አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የሰ/መዝ/188483
===/////====
~~~
★የክልል ፍርድ ቤቶች በህገ መንግስቱ የተሰጣቸው ውክልና እስካልተነሳ ድረስ በግዛት ክልላቸው የተፈጠሩ የፌደራል ጉዳዬችን አይቶ የመወሰን ስልጣን ያላቸው መሆኑን እና
★የፌደራል ፍ/ቤቶችም በክልሎች የሚፈጠሩ የፌደራል ጉዳዬችን የማየት ስልጣን አለን በሚል ከክልል ፍ/ቤቶች ወስደው የማየት ስልጣን የሌላቸው ስለመሆኑ
#Via
#henoktayelawoffice
የስንብት ክፍያ እና ካሳ እንደ ገቢ ይቆጠራሉ?

በሰ/መ/ቁ 61549 (አመልካች የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን እና ተጠሪ ወ/ሮ ብርቄሣ አብራሂም ህዳር 6 ቀን 2004 ዓ.ም. ቅጽ 13) በተሰጠ የህግ ትርጉም ካሳና የስንብት ክፍያ የመክፈል ግዴታ የተጣለበት አሠሪ ክፍያውን ከመፈጸሙ በፊት የገቢ ግብር ቀንሶ ማስቀረት ይኖርበታል፡፡ ለአመልካች አቤቱታ መንስኤ የሆነው የሰበታ ሐዋሳ ወረዳ ፍ/ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር በነበራቸው የሥራ ክርክር እንዲከፈላቸው የተወሰነላቸው የስንብት ክፍያ፣ ካሳና ሌሎች ክፍያዎች ግብር ተቀናሽ ሳይደረግ አመልካች በደመወዛቸው በጥቅሉ አስቦ እንዲከፍላቸው ትዕዛዝ በመስጠቱ ሲሆን በትዕዛዙ ቅር በመሰኘት አመልካች ለዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበው ይግባኝ ተሰርዟል፡፡ በመቀጠል አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰ/ሰ/ችሎት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በመጨረሻ አመልካች ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/ሰ/ችሎት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ ትዕዛዙና ውሳኔዎቹ ተሽረዋል፡፡

አመልካች ለሰበር አቤቱታ መሰረት ያደረገው የገቢ ግብር አዋጅ ቁ. 286/94 እና የገቢ ግብር ደንብ ቁ. 78/1994 ሲሆን ችሎቱ የገቢ ግብር አዋጁን አንቀጽ 10 በመጥቀስ እንዳብራራው ማናቸውም ሰው በመቀጠር ከሚያገኘው ገቢ ግብር የመክፈል ኃላፊነት ያለበት ሲሆን ማናቸውም ቀጣሪም በሚከፍለው እያንዳንዱ ክፍያ ግብሩን የመቀነስና ለመንግስት ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ በተጨማሪም በገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 78/1994 አንቀጽ 13 ስር የገቢ ግብር እንደማይከፈልባቸው ከተዘረዘሩት ውስጥ የስንብት ክፍያ፣ካሳ እና ለተጠሪ ይከፈሉ የተባሉት ሌሎች ክፍያዎች ግብር እንደማይከፈልባቸው አልተደነገገም፡፡ ስለሆነም ተጠሪ ከተወሰኑላት ክፍያዎች ላይ የገቢ ግብር ተቀናሽ ሊደረግ ይገባል፡፡

