አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው የ17 ዓመት ወጣት 6 ወር ተፈረደበት ይለናል የወምበራ ኮሚኒኬሽን።

የ5 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው የ17 ዓመቱ ወጣት #በ6ወር እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል።

የ10ኛ ክፍል ተማሪና የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ግለሰብ በአስገድዶ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በደብረ―ዘይት ከተማ 02 ቀበሌ በተለምዶ " ሳንቂ በር " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

በዕለቱ የ5 ዓመቷ ህፃን ላይ አስገድዶ የመድፈር ድርጊት ከፈፀመ በኃላ በመኖሪያ ቤቱ ነው የተያዘው።

ጉዳዩን የተከታተለው የወምበራ ወረዳ ፍርድ ቤት  መጋቢት 9 በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ወጣት የ6 ወር እስራት ፈርዶበታል።

ይህን መረጃ በ @tikvahethMagazine ላይ የተመለከቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት " ቀልድ ነው ? ምን አይነት ፍርድ ነው ? ወንጀሉን ፍፁም የማይመጥን አሳዛኝ ፍርድ ነው " ብለውታል።

@tikvahethiopia

ፍትሕ የት ነሽ
አለሕግAleHig ️
የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው የ17 ዓመት ወጣት 6 ወር ተፈረደበት ይለናል የወምበራ ኮሚኒኬሽን። የ5 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው የ17 ዓመቱ ወጣት #በ6ወር እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል። የ10ኛ ክፍል ተማሪና የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ግለሰብ በአስገድዶ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በደብረ―ዘይት ከተማ…
ሕግ አላማው በዋናነት መቅጣት ሳይሆን ማስተማር እና በሌሎች እንዳይደገም መቀጣጫ ማድረግ ቢሆንም👈👈

ይህ ውሳኔ ግን አያስተምርም ፣ ወንጀሉ ድጋሜ እንዳይፈፀም ሊከለክልም አይችልም

የሴቶችን መብት ጥሰት ወንጀል ያቃለለ መስሎ ይሰማኛል። 🔊🔊🔊
በ 5 ዓመት ህፃን ላይ ለደረሰ የመደፈር ወንጀል #6 (ስድስት) ወር ቅጣት

#አለሕግ #Alehig
Any comment ....
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
ሊሞቱ የደረሱ ሰዎች የሚቆጫቸው
10 ነገሮች

#Ethiopia | በተለያየ ህመም ምክኒያት በህይወት ጥቂት ጊዜ የቀራቸው ሰዎች ቀሪ ጊዜያቸውን ያለ ስቃይ እንዲያሳልፉ ህክምና የሚያገኙበት ቦታ Hospice ይባላል። ሆስፒስ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች እነዚህን ከጥቂት ሳምንታት እስከ ጥቂት ወራት የቀራቸው ሰዎች በህይወታቸው ምን እንደሚቆጫቸው ጠይቀዋቸው የሚከተሉትን 10 ነጥቦች አግኝተዋል።
1) ደስተኛ አልነበርኩም- ህይወቴን በሚገባ enjoy አላደረግሁም።
2) በእውቀት ራሴን አላሳደግሁም። ለመማር ብዙ እድል ነበረኝ ግን አልተማርኩም።
3) እራሴን አልተንከባከብኩም-ጥሩ እንቅልፍ አልተኛሁም፤ ስፖርት አልሰራሁም፤ አመጋገቤ ላይ አልተጠነቀቅኩም፤ የጤና ምርመራ በሰአቱ አላደረግሁም።
4) የኖርኩት በቂምና በጥላቻ ነው-ሁሉም ነገር እንደዚህ ማለፉ ለማይቀር ለምን በቂምና በጥላቻ ራሴንም ሰዎችንም ጎዳሁ?
5) ለቤተሰቤ ጊዜ አልሰጠሁም-ላይ ታች ስል ከልጆቼ ጋር አልተጫወትኩም፤ ወላጆቼን እንደምወዳቸው አልነገርኳቸውም። አብሬያቸው ጊዜ አላሳለፍኩም።

6) ሰዎችን አልረዳሁም- ብዙ የእኔን እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ነበሩ። አቅሙ እያለኝ እኔ ግን 'ቢዚ' ስለነበርኩ አልደረስኩላቸውም።

7) ህልሜን አልኖርኩም- ለብዙ አመታት ለአንድ መስሪያቤት ተቀጥሬ ነው የሰራሁት እንጂ የራሴን ህልም አልኖርኩም።

8) ያለምክኒያት ነው የለፋሁት- በማይጠቅሙኝ ነገሮች ተጠምጄ በጣም ስለፋ ነበር።
9) ለሰዎች ፍቅሬን አልገለፅኩም- ለምወዳቸው ሰዎች 'እወድሀለሁ' ወይም 'እወድሻለሁ' አላልኩም።ፍቅሬን ከመግለፅ ይልቅ እኮሳተራለሁ።
10) ሀይማኖትን እንቅ ነበረ- መንፈሳዊነትን እጠላ ነበር። አሁን መጨረሻዬ ላይ እስከምደርስ ወደ አምላኬ ዞር አላልኩም ነበር።
ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ https://t.me/lawsocieties
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#update

