#የዳኝነት_ሳይከፈል_በነፃ_ስለሚቀርብ_ክስ
ማንኛውም የፍትሐብሔር ክስ ሲከፈት በፍርድ ቤት ለሚሰጠው የዳኝነት አገልግሎት የዳኝነት እንዲከፈል ይጠበቃል፡፡ ክስ ለማቅረብ የፈለገ ወገን ለሚያገኘው የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል የገንዘብ አቅም የሌለው ከሆነ ለግዜው የዳኝነት መክፈል ባለመቻሉ ብቻ መብቶቹን እንዳያጣ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህጉ መፍትሄ አስቀምጧል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ስለሚቀርብ ክስ ምንነት እና ስለሚቀርብበት ሥነ ሥርዓት እንመለከታለን፡፡
የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ የሚቀርብ ክስ ምንነት
በ1958 ዓ.ም በወጣው የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 467 መሰረት የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ የሚቀርብ ክስ ማለት ገንዘብ የሌለው እና ገንዘብ ለማግኘት የማይችል ማንኛውም ደሀ ሰው የዳኝነት ሳይከፍል በነፃ ፋይል ክፍቶ ክስ የሚያቀርብበት ሂደት ነው፡፡
የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ የሚቀርብ ክስ ሥነ-ሥርዓት
በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 467 መሰረት ዳኝነት መክፈል የማይችል ደሀ ሰው የዳኝነት ገንዘብ በሙሉ ወይም በከፊል ሳይከፍል የነፃ ፋይል ማስከፈት የሚችለው ከክሱ አቤቱታ ጋር የነፃ ዳኝነት ማመልከቻ በቃለ መሀላ አስግፎ ዋናውን ጉዳይ ለሚያየው ፍርድ ቤት ሲያቀርብ ነው (ቁ.468)፡፡ ፍርድ ቤቱም ማመልከቻውን ተመልክቶ ስለአመልካች የሀብት ሁኔታ እና ስለማመልከቻው ተገቢነት አስፈላጊ ማስረጃ ለማግኘት አመልካችን ወይም ወኪሉን አስቀርቦ ሊጠይቀው ይችላል፡፡
ፍርድ ቤቱ የቀረበው ማመልከቻ ሲመረምር የሚነቀፍበት ምክንያት ካላገኘ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 471 መሰረት አመልካች ድሀ ስለመሆኑ እንዲያስረዳ እና በአንፃሩም አመልካቹ ሀብት አለው የሚሉ ሰዎች እንዳሉ እንዲያስረዱ ቀጠሮ በመስጠት ከቀጠሮ አስር ቀን በፊት ለባለጋራው ማስታወቂ እንዲደርሰው ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ማስረጃው ተሰምቶ ከተመረመረ በኋላ ፍርድ ቤቱ ማመልከቻውን ሊቀበል ወይም ውድቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ማመልከቻው ተቀባይነት ካገኘ አመልካቹ ዳኝነት ሳይከፍል ያቀረበው ክስ ዳኝነት እንደተከፈለበት እንደማንኛውም ክስ ተቆጥሮ በመደበኛ ሥነ ሥርአት ይመራል፡፡
ይህም ውሳኔ በነፃ ዳኝነት የቀረበው ክስ ቀጥሎ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ የሚያገለግል እና ማስረጃነቱ የሚቀጥል ሲሆን ይህ ማስረጃ ግን ለሌሎች ክርክሮች እንደ ማስረጃ ሊሆን አይችልም፡፡ በይግባኝ ደረጃ የሚሄድ ክርክር አመልካች ይግባኝ ባይ ከሆነ በነፃ ይግባኝ መዝገብ እንደ አዲስ ይከፈትልኝ እስካላለ ድረስ በነፃ እንዲከራከር በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው የድህነት ማስረጃ አያገለግለውም፡፡ ነገር ግን በይግባኝ ክርክሩ መልስ ሰጪ ከሆነ የድህነት ማስረጃው ያገለግለዋል (ቁ.474)፡፡
በሌላ በኩል ዳኝነት ሳይከፈል በነፃ እንዲታይ የሚቀርብ ማመልከቻ ተቀባይነት ላያገኝ ይችላል፡፡ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 470 መሰረት ማመልከቻው ተቀባይነትን ላያገኝ የሚችለው፡-
አመልካቹ ድሀ አለመሆኑ ከተረጋገጠ፣
በነፃ ለመክሰስ ያቀረበው ነገር የማያስከስስ የሆነ እንደሆነ፣
ክስ ከማቅረቡ ከሁለት ወር በፊት የነበረውን ንብረት ለሌላ ሰው አስተላልፎ እንደሆነ ወይም በማጭበርበር መንገድ ንብረቱን አዛውሮ ከሆነ ወይም ዳኝነት ከመክፈል ለመዳን ዘዴ ፈጥሮ ከሆነ፣
ክርክር በሚያቀርብበት ንብረት ወይም መብት ውስጥ ሌላ ሶስተኛ ሰው እንዲጠቀም ወይም ማናቸውንም መብት እንዲያገኝ ተዋውሎ ወይም ተስማምቶ እንደሆነ ነው፡፡
የዳኝነት ሳይከፍል ልከራከር የሚለው ማመልከቻ ውድቅ ከተደረገ በዚሁ ጉዳይ ድጋሚ መቅረብ የማይችል ሲሆን ክስ ማቅረብ የሚችለው የዳኝነት ክፍያ እንዲሁም የነፃ ዳኝነት እንዲፈቀድለት ባቀረበ ጊዜ ባለጋራው ለመቃወም ያወጣውን ወጪና ኪሳራ ከፍሎ እንደሆነ ከፍሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 477 መረዳት ይቻላል፡፡
በነፃ ለመከራከር የተፈቀደለት ሰው በነፃ የመከራከር መብቱን ሊያጣ የሚችልባቸው