#በብር_ኖት_ወይም_በገንዘቦች_ላይ_የሚፈፀሙ_ወንጀሎች_ምንነት
ገንዘብ በአንድ ሀገር ውስጥ ህጋዊ መገበያያ ሰነድ ነው፡፡ ሀገራት የገንዘብ ኖታቸውን የመወሰን ሉአላዊ ስልጣን ያላቸው በመሆኑ አገራችንን ጨምሮ ሀገራት የመገበያያ ገንዘባቸውን ይወስናሉ፡፡ በሀገራችን ብር ህጋዊ ገንዘብ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ ስለሀገራችን ህጋዊ ገንዘብ እና በገንዘብ ላይ ስለሚፈፀሙ ወንጀሎች እንመለከታለን፡፡
ህጋዊ የገንዘብ ኖት
ህጋዊ የገንዘብ ኖትን በተመለከተ በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀጽ 17(1) መሰረት የኢትዮጵያ ህጋዊ የገንዘብ መደብ ብር እንደሆነ እና ይኸውም የሀገሪቱ ህጋዊ ገንዘብ እንደሆነ ድንግጎ ይገኛል፡፡ የዚህ ህጋዊ መገበያያ ኖት ስም በአገር አቀፍ ደረጃ “ብር” ተብሎ የተሰየመ ሲሆን በአለምአቀፍ ደረጃ ዒቲቢ(ETB) ተብሎ በዚሁ አዋጅ ተሰይሟል፡፡ ህጉ ከብር ውጪ ሳንቲሞችንም እንዲሁ እውቅና ሰጥቷል፡፡ ብሄራዊ ባንክ በተለየ ሁኔታ በፈቀደው አግባብ ካልሆነ በስተቀር በአገራችን ውስጥ የሚደረግ ማናቸውም የገንዘብ ስምምነቶች እና ውሎች በብር እንደተፈጸሙ ይቀቆጠራል፡፡ ይህ ማለት ገንዘብን በተመለከተ የሚደረግ ስምምነት በአገር ውስጥ ሲደረግ የግዴታ በብር መደረግ አለበት ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጨ በሌላ አገር ምንዛሬ ለማከናወን የግድ ብሄራዊ ባንክ ሊፈቅድ ይገባል ማለት ነው፡፡ ይህ ፍቃድም በልዩ ሁኔታ በጥብቅ መስፈርት የሚሰጥ መሆኑን ከህጉ ንባብ እና አንድምታ መረዳት ይቻላል፡፡
ነገር ግን አገራችን ተቀብላ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና በሌላ የአገራችን ህግ ከዚህ በተለየ ሁኔታ ግንኙቶች በሌላ የገንዘብ ኖት እንዲደረጉ በግልጽ በተደነገገ ጊዜ ገንዘብ ነክ ውሎች ወይም ግንኘነቶች በአለም አቀፍ ህጉ ወይም በግልፅ በደነገገው ህግ ወይም ብሄራዊ ባንክ ባዘዘው መሰረት በሚፈቀድ የገንዘብ ኖት ሊመዘገብ ይችላል፡፡ ህጋዊ ገንዘብን የመወሰን እና የማሳተም ስልጣን
በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገመንግስት አንቀጽ 51 ንኡስ አንቀጽ 7 መሰረት ብሄራዊ ባንክን የማስተዳደር፣ ገንዘብ ማተም፣ መበደር እና የውጭ ምንዛሬን መቆጣጠር የፌደራል መንግስት ስልጣን እና ሀላፊነት እንደሆነ ተደንጓል፡፡ በፌደራል መንግስት ደረጃ ስልጣን እና አወቃቀር መሰረት እነዚህን ብሮች እና ሳንቲሞች የመቅረጽ፣ የማተም፣ የማስቀረጽ፣ የማሳተም፣ የማሰራጨት፣ የማስወገድ እና እንዲወገዱ የማድረግ ብቸኛ ስልጣን ያለው ብሄራዊ ባንክ እንደሆን በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 መረዳት ይቻላል፡፡ በእነዚህ ህጋዊ ገንዘቦች ላይ የሚጻፈውን ፅሁፍ፣ የኖቶቹ ስፋት፣ ቅርጽ እና መደባቸው እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳየች በብሄራዊ ባንክ እንደሚወሰን የአዋጁ አንቀጽ 18 ያመለክታል፡፡
የወንጀል ተጠያቂነት የሚስከትሉ የወንጀሎች ድርጊቶች
ህጋዊ የገንዘብ ኖቶችን በተመለከተ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ ከአንቀጽ 356 ጀምሮ እስከ አንቀጽ 362 አስቀጪ የሆኑ የወንጀል ድርጊቶች እና የሚያስቀጠቱን የቅጣት መጠን ደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚሁም መሰረት በህጉ አንቀጽ 356 መሰረት ህጋዊ መገበያያ የሆኑትን ገንዘቦች ያለ ፍቃድ መስራት ወይም አስመስሎ መስራት ከ5 አመት በማያንስ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ የወንጀል ድርጊት ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በአንቀጽ 357 መሰረት ህጋዊ ገንዘቦችን ከትክክለኛ ዋጋቸው በላይ እንዲዘዋወሩ ለማድረግ በማሰሰብ መልካቸውን መለወጥ፣ እውነተኛ መልካቸው ላይ ሌላ ነገርን መጨመር፣ ቀለማቸውን መለወጥ ወይም በሌላ ማናቸውም አይነት ዘዴን በመጠቀም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ወደሀሰተኛነት መለወጥ ከ15 አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአንቀጽ 358 መሰረት በኬሚካል፣ በፊዚካል፣ መካኒካል ወይም ማናቸውንም ዘዴ ተጠቅሞ ህጋዊ የሆኑትን ገንዘቦች ዋጋቸውን ዝቅ እንዲል ማድረግ ከ10 አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡ ይህ ወንጀል በአገራች ውስጥም ሆነ በውጪ አገር ቢፈፀም የሚያስቀጣ ነው፡፡