" ዓቃቢ ህግ በፍርድ ቤቱ በኩል ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ ይግባኝ በመጠየቅ ክሱ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል እንዲታይ ተደርጓል" - የወምበራ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት

" ይህንን የፍርድ ዉሳኔ የሰጠዉ ዳኛ ከስራና ከደመወዝ ታግዶ እንዲቆይና ጉዳዩ በኮሚቴ ተጣርቶ እንዲቀርብ ትእዛዝ ተሰጥቷል " - የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት

በወምበራ ወረዳ ፍ/ቤት ከዚህ ቀደም ስሙ ያልተጠቀሰው ' ተክለአብ ገለታ ' የተባለው ተከሳሽ የ5 አመት ህጻን ልጅ በመድፈር ወንጀል ተከስሶ #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ይታወሳል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የወረዳው ፍርድ ቤት ያስተላለፈው ውሳኔ አግባብ አለመሆኑንና አስተማሪነቱን ባለመቀበል ዓቃቢ ህግ በፍርድ ቤቱ በኩል ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ #ይግባኝ መጠየቁን የወምበራ ወረዳ ፍትህ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ አመንቴ ገልፀዋል።

ጉዳዩን አስመልክተው ለወረዳው ኮሚዩኒኬሽን ማብራሪያ የሰጡት የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ የወረዳው ፍርድ ቤት ባስተላለፈው የቅጣት ውሳኔ ከተፈፀመው ወንጀል ጋር ተመጣጣኝና አስተማሪ ባለመሆኑ ይግባኝ ተጠይቆ ክሱ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል እየታየ መሆኑን  አስረድተዋል።

ይህንን ተከትሎ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የመዝገቡን የክስ ሂደት ማጣራትና ማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ወደ መተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ኮሚቴ በመላክ ጉዳዩ በአስቸኳይ እንዲጣራ ኮሚቴ መላኩን አሳውቋል።

ጠቅላይ ፍ/ቤቱ " ይህንን የፍርድ ዉሳኔ የሰጠዉ ዳኛ ከስራና ከደመወዝ ታግዶ እንዲቆይና በኮሚቴዉ ጉዳዩ  ተጣርቶ ሲቀርብ ቀጣይ በዲስፕሊን ታይቶ በክልሉ ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ተገቢውን የእርምት እርምጃ ይወሰዳል " ብሏል።

የተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ቅጣት ማነስ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በመተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ እየታየ መሆኑን ያረጋገጠው የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሚሰጠውን ዉሳኔ በቀጣይ መረጃዉን ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከወምበራ ኮሚኒኬሽን እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እንዳገኘው ያሳውቃል።

@TikvahethMagazine
አለሕግAleHig ️
የ5 አመት ህጻን ልጅ በመድፈር ወንጀል ተከሳሽን #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ የፍርድ ዉሳኔ የሰጠዉ ዳኛ ከስራና ከደመወዝ ታግዶ እንዲቆይና ጉዳዩ በኮሚቴ ተጣርቶ እንዲቀርብ ትእዛዝ ተሰጥቷል - የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እርምጃ የዳኝነት ነጻነትን ይጻረራል‼️
የተፈጠረውን ስህተት ለማስተካከል ይግባኝ ማለት መብት ሆኖ ሳለ👈
ቅጣቱ ለድርጊቱ ተመጣጣኝ ሆኖ የታየውን በህጉ መሰረት ወሰንኩኝ ካለ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ውሳኔ ትክክል አይደለም ብሎ ሊሽር እንደሚችል እየታወቀ ዳኛው የተሰጠውን ህገመንግስታዊ ተጠያቂነት ለህሌናው መሆኑን ታሳቢ በማድረግ በዳኛው ላይ እንደዚህ አይነት እርምጃ መወሰዱ የደኝነት ነፃነትን የሚጻረር ነው።
ምን ትላላችሁ
አንድን ስህተት ለማስተካከል በሌላ ስህተት ለማረም ወይም ለማስተካከል ለምን ይሞከራል?
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የሕሊና (የሞራል) ጉዳት ካሳ 1 ሺህ ብር የሚለው ሕግ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለውን የሕሊና (የሞራል) ግምት አናሳ መሆኑን ያሳያል!!
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2116(3) የእኔን የሕሊና (የሞራል) ጉዳት በገንዘብ የማይተካ ሆኖ ሳለ በ1ሺ ብር ካስኩህ ካለኝ በዚህግ ምክንያት ሌላ ጉዳት በሕጉ ምክንያት ስለደረሰብኝ ሌላ ካሳ ያስፈልገኛል።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM