገር ሁልጊዜ የተፈጸመው ጥፋት የሥራ ጥፋት ነው ተብሎ ይገመታል። ሁለተኛ ነገር ለተፈጸመው የሥራ ጥፋት መንግሥት ካሳ ይከፍላል። ሦስተኛ ጥፋቱ የሹሙ ወይም የሠራተኛው የግል ጥፋት ሆኖ ቢገኝ እንኳን በግሉ ከመጠየቅ አያመልጥም። በእርግጥ መንግሥት ካሣ የከፈለ እንደሆነ የከፈለውን ካሳ ጥፋቱን ከፈጸመው ፖሊስ ወይም ዐቃቤ ሕግ በግል የመጠየቅ መብት አለው።

አሁን ይሄ በፖሊስና ዐቃቤ ሕግ ላይ ሲተገበር አይሰተዋልም እንጂ ቢተገበር ምን ይጎድለዋል ?
በጠበቃና የሕግ አማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍81
ለፈፀሙት ግብይት ደረሰኝ ካላገኙ አይክፈሉ››
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ደረሰኝ አለመቁረጥ በወንጀል ተጠያቂ ያደርጋል

ደረሰኝ ማለት የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለበት ማንኛውም ታክስ ከፋይ ከደንበኞቹ ጋር ለሚያከናውነው ግብይትና ለሚሰበስበው ገንዘብ እውቅና የሚሰጥ ሕጋዊ ሰነድ ለደንበኞቹ ቆርጦ በመስጠት በመንግስት የተጣለበትን ግብር የማስከፈል እና የመክፈል ግዴታው የተወጣ ስለ መሆኑ የሚረጋገጥበት የማረጋገጫ ወረቀት ነው ፡፡

የሽያጭ መመዝገብያ መሣርያዎች ስለመጠቀም ለመደንገግ በሚኒስትሮች ምክርቤት የወጣ ደንብ ቁጥር 139/2007 አንቀጽ 2(3) ላይም ደረሰኝ (Receipt) ማለት የጥሬ ገንዘብ ሽያጭ ሲሆን ፣ የዱቤ ሽያጭ ኢንቮይስና ያለክፍያ የሚሰጥ እቃ ወይም የአገልግሎት ማስተላለፍያ ደረሰኝን ይጨምራል በማለት ይደነግጋል ፡፡

በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19(3) መሠረት የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለበት ማንኛውም ግብር ከፋይ ደረሰኝ እንዲሰጥ ይገደዳል ፡፡

የደረሰኙ አይነት በህግ መሠረት የሚወሰን ሆኖ ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ግብር ከፋይ ካለደረሰኝ ግብይት ካከናወነ እንደየሁኔታው በአንቀጽ 120 ወይም በአንቀጽ 131(1)(ለ) መሠረት በወንጀል ይጠየቃል ፡፡

ግብር አለመክፈል ወንጀል ነው ይህንን እኩይ ድርጊት ለመቆጣጠር እና አጥፊዎችን ለማስተማር በማሰብ የፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 120 (1) ላይ ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ያለደረሰኝ ግብይት ያከናወነ እንደሆነ ከብር 25ሺ (ሀያ አምስት ሺ ብር) እስከ ብር 50ሺ (ሀምሳ ሺ ብር) የገንዘብ መቀጮ እና ከ3-5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣ እና በአንቀፅ 131(1)(ለ) ላይ ማንኛውም ደረሰኝ የመቁረጥ ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ያለደረሰኝ ግብይት ካከናወነ ወይም አገልግሎት ከሰጠ ከ2-5 ዓመት ፅኑ እስራት እና የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ በግልፅ ደንግጓል።

ከዚህም በተጨማሪ ግብይት ሳይፈፅም ደረሰኝ የሰጠ ወይም የተቀበለ ሰው ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከ7-10 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣ ከአዋጁ ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል።

