አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው የ17 ዓመት ወጣት 6 ወር ተፈረደበት ይለናል የወምበራ ኮሚኒኬሽን።

የ5 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው የ17 ዓመቱ ወጣት #በ6ወር እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል።

የ10ኛ ክፍል ተማሪና የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ግለሰብ በአስገድዶ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በደብረ―ዘይት ከተማ 02 ቀበሌ በተለምዶ " ሳንቂ በር " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

በዕለቱ የ5 ዓመቷ ህፃን ላይ አስገድዶ የመድፈር ድርጊት ከፈፀመ በኃላ በመኖሪያ ቤቱ ነው የተያዘው።

ጉዳዩን የተከታተለው የወምበራ ወረዳ ፍርድ ቤት  መጋቢት 9 በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ወጣት የ6 ወር እስራት ፈርዶበታል።

ይህን መረጃ በ @tikvahethMagazine ላይ የተመለከቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት " ቀልድ ነው ? ምን አይነት ፍርድ ነው ? ወንጀሉን ፍፁም የማይመጥን አሳዛኝ ፍርድ ነው " ብለውታል።

@tikvahethiopia

ፍትሕ የት ነሽ
👍17
አለሕግAleHig ️
የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው የ17 ዓመት ወጣት 6 ወር ተፈረደበት ይለናል የወምበራ ኮሚኒኬሽን። የ5 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው የ17 ዓመቱ ወጣት #በ6ወር እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል። የ10ኛ ክፍል ተማሪና የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ግለሰብ በአስገድዶ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በደብረ―ዘይት ከተማ…
ሕግ አላማው በዋናነት መቅጣት ሳይሆን ማስተማር እና በሌሎች እንዳይደገም መቀጣጫ ማድረግ ቢሆንም👈👈

ይህ ውሳኔ ግን አያስተምርም ፣ ወንጀሉ ድጋሜ እንዳይፈፀም ሊከለክልም አይችልም

የሴቶችን መብት ጥሰት ወንጀል ያቃለለ መስሎ ይሰማኛል። 🔊🔊🔊
በ 5 ዓመት ህፃን ላይ ለደረሰ የመደፈር ወንጀል #6 (ስድስት) ወር ቅጣት

#አለሕግ #Alehig
👍32👎31🤯1
Any comment ....
👍27
4👍1
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
ሊሞቱ የደረሱ ሰዎች የሚቆጫቸው
10 ነገሮች

#Ethiopia | በተለያየ ህመም ምክኒያት በህይወት ጥቂት ጊዜ የቀራቸው ሰዎች ቀሪ ጊዜያቸውን ያለ ስቃይ እንዲያሳልፉ ህክምና የሚያገኙበት ቦታ Hospice ይባላል። ሆስፒስ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች እነዚህን ከጥቂት ሳምንታት እስከ ጥቂት ወራት የቀራቸው ሰዎች በህይወታቸው ምን እንደሚቆጫቸው ጠይቀዋቸው የሚከተሉትን 10 ነጥቦች አግኝተዋል።
1) ደስተኛ አልነበርኩም- ህይወቴን በሚገባ enjoy አላደረግሁም።
2) በእውቀት ራሴን አላሳደግሁም። ለመማር ብዙ እድል ነበረኝ ግን አልተማርኩም።
3) እራሴን አልተንከባከብኩም-ጥሩ እንቅልፍ አልተኛሁም፤ ስፖርት አልሰራሁም፤ አመጋገቤ ላይ አልተጠነቀቅኩም፤ የጤና ምርመራ በሰአቱ አላደረግሁም።
4) የኖርኩት በቂምና በጥላቻ ነው-ሁሉም ነገር እንደዚህ ማለፉ ለማይቀር ለምን በቂምና በጥላቻ ራሴንም ሰዎችንም ጎዳሁ?
5) ለቤተሰቤ ጊዜ አልሰጠሁም-ላይ ታች ስል ከልጆቼ ጋር አልተጫወትኩም፤ ወላጆቼን እንደምወዳቸው አልነገርኳቸውም። አብሬያቸው ጊዜ አላሳለፍኩም።

6) ሰዎችን አልረዳሁም- ብዙ የእኔን እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ነበሩ። አቅሙ እያለኝ እኔ ግን 'ቢዚ' ስለነበርኩ አልደረስኩላቸውም።

7) ህልሜን አልኖርኩም- ለብዙ አመታት ለአንድ መስሪያቤት ተቀጥሬ ነው የሰራሁት እንጂ የራሴን ህልም አልኖርኩም።

8) ያለምክኒያት ነው የለፋሁት- በማይጠቅሙኝ ነገሮች ተጠምጄ በጣም ስለፋ ነበር።
9) ለሰዎች ፍቅሬን አልገለፅኩም- ለምወዳቸው ሰዎች 'እወድሀለሁ' ወይም 'እወድሻለሁ' አላልኩም።ፍቅሬን ከመግለፅ ይልቅ እኮሳተራለሁ።
10) ሀይማኖትን እንቅ ነበረ- መንፈሳዊነትን እጠላ ነበር። አሁን መጨረሻዬ ላይ እስከምደርስ ወደ አምላኬ ዞር አላልኩም ነበር።
ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ https://t.me/lawsocieties
👍1514
New_No_repayment_alphabet_e1dcbe678e.pdf
339.6 KB
ንግድ ባንክ “የወሰዱትን ግንዘብ ለመመለስ ፍቃደኛ አልሆኑም” ያላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ

ባንኩ ስመ ዝርዝራቸው የወጣ ሰዎች እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ድረስ ገንዘቡን እንዲመልሱ አሳስቧል ። እስካሁን 14 ሺህ 441 ሰዎች ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መልሰዋል ተብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ
https://t.me/lawsocieties/9336
👆👆👆👆👆👆

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!


ምንም ውሳኔ ከመወሰንዎ በፊት አማራጭ የሕግ እውቀት ያግኙ::
   
0920666595


👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties


👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍7
በአሜሪካ የሚኒሶታ የሀይማኖት ተቋማት ፆታ የሚቀይሩ ሰዎችን የመቅጠር የህግ ግዴታ እንዳይጣልባቸው ጠየቁ

በአሜሪካ ሚኒሶታ የካቶሊኮች፣ ሉተራኖች፣ አይሁዶች እና ሙስሊሞች የሃይማኖት ጥምረት ቡድን የሃይማኖት ድርጅቶች እና ትምህርት ቤቶች ሀይማኖታዊ እሴቶችን የሚጥሱ ጾታ ቀያሪ ግለሰቦችን ከመቅጠር ግዴታ ነፃ እንዲሆኑ የሚያደርገውን የሚኒሶታ የሰብአዊ መብት ድንጋጌ እንዲሻሻል ጠይቀዋል።

ባለፈው አመት ህግ አውጪዎች የሚኒሶታ የሰብአዊ መብት ድንጋጌ ላይ በፆታ ማንነት ላይ የተመሰረተ መድልዎን የሚከለክል ህግ ማውጣታቸው ሲገለፅ የሀይማኖት ተቋማቱ ግብረ ሰዶማውያንን በተቋሞቻቸው የመቅጠር ግዴታ እንዳይኖርባቸው ቢደረግም ፆታን የሚቀይሩ ዜጎች ላይ የተቀመጠ አመልካች ህግ አልነበረም።

አሁን ላይ እንዲፀድቅ የተጠየቀው አዲስ ድንጋጌ ሁሉም የሃይማኖት ድርጅቶች እና ተቋማት ከፆታ ማንነት ጋር በተገናኘ ጾታ ቀያሪዎችን በግዴታ የመቅጠር ፖሊሲውን ከመከተል ነፃ ለማድረግ ያለመ ነው ሲባል የሀይማኖት ተቋማቱ ያለ ህዝባዊ የመብት ሙግት ጾታ ቀያሪ ሰዎችን መቅጠር መተው እንደሚፈልጉ ተነግሯል።
#TikvahethMagazine

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!


ምንም ውሳኔ ከመወሰንዎ በፊት አማራጭ የሕግ እውቀት ያግኙ::
   
0920666595


👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties


👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig?si=BQvQV6OdOb6G8WI1

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍51
#update

" ዓቃቢ ህግ በፍርድ ቤቱ በኩል ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ ይግባኝ በመጠየቅ ክሱ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል እንዲታይ ተደርጓል" - የወምበራ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት

" ይህንን የፍርድ ዉሳኔ የሰጠዉ ዳኛ ከስራና ከደመወዝ ታግዶ እንዲቆይና ጉዳዩ በኮሚቴ ተጣርቶ እንዲቀርብ ትእዛዝ ተሰጥቷል " - የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት

በወምበራ ወረዳ ፍ/ቤት ከዚህ ቀደም ስሙ ያልተጠቀሰው ' ተክለአብ ገለታ ' የተባለው ተከሳሽ የ5 አመት ህጻን ልጅ በመድፈር ወንጀል ተከስሶ #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ይታወሳል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የወረዳው ፍርድ ቤት ያስተላለፈው ውሳኔ አግባብ አለመሆኑንና አስተማሪነቱን ባለመቀበል ዓቃቢ ህግ በፍርድ ቤቱ በኩል ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ #ይግባኝ መጠየቁን የወምበራ ወረዳ ፍትህ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ አመንቴ ገልፀዋል።

ጉዳዩን አስመልክተው ለወረዳው ኮሚዩኒኬሽን ማብራሪያ የሰጡት የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ የወረዳው ፍርድ ቤት ባስተላለፈው የቅጣት ውሳኔ ከተፈፀመው ወንጀል ጋር ተመጣጣኝና አስተማሪ ባለመሆኑ ይግባኝ ተጠይቆ ክሱ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል እየታየ መሆኑን  አስረድተዋል።

ይህንን ተከትሎ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የመዝገቡን የክስ ሂደት ማጣራትና ማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ወደ መተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ኮሚቴ በመላክ ጉዳዩ በአስቸኳይ እንዲጣራ ኮሚቴ መላኩን አሳውቋል።

ጠቅላይ ፍ/ቤቱ " ይህንን የፍርድ ዉሳኔ የሰጠዉ ዳኛ ከስራና ከደመወዝ ታግዶ እንዲቆይና በኮሚቴዉ ጉዳዩ  ተጣርቶ ሲቀርብ ቀጣይ በዲስፕሊን ታይቶ በክልሉ ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ተገቢውን የእርምት እርምጃ ይወሰዳል " ብሏል።

የተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ቅጣት ማነስ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በመተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ እየታየ መሆኑን ያረጋገጠው የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሚሰጠውን ዉሳኔ በቀጣይ መረጃዉን ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከወምበራ ኮሚኒኬሽን እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እንዳገኘው ያሳውቃል።

@TikvahethMagazine
👍246🥰3
አለሕግAleHig ️
የ5 አመት ህጻን ልጅ በመድፈር ወንጀል ተከሳሽን #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ የፍርድ ዉሳኔ የሰጠዉ ዳኛ ከስራና ከደመወዝ ታግዶ እንዲቆይና ጉዳዩ በኮሚቴ ተጣርቶ እንዲቀርብ ትእዛዝ ተሰጥቷል - የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እርምጃ የዳኝነት ነጻነትን ይጻረራል‼️
የተፈጠረውን ስህተት ለማስተካከል ይግባኝ ማለት መብት ሆኖ ሳለ👈
ቅጣቱ ለድርጊቱ ተመጣጣኝ ሆኖ የታየውን በህጉ መሰረት ወሰንኩኝ ካለ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ውሳኔ ትክክል አይደለም ብሎ ሊሽር እንደሚችል እየታወቀ ዳኛው የተሰጠውን ህገመንግስታዊ ተጠያቂነት ለህሌናው መሆኑን ታሳቢ በማድረግ በዳኛው ላይ እንደዚህ አይነት እርምጃ መወሰዱ የደኝነት ነፃነትን የሚጻረር ነው።
ምን ትላላችሁ
አንድን ስህተት ለማስተካከል በሌላ ስህተት ለማረም ወይም ለማስተካከል ለምን ይሞከራል?
👍17👎9
ለሕሊና (ለሞራል) ጉዳት ካሳ 1 ሺህ ብር ይበቃል?

