አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#የዳኝነት_ሳይከፈል_በነፃ_ስለሚቀርብ_ክስ

ማንኛውም የፍትሐብሔር ክስ ሲከፈት በፍርድ ቤት ለሚሰጠው የዳኝነት አገልግሎት የዳኝነት እንዲከፈል ይጠበቃል፡፡ ክስ ለማቅረብ የፈለገ ወገን ለሚያገኘው የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል የገንዘብ አቅም የሌለው ከሆነ ለግዜው የዳኝነት መክፈል ባለመቻሉ ብቻ መብቶቹን እንዳያጣ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህጉ መፍትሄ አስቀምጧል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ስለሚቀርብ ክስ ምንነት እና ስለሚቀርብበት ሥነ ሥርዓት እንመለከታለን፡፡
የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ የሚቀርብ ክስ ምንነት
በ1958 ዓ.ም በወጣው የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 467 መሰረት የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ የሚቀርብ ክስ ማለት ገንዘብ የሌለው እና ገንዘብ ለማግኘት የማይችል ማንኛውም ደሀ ሰው የዳኝነት ሳይከፍል በነፃ ፋይል ክፍቶ ክስ የሚያቀርብበት ሂደት ነው፡፡
የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ የሚቀርብ ክስ ሥነ-ሥርዓት
በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 467 መሰረት ዳኝነት መክፈል የማይችል ደሀ ሰው የዳኝነት ገንዘብ በሙሉ ወይም በከፊል ሳይከፍል የነፃ ፋይል ማስከፈት የሚችለው ከክሱ አቤቱታ ጋር የነፃ ዳኝነት ማመልከቻ በቃለ መሀላ አስግፎ ዋናውን ጉዳይ ለሚያየው ፍርድ ቤት ሲያቀርብ ነው (ቁ.468)፡፡ ፍርድ ቤቱም ማመልከቻውን ተመልክቶ ስለአመልካች የሀብት ሁኔታ እና ስለማመልከቻው ተገቢነት አስፈላጊ ማስረጃ ለማግኘት አመልካችን ወይም ወኪሉን አስቀርቦ ሊጠይቀው ይችላል፡፡
ፍርድ ቤቱ የቀረበው ማመልከቻ ሲመረምር የሚነቀፍበት ምክንያት ካላገኘ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 471 መሰረት አመልካች ድሀ ስለመሆኑ እንዲያስረዳ እና በአንፃሩም አመልካቹ ሀብት አለው የሚሉ ሰዎች እንዳሉ እንዲያስረዱ ቀጠሮ በመስጠት ከቀጠሮ አስር ቀን በፊት ለባለጋራው ማስታወቂ እንዲደርሰው ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ማስረጃው ተሰምቶ ከተመረመረ በኋላ ፍርድ ቤቱ ማመልከቻውን ሊቀበል ወይም ውድቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ማመልከቻው ተቀባይነት ካገኘ አመልካቹ ዳኝነት ሳይከፍል ያቀረበው ክስ ዳኝነት እንደተከፈለበት እንደማንኛውም ክስ ተቆጥሮ በመደበኛ ሥነ ሥርአት ይመራል፡፡
ይህም ውሳኔ በነፃ ዳኝነት የቀረበው ክስ ቀጥሎ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ የሚያገለግል እና ማስረጃነቱ የሚቀጥል ሲሆን ይህ ማስረጃ ግን ለሌሎች ክርክሮች እንደ ማስረጃ ሊሆን አይችልም፡፡ በይግባኝ ደረጃ የሚሄድ ክርክር አመልካች ይግባኝ ባይ ከሆነ በነፃ ይግባኝ መዝገብ እንደ አዲስ ይከፈትልኝ እስካላለ ድረስ በነፃ እንዲከራከር በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው የድህነት ማስረጃ አያገለግለውም፡፡ ነገር ግን በይግባኝ ክርክሩ መልስ ሰጪ ከሆነ የድህነት ማስረጃው ያገለግለዋል (ቁ.474)፡፡
በሌላ በኩል ዳኝነት ሳይከፈል በነፃ እንዲታይ የሚቀርብ ማመልከቻ ተቀባይነት ላያገኝ ይችላል፡፡ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 470 መሰረት ማመልከቻው ተቀባይነትን ላያገኝ የሚችለው፡-
 አመልካቹ ድሀ አለመሆኑ ከተረጋገጠ፣
 በነፃ ለመክሰስ ያቀረበው ነገር የማያስከስስ የሆነ እንደሆነ፣
 ክስ ከማቅረቡ ከሁለት ወር በፊት የነበረውን ንብረት ለሌላ ሰው አስተላልፎ እንደሆነ ወይም በማጭበርበር መንገድ ንብረቱን አዛውሮ ከሆነ ወይም ዳኝነት ከመክፈል ለመዳን ዘዴ ፈጥሮ ከሆነ፣