ከካሳ እና ስንብት ክፍያ በተጨማሪ ሌሎች ከአሠሪና ሠራተኛ ህግ የሚመነጩ ክፍያዎችም የገቢ ግብር ይከፈልባቸዋል፡፡ በሰ/መ/ቁ 101040 /አመልካች ዳሽን ባንክ አክስዮን ማህበር እና ተጠሪ እነ አቶ ተፈሪ አሳልፈው ሚያዝያ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. ቅጽ 18/ የሥራ ውል ሲቋረጥ በገንዘብ ተለውጦ በሚከፈለው የዓመት ፈቃድ ላይ እንዲሁም በሰ/መ/ቁ 65330 /አመልካች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ እነ አቶ ተክሌ ጋረደው (6 ሰዎች) ሰኔ 30 ቀን 2003 ዓ.ም. ቅጽ 11/ ለጡረታ ክፍያ የአገልግሎት ዘመን እና የዕድሜ መስፈርት የማያሟሉ የመንግስት ሠራተኞች ከሥራ ሲሰናበቱ ለመልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ እንዲውል በሚከፈላቸው ክፍያ ላይ የገቢ ግብር ተቀናሽ መደረግ እንዳለበት ተመልክቷል፡፡
#henoktayelawoffice


ሼር #Share @lawsocieties
🟩@lawsocieties
🟨@lawsocieties
🟥@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
በኮንስትራክሽን ውል ስለ ግንባታ ስራ ርክክብ/Acceptance/
======**=======
#በኮንስትራክሽን ውል ሁለት አይነት የግንባታ ስራ ርክክብ ያለ ሲሆን ይሄውም ግዚያዊ ርክክብ(provisional acceptance) እና የመጨረሻ ርክክብ(final acceptance) የሚያካትት ነው፡፡
#በዚህ ጽሁፍ በዋናነት በኮንስትራክሽን ውል ህግ እውቅና የተሰጣቸውን የርክክብ አይነቶች ምንነትና ተያያዥ ውጤታቸውን አስመልክቶ የህግ ድንጋጌዎችን እና አሁን ላይ በመንግስት ተቋማት እየተሰራበት ያለውን የፒፒኤ 2011 ጀኔራል ኮንዲሽን ድንጋጌዎችን ባካተተ ሁኔታ ለማብራራት ተሞክሯል፡፡
**
#ግዚያዊ ርክክብ/Provisional Acceptance/
#ግዜአዊ ርክክብ በተለይ በኮንስትራክሽን ውል የተመለከቱ የግንባታ ስራዎች ተከናውነው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ማለትም አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በስራው ላይ የሚደረግ የምርመራ ማረጋገጫ ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3274(1) ይደነግጋል፡፡ ይሄውም አሰሪው በትክክል የተገነባውን ግንባታ በእጁ አግብቶ መያዙን ጭምር ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ ጊዜአዊ ርክክብ በዋናነት የተሰራውን የግንባታ ስራ አሰሪው መብቱን ጠብቆ በመጀመሪያ የሚረከብበት ሂደት ነው ማለት ነው፡፡በስራው ላይ ምርመራ መደረጉንም የሚያረጋግጥ ነው፡፡
#ፒፒኤ 2011 ክሎስ 84.1 ላይ የስራ ምርመራ/verification and test/ በመሀንዲሱ ተቋራጭ ባለበት ሊደረግ እንደሚገባ በመርህ ደረጃ ተቀምጧል፡፡ሆኖም ግን ተቋራጩ ምርመራው ከሚካሄድበት እለት ከ30 ቀን በፊት በተገቢ ሁኔታ እንዲያውቀው ተደርጐ በምርመራው እለት ያልተገኘ እንደሆነ የስራ ምርመራው ተቋራጩ በሌለበት ሊካሄድ እንደሚችል ይፈቅዳል፡፡
#እንግዲህ መሀንዲሱ ስራውን ከመረመረ በኋላ ያላመነበትን የስራ ክፍል ፈርሶ እንደገና እንዲሰራ ወይም እንዲጠገን ተደርጐ የጥራት ደረጃውን ባሟላ ሁኔታ እንዲከናወን ለማዘዝ እንደሚችል ፒፒኤ ክሎስ 85 ይፈቅድለታል፡፡