ከላይ የተቀመጡትን የህግ ድንጋጌዎች በመረዳት እና በማክበር አገልግሎት ስንፈፅም ደረሰኝ መስጠትና መቀበል እንዳለብን በማወቅና ለህግ ተገዥ በመሆን ግብርን በአግባቡ በመክፈል ለሀገራችን አድገት የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናበርክት ፡፡

‹‹ለፈፀሙት ግብይት ደረሰኝ ካላገኙ አይክፈሉ››
በጠበቃና የሕግ አማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍9😁2
👇👉 358 እና 418 👈👇⁉️
በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሠረት አቤቱታ አቅራቢ በዋናው ፍርድ ላይ ምንም ዓይነት ክርክር የሌለውና አፈጻጸም እንዲቀጥል ትዕዛዝ በተሰጠበት ንብረት ላይ መብት አለኝ የሚል ወገን መሆን አለበት፡፡
በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.358 መሠረት መብቱ የተነካው ወገን ፍርዱን ለሰጠው ፍ/ቤት መቃወሚያ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
መቃወሚያውን ማቅረብ የሚችሉትም ቀደም ሲል በተደረገው ክርክር ተካፋይ ያልነበሩት ወገኖች ናቸው፡፡

በጠበቃና የሕግ አማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍10
ሁሉን አቀፍ የአካል ጉዳተኞች አዋጅ እንዲጸድቅ የሚጠይቅ ሪፖርት
ለተ.መ.ድ ሰብአዊ መብት ምክርቤት ቀረበ!

ይህ ሪፖርት በኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ አይነስውራን ማህበር በጋራ ተዘጋጅቶ ለተ.መ.ድ ሰብአዊ መብቶች ምክርቤት የቀረበ ሲሆን፤ የማህበራቱ የጋራ ሪፖርት በየግዜው እየጨመረ  የመጣውን በአካል ጉዳተኞች ላይ የሚፈጸመውን የመብት ጥሰት በተጨባጭ ማስረጃዎች አስደግፎ በመተንተን፣ በአጥፊዎች ላይ  አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ  ተጠያቂነት እንዲሰፍን ይጠይቃል።  የጋራ ሪፖርቱ  የኢትዮጵያ መንግስት፣ በእኩልነት መብት እና ከአድልዎ በመጠበቅ መብት፤ በትምህርት፣ በጤና እና በሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች መብቶች፤ በሥራ እና በቅጥር መብት፤ እንዲሁም  ተደራሽነትን በተመለከተ የህግ ማሻሻያዎች እንዲያደርግ ይጠይቃል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት  የተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች ስምምነት ተጨማሪ ፕሮቶኮልን እንዲቀበል፤ የአፍሪካ የአካል ጉዳተኞችን ፕሮቶኮል እንዲቀበል እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የአካል ጉዳተኞች አዋጅን የአካል ጉዳተኞችን ማህበራት ጉልህ ተሳትፎ ባረጋገጠ ሁኔታ እንዲወጣ ምክረሀሳብ ያቀርባል።
በጋራ ሪፖርቱ ውስጥ የተመላከቱ ቁልፍ ምክረሀሳቦች በአራተኛው ሑሉን አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ (UPR) መድረክ በተ.መ.ድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት እንደምክረሀሳብ ሖነው በምክር ቤቱ ሀገራት እንዲነሱ ለማስቻል ኢንባሲያቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ሀገራት ሪፖርቱን ተደራሽ የማድረግ ስራ እና በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ እና ግንዛቤ እንዲያገኙ ጠንካራ  ተግባራጥ በትኩረት በመከናወን ላይ ይገኛሉ።
ከ Ethiopian center for disability and development (ECDD)
በጠበቃና የሕግ አማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍9
................👇👇👇👇👇
👉በወንጀልም ሆነ በፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች ላይ ለምስክርነት ስንጠራም እነኚህን ጉዳዮች ልብ ማለት እና ሕግ የጣለብንን ግዴታ መወጣት ይጠበቅብናል።