#ሕጉ #ምን #ይላል?
እነዚህን ሁለት በሀገራችን የመጨረሻ የዳኝነት አካል እስከሆነው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የደረሱ የጉዳት ካሳ ክርክሮችን በአጭሩ አስነብባችሁና የራሳችሁን ዳኝነት ከሰጣችሁ በኋላ ሰበር የሰጠውን ውሳኔ በአጭሩ እናያለን።

የልጅ ሞትና የሕሊና ጉዳት

ወ/ሮ ዘሀራ አባኑር እና አቶ መሀመድ አባአሊ ልጃቸው በደረሰበት የመኪና አደጋ በመሞቱ የመድሕን ሽፋን ሰጥቶ ከነበረው የኢንሹራስ ኩባንያ ጋር ተከራከሩ፡፡

ልጃቸውን በአደጋው ምክንያት በማጣታቸው የቀረባቸው የገንዘብ ጥቅም ብር 52 ሺህ ሕሊናቸው ላይ ለደረሰው ጉዳት ደግሞ ብር 2 ሺህ እንዲከፈላቸው የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ይግባኝ የተጠየቀበት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰኑ፡፡

ይሄ ውሳኔ የተሰጠበት የኢንሹራንሱ ኩባንያ ቅር በመሰኘቱ የሕሊና ጉዳት (የሞራል ጉዳት) ካሳ ከ1 ሺህ ብር እንደማይበልጥ በሕግ ተደንግጓልና በሕግ ከተደነገገው የገንዘብ መጠን በላይ የሕሊና ጉዳት ካሳ እንድከፍል በመወሰኑ የተፈፀመው የሕግ ስሕተት ይታረምልኝ ሲል አመለከተ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም ሕጉን ተርጉሞ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በቅድሚያ እናንተ ሕሊናችሁን ብቻ በመጠቀም ዳኙ ብትባሉ ኖሮ ወ/ሮ ዘሀራና አቶ መሀመድ ልጃቸውን በማጣታቸው ሕሊናቸው ወይም መንፈሳቸውና ቅስማቸው ላይ ለደረሰባቸው ጉዳት ካሳ ይገባቸዋል?

የሕሊና ጉዳት በገንዘብ ሊካስ ይችላል? ከተቻለ በምን ያህል?

ባይወልዱትም ያሳደጉትን ልጅ ማጣት

ኒሻን አለማየሁ የእህቷን ልጅ ወንድማገኝ ይልማን አንደ ልጇ አድርጋ እያሳደገች ትኖር ነበር ፡፡

ከእህቷ ልጅ ጋር የምትኖረው የምትሰራበት የመንግስት የእርሻ ልማት በሰጣት ቤት ውስጥ ሲሆን፤ ወንድማገኝ የሚኖርበት ግቢ ሲቦርቅ ያደገበት ቢሆንም አንድ ቀን ግን በመጫወት ላይ እያለ በግቢው የተዘረጋው ኤሌትሪክ ይዞት ሞተ፤ 14 ዓመቱ ነበር፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-
https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6323

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!


ምንም ውሳኔ ከመወሰንዎ በፊት አማራጭ የሕግ እውቀት ያግኙ::
   
0920666595


👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig?si=BQvQV6OdOb6G8WI1

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
4👍3
የሕሊና (የሞራል) ጉዳት ካሳ 1 ሺህ ብር የሚለው ሕግ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለውን የሕሊና (የሞራል) ግምት አናሳ መሆኑን ያሳያል!!
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2116(3) የእኔን የሕሊና (የሞራል) ጉዳት በገንዘብ የማይተካ ሆኖ ሳለ በ1ሺ ብር ካስኩህ ካለኝ በዚህግ ምክንያት ሌላ ጉዳት በሕጉ ምክንያት ስለደረሰብኝ ሌላ ካሳ ያስፈልገኛል።
👍266
የህሊና ጉዳት ካሳ
(Moral Damage)

የፍትሐብሔር ሕግ የግለሰቦች፣ መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እርስ በርስ በሚያደርጉት ገንዘብ እና ንብረት ነክ ግንኙነት ያላቸውን መብትና ግዴታ የሚያስተዳድር ህግ ነው፡፡ የፍትሐብሔር ህግ ገንዘብ እና ገንዘብ ነክ ጉዳዮችን የሚያስተዳድር ህግ በመሆኑ ጉዳት የደረሰበት ሰው የሚጠይቀው የጉዳት ካሳ የሚገዛው በዚሁ ህግ ማዕቀፍ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የህሊና ጉዳት ካሳ (Moral Damage) በፍትሐብሔር ህጋችን ያለውን ሽፋን እንመለከታለን።

የህሊና ጉዳት ካሳ (Moral Damage) ምንነት

የህሊና ጉዳት ካሳ (Moral damage) በአንድ ሰው ድርጊት ምክንያት ለደረሰ የስሜትና የመንፈስ ጉዳት በፍርድ ቤቶች የሚወሰን የካሳ ዓይነት ነው፡፡ የህሊና ጉዳት በተጎጂው ላይ የደረሰውን የስሜት መጎዳት፣ የሥነ-ልቦና ጉዳት፣ ሐዘን፣ ሀፍረት፣ ውርደት፣ አእምሮአዊ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ መጥፎ ስም፣ የቆሰሉ ስሜቶች፣ የሞራል ድንጋጤ፣ ማህበራዊ ውርደት፣ በአካላዊ ስቃይ ምክንያት የተከሰተ የሞራል ጉዳት እና ተመሳሳይ ጉዳቶች ያካትታል። ከፍትሐብሔር ግንኙነት በተጨማሪ በወንጀል ጉዳይ ተጎጂው በተከሳሹ የወንጀል ድርጊት ምክንያት የደረሰበትን የሞራል ስቃይ ለመካስ ያገለግላል።

የህሊና ጉዳት ካሳ ፅንሰ-ሀሳብ በባህሪው ተጎጂው የደረሰበት ጉዳት ለማካካስ የሚሰላ ነው፡፡ እንዲሁም ተጎጂው በገንዘብ ረገድ ለደረሰበት ጉዳት ሳይሆን በህሊናው ላይ ለደረሰበት ጉዳት የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡ ስለሆነም የሞራል ጉዳት ወይም የህሊና ጉዳት ካሳ ቁሳዊ ላልሆኑ ጉዳቶች እንደ ማከሚያ የተሰጡ የጉዳት ክፍያዎች ናቸው፡፡

የህሊና ጉዳት ካሳ የሚያስከፍሉ ጉዳቶች በፍትሐብሔር ህግ

የህሊና ጉዳት ካሳ በመሰረቱ ለደረሰው ጉዳት ካሣ ለመክፈል ተመዛዛኝ በሆነ አድራጎት ሊፈፀም በሚቻልበት ጊዜ ሁሉ ጥፋተኛው በደሉ ለሚያስከትለው የሕሊና ጉዳት ካሳን መክፈል እንደሚገባ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2105(1) ስር ተደንጓል፡፡
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2105(2) የህሊና ጉዳት በሕጉ በግልፅ ካልተመለከተ በቀር የገንዘብ ካሳ የማያስከፍል መሆኑ ተቀምጧል። በሌሎች ህጎች ስለ ሞራል ካሳ የተደነገጉ ድንጋጌዎች እንዳሉ ሆነው በፍትሐብሔር ሕጉ ከውል ውጪ ስለሚደርስ ሃላፊነት ሥር የገንዘብ ካሳ የሚያስገኙ የህሊና ጉዳት ዓይነቶች በፍትሐ ብሔር ሕጉ ከቁጥር 2106 እስከ ቁጥር 2115 ድረስ ያሉት ብቻ ናቸው።

