አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
November 26, 2023
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
November 27, 2023
November 27, 2023
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
November 29, 2023
November 29, 2023
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
November 29, 2023
November 30, 2023
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
December 1, 2023
የተጠርጣሪ፣ የተከሳሽ እና የታራሚ ልዩነት

ተጠርጣሪ፣ ተከሳሽ እና ታራሚ የሚሉት ቃላቶች በወንጀል ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚነሱ ሲሆኑ ነገር ግን በአብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል በእነዚህ ቃላቶች መካከል ያለውን ልዩነት ባለማወቅ እና ባለመረዳት አንዱን ቃል ለአንዱ በመተካት እና በመቀያየር ሲጠቀምበት ይስተዋላል፡፡ በመሆኑም በዚህ ፅሁፍ የተጠርጣሪ፣ የተከሳሽ እና የታራሚን ምንነት፣ በመካከላቸው ያለውን አንድነት እና ልዩነት ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡

ተጠርጣሪ

ተጠርጣሪ ማለት የወንጀል ድርጊት ፈፅሟል ተብሎ የተጠረጠረ እና በወንጀል ሥነ ሥርአት ህጉ መሰረት ለፖሊስ ወይም በህግ ክስ ለመቀበል ስልጣን ለተሰጠው አካል የወንጀል ክስ አቤቱታ ወይም ጥቆማ የቀረበበት ማንኛውም ሰው ነው፡፡ በዚህም ፖሊስ ተጠርጣሪው የተባለውን የወንጀል ድርጊት ስለመፈፀም ወይም አለመፈፀሙ ማስረጃ የማሰባሰብ እና የምርመራ ሥራ ያከናውናል፡፡ በዚህ መልኩ የሚሰራው ምርመራ ከተጠናቀቀ በኋላ የምርመራ መዝገቡ ለዐቃቤ ህግ የሚቀርብ ሲሆን ዐቃቤ ህግም የቀረበውን ማስረጃ በመመልከት ተጠርጣሪው ወንጀሉን ስለመፈፀሙ የሚያስረዳ በቂ ማስረጃ ያለ ከሆነ በፍርድ ቤት ክሰ ሊመሰርት፣ በተጨማሪነት መቅረብ ያለበት ማስረጃ ካለ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ ሊሰጥ ወይም ማስረጃው አጥጋቢ ካልሆነ የአያስከስስም ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል፡፡

ተጠርጣሪው የተጠረጠረበትን የወንጀል ድርጊት ስለመፈፀሙ የሚያመለክት አጥጋቢ ማስረጃ እስካልተገኘበት ድረስ በቁጥጥር ስር የማይውል ሲሆን የወንጀል ምርመራ በሚደረግበት ወቅትም ተጠርጣሪው እንደተጠረጠረበት የወንጀል አይነት፣ ክብደት፣ የአፈፃፀም ሁኔታ፣ እንደ ተጠርጣሪው ባህሪ እና ሌሎች ሁኔታዎች በፖሊስ ዋስትና፣ በፍርድ ቤት ዋስትና ወይም በማረፊያ ቤት ሆኖ የወንጀል ምርመራ ሂደቱ ሊከናወን ይቻላል፡፡

ተከሳሽ

ተከሳሽ ማለት በወንጀል ድርጊት ተጠርጥሮ በፖሊስ የወንጀል ምርመራ የተጠረጠረበትን የወንጀል ድርጊት ስለመፈፀሙ በቂ እና አሳማኝ ማስረጃ ተገኝቶ በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ያለ እና የፍርድ ውሳኔ ያልተሰጠበት ማንኛውም ሰው ነው፡፡

ተከሳሽ በፍርድ ቤት ዋስትና ወይም በማረፊያ ቤት ሆኖ የወንጀል ክስ ሂደቱን ሊከታተል ይችላል፡፡ ተከሳሽ በክስ መሰማት ሂደት ወቅት ለህዝብ ግልጽ በሆነ ችሎት የመሰማት፣ ክሱ በቂ በሆነ ዝርዝር እንዲነገረው እና በፅሁፍ የማግኘት፣ በተከሰሰበት ወንጀል እንደጥፋተኛ ያለመቋጠር፣ በራሱ ላይ በምስክርነት እንዲቀርብ ያለመገደድ፣ የቀረበበትን ማንኛውንም ማስረጃ የመመልከት እና የቀረበበትን ማንኛውንም ምስክሮች የመጠየቅ፣ ራሱን ለመከላክል የሚያስችለውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ፣ በመረጠው የህግ ጠበቃ የመወከል፣ በተሰጠው ፍርድ ላይ ይግባኝ የማለት እና በመንግስት ውጪ አስተርጎሚ የማግኘት መብት አለው፡፡

ታራሚ

በፌደራል ማረሚያ ቤት አዋጅ ቁጥር 1174/2012 አንቀጽ 2(8) መሰረት ታራሚ ማለት በፍርድ ቤት የተወሰነበትን ፍርድ በማረሚያ ቤት ውስጥ በመፈፀም ላይ የሚገኝ ሰው ነው፡፡ በህገ መንግስቱ እና በዚህ አዋጅ መሰረት ማንኛውም ታራሚ ሰብአዊ ክብሩ በሚጠብቁ ሁኔታዎች የመያዝ፣ ከትዳር ጎደኛው፣ ከቅርብ ዘመዶቹ፣ ከጎደኞቹ፣ ከሀይማኖት አባት፣ ከሐኪም እና ከህግ አማካሪዎቹ ጋር ለመገናኘት እና እንዲጎበኙት እድል የማግኘት መብት አለው፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
December 1, 2023
December 1, 2023
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
December 2, 2023
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
December 5, 2023
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
December 6, 2023
8. የንግድ ሕጉ አንቀፅ 57(4) ደላላው ኃላፊነት አለበት ይላል። ደላላው ለደንበኛው ወይም አገልግሎቱን ለጠየቀው ወገን ያሉበትን ግዴታዎች ተላልፎ የደንበኛውን ጥቅም በሚጎዳ አኳኀን ለሌላ 3ኛ ወገን ጥቅም የሠራ እንደሆነ ወይም ደንበኛው ሳያውቅ ከ3ኛ ወገን ክፍያ ከተቀበለ አበል የማግኘት መብቱ ቀሪ ይሆናል። በተግባር ግን ብዙዎች ደላላ ቢጎዳቸውም ከመበሳጨት በስተቀር በፍርድ ቤት ከሰው በኃላፊነት ካሳ ሲጠይቁ አይታይም።

ለማንኛውም ደላላ ስትጠቀሙ በተለይ አበሉን በተመለከተ በቁርጥ በቅድሚያ ተስማሙ። በመቶኛ ከሆነ አበላቸውን ለመጨመር ዋጋውን ከፍ ሊያደርጉት ስለሚችሉ በቁርጥ አድርጉት። አበሉን ተስማምታችሁም ቢሆን ከሰጡት አገልግሎት ጋር የክፍያው መጠን ከተጋነነ ይገባል ከምትሉት በላይ አልከፍልም በሉ። ጉዳዩ ፍ/ቤት ከደረሰ ሊቀነስላችሁ ይችላል። ቢቻል የንግድ ፍቃድ ባላቸው ደላሎች ተጠቀሙ። ደላላው የሚጠራውን ዋጋ ከማመናችሁ በፊትም በተለያየ ዘዴ የገበያውን ዋጋም ለማጣራት ሞክሩ።
EBC
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
December 6, 2023
December 6, 2023
December 7, 2023
December 7, 2023
December 7, 2023