1.መጥሪያን መቀበል

የሚላክልን መጥሪያ ለምን ጉዳይ፣ መቼ እና የት እንደተጠራን ይገልፅልናል። ስለ ጉዳዩ እንኳን ባናውቅ የተላከልንን መጥሪያ አልቀበልም ማለት አይገባም፡፡

ፍርድ ቤቱ መጥሪያ አልቀበልም ማለታችንን ካረጋገጠ ታስረን በግድ እንድንቀርብ ትዕዛዝ ሊያስትላልፍብን ይችላል። ስለዚህ ግልፅ ያልሆነልን ወይም መጥሪያው አይመለከተኝም የምንል ከሆነ መጥሪያውን ተቀብለን በቀጠሮው ቀንና ሰዓት ቀርበን ማስረዳት ወይም ማጣራቱ ተገቢ ነው።

2.ቀጠሮ ማክበር

ማንኛውም መጥሪያ ከደረሰን በቀጠሮው ቀንና ሰዓት በፍርድ ቤቱ መገኘት አለብን። በፍርድ ቤቱ ስንጠራም በአካል መቅረብ እና መቅረባችንን ማሳወቅ አለብን። ፍርድ ቤቱ ሳያሰናብተንም ችሎቱን ለቅቀን መሄድ አንችልም፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡- 👇👇👇👇👇👇👇
https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=7390

በጠበቃና የሕግ አማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍121
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፸፪/፪ሺ፤
PROCLAMATION No.1072/2018

የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ለመደንገግ የወጣ አዋጅ
A PROCLAMATION TO PROVIDE FOR ELECTRONIC SIGNATURE


በሀገሪቱ ኤሌክትሮኒክ ንግድን እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዙ የመንግስት አገልግሎቶችን ለማበረታታት ምቹ የሕግ ማዕቀፍ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤

የኤሌክትሮኒክ መልዕክት ልውውጥን በተመለከተ ሕጋዊ እውቅና መስጠትና የተሳታፊዎችን መብትና ግዴታ በግልጽ መደንገግ በማስፈለጉ፤

በኤሌክትሮኒክ መልዕክት ልውውጥ ወቅት የተሳታፊዎችን ማንነት፣ የመልዕክቶችን ትክክለኛነት እና አለመካካድን በማረጋገጥ መተማመን AGMC የሚያስችሉ የኤሌክትሮኒክ ፊርማዎችን ሕጋዊ እውቅና መስጠት በማስፈለጉ፤

በጠበቃና የሕግ አማካሪ #ሚኪያስመላክ #አለሕግ #Attorney #MikiasMelak #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍3
ከነገ ጀምሮ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት 5 ሺህ ብር ፈጣን ደግሞ 25 ሺህ ብር እንዲሆን ተደርጓል " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ በሚደረገው የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት 5 ሺህ ብር የሚጠይቅ ሲሆን፣ ፈጣን ፓስፖርት ለማግኘት ደግሞ 25 ሺህ ብር እንዲሆን ተደርጓል ብሏል።

የተቋሙ አገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መደረጉን ተከትሎ ከነገ ከነሐሴ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ተሰምቷል።

አገልግሎት ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ በሚያደርገው ማሻሻያ ለአዲስ ፓስፖርትና ለእድሳት 5 ሺህ ብር፣ አስቸኳይ በ 2 ቀን የሚደርስ 25 ሺህ  እንዲሁም በ 5 ቀን ደግሞ 20 ሺህ ብር መሆኑ ተገልጿል።

የጠፋ ፖስፖርት ለማግኘት ተገልጋዮች 13 ሺህ መክፈል ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

ሙሉ ደንቡን ከድረ ገፃችን ማግኘት ይችላሉ።
አማርኛ🇪🇹: http://ics.gov.et/download/328/?tmstv=1722940201