 ክርክር በሚያቀርብበት ንብረት ወይም መብት ውስጥ ሌላ ሶስተኛ ሰው እንዲጠቀም ወይም ማናቸውንም መብት እንዲያገኝ ተዋውሎ ወይም ተስማምቶ እንደሆነ ነው፡፡
የዳኝነት ሳይከፍል ልከራከር የሚለው ማመልከቻ ውድቅ ከተደረገ በዚሁ ጉዳይ ድጋሚ መቅረብ የማይችል ሲሆን ክስ ማቅረብ የሚችለው የዳኝነት ክፍያ እንዲሁም የነፃ ዳኝነት እንዲፈቀድለት ባቀረበ ጊዜ ባለጋራው ለመቃወም ያወጣውን ወጪና ኪሳራ ከፍሎ እንደሆነ ከፍሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 477 መረዳት ይቻላል፡፡
በነፃ ለመከራከር የተፈቀደለት ሰው በነፃ የመከራከር መብቱን ሊያጣ የሚችልባቸው ሁኔታዎች
በፍሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 475 መሰረት የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ መከራከር ማስረጃ ዋጋ ሊያጣ የሚችል ሲሆን ይኸውም
 ክርክሩ እንዲሰማ በተቀጠረው ቀነ ቀጠሮ የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ልከራከር ባይ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ ወይም የማወክ፣ የማስቸገርና የተንኮለኛነት ጠባይ ያሳየ እንደሆነ፣
 ክርክሩ በሚቀጥልበት ጊዜ ሀብት ያለው መሆኑ የተገለፀበት እንደሆነና በነጻ ዳኝነት መጠቀም ወይም በዚህ መቀጠል የማይገባው መሆኑን ፍርድ ቤቱ የተረዳ እንደሆነ፤
 ለክርክሩ መነሻ በሆነው ሀብት ላይ ሌላ ሶስተኛ ወገን ጥቅም እንዲያገኝ ስምምነት አድርጎ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡
ሀብት ያለው መሆኑ ተገልፆበት ወይም ለክርክሩ መነሻ በሆነው ሀብት ላይ ሌላ ሶስተኛ ወገን ጥቅም እንዲያገኝ ስምምነት አድርጎ በመገኘቱ በነፃ መከራከር መብቱ የተሰረዘበት ሰው ተገቢውን የዳኝነትና ማናቸውንም ለፍርድ ቤት የሚከፈለውን ገንዘብ እንዲከፍል ይታዘዛል፡፡
በነፃ እንዲከራከር የተፈቀደለት ድሀ በክርክሩ የመርታት ወይም ሀብት የማግኘት ውጤት
በነፃ እንዲከራከር የተፈቀደለት ሰው የዳኝነት ሳይከፍል የሚከራከርበትን ጉዳይ ራሱ በፍርድ አፈፃፀም የረታ እንደሆነ ፍርድ አስፈፃሚው በፍሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 476 መሰረት ለመንግስት የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብና ማናቸውንም ወጪ ከረታው ሀብት ላይ ተቀናሽ በማድረግ ገቢ ካደረገ በኋላ ቀሪው ሀብት ረቺው እንደ ፍርዱ እንዲረከብ ማድረግ እንዳለበት ተደንግጎአል፡፡ ሌሎች በነፃ ለመዳኘት የሚቀርቡ ማመልከቻዎችና ይህንን ለመመርመር የሚያስፈልጉ ማናቸውም ወጭዎች ሁሉ ለዳኝነት ከሚከፈል ገንዘብ ጋር የሚታሰቡ እንደሆኑ ከፍሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 479 መረዳት ይቻላል፡፡
በተጨማሪም የዳኝነት ሳይከፍል የሚከራከር ወገን ማስረጃው በተሰጠው በአስር አመት ግዜ ውስጥ ወይም ክርክሩ በሚቀጥልበት ጊዜ ሀብት ካገኘ ይህንኑ አስታውቆ ዳኝነቱን መክፈል እንዳለበት በፍሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 478 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ገንዘብ አግኝቶ እያለ ይህንን የማያስታወቅ ወይም የመክፈል ግዴታውን ባይወጣ በአታላይነት ወንጀል እንደሚጠየቅ በድንጋጌው ተመልክቷል፡፡
ዳኝነት ሳይከፈልበት በነፃ የሚቀርብ ክስ የዳኝነት ለመክፈል አቅም ያጡ ሰዎች ገንዘብ በማጣት መብቶቻቸውን እንዳያጡ ለማድረግ በህጉ የተቀመጠ መፍትሄ ሲሆን በዚሁ መልኩ የተከራከረ ሰው ሀብት ሲያገኝ በአግባቡ አስታውቆ የዳኝነት መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ስለሆነም ገንዘብ ሲያገኙ መክፍል እንደተጠበቀ ሆኖ የዳኝነት ለመክፈል አቅም የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ገንዘብ ማጣታቸው ዳኝነት እንዳያገኙ እንደማይከለክላቸው አውቀው ተገቢውን ማስረጃ በማቅረብ በህጉ በተቀመጠው መልኩ መስተናገድ ይችላሉ፡፡
መረጃው፡- ከፍትሕ ሚኒስቴር የተገኘ ነው!
Federal Justice and Law Institute