በፍትሐብሄር ህጉ የህሊና ጉዳት ካሳ የሚያስከፍሉ ጥፋቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

👉 ታስቦ የተደረገ ጥፋት (በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2106)፡- በከሳሹ ላይ ታስቦ የህሊና ጉዳት በሚደርስበት ጊዜ ዳኞች በዚሁ በደል ካሳ ስም ተከሳሹ ለከሳሹ በርትዕ ካሳ እንዲከፍል ወይም ከሳሹ ላመለከተው በጎ አድራጎት ድርጅት እንዲከፈል ለመፍረድ ይችላሉ።
👉 በተበዳዩ ሰውነት ላይ ስለሚደርስ ጉዳት (በፍ/ሕ/ቁ 2107)፡- ተከሳሹ በከሳሹ ላይ አስቀያሚ ወይም የሚያስጠላ መጥፎ መንካት በሚያደርግበት ወቅት ለተበዳይ ካሳ ይከፈለዋል።
👉ያለአግባብ ሰውን በመያዝና በማገድ የሚደርስ ጥፋት (በፍ/ሕ/ቁ 2108)፡- ተከሳሹ ህግን ተቃራኒ በሆነ አኳኋን የከሳሹን ነፃነት አግዶ በተገኘ ጊዜ የሚከፈል የህሊና ጉዳት ካሳ ነው፡፡
👉በስም ማጥፋት ስለሚደርስ ጉዳት (በፍ/ሕ/ቁ 2109)፡- ከሳሹ ተሰድቦ ወይም ስሙ ጠፍቶ ሲገኝ
👉ከሳሹ በወንጀል ህግ የሚያስቀጣ ወንጀል ሰርቷል በማለት ስሙን በማጠፋት የበደለው እንደሆነ፣
👉 የስም ማጥፋት ሥራዎች ከሳሹን በሞያ ሥራ ችሎታ የሌለው ወይም እውነተኛነት የሌለው መሆኑን ለማሳመን የተደረገ እንሆነ፣
👉 ነጋዴ ሆኖ ዕዳውን ለመክፈል አይችልም በማለት አስመስሎ ለማሳመን የሆነ እንደሆነ፣
👉 ተላላፊ በሽታ አድሮበታል በማለት ለማሳመን የሚጥር እንደሆነ፣
👉አስነዋሪ የሆነ ጠባይ አለው በማለት አስመስሎ ለማሳመን የሚጥር እንደሆነ የህሊና ጉዳት ካሳ እንዲከፈለው ይሆናል።
👉 የባልና ሚስትን መብት በመድፈር የሚደርስ ጥፋት (በፍ/ሕ/ቁ 2110)፡- ተከሳሹ የባልነት ወይም የሚስትነትን መብቶች ነክቶ የተገኘ እንደሆነ የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡
👉 ልጅን ነጥቆ በመውሰድ የሚደርስ ጥፋት (በፍ/ሕ/ቁ 2111)፡- የልጁ ጠባቂነት የከሳሹ ሆኖ ተከሳሹ ልጁን ነጥቆ በመውሰዱ ጥፋተኛ ሆኖ በወንጀል በሚቀጣበት ወቅት የሚከፈል ክፍያ ነው።
👉 ንብረቶችን በመድፈር የሚደርስ ጥፋት (በፍ/ሕ/ቁ 2112)፡- ከሳሹ እንዳይደርስበት በግልፅ ያስታወቀውን በመቃወም ተከሳሹ በደንብ በእጁ ወይም በይዞታው የሚገኘውን ንብረት የወሰደበት እንደሆነ ወይም በርስቱና በቤቱ የገባበት እንደሆነ በከሳሹ ላይ ስለ ደረሰው ጉዳት ለዚህ በደል ካሳ ሊወሰን ይችላል።
👉 በአካል ጉዳት ወይም በሞት የሚደርስ ጉዳት(በፍ/ሕ/ቁ 2113)፡- አካሉ በመጉደሉ ለተበደለው ሰው ወይም ሰውየው የሞተ እንደሆነ ለዘመዱ የጉዳት ካሳ በአስተያየት ተገቢ ኪሳራ ዳኞች ሊቆርጡ ይችላሉ፡፡
👉የንፁህ ህሊናን ክብር በመድፈር የሚደርስ ጉዳት (በፍ/ሕ/ቁ 2114)፡- ማንኛውም ሰው በመድፈር ሥራ ወይም ለክብረ ንፅህና ተቃራኒ በሆነ ተግባር በወንጀል የተቀጣ እንደሆነ ዳኞቹ ለተደፈረችው ሴት በህሊና በደል ካሳ ስም ተከሳሹ የሚሰጠውን በርትዕ የሚገባ ካሳ ሊቆርጡ ይችላሉ። እንዲሁም ለሴቲቱ ባል ወይም ቤተ ዘመዶች ካሳ ሊቆረጥ ይችላል።
👉 በሚስት ላይ ስለሚደርስ ጉዳት (በፍ/ሕ/ቁ 2115)፡- ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው ሚስት ላይ የአካል ጉዳት በማድረሱ በትዳር በኩል ለባሏ የምትሰጠው ጥቅም ወይም ደስታ እንዲቀንስ ያደረገ እንደሆነ ስለበደል ካሳ ዳኞች በበዳዩ ላይ ለባለቤቷ በርትዕ ተገቢ የሆነ ኪሳራ ሊቆርጡለት ይችላሉ፡፡ በዚህ ምክንያት በሚስት ላይ ለደረሰው ጉዳት ባል የሚያቀርበው ክስ ሚስቱ ለደረሰባት ጉዳት ስለካሳ ጥቅም ከምታቀርበው ክስ ተጨማሪና የተለየ ነው፡፡