በጠበቃና የሕግ አማካሪ #ሚኪያስመላክ #አለሕግ #Attorney #MikiasMelak #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍10👎5😢3
በይርጋ የማይታገዱ የፍትሃብሄር ጉዳዬች

የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚቀርብ የመፋለም ክስ

ሰ/መ/ቁ 43800 ቅጽ 10
ወራሽነት በህጉ በተቀመጠዉ ጊዜ ዉስጥ ተረጋግጦ የዉርስ ሃብት ክፍፍል ዳኝነት መጠየቅ( ሰ/መ/ቁ 38533 ቅጽ 10)
በአደራ የተሰጠ ንብረትን ከአደራ ተቀባዩ ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ

(ሰ/መ/ቁ 48048 ቅጽ 10)

ህገወጥ መመሪያን በፍርድ ቤት ለማሻር የሚቀርብ አቤቱታ

( አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 53/2/ )
ህገወጥ ዉልን አስመልክቶ የሚነሳ ክርክር

( የሰ/መ/ቁ 43226 ቅጽ 12 )

በህገወጥ መንገድ የአንድን ግለሰብ መሬት የያዘ ሰዉ እንዲለቅ በፍርድ ቤት ክስ ሲቀርብበት ይርጋን መቃወሚያ አድርጎ ማቅረብ አይችልም
( አዋጅ ቁጥር 252/09 አንቀጽ 55 ን መሰረት በማድረግ ሰ/መ/ቁ 179827 ቅጽ 24) ቀድም ሲል በቅጽ 13 በሰ/መ/ቁ 69302 እና በቅጽ 22 በሰ/መ/ቁ 140538 በ10 ዓመት ይርጋ የታገዳል የተባለዉ መሬቱ በህገወጥ መንገድ የተያዘ ከሆነ በይርጋ አይታገድም በሚል ተለዉጧል፡፡

የመንግሰትን መሬት ግለሰቦች በህገወጥ መንገድ በያዙ ጊዜ ለማስለቀቅ መንግስት የሚያቀርበዉ የመፋለም ክስ በይርጋ አይታገድም
( የሰ/መ/ቁ 93013 እና 96203 ያልታተሙ)
በይርጋ የማይታገዱ የወንጀል ጉዳዬች
የሰዉ ዘር ማጥፋት / Genocide/

ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ መዉሰድ/ summary execution/
ሰዉን አስገድዶ መሰወር/ Forced disapprearance/

ኢሰብአዊ ድብደባ /Torture / በኢፊድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 28/1/ መሰረት
ምንጭ:-
𝗠𝘂𝘀𝗮 𝗛𝗮𝘀𝗵𝗶𝗺:𝐒𝐞𝐞𝐫𝐫𝐢 𝐌𝐚𝐚𝐥 𝐉𝐞𝐝𝐡𝐚? ተገኘ
በጠበቃና የሕግ አማካሪ #ሚኪያስመላክ #አለሕግ #Attorney #MikiasMelak #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍266🔥3😁1
Forwarded from አለሕግAleHig ️
የጋብቻ ምዝገባ-ግለሰባዊ ጥቅሞች

ጋብቻ ለመከሰቱ ህጋዊ ማስረጃ በመሆን

ጋብቻዉ ህጋዊ መሆኑን ለማረጋገጥ፣

የተጋቢዎቹን ዝምድና እና ግንኙነት ለማረጋገጥ፣

የጋብቻ ውጤት ለሆኑት ህፃናት በቤተሰብነት የመጠበቅ ህጋዊ መብትን ለማረጋገጥ፣

ህጋዊ ወራሽነትን ለማረጋገጥ፣

ለቤተሰብ ድጎማ ለመንግስት ጥያቄ ለማቅረብ፣

ከተጋቢዎች አንዳቸው ቢሞቱ ቋሚው የኢንሹራንስ ጥያቄን ለማቅረብ፣

ጋብቻ በሚፈርስበት ጊዜ የልጆችን አስተዳደግ ለመወሰን፣

ወደ ውጪ ሃገር ለመጓጓዝ ፓስፖርት የማግኘት ፈቃድን ለማቅረብ፣

የልጆችን ህጋዊነት ለማረጋገጥ፣

የራስን ልጆች ህጋዊነት ለመመስረት እንዲሁም ከሌላ የተወለዱትን ለማስመዝገብ፣

የዜግነት ቅያሬን ለመጠየቅ፣

ጋብቻዉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ቦታ በማሳወቅ ህጋዊ መረጃ በመሆን፣

Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!

በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍21👎1
#ፍትህ_ለፌቨን #ፍትህ_ለፌቨን

ፌቨን የ7 ዓመት ህፃን ነች።እናቷ ነርስ ስለሆነች የተከራዩበት ቤት ትታት ትሄዳለች።ነገር ግን ቤት ያክራያቸውና አሁን በማረሚያ ቤት የሚገኘው ጌታቸው የተባለ የ3 ልጆች አባት ህፃኗን በአሰቃቂ ሁኔታ አስገድዶ ደፍሮ ገድሏት ተገኘች።

የ7 ዓመት ህፃኗ ልጅን ግቢ ውስጥ ወደ ሽንት ቤት ስትሄድ ጠብቆ አፏ ውስጥ አሽዋ በመጨመር ለመግለፅ በሚከብድ ሁኔታ አሰቃይቶ እንደገደላት እናት አስረድታለች።25 ዓመት ተፈርዶበት ማረሚያ ቤት ቢሆንም በይግባኝ ለማስወጣት እየሠሩ ነው።እኔን አስፈችው በማለት ዛቻና ማስፈራሪያው ከአቅሜ በላይ ሆኗል።ህዝብ ይፍረደኝ እያለች ነው።

#ፍትህ_ለፌቨን #ፍትህ_ለፌቨን
#ፍትህ_ለፌቨን #ፍትህ_ለፌቨን
በጠበቃና የሕግ አማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
😭22💔17👍8🤨2🤬1
የወሊድ መከላከያ ህክምና የወሰደው አባወራ ድጋሚ አባት መሆኑን ተከትሎ ክስ መሰረተ

የአራት ልጆች አባት የሆነው ሰው እርግዝና እንዳይፈጠር የሚከላከል ህክምና ቢያደርግም ሳይፈልግ አምስተኛ ልጅ አባት ለመሆን ተገዷል

የሕክምና ስህተት የሰራው ተቋም ልጄ 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ የማሳደጊያ ይከፈለኝ ሲል ክስ መስርቷል

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3AxaCl6

#የሕግአማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
😁34👍201
በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ከስቅላት እስከ ብልት ማኮላሸት የሚደርስ እርምጃ የሚወስዱ የዓለማችን ሀገራት👇👇👇


ቻይና እና ሳውዲ አረቢያ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን በሞት ከሚቀጡ ሀገራት መካከል ናቸው

አሜሪካንን ጨምሮ ስድስት የዓለማችን ሀገራት በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን ብልት እንዲኮላሽ የሚፈቅድ ህግ አላቸው

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3Av2AZS

#የሕግአማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍161
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከባድ ቅጣት የሚጥሉ ሀገራት እነማን ናቸው?


ሰሜን ኮሪያ በአስገድዶ  መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ የሚፈቅድ ህግ አላት


ስድስት ሀገራት ደግሞ ብልት እስከ ማኮላሸት ድረስ ወንጀለኞችን ይቀጣሉ

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://bit.ly/46PX9AE

#የሕግአማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍9
በዓለም ላይ ከሚገኙ ሴቶች መካከል 35 በመቶው ለጾታዊ ጥቃት የተጋለጡ ናቸው።

ይሁንና ጥቃቱን ከሚፈጽሙት ውስጥ 10 በመቶዎቹ ብቻ ህግ ፊት ቀርበው ውሳኔ ሲሰጣቸው ቀሪዎቹ በብዙ ምክንያቶች ተገቢውን ፍትህ አያገኙም ይላል ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው በሪፖርቱ።

የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመላው ዓለም ያለ ክስተት ቢሆንም የተወሰኑ ሀገራት ወንጀሉን ፈጽመዋል በተባሉ ጥፋተኞች ላይ ከባድ ቅጣት እንዲጥሉ የሚፈቅድ ህግ አዘጋጅተዋል።

ሰሜን ኮሪያ በአስገድዶ መድፈር ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞች በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ የሚፈቅድ ህግ አላት።

በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከባድ ቅጣት የሚጥሉት ሀገራት የትኞቹ ናቸው? በዝርዝር ያንብቡ፦ https://bit.ly/3Av2AZS

#የሕግአማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍11
#ኢራን

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በስቅላት ገድላለች።

በማዕከላዊ ኢራን " ዝድ ክልል "አስገድዶ መድፈር መፈጸሙ በፍርድ ቤት የተረጋገጠበት ግለሰብ ሞት ተቀጥቷል።

ግለሰቡ " በጥንቆላ ይተዳደራል " የተባለ ሲሆን ወደሱ የሚመጡ ሴቶችን በማታለል አስገድዶ ሲደፍር እንደነበር ተገልጿል፡፡

ከ12 በላይ የክስ መዝገቦች የተከፈቱበት ይህ ሰው አሱን ጨምሮ ከነ ረዳቱ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው በሞት ፍርድ እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረትም ጥፋተኛ የተባሉት ሰዎች ታንቀው እንዲገደሉ ተደርጓል።

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉ ወንጀለኞች ላይ ከባድ ቅጣት ከሚጥሉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት።

መረጃው የአን አይን ኒውስ / አል አረቢያ ነው።
#የሕግአማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍18👏42🎉1
ሞት የተፈረደባቸው እስረኞች ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅን ዘውዴን በደብዳቤ ተማፀኑ‼️
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙና የሞት ፍርድ የተወሰነባቸው ታራሚዎች ቅጣቱ እንዲፈጸም የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴን በደብዳቤ ጠይቀዋል‼️
የሞት ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው የጠየቁት በለጠ አሰፋ አምሜ፣ ጀበሳ ድንቁ ኦርዶፋ፣ ባዩ ጌታነህ ዜና፣ ግርማ ገዛኸኝ ማሞ እና መስታወት ጌታነህ ወ/የስ ናቸው።
ታራሚዎቹ ከ17 ዓመታት በላይ በእስር መቆየታቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች አለም አቀፍ ቃል ኪዳን፤ ማንኛውም የሞት ቅጣት የተፈረደበት ሰው ይቅርታ የመጠየቅ ወይም የሞት ቅጣቱ ወደ እስራት እንዲቀየርለት የመጠየቅ መብት እንዳለው ይደነግጋል። በተጨማሪም በሁሉም ጉዳዮች ይቅርታ ወይም ምህረት ማድረግ ወይም የሞት ቅጣቱን ወደ እስራት ቅጣት መለወጥ ይቻላል ይላል።

የሞት ቅጣቱ እንዲፈጸምባቸው የጠየቁት እስረኞቹ ፤ የሞት ፍርዱ ወደ ቁጥር እስራት እንዲቀየር ቢያመለክቱም ምላሽ እንዳላገኙ ነው ቤተሰቦቻቸው ለአዩዘሀበሻ የገለፁት ።
ታራሚዎቹ ፤ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር በሚሰጠው ምህረትና ይቅርታ ተጠቃሚ አለመሆናቸውንና ነገ የሚሉት ተስፋ እንደሌላቸው በመግለጽ የሞት ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅን በደብዳቤ ጠይቀዋል።