2016 VOL -3 BY DANIEL FIKADU LAW OFFICE.pdf
13.8 MB
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በ2016 ዓ.ም. የተሰጡ ያልታተሙ አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች
የ2016 3ተኛ ስብስብ ቅጽ - 3 በዳንኤል ፍቃዱ /ጠበቃ/
https://t.me/lawsocieties
የቀረጥና ታክስ ነጻ መብት አሰጣጥን በተመለከተ

በጉምሩክ አዋጅ 1160/2011 መሰረት

1.  በገቢና ወጪ እቃዎች ላይ የቀረጥ ነጻ መብት የሚሰጠው የገንዘብ ሚኒስቴር ብቻ ይሆናል
2.  ከዲፕሎማሲ ግንኙነት ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ በፈረመችባቸው እና ተቀብላ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት የሚሰጡ የቀረጥና ታክስ ነጻ መብቶች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየተረጋገጠ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡  
3.  የቀረጥና ታክስ ነጻ መብት እንዲፈቅዱ በሕግ ለተለየዩ የመንግስት አካላት የተሰጠው ስልጣን ለገንዘብ ሚኒስቴር ተላልፏል፡፡
4.  ማንኛውም የመንግስት አካል በሚዋዋለው የፕሮጀክት ስምምነት መሰረት የሚፈቀድ የቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ተፈጻሚ የሚሆነው በገንዘብ ሚኒስቴር ሲጸድቅ ብቻ ይሆናል፡፡
5.  የጉምሩክ ኮሚሽን ከቀረጥና ታክስ ነጻ ሆነው ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ወይም ከአገር የሚወጡ እቃዎች ለታለመላቸው ዓላማ ስለመዋላቸው መረጃ ይይዛል፤ ይከታተላል፤ እርምጃ ይወስዳል፡፡
6.  የቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ስለሚፈቀድበት ሁኔታ እና ስለአፈጻጸሙ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡
ገቢዎች ቢሮ
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
#በብር_ኖት_ወይም_በገንዘቦች_ላይ_የሚፈፀሙ_ወንጀሎች_ምንነት
ገንዘብ በአንድ ሀገር ውስጥ ህጋዊ መገበያያ ሰነድ ነው፡፡ ሀገራት የገንዘብ ኖታቸውን የመወሰን ሉአላዊ ስልጣን ያላቸው በመሆኑ አገራችንን ጨምሮ ሀገራት የመገበያያ ገንዘባቸውን ይወስናሉ፡፡ በሀገራችን ብር ህጋዊ ገንዘብ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ ስለሀገራችን ህጋዊ ገንዘብ እና በገንዘብ ላይ ስለሚፈፀሙ ወንጀሎች እንመለከታለን፡፡
ህጋዊ የገንዘብ ኖት
ህጋዊ የገንዘብ ኖትን በተመለከተ በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀጽ 17(1) መሰረት የኢትዮጵያ ህጋዊ የገንዘብ መደብ ብር እንደሆነ እና ይኸውም የሀገሪቱ ህጋዊ ገንዘብ እንደሆነ ድንግጎ ይገኛል፡፡ የዚህ ህጋዊ መገበያያ ኖት ስም በአገር አቀፍ ደረጃ “ብር” ተብሎ የተሰየመ ሲሆን በአለምአቀፍ ደረጃ ዒቲቢ(ETB) ተብሎ በዚሁ አዋጅ ተሰይሟል፡፡ ህጉ ከብር ውጪ ሳንቲሞችንም እንዲሁ እውቅና ሰጥቷል፡፡                       ብሄራዊ ባንክ በተለየ ሁኔታ በፈቀደው አግባብ ካልሆነ በስተቀር በአገራችን ውስጥ የሚደረግ ማናቸውም የገንዘብ ስምምነቶች እና ውሎች በብር እንደተፈጸሙ ይቀቆጠራል፡፡ ይህ ማለት ገንዘብን በተመለከተ የሚደረግ ስምምነት በአገር ውስጥ ሲደረግ የግዴታ በብር መደረግ አለበት ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጨ በሌላ አገር ምንዛሬ ለማከናወን የግድ ብሄራዊ ባንክ ሊፈቅድ ይገባል ማለት ነው፡፡ ይህ ፍቃድም በልዩ ሁኔታ በጥብቅ መስፈርት የሚሰጥ መሆኑን ከህጉ ንባብ እና አንድምታ መረዳት ይቻላል፡፡