#በዚህም መሰረት ግንባታው የስራ ምርመራውን ካለፈ አሰሪው ግንባታውን የሚረከበው ይሆናል ማለት ነው፡፡ስለዚሁም የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት ለተቋራጩ የሚሰጠው ይሆናል፡፡በመሰረቱ ተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንዲሰጠው መጠየቅ ያለበት ስራው ሊጠናቀቅ ይችላል ብሎ ከሚያስብበት ከ15 ቀን በፊት መሆን ይኖርበታል፡፡ከዚያም መሀንዲሱ ጥያቄው በደረሰው በ30 ቀን ውስጥ የስራ ምርመራውን አጠናቆ ሰርተፍኬቱን መስጠት ወይም ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡መሀንዲሱ ሰርተፍኬቱን ሳይሰጥ ወይም ጥያቄውን ውድቅ ሳያደርግ 30 ቀኑ ያለፈ እንደሆነ ለተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንደተሰጠው ግምት እንደሚወሰድ ፒፒኤ ክሎስ 87 ያስቀምጣል፡፡
#ሌላው ተቋራጩ በስራው ላይ ያደረገው መሻሻል/መለወጥ ቢኖር እንኳ በዝምታ ግዜአዊ ርክክብ ከተደረገ መሻሻሉ ተቀባይነት እንዳገኘ የህግ ግምት እንደሚያስወስድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(2) ይደነግጋል፡፡እዚህ ላይ ተቋራጩ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት የመስራት ግዴታ ያለበት መሆኑ ይታዎቅ፡፡ ስለዚህ የህግ ግምቱ እሳቤ ተቋራጩ ከዲዛይኑ በመውጣት አሻሽሎ የሰራው ስራ ኖሮ በግዜአዊ ርክክብ ወቅት በዝምታ አሰሪው ካለፈው እንደተቀበለው ይቆጠራል ነው፡፡
#እንዲሁም ግዜአዊ ርክክብ መደረጉ የመድህንነት ጊዜው(warranty period) መጀመሩን እንደሚያመለክት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(3) ይደነግጋል፡፡
**
#የመድህንነት ጊዜ(warranty period/Defects Liability period)
#የመድህንነት ጊዜ(warranty period) የሚባለው ከጊዜአዊ ርክክብ እስከ መጨረሻ ርክክብ ያለው ጊዜ ሲሆን አሰሪው ግንባታው በተቋራጩ በደህና ሁኔታ ስለመሰራቱ ለመመርመርና ለማረጋገጥ የሚያስችለው ጊዜ ነው፡፡የጊዜው ርዝማኔም በውላቸው ላይ የሚወሰን ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3277 ይደነግጋል፡፡ ሆኖም በውሉ ላይ የመድህንነት ጊዜው ርዝማኔ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ከጊዜአዊ ርክክብ ቀን ጀምሮ 365 ቀን ስለመሆኑ የፒፒኤ ክሎስ 88.7 ያስቀምጣል፡፡
#ተቋራጩ በዚሁ በመድህንነት ጊዜ በተለይ የተበላሹ ስራዎችን እንዲያድሳቸው በአሰሪው በታዘዘ ጊዜ የማስተካከል ግዴታ እንዳለበት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3278 ይደነግጋል፡፡ ለዚህም ለጥገና ወጭ ሲባል ከተቋራጩ ክፍያ ላይ ሪቴንሽን ገንዘብ(retention money or bond) 5% እየተቀነሰ በአሰሪው ይያዛል፡፡
#በመድህንነት ጊዜ ውስጥ የተለዩ ብልሽት ያለባቸው ስራዎችን እንዲያስተካክል ተቋራጩ ተጠይቆ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያላስተካከለ እንደሆነ አሰሪው የማስተካከያ ስራውን በተቋራጩ ወጭ በራሱ ወይም ሌላ ቀጥሮ ሊያሰራው ወይም ውሉን ሊያቋርጥ ስለመቻሉ ፒፒኤ ክሎስ 88.3 ለአሰሪው መብት ይሰጠዋል፡፡
**
#ከፊል ርክክብ/Partial Acceptance/