በይቅርታና በምህረት ተጠቃሚ ካለመሆናቸውም በላይ በማረሚያ ቤቱ የሚቀርበው ምግብና ያለው አያያዝ አስከፊ በመሆኑ በሕይወት ከመቆየት መሞትን መምረጣቸውን ገልጸዋል።
Ayu Zehabesha-Official አዩዘሀበሻ
#የሕግአማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👍22😢31🥰1
ከባድ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ሁለት ተከሳሾች እስከ 70 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ::

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች በመንቀሳቀስ ከባድ የስርቆት ወንጀሉን በተለያዩ ጊዜያት የፈፀሙት ሳሙኤል ሀይሉ እና ሳቢር ከድር የተባሉት ተከሳሾች መሆናቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ተከሳሾቹ የግለሰቦችን መኖሪያ ቤት እና የንግድ ቤቶችን በር በመገንጠልና በተመሳሳይ ቁልፍ ከፍተው በመግባት ላፕቶፕ፣ ኮምፒውተር፣ ቴሌቪዥኖች እና ሌሎች የተለያዩ እቃዎችን ሰርቀው መውሰዳቸውን የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ማስተባበሪያ ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር በልሁ ወልደኢየሱስ ገልፀዋል።

ፖሊስ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በቁጥጥር ስር አውሎ ባከናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ የተሰረቁትን ንብረቶች ማስመለስ መቻሉም ነው የተገለፀውል።

ንብረቶችን ከወንጀል ፈፃሚዎቹ እየተቀበለች በቤቷ ውስጥ ደብቃ ስታስቀምጥ የነበረች ትዕግስት ስመኝ የተባለች ግለሰብም ተይዛ ምርመራ እንደተጣራባት መርማሪው አስረድተዋል።

በሶስቱ ተከሳሾች ላይ በአጠቃላይ ዘጠኝ የክስ መዝገብ የተደራጀባቸው ሲሆን ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በአምስቱ መዝገቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም መሠረት ተከሳሽ ሳሙኤል ሀይሉ በእያንዳንዱ 5 የክስ መዝገቦች ላይ የተሰጠው ውሳኔ በድምሩ #70 ዓመት እስራት ሲሆን፣ በሁለተኛ ተከሳሽ ሳቢር ከድር ላይ በእያንዳንዱ 5 የክስ መዝገቦች በድምሩ የ65 ዓመት እስራት ቅጣት መወሰኑን ዋና ኢንስፔክተር በልሁ አስረድተዋል።

የተሰረቁትን ንብረቶች በመሸሸግ ወንጀል የተከሰሰችው ትዕግስት ስመኝ ከአምስቱ የክስ መዝገቦች በአራቱ በእያንዳንዱ የሶስት አመት እስራት እንድትቀጣ እና ቅጣቱ በገደብ እንዲሆንላት የተደረገ ሲሆን በአንደኛው መዝገብ በተመሳሳይ በ 3 አመት እስራት እንድትቀጣና ቅጣቷን ማረሚያ ቤት ሆና እንድትፈፅም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማስተላለፉን የምርመራ ሃላፊው አብራርተዋል።

ተከሳሾቹ ከተደራጀባቸው ዘጠኝ የክስ መዝገቦች መካከል ውሳኔ ያላገኙት ቀሪ 4 መዝገቦች በሂደት ላይ እንደሚገኙም ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋል።
#EBC
#የሕግአማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍15🥱2😁1
የግብር ከፋይ/ተገልጋዮች መብቶች

ግብር ከፋዮቻችን ወይም ተገልጋዮቻችን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ጋር በሚኖርዎት ግንኙነት የሚከተሉት መብቶች እንዳልዎት ያውቁ ይሆን? ለግንዛቤ እንዲሆንዎ እንደሚከተለው አቅርበንልዎታል፡፡