ወደ አገር ከማስገባት ጋር ተያይዞ ሀሰተኛ የሆኑ ወይም ዋጋቸው ዝቅ እንዲል የተደረጉ ገንዘቦችን እውነተኛ እንደሆኑ ወይም ሙሉ ዋጋቸውን እንደያዙ አስመስሎ ራሱ እንዲገበያይባቸው ወይም እንዲዘዋወሩ ለማድረግ በማሰብ ወደ አገር ውስጥ ማስገባትም ሆነ ከአገር ማስወጣት እንዲሁም ይዞ መገኘት፣ ማስቀመጥና ማቅረብም ጭምር ከ15 አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡ እነዚህ በገንዘብ ኖቶች ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች ከተፈጸሙ ህጉ ድርጊቱ የተፈጸመው ገንዘቦቹን ለማዘዋወር እንደሆነ ግምት ይወስዳል፡፡
ማዘዋወርንም በተመለከተ በአንቀጽ 361 ላይ እንደተደነገገው ሀሰተኛ የሆኑትን ወይም ወደ ሀሰት የተለወጡትን ገንዘቦች እውነተኛ አስመስሎ ወይም ከተወሰነው በላይ ዋጋ እንዳላቸው አስመስሎ በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም ከአገር ውጭ ማዘዋወር ከ10 አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡ በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 2 እንደተገለጸው ዋጋቸው የተቀነሰውን ገንዘቦች ሙሉ ዋጋ እንደያዙ አስመስሎ ማዘዋወር ከ5 አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡ ወንጀል አድራጊው ገንዘቡን እውነተኛ ነው በሚል እምነት ወይም በትክክለኛ ዋጋው ከተቀበለ በኋላ ሀሰተኛ መሆኑን ወይም ዋጋው መቀነሱን እያወቀ ከኪሳራ ለመዳን ሀሰተኛውን ወይም ወደ ሀሰት የተለወጠውን ገንዘብ ያዘዋወረ እንደሆነ በቀላል አስራት ይቀጣል፡፡ በተጨማሪም ዋጋው የተቀነሰውን ገንዘብ ሙሉ ዋጋው እንዳለ በማስመሰል ያዘዋወረ እንደሆነ በመቀጮ የሚቀጣ ይሆናል።
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 362 መሰረት ከላይ የተገለጹት ወንጀሎች የተፈጸሙበት የገንዘብ መጠን ማነሱ ከወንጀል ተጠያቂነት ያስመልጥም፡፡ ይልቁንም ህጉ ባስቀመጠው መሰረት የገንዘቡ መጠን ትንሽ ከሆነ ቅጣቱ ቀላል እስራት ይሆናል፡፡
ገንዘቦችን አስመስሎ መስራትን ስናይ ወንጀል ፈፃሚው የማታለል ሀሳብ ባይኖረውም ገንዘቦችን በማስመሰል መስራት፣ በሚያሳሳት መልኩ አምሳያ ሆነው እንዲዘዋወሩ በማስታወቂያነት አስመስሎ ማወጣት ድርጊቱ የማሳሳት አደጋ የሚፈጥር ወይም ለመፍጠር የሚችል ከሆነ እንዲሁም እነዚህኑ መስለው የተሰሩትን ገንዘቦች ወደ አገር ማስገባት፣ ከአገር ማስወጣት፣ በአደራ በቀበል፣ ለሽያጭ ወይም በስጦታ ማቅረብ ወይም እንዲዘዋወሩ ማድረግ በህጉ አንቀጽ 369 መሰረት በመቀጮ ወይም ከሶስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ያስቀጣል፡፡ እነዚህን የሀሰት ገንዘቦች ከመስራት ጋር በተገናኘ ሌላው መታወቅ ያለበት ነገር ማንም ሰው አግባብ ያለው ባለስልጣን በግልፅ ሳያዘው ለገንዘብ ማተሚያ ወይም መስሪያነት የሚያገለግሉትን መሳሪያዎች ፎርሞች፣ ከውሮች ወረቀቶች፣ ሞዴሎች እና መሰል እቃዎች የሰራ፣ በእጁ ያስገባ፣ ወደ አገር ያስገባ ወይም ያስወጣ፣ ለሌላ ሰው ያቀረበ ወይም አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ እንዲሁም እነዚህ ገንዘቦች እንዲሰሩ የሚሰጡ ትእዛዞችን የተቀበል፣ የፈጸመ፣ ያስፈጸመ፣ ለሌላ ሰው ያስረከበ እንደሆነ በህጉ አንቀጽ 370 መሰረት በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ይቀጣል፡፡

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/