-በፒፒኤ ክሎስ 86 ላይ የግንባታ ስራው በከፊል እርክክብ የሚደረግበትንም አማራጭ ያስቀምጣል፡፡ይህ ማለት የተወሰነውን የስራ ክፍል(part of the work) ከአጠቃላይ ውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ በውል ላይ ከተቀመጠ ተቋራጩ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከአጠቃላይ የውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ ይገደዳል ማለት ነው፡፡በዚህም በአንድ ውል ውስጥ በተለያየ ጊዜ ጊዜአዊ ርክክብ ሊደረግ የሚችልበትን ሁኔታ ይፈጥራል ማለት ነው፡፡
**
#የመረሻ ርክክብ/Final Acceptance/
#የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/ በተለይ የመድህንነት ጊዜ ካለቀ በኋላ እና ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደህና ሁኔታ የፈጸመ መሆኑን አሰሪው ሲያረጋግጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በእጁ የሚያደርግበት(definitively appropriate) ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279 ይደነግጋል፡፡
#የመጨረሻ ርክክብ አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት በአስገዳጅ ሁኔታ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279(2) ላይ ተደንግጓል፡፡ሆኖም ጊዜአዊ ርክክብ/ Provisional Acceptance/ በሚመለከት ግን በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት የሚያስገድድ ግልጽ ህግ የለም፡፡ስለዚህ ስራው ተጠናቆ አሰሪው ግንባታውን በእጁ ካስገባ ጊዜአዊ ርክክብ መደረጉን የሚያስገነዝብ ይሆናል ማለት ነው፡፡በእርግጥ በጽሁፍ መደረጉ ይመከራል፡፡
#በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3282 ላይ እንደተቀመጠው ከመጨረሻ ርክክብ በኋላ ተቋራጩ እስከ 10 አመት ድረስ ስለስራው አሰራር ጉድለት ተቋራጩ ሀላፊነት አለበት፣መድህን ሆኖ ይቀጥላል፡፡በመጨረሻ ርክክብ ወቅት የሚታዩ ለነበሩ ጉድለቶች(apparent defect) ግን ተቋራጩ ሀላፊነት የለበትም፡፡ሀላፊነቱ የሚመለከተው ግንባታው በውሉ የተመለከተውን የታለመለትን ጥቅም እንዳይሰጥ የሚያደርጉ ወይም አጠቃቀሙን በጣም ውድ የሚያደርጉና አክሳሪ የሚያደርጉ ጉድለቶችን ነው፡፡
#henoktayelawoffice
ስጦታ ፈራሽ የሚሆንባቸው ምክንያቶች

የስጦታ ምንነት

በአጭሩ ለማስቀመጥ ስጦታ ማለት ሰጪው ተቀባይ ለተባለ ሌላ ሰው ከንብረቶቹ አንዱን ያለ ዋጋ የሚለቅበት ወይም ግዴታ የሚገባበት ውል ነው።
በመሆኑም ስጦታ በራሱ ውል ነው ማለት ነው።

የስጦታ ልዩ ባህሪያት

በመርህ ደረጃ ስጦት ግላዊ ተግባር ነው ይህም ማለት ስጪው እራሱ የሚያድረገው ተግባር ነው ማለት ነው። ስጦታ የሚደረገው በወኪሉ ሲሆን ደግሞ የሚሰጠው ንብረት አይነት እና ለማን እንደሚሰጥ በግልጽ ሊመለከት ይገባል። ስጦታ የሚደረገው የሰጪው ንብረት በሆነው ለይ ብቻ ነው።ስጦታ አድርጋለሁ ብሎ የተስፋ ቃል መስጠት በህጉ መሠረት ግዴታን አያስከትልም ከዚህም በተጨማሪ ስጦታ ተቀባዩ ስጦታውን እቀበላለሁ በሚል ሀሳቡን
መግለፅ ይኖርበታል።ስጦታ እንዲቀነስ ወይም እንዲሻር የሚቀርበው ጥያቄ ስጦታው ከተደረገበት ቀን አንስቶ እስከ ሁለት አመት ለዳኞች ካልቀረበ በቀር ዋጋ አይኖረውም።

የስጦታ ሥርዓት ፎርም*