👉ተገልጋዮች በሥራ ላይ ስላሉ የግብር ድንጋጌዎች፣ ተቋሙ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶችና ቅድመ ሁኔታዎች ተገቢውን መረጃ እንደ አግባብነቱ በስልክ እና በአካል በመቅረብ መረጃዎቹን የመጠየቅ፣ ምላሽ የማግኘት እና አገልግሎቶቹን የመጠቀም መብት አላቸው፡፡
👉 ማንኛውም የተቋሙ ተገልጋይ በጾታ፣ በዘርና ቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደረጃው መገለል እና አድልዎ ሳይደርስበት በተገቢው ሁኔታ አገልግሎት የማግኘት መብት አለው፡፡
👉 ማንኛውም ተገልጋይ ክብሩና ስብዕናው ተጠብቆ የመስተናገድ እና ለሚያቀርባቸው አግባብነት ያላቸው የአገልግሎት ጥያቄዎች እንደሁኔታው አዎንታዊ ይሁን አሉታዊ ምላሽ የማግኘት መብት አለው፡፡
👉 ተገልጋዮች ለሚያቀርቡት የአገልግሎት ጥያቄ ወዲያው ምላሽ ለመስጠት የማይቻልበት ሁኔታ ሲኖር እና ቀጠሮ የሚሰጣቸው ከሆነ በሂደት ላይ የሚገኘው ጉዳያቸው ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ እንዲሁም የትና በየትኛው ክፍል እንደሚገኝ (ጉዳዩ እስኪጠናቀቅ በምስጥር መያዝ የሚገባቸውን ጉዳዮች ካልሆኑ በስተቀር) ጠይቀው የመረዳት መብት አላቸው፡፡
👉 የተቋሙ ተገልጋዮች በተቋሙ አሠራር፣ በሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሥነ ምግባር እና በአጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ካላቸው ቅሬታቸውን የማቅረብ፣ ተገቢውን ወቅታዊ ምላሽ የማግኘትና የመደመጥ መብት አላቸው፡፡
👉 በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥና አሠራር ዙሪያ የታዘቡትንና ቢሆን ይሻላል የሚሉትን ተገቢ አስተያየት በማመስገንም ሆነ በመተቸት በነፃነት የመግለጽ መብት አላቸው፡፡
👉 አርአያነት ባለው ሁኔታ የግብር ግዴታቸውን የሚወጡ ግብር ከፋዮች ሽልማት የመቀበል መብት አላቸው፡፡

በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩት መብትዎ መሆኑን ተገንዝበው ይጠቀሙበት፡፡

በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
#የሕግአማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍7
Forwarded from አለሕግAleHig ️
የጋብቻ ምዝገባ-ግለሰባዊ ጥቅሞች

ጋብቻ ለመከሰቱ ህጋዊ ማስረጃ በመሆን

ጋብቻዉ ህጋዊ መሆኑን ለማረጋገጥ፣

የተጋቢዎቹን ዝምድና እና ግንኙነት ለማረጋገጥ፣

የጋብቻ ውጤት ለሆኑት ህፃናት በቤተሰብነት የመጠበቅ ህጋዊ መብትን ለማረጋገጥ፣

ህጋዊ ወራሽነትን ለማረጋገጥ፣

ለቤተሰብ ድጎማ ለመንግስት ጥያቄ ለማቅረብ፣

ከተጋቢዎች አንዳቸው ቢሞቱ ቋሚው የኢንሹራንስ ጥያቄን ለማቅረብ፣

ጋብቻ በሚፈርስበት ጊዜ የልጆችን አስተዳደግ ለመወሰን፣

ወደ ውጪ ሃገር ለመጓጓዝ ፓስፖርት የማግኘት ፈቃድን ለማቅረብ፣

የልጆችን ህጋዊነት ለማረጋገጥ፣

የራስን ልጆች ህጋዊነት ለመመስረት እንዲሁም ከሌላ የተወለዱትን ለማስመዝገብ፣

የዜግነት ቅያሬን ለመጠየቅ፣

ጋብቻዉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ቦታ በማሳወቅ ህጋዊ መረጃ በመሆን፣

Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!

በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/alehig

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.com
👍16