ነገር ግን አገራችን ተቀብላ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና በሌላ የአገራችን ህግ ከዚህ በተለየ ሁኔታ ግንኙቶች በሌላ የገንዘብ ኖት እንዲደረጉ በግልጽ በተደነገገ ጊዜ ገንዘብ ነክ ውሎች ወይም ግንኘነቶች በአለም አቀፍ ህጉ ወይም በግልፅ በደነገገው ህግ ወይም ብሄራዊ ባንክ ባዘዘው መሰረት በሚፈቀድ የገንዘብ ኖት ሊመዘገብ ይችላል፡፡                                                          ህጋዊ ገንዘብን የመወሰን እና የማሳተም ስልጣን
በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገመንግስት አንቀጽ 51 ንኡስ አንቀጽ 7 መሰረት ብሄራዊ ባንክን የማስተዳደር፣ ገንዘብ ማተም፣ መበደር እና የውጭ ምንዛሬን መቆጣጠር የፌደራል መንግስት ስልጣን እና ሀላፊነት እንደሆነ ተደንጓል፡፡ በፌደራል መንግስት ደረጃ ስልጣን እና አወቃቀር መሰረት እነዚህን ብሮች እና ሳንቲሞች የመቅረጽ፣ የማተም፣ የማስቀረጽ፣ የማሳተም፣ የማሰራጨት፣ የማስወገድ እና እንዲወገዱ የማድረግ ብቸኛ ስልጣን ያለው ብሄራዊ ባንክ እንደሆን በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 መረዳት ይቻላል፡፡ በእነዚህ ህጋዊ ገንዘቦች ላይ የሚጻፈውን ፅሁፍ፣ የኖቶቹ ስፋት፣ ቅርጽ እና መደባቸው እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳየች በብሄራዊ ባንክ እንደሚወሰን የአዋጁ አንቀጽ 18 ያመለክታል፡፡
የወንጀል ተጠያቂነት የሚስከትሉ የወንጀሎች ድርጊቶች
ህጋዊ የገንዘብ ኖቶችን በተመለከተ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ ከአንቀጽ 356 ጀምሮ እስከ አንቀጽ 362 አስቀጪ የሆኑ የወንጀል ድርጊቶች እና የሚያስቀጠቱን የቅጣት መጠን ደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚሁም መሰረት በህጉ አንቀጽ 356 መሰረት ህጋዊ መገበያያ የሆኑትን ገንዘቦች ያለ ፍቃድ መስራት ወይም አስመስሎ መስራት ከ5 አመት በማያንስ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ የወንጀል ድርጊት ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በአንቀጽ 357 መሰረት ህጋዊ ገንዘቦችን ከትክክለኛ ዋጋቸው በላይ እንዲዘዋወሩ ለማድረግ በማሰሰብ መልካቸውን መለወጥ፣ እውነተኛ መልካቸው ላይ ሌላ ነገርን መጨመር፣ ቀለማቸውን መለወጥ ወይም በሌላ ማናቸውም አይነት ዘዴን በመጠቀም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ወደሀሰተኛነት መለወጥ ከ15 አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአንቀጽ 358 መሰረት በኬሚካል፣ በፊዚካል፣ መካኒካል ወይም ማናቸውንም ዘዴ ተጠቅሞ ህጋዊ የሆኑትን ገንዘቦች ዋጋቸውን ዝቅ እንዲል ማድረግ ከ10 አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡ ይህ ወንጀል በአገራች ውስጥም ሆነ በውጪ አገር ቢፈፀም የሚያስቀጣ ነው፡፡
ወደ አገር ከማስገባት ጋር ተያይዞ ሀሰተኛ የሆኑ ወይም ዋጋቸው ዝቅ እንዲል የተደረጉ ገንዘቦችን እውነተኛ እንደሆኑ ወይም ሙሉ ዋጋቸውን እንደያዙ አስመስሎ ራሱ እንዲገበያይባቸው ወይም እንዲዘዋወሩ ለማድረግ በማሰብ ወደ አገር ውስጥ ማስገባትም ሆነ ከአገር ማስወጣት እንዲሁም ይዞ መገኘት፣ ማስቀመጥና ማቅረብም ጭምር ከ15 አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡ እነዚህ በገንዘብ ኖቶች ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች ከተፈጸሙ ህጉ ድርጊቱ የተፈጸመው ገንዘቦቹን ለማዘዋወር እንደሆነ ግምት ይወስዳል፡፡
ማዘዋወርንም በተመለከተ በአንቀጽ 361 ላይ እንደተደነገገው ሀሰተኛ የሆኑትን ወይም ወደ ሀሰት የተለወጡትን ገንዘቦች እውነተኛ አስመስሎ ወይም ከተወሰነው በላይ ዋጋ እንዳላቸው አስመስሎ በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም ከአገር ውጭ ማዘዋወር ከ10 አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡ በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 2 እንደተገለጸው ዋጋቸው የተቀነሰውን ገንዘቦች ሙሉ ዋጋ እንደያዙ አስመስሎ ማዘዋወር ከ5 አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡ ወንጀል አድራጊው ገንዘቡን እውነተኛ ነው በሚል እምነት ወይም በትክክለኛ ዋጋው ከተቀበለ በኋላ ሀሰተኛ መሆኑን ወይም ዋጋው መቀነሱን እያወቀ ከኪሳራ ለመዳን ሀሰተኛውን ወይም ወደ ሀሰት የተለወጠውን ገንዘብ ያዘዋወረ እንደሆነ በቀላል አስራት ይቀጣል፡፡ በተጨማሪም ዋጋው የተቀነሰውን ገንዘብ ሙሉ ዋጋው እንዳለ በማስመሰል ያዘዋወረ እንደሆነ በመቀጮ የሚቀጣ ይሆናል።
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 362 መሰረት ከላይ የተገለጹት ወንጀሎች የተፈጸሙበት የገንዘብ መጠን ማነሱ ከወንጀል ተጠያቂነት ያስመልጥም፡፡ ይልቁንም ህጉ ባስቀመጠው መሰረት የገንዘቡ መጠን ትንሽ ከሆነ ቅጣቱ ቀላል እስራት ይሆናል፡፡
ገንዘቦችን አስመስሎ መስራትን ስናይ ወንጀል ፈፃሚው የማታለል ሀሳብ ባይኖረውም ገንዘቦችን በማስመሰል መስራት፣ በሚያሳሳት መልኩ አምሳያ ሆነው እንዲዘዋወሩ በማስታወቂያነት አስመስሎ ማወጣት ድርጊቱ የማሳሳት አደጋ የሚፈጥር ወይም ለመፍጠር የሚችል ከሆነ እንዲሁም እነዚህኑ መስለው የተሰሩትን ገንዘቦች ወደ አገር ማስገባት፣ ከአገር ማስወጣት፣ በአደራ በቀበል፣ ለሽያጭ ወይም በስጦታ ማቅረብ ወይም እንዲዘዋወሩ ማድረግ በህጉ አንቀጽ 369 መሰረት በመቀጮ ወይም ከሶስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ያስቀጣል፡፡ እነዚህን የሀሰት ገንዘቦች ከመስራት ጋር በተገናኘ ሌላው መታወቅ ያለበት ነገር ማንም ሰው አግባብ ያለው ባለስልጣን በግልፅ ሳያዘው ለገንዘብ ማተሚያ ወይም መስሪያነት የሚያገለግሉትን መሳሪያዎች ፎርሞች፣ ከውሮች ወረቀቶች፣ ሞዴሎች እና መሰል እቃዎች የሰራ፣ በእጁ ያስገባ፣ ወደ አገር ያስገባ ወይም ያስወጣ፣ ለሌላ ሰው ያቀረበ ወይም አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ እንዲሁም እነዚህ ገንዘቦች እንዲሰሩ የሚሰጡ ትእዛዞችን የተቀበል፣ የፈጸመ፣ ያስፈጸመ፣ ለሌላ ሰው ያስረከበ እንደሆነ በህጉ አንቀጽ 370 መሰረት በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ይቀጣል፡፡
ከላይ በአዋጅ ቁጥር 591/2000 መሰረት እንዳየነው የሀገሪቱ መገበያ ብር ነው፡፡ ይሄንን ህጋዊ ገንዘብ በቂ ምክንያት ሳይኖረው አልቀበልም ማለት ወንጀል እንደሆነ ስለ ደንብ መተላለፍ በደነገገው የወንጀል ህግ አንቀጽ 778 ደንግጎ ይገኛል፡፡ ቅጣቱም በመቀጮ ወይም በማረፊያ ቤት እስራት ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በአንቀጽ 779 መሰረት በሀሰት የተዘጋጀ ወይም ወደ ሀሰት የተለወጠ ገንዘብ በእጁ የገባ ሰው ገንዘቡ የመጣበትን ሁኔታ ካወቀ ይሄንኑ ወይም የሀሰት ገንዘቡ በእጁ የሚገኝ መሆኑን ለሚመለከተው የመንግስት አካል ሳይዘገይ ካላስታስታወቀ እና ገንዘቡን ካላስረከበ በመቀጮ ወይም ማረፊያ ቤት እስራት የሚቀጣ ይሆናል፡፡