የህሊና ጉዳት ካሳ ክፍያ መጠን

በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2116 ስር እንደተደነገገው የካሳ ልክ ምን ያህል መሆኑን በርትዕ በአስተያየት ለመወሰንና የቤተ ዘመዱ እንደራሴ ሆኖ ለመነጋገር የሚችል ማን እንደሆነ ለማወቅ ዳኞች የአገር ልማድን መሰረት በማድረግ የሚወስኑ ሲሆን የጉዳት ካሳውም በማናቸውም ምክንያት
ከ1000 የኢትዮጵያ ብር

የበለጠ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ የገንዘብ መጠን ሕጉ በወጣበት ዘመን ከፍተኛ ነው ሊባል ቢችልም በአሁኑ ጊዜ ግን በጣም አነስተኛ ነው፡፡ በመሆኑም በዛ በኋላ በወጡ ልዩ ህጎች የህሊና ጉዳት ካሳ መጠን ላይ መሻሻሎች ታይተዋል፡፡ ለምሳሌ የቤተሰብ ሕግጋት ሲሻሻሉ ሕግ አውጪው የሞራል ካሳውን መጠን በገንዘብ መጠን ሳይወስን 👉ዳኞች እንደጉዳዩ እንዲወስኑ ሥልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡
የደቡብ ክልል የቤተሰብ ሕግ ግን በባልና ሚስት መካከል ያለው የመከባበር፣ የመተጋገዝና የመተማመን ግዴታ ከተጣሰ እስከ 👉ብር 10,000 ድረስ ካሳ ዳኞች ሊወስኑ እንደሚችሉ በሕጉ መቀመጡ የተሻለ ሕግ አድርጎታል፡፡ እንዲሁም 👉በቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ ቁጥር 410/1996 አንቀፅ 34(4) መሰረት የሕሊና ጉደት ካሳ #100,000 ብር የማያንስ መሆኑ ይደነግጋል፡፡ በሌላ በኩል የመገናኛ ብዙሀን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀፅ 84(2) ለስም ማጥፋት ወንጀል የሚወሰነው የሞራል ካሳ መጠን ከብር #300,000 እንደማይበልጥ ይደነግጋል፡፡

በጠበቃባ ሕግ አማካሪ ዳንኤልን ፈቃዱ by Daniel Fikadu
ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
0920666595
👍125