አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ለሕሊና (ለሞራል) ጉዳት ካሳ 1 ሺህ ብር ይበቃል?

#ሕጉ #ምን #ይላል?
እነዚህን ሁለት በሀገራችን የመጨረሻ የዳኝነት አካል እስከሆነው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የደረሱ የጉዳት ካሳ ክርክሮችን በአጭሩ አስነብባችሁና የራሳችሁን ዳኝነት ከሰጣችሁ በኋላ ሰበር የሰጠውን ውሳኔ በአጭሩ እናያለን።

የልጅ ሞትና የሕሊና ጉዳት

ወ/ሮ ዘሀራ አባኑር እና አቶ መሀመድ አባአሊ ልጃቸው በደረሰበት የመኪና አደጋ በመሞቱ የመድሕን ሽፋን ሰጥቶ ከነበረው የኢንሹራስ ኩባንያ ጋር ተከራከሩ፡፡

ልጃቸውን በአደጋው ምክንያት በማጣታቸው የቀረባቸው የገንዘብ ጥቅም ብር 52 ሺህ ሕሊናቸው ላይ ለደረሰው ጉዳት ደግሞ ብር 2 ሺህ እንዲከፈላቸው የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ይግባኝ የተጠየቀበት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰኑ፡፡

ይሄ ውሳኔ የተሰጠበት የኢንሹራንሱ ኩባንያ ቅር በመሰኘቱ የሕሊና ጉዳት (የሞራል ጉዳት) ካሳ ከ1 ሺህ ብር እንደማይበልጥ በሕግ ተደንግጓልና በሕግ ከተደነገገው የገንዘብ መጠን በላይ የሕሊና ጉዳት ካሳ እንድከፍል በመወሰኑ የተፈፀመው የሕግ ስሕተት ይታረምልኝ ሲል አመለከተ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም ሕጉን ተርጉሞ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በቅድሚያ እናንተ ሕሊናችሁን ብቻ በመጠቀም ዳኙ ብትባሉ ኖሮ ወ/ሮ ዘሀራና አቶ መሀመድ ልጃቸውን በማጣታቸው ሕሊናቸው ወይም መንፈሳቸውና ቅስማቸው ላይ ለደረሰባቸው ጉዳት ካሳ ይገባቸዋል?

የሕሊና ጉዳት በገንዘብ ሊካስ ይችላል? ከተቻለ በምን ያህል?

ባይወልዱትም ያሳደጉትን ልጅ ማጣት

ኒሻን አለማየሁ የእህቷን ልጅ ወንድማገኝ ይልማን አንደ ልጇ አድርጋ እያሳደገች ትኖር ነበር ፡፡

ከእህቷ ልጅ ጋር የምትኖረው የምትሰራበት የመንግስት የእርሻ ልማት በሰጣት ቤት ውስጥ ሲሆን፤ ወንድማገኝ የሚኖርበት ግቢ ሲቦርቅ ያደገበት ቢሆንም አንድ ቀን ግን በመጫወት ላይ እያለ በግቢው የተዘረጋው ኤሌትሪክ ይዞት ሞተ፤ 14 ዓመቱ ነበር፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-
https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6323

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!


ምንም ውሳኔ ከመወሰንዎ በፊት አማራጭ የሕግ እውቀት ያግኙ::
   
0920666595


👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig?si=BQvQV6OdOb6G8WI1

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
4👍3