በጥቅሉ ህጋዊ ገንዘቦችን የማዘጋጀት፣ ማሳተም እና ወደ ገበያው ማስገባት እንዲሁም አስፈላጊ ሲሆን ከገበያው ማስወጣት እና ማስወገድ የብሄራዊ ባንክ ስልጣን እና ሀላፊነት ሲሆን በእነዚሁ ህጋዊ ገንዘቦች ገጽታ፣ በገንዘቦች ላይ የሚጻፈውን ነገር፣ የኖቶቹ ስፋት፣ ቅርጽ እና መደባቸው እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳዮች መወሰን የብሄራዊ ባንክ ሀላፊነት ብቻ ነው፡፡ ይህ ታውቆ ተጠቃሚዎች እና ሰፊው ማህበረሰብ ብሄራዊ ባንኩ ባወጣው እና በየጊዜው በሚሰጣቸው መመሪያዎች መሰረት የብር ኖቶቹን በአግባቡ መያዝና መጠቀም እንዲሁም ከገንዘብ ኖቶች ጋር በተያያዘ ከሚፈፀሙ ወንጀሎች መቆጠብ ይጠበቅበታል፡፡
መረጃው፡- ከፍትሕ ሚኒስቴር የተገኘ ነው!
Federal Justice and Law Institute
ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
የመደራጀት መብት

መደራጀት በዓለም ዐቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች ማእቀፍ እንዲሁም በበርካታ ሀገራት ህግጋት ዉስጥ የተፈቀደ መብት ነዉ፡፡ ሰዎች በማህበር በመሆን የግልና የጋራ መብታቸውን ለማስከበር እና የጋራ ግዴታቸውን ለመወጣት፣ የጋራ ጥቅም ለማግኘት ወይም ጥቅሞቻቸውን ለማረጋገጥ፣ የሀገር ሰላምና የህዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ ዓላማ ሊደራጁ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ የመደራጀት መብት በልዩ ሁኔታ በጠባቡ ሊገደብ የሚችልባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ በዚህ ፅሑፍ የመደራጀት መብት በዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ሰነዶች እና በሀገራችን ያለውን የህግ ጥበቃ እንመለከታለን፡፡

የመደራጀት መብት የህግ ማዕቀፍ

ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት እንዳለው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 31 ተመላክቷል፡፡ ሀገራችን አፅድቃ የህጓ አካል ያደረገቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ (UDHR) በአንቀፅ 20 እንዲሁም የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት (ICCPR) በአንቀፅ 22 ማንኛዉም ሰው የመደራጀት ነጻነት እንዳለው ደንግገዋል፡፡ በተጨማሪም አለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች መግለጫ (UDHR) ማንኛዉም ሰው ያለፈቃዱ የማህበር ወይም የድርጅት አባል ያለመሆን መብት ጭምር ያለዉ መሆኑን ደንግጓል፡፡
በዚህም መነሻነት በሀገራችን የመደራጀት መብትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የተለያዩ ህግጋት በሥራ ላይ ውለዋል፡፡ ለአብነት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት ሠራተኞችና አሠሪዎች እንደ አግባቡ የሠራተኞች ወይም የአሠሪዎች ማኅበር ለማቋቋምና ለመደራጀት፣ የማህበር አባል ለመሆንና በማህበርም ለመሳተፍ መብት አላቸው፡፡ ይህ መብት ሰራተኞች በማህበራት በመደራጀት ከአሰሪዎች እና ጥቅማቸውን ከሚነኩ ሌሎች ድርጅቶች ጋር ደሞዝን፣ በሥራ እድገትን፣ የእረፍት ጊዜን እና ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞችን በተመለከተ ለመደራደር እና መብታቸውን ለማስከበር የሚያግዛቸው ነው፡፡
በተጨማሪም ዜጎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በሙያ ማህበራት፣ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ በብዙሀን ማህበራት፣ በድርጅቶች ህብረቶች እና መሰል ለትርፍ ባልቋቋሙ ድርጅቶች መደራጀት ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል ተደራጅተው በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ የሚፈልጉ ደግሞ በምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ሥርአት አዋጅ 1162/2011 መሰረት መደራጀት ይችላሉ፡፡

