አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩበትን ጊዜ ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት አራዘሙ
***
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶችና ም/ፕሬዝደንቶች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ወቅታዊ ሁኔታ በመገምገም ፍርድ ቤቶቹ ከሰኔ 1 ቀን 2012 ጀምሮ እስከ ሀምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት በከፊል ዝግ ሆነው አንዲቆዩ መወሰናቸውን ለኢቢሲ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው እንዲቆዩና አስቸኳይነት ያላቸውን ጉዳዮች ብቻ በተረኛ ችሎት እንዲመለከቱ መደረጉ ይታወቃል፡፡
የወረርሽኙ ስርጭት እየተስፋፋ በመምጣቱ ምክንያት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረና የስርጭት አድማስም እየሰፋ መምጣቱን የጤና ጥብቃ ሚኒስቴር በየጊዜው ከሚያስራጫቸው መረጃዎች የፍርድ ቤቱ አመራር መገንዘብ ችሏል፡፡
አመራሩ ባካሄደው ስብሰባ የዳኝነት አገልግሎት ለማግኘት ከክልሎች፣ ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ከተሞች ወደ ፍርድ ቤቶች የሚመጡ ባለጉዳዮች ቁጥራቸው በርካታ በመሆኑና የእነዚህ ባለጉዳዮች ለቫይረሱ ስርጭት ያላቸወን ተጋላጭነት ለመቀነስ እንዲሁም ዳኞችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ ስራቸውን እንዲያከናውኑ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማመን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከሰኔ 1 ቀን 2012 ጀምሮ እስከ ሀምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት በከፊል ዝግ ሆነው አንዲቆዩ ወስኗል፡፡
ፍ/ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩበት ጊዜ በተረኛ ችሎት እንዲታዩ ከተለዩት ጉዳዮች በተጨማሪ አነስተኛ የተገልጋይ ቁጥር ያላቸው ሌሎች የዳኝነት አገልግሎት ሊሰጥባቸው የሚችሉ የጉዳዮችን በመለየት አገልግሎቱን በየጊዜው ቀስ በቀስ ለባለጉዳዮች ክፍት እየተደረገ እንዲሄድ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም በአመራሩ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ይህን መሰረት በማድረግም ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ጊዜ፡-
1. ከሰኔ 30/2011 ዓ/ም በፊት የተከፈቱ ዉዝፍ ይግባኝ መዝገቦችን ለመወሰን በችሎት ባለጉዳዮችን የመስማት አስፈላጊነት የታመኑባቸው ጉዳዮች ተለይተው ውሳኔ እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡
2. የወንጀል ይግባኝ ጉዳዮችን በተመለከተ ከማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጋር የቪዲዮ ኮንፈረንስ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ተከራካሪ ወገኖች ይሰማሉ፤ እንደየሁኔታው ከባለጉዳዮች ጋር በመነጋገር የቃል ክርክራቸውን በጽሁፍ የሚያቀርቡ ሲሆን ወሳኔ እንዲያገኙም ይደረጋል፡፡
3. የፍታብሔር ይግባኝ ጉዳዮችን በተመለከተ ባለጉዳዮችን መስማት አስፈላጊነቱ በዳኞች ከታመነባቸው ጉዳዮች ውጭ የሆኑ መዛግብት እልባት እንዲያገኙ ይደረጋል።
4. አስቸኳይ በሆኑ ጉዳችዮች በተረኛ ችሎት የተሰጠውን ትዕዛዝ፣ ብይን እና ውሳኔ መሰረት በማድረግ የሚቀርቡ የይግባኝ ጉዳዮች በአፋጣኝ እልባት የሚሰጣቸው ይሆናል፣
5. አስቸኳነት ያላቸው ጉዳዮች ማለትም ከህጻናት ቀለብና አስተዳደግ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች፣ የዋስትና ጉዳይ፣ የአሰሪና ሰራተኞች ጉዳይ፣ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጸሙ የቤት ውስጥ ጥቃቶች እና ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈጸሚያ መመሪያ ወይም ደንብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ይሆናሉ፡፡
6. የፌዴራልና የክልል ጉዳዮች ውሳኔን መሰረት በማድረግ ተከፍተው በሂደት ላይ የነበሩ የአፈጻጸም ጉዳዮች የስራና አፈጻጸም አቅጣጫ እስከሚሰጥባቸው ጊዜ ድረስ በደረሱበት ደረጃ ቆመው የሚቆዩ ይሆናል፡፡
7. በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች ተዘጋጅቶ በሚገለጸው መርሃ-ግብር መሰረት የውሳኔ፣ የትዕዛዝ፣ የብይንና የመዝገብ ግልባጭ የመስጠት ተግባር የሚከናወን ይሆናል፡፡ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭት ለመከላከል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሆኑባቸው ጊዜያት ወደ ፍርድ ቤቶቹ ቅጥር ጊቢ የሚገቡና የሚስተናገዱት ባለጉዳዮቹ ብቻ ይሆናሉ፡፡
ባለጉዳዮች ለአገልግሎት ወደ ፍርድ ቤት ሲመጡም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መልበስ እንዲሁም በመግቢያ በር ላይ በተዘጋጀ እጅ መታጠቢያ እጃቸውን መታጠብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የእርስ በእርስ ርቀታቸውንም ጠብቀው እንዲስተናገዱ የፍርድ ቤቱ አመራር አሳስቧል፡፡ የመከላከያ ጥንቃቄዎችን በአግባቡ በመተግበር ወረርሽኙ ከሚያደርሰው አስከፊ ጥቃት ህብረተሰቡ አራሱን እንዲከላከል የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
#EBC