ስጦታ በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ ወይም በሚይንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ ሊደረግ ይችላል።

*1)በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ *

በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በፍትሐብሔር ህግ አንቀጽ 881 ላይ በተደነገገው መሠረት በግልጽ ኑዛዜ ሥርዓት ፎርም መሠረት የሚፈጸም መሆኑን ህጉ ያስረዳል።በሌላ በኩል በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ለይ የሚደረገው ስጦታ በፍ/ህግ አንቀጽ 1723 መሠረት በጽሁፍ ሆኖ በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መሆን አለበት።

*2) በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ለይ የሚደረግ ስጦታ*

በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በሁለት አይነት መልኩ ሊደረግ ይችላል ይህም እጅ በእጅ በሚደረግ ማስተላለፍ ብቻ ወይም ለማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ በሚደረገው ፎርም ሊሰጥ ይችላሉ።

ስጦታ እንደማድረግ የማይቆጠርባቸው ሁኔታዎች ያሉ ሲሆን እነኚህም ሁኔታዎች።

1)ያለ ዋጋ የሚደረግ የአገልግሎት ሥራ ወይም የራሱን እቃ ያለ ዋጋ ዝግጁ ማድረግ ስጦታ አይባልም የፍ/ህግ አንቀጽ 2430።

2)መንፈሳዊ ተግባርን ለመፈጸም የሚደረገው የገንዘብ መክፈል ስራ ስጦታ አይባልም የፍ/ህ አንቀጽ 2432።

3) አንድ ሰው ለሰጪው ወይም ለቤተሰቡ አገልግሎት በልማድ መሠረት ያደረገው የሥራ ዋጋ መክፈል ስጦታ አይባልም የፍ/ህ አንቀጽ 2433።

4)ወራሽነትን አልፈልግም ብሎ መተው ወይም ኑዛዜ የተደረገለትን ስጦታ አልቀበልም ማለት ስጦታ ነው ተብሎ አይቆጠርም የፍ/ህግ 2431።

ስጦታ ፈራሽ የሚሆንባቸው ምክንያቶች*

በሚንቀሳቀስ ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ለይ የተደረገው ስጦታ በህጉ በተጠቀሱት በተለያየ ምክንያቶ ፈራሽ ሊሆን የሚችሉባቸው ምክንያቶች ያሉ ሲሆን እነኚህም:-

1ኛ የሰጪው አዕምሮ ትክክል አለመሆን

ሰጪው ስጦታውን በሚያድርግበት ወቅት በአዕምሮ መታወክ(ህመም ምክንያት) በፍርድ የተከለከለ ሲሆን ያደረገው ስጦታ ፈራሽ ሊሆን ይችላል ።የፍ/ህ አንቀጽ 2437

2ኛ ግብረ ገብነት የሌለው ወይም ህገ ወጥ ምክንያት ያለበት ስጦታ ፈራሽ ነው። የፍ/ህ አንቀጽ 2438

3)በመንፈስ መጫን ምክንያት የተደረገውን ስጦታ ዳኞች ለመቀነስ ወይም ለመሻር ይችላሉ።የፍ/ህ አንቀጽ 2439

4ኛ በ ፍ/ህ አንቀጽ 2442 ሥር በሚፈቅደው መሠረት ስጦታው የተደረገው በስህተት ወይም በተንኮል የሆነ እንደሆነ ፈራሽ ይሆናል።

5 ስጦታ የተደረገው ክርክር ያለበት ሀብት ላይ ሲሆን ስጦታው ፈራሽ ይሆናል።
Via #lawyerhenoktaye #henoktayelawoffice

Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴

#አለሕግ #Alehig

Subscribe Now!

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/