የመደራጀት መብት በህግ ክልከላ የሚደረግበት አግባብ

የመደራጀት መብት በአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ሰነዶች እንዲሁም በሀገራችን ህገ መንግስት የተደነገገ መብት ሲሆን ሳይሻራረፍ እንዲከበር የህግ ጥበቃ ተደርጎለታል፡፡ ይህ መብት ለሀገር ደህንነት፣ ለህዝብ ሰላምና ጸጥታ፣ ለህዝብ ጤና እና ሞራል እንዲሁም የሌሎችን መብትና ነፃነት ለመጠበቅ ሲባል በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ውስጥ አስፈላጊ በሆኑ በህግ በተደነገጉ ገደቦች ብቻ በጠባቡ ሊገደብ የሚችል ሲሆን ከዚህ ውጪ ምንም አይነት ገደብ ሊጣልበት እንደማይገባ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት (ICCPR) በበግልፅ አመላክቷል፡፡ በተመሳሳይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 31 መሰረት አግባብ ያለውን ህግ በመጣስ ህገወጥ ተግባራት ለመፈፀም መደራጀት የተከለከለ ስለመሆኑ ይደነግጋል፡፡
የመደረጀት መብት ዓለም ዐቀፋዊ ጥበቃ እንዲሁም በሀገራችን የህግ ጥበቃ የተደረገለት መብት በመሆኑ በህግ በልዩ ሁኔታ በግልፅ ከተደነገጉ ገደቦች ውጪ ሊገደብ አይችልም፡፡ በመሆኑም ዜጎች ይህን መብትና ግዴታቸውን አውቀው በመጠቀም ከራሳቸው አልፈው ለማህበረሰባቸው እና ለሀገር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ይጠበቃል፡፡
Source_ Federal ministry of justice
ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ስለ ይርጋ ሕጉ ምን ይላል?
****

በጊዜው ካልተጠቀምንበት መብትም የመጠቀሚያ ጊዜው ያልፍበታል። መድኃኒት፣ ምግቦች እና ሌሎች የተለያዩ ምርቶች የተመረቱበት ጊዜ እና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው የሚያበቃበት ጊዜ በማሸጊያቸው ላይ ይጻፋል።

ምርቶቹ ጊዜያቸው ካለፈ በኋላ ይወገዳሉ እንጂ ጥቅም ላይ አይውሉም። ምክንያቱም በጊዜያቸው ጥቅም ላይ ካልዋሉ ለጤና ጎጂ እና የሚፈለገውን አገልግሎት የማይሰጡ ስለሚሆኑ ነው።

በፍርድ ወይም በዳኝነት ወይም በአስተዳደር ውሳኔ መብትን የመጠየቂያ የጊዜ ገደቦችም በፍትሐ ብሔር ሕግ (በፍ/ብ/ሕግ)፣ በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ (በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ)፣ በአሠሪ እና ሠራተኛ ሕግ፣ በወንጀል ሕግ እና በሌሎችም ሕጎች ላይ ተደንግገዋል።

በዚህ ጽሑፍ መብትን ለማስከበር በፍትሐ ብሔር ጉዳዮች አልያም ከውል ወይም ከሕግ የሚመነጩ የንብረት እና የገንዘብ መብትን ለማስከበር ዳኝነት የመጠየቂያ ወይም ሌሎች ሕጋዊ ውጤት ያላቸው ድርጊቶችን የማከናወኛ የጊዜ ገደቦችን እና በጊዜ ገደቡ አለመጠቀም የሚያስከትላቸውን ውጤቶች እናያለን።

በእውነተኛ የፍርድ ቤት ሙግቶች ላይ በመጨረሻው የዳኝነት አካል የተሰጡ ይርጋን የሚመለከቱ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔዎችን እና ይርጋን የሚደነግጉትን ሕጎችም እንቃኛለን።

1. የሟች እህታቸውን ውርስ ጊዜ ያሳጣቸው ወራሾች

ሟች ወ/ሮ ያልጋ ከአቶ ተገኝ ጋር ተጋብተው ሲኖሩ በ1982 ዓ.ም ይሞታሉ። ከባላቸው ጋር በጋብቻ ያፈሩት የጋራ ሀብት እንዳለ የሚያውቁት እህት ወንድሞቻቸው በጋራ የሟች እህታችን ወራሽ ነንና የሟችን ያካፍሉን ሲሉ አቶ ተገኝ ላይ ክስ ያቀርባሉ። መቼ? ነሐሴ 7 ቀን 1995 ዓ.ም። አቶ ተገኝም ወራሾች ሟች ከሞተች ከ13 ዓመት በኋላ ክሱን በማቅረባቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000(2) እና 1845 በሕጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ክሱን ስላላቀረቡ የውርስ ድርሻ የመጠየቅ መብታቸው በይርጋ ታግዷል ሲሉ መቃወሚያ ያቀርባሉ።
የፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤትም ክሱ በይርጋ አይታገድም ብሎ የወራሾችን ድርሻ እንዲያካፍሉ አቶ ተገኝ ላይ ፈረደባቸው። ለፌ/ከ/ፍ/ቤት ያቀረቡት ይግባኝም ስላልተሳካ የይርጋ መቃወሚያዬ ውድቅ በመደረጉ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ሲሉ ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ ያቀርባሉ።

ሰበር ሰሚ ችሎትም ክሱ የቀረበው ሟች ከሞቱ ከ13 ዓመት በኋላ መሆኑን ጠቅሶ የፍትሐ ብሔር ሕግ በወራሾች መካከል የሚነሣ የውርስ ይገባኛል ክርክር በ10 ዓመት ውስጥ መቅረብ እንዳለበት ገለጸ።

የሟች ወራሾች ክስ ያቀረቡት ግን በሟች ወራሽ ላይ ሳይሆን የጋብቻ የጋራ ንብረት ተጋሪ ላይ በመሆኑ ይህን የሚመለከት የክስ ማቅረቢያ ጊዜ ገደብ የለም። በልዩ ሕግ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ በሌለ ጊዜ ውልን የሚመለከተው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የይርጋ ገደብ ተፈፃሚ ይሆናል። በመሆኑም ክሱ ሟች ከሞቱ ከ13 ዓመት በኋላ የቀረበ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች በይርጋ አይታገድም ብለው የሰጡት ውሳኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ሲል በሰ.መ.ቁ 25664 ላይ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔ ሰጥቷል።

2. ከውል የሚመነጭ መብትን የመጠየቂያው ጊዜ

የአሁኑ የመንግሥት ቤቶች ኮርፖሬሽን የቀድሞው ኪራይ ቤቶች አስተዳደር ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት በ1977 ዓ.ም ቤት ያከራየኋቸው ደንበኛ ቤቱን ካለ አከራዩ ፍቃድ ወደ ንግድ ድርጅት ቀይረው እየተጠቀሙበት ስላሉ ውሉ ይሰረዝና ቤቱን ያስረክቡኝ ሲል ክስ ያቀርባል።

የፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤትም አከራይ ቤቱ ወደ ንግድ ቤት መቀየሩን ያወቀው በ1979 ዓ.ም ሲሆን በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ ክስ ስላላቀረበ ክስ የማቅረብ መብቱ በይርጋ ታግዷል ሲል ክሱን ውድቅ አደረገው። አከራይ ይግባኝ ቢያቀርብም ስላልተሳካ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ሲል ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ አቀረበ።

ሰበር ሰሚ ችሎትም በሰ.መ.ቁ 28686 በሰጠው ውሳኔ "ውል ባለመፈጸሙ ምክንያት እንዲፈጸም በመጠየቅ ወይም በውል አለመፈጸም ምክንያት የጉዳት ኪሣራ በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ ወይም እንዲሰረዝ በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ በ10 ዓመት የጊዜገደብ ካልቀረበ በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 1845 ላይ የተመለከተ ሲሆን የይርጋው ጊዜ መቆጠር የሚጀምረውም ግዴታውን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነው ወይም ውሉ የሚሰጠው መብት ከተሠራበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ በቁጥር 1845 ላይ ተመልክቷል" ሲል ለውሳኔው መሠረት የሆነውን ሕግ አብራርቷል።

በመቀጠልም "በተያዘው ጉዳይ አከራይ በተከራይ ላይ ክስ የመሠረተው ለመኖሪያ ቤት የተከራየውን ቤት ወደ ንግድ ቤትነት የቀየረ ስለሆነና ይህም ውሉን መጣስ ስለሆነ ውሉ በፍርዱ ተሰርዞ ቤቱን እንድረከብ ይወስንልኝ በማለት እንደመሆኑ መጠን የውል መጣስ ተግባሩ በዚህ ቀን ተጀምሮ በዚህ ቀን ቆሟል ለማለት ከውሉ ባህሪይ አኳያ የማይቻል ከመሆኑም በላይ አሁንም እየቀጠለ ያለ ተግባር በመሆኑ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 መሠረት በማናቸውም ጊዜ ግዴታውን ለመጠየቅ ተገቢ ስለሚሆን ተከራይ የመኖሪያ ቤቱን ወደ ንግድ ቤት ከቀየሩበት ጊዜ ጀምሮ 10 ዓመት በመቁጠር ‘የስር ፍ/ቤት ክሱን በይርጋ ተገድቧል ማለቱ’ እና ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህን ውሳኔ በማፅናቱ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ሲል የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሮታል።

ለማሳያነት ያነሳናቸው የፍ/ብ/ሕ የይርጋ ጉዳዮች ናቸው። የአሠሪ እና ሠራተኛ ሕጉ ላይ ከቅጥር ውል ጋር እና ከሥራ ስንብት ጋር የተያያዙ መብቶችን ለመጠየቅ ገደቡ የስድስት ወር እንዲሁም አሠሪ ሠራተኛው ላይ ለሚወስደው የቅጣት እርምጃ ጥፋቱን መፈፀሙን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ እንዲሆን ተደንግግጓል።

የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ላይ ከክስ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት ጋር የተገናኙ የይርጋ ገደቦችም አሉ። እንዲሁም ይርጋን መቆጠር ሊያቋርጡ የሚችሉ ተግባራትም አግባብ ባላቸው ሕጎች ላይ ተደንግገዋል።

በመሆኑም ክስ ቀርቦብን ምላሽ ስንሰጥም ሆነ መብታችንን ለመጠየቅ ክስ ስናቀርብ በሕጉ የተቀመጠው መብትን የመጠቀሚያ የጊዜ ገደብ አለማለፉን፣ ካለፈም ይርጋን ሊያቋርጥ የሚችል ሁኔታ መከሰቱን ጉዳዩን የሚመለከቱ ሕጎችን በማጣቀስ ማጣራት አለብን። ምክንያቱም መብትን ለመጠየቅም የተቀመጠ ጊዜ አለው።
EBC
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በመስተንግዶ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሴቶች ያልተገባ አለባበስ እንዳይለብሱ የሚከለክል ረቂቅ ደንብ ወጣ
*******

በሆቴል እና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች የአለባበስ ሥነ-ሥርዓት ሊኖራቸው እንደሚገባ የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው በሆቴል እና መሰል አገልግሎቶች ሰጪ ተቋማት የሚሠሩ ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የጌጣ ጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ደንብ የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲስ ረቂቅ ደንብ አውጥቷል።

አዲሱ ረቂቅ ደንብ በሆቴል እና መሰል አገልግሎቶች ሰጪ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ባለሙያዎችን አለባበስ፣ የፀጉር አያያዝ፣ በሚታዩ የሰውነት አካላት ላይ የሚደረጉ ጌጣ ጌጦች አጠቃቀምን እና የሚጠቀሟቸው ሽቶዎች መጠንን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን ይዟል።

ኢቢሲ ሳይበር ሚዲያ ይህንኑ ደንብ በተመለከተ በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪስት አገልግሎቶች እና ብቃት ማረጋገጥ ደረጃ ምደባ ዳይሬክተሮት ዳይሬክተር ከሆኑት ወ/ሮ ገነት ይመር ጋር ቆይታ አድርጓል።

ወ/ሮ ገነት በጉዳዩ ላይ በሰጡት ሐሳብ፣ የማኅበረሰቡ አካል እንደመሆናችን በዕለት ተዕለት እቅስቃሴያችን ውስጥ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ያለውን የሠራተኞች ያልተገባ አለባበስ አስተውለናል፤ ጉዳዩ ከምልከታችን በተጨማሪ የማኅበረሰቡ ቅሬታ ጭምር ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህም በመስተንግዶ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሴቶች የተራቆተ እና ሰውነታቸውን ከልክ በላይ የሚያሳይ ልብስ መልበስ እንደየማይችሉ ደንቡ ላይ መቀመጡን ገልጸዋል።

የሚታይ የሰውነት አካል ላይ ያለ ንቅሳት በአግባቡ መሸፈን እንዳለበት እና ሊታይ እንደማይገባውም በደንቡ መቀመጡን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ሽታው ከበድ ያለ ሽቶ መቀባት፣ ‘ሂዩማን ሄር’ ማድረግ፣ ከሸሚዝ በላይ የሚደረግ የአንገት ጌጥ እንዲሁም በጆሮ ላይ የተደረደሩ ጌጦች ማድረግ የማይቻል ሲሆን፤ ወንዶች በፍፁም የጆሮ ጌጥ ማድረግ እንደማይችሉ በረቂቅ ደንቡ ተደንግጓል።

ይህ ረቂቅ ደንብ የመስተንግዶ ሥራ ላይ ብቻ እንደማያተኩር እና ለሁሉም የሥራ ዘርፍ የሚሆን የአለባበስ ሥርዓትን ያካተተ መሆኑን አንሥተዋል።

ለአብነትም በላውንደሪ ቤቶች የማያንሸራትቱ መጫሚያዎች፣ በምግብ ማብሰያ ቦታዎች ከሚፈናጠሩ እና ከሚያቃጥሉ ነገሮች ሊከላከሉ የሚችሉ አልባሳት እና ሌሎችም ከተለያዩ የሥራ ዘርፎች ጋር የሚጣጣሙ እና ለሠራተኛው ደኅንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ የሚያስገድድ ረቂቅ ደንብ መሆኑን አክለዋል።

ይህ ረቂቅ ደንብ ፀድቆ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር ቅድሚያ ለሠራተኛ ደኅንነት ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ በተጨማሪም ማንኛውም ተገልጋይ ለባለድርጅቶቹ እና ለሠራተኞቹ ክብር እንዲኖረው የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን ኢትዮጵያውያን ያላቸው ባህል፣ ሥርዓት እና እሴት እንዳይሸረሸር የሚያደርግ መሆኑም ልብ ሊባል ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል።

በአፎሚያ ክበበው
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ካሉበት ሆነው በኦላይን www.eservices.gov.et ላይ ተመዝግበው በፍትሕ ሚኒስቴር የሚሰጡ የጥብቅና ፈቃድ፣ የይቅርታና የቅሬታ ማቅረቢያ አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

ፍትሕ ሚኒስቴር
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የዳኝነት-ክፍያ-ደንብ.pdf
1.2 MB
ረቂቁ የዳኝነት ክፍያ ደንብ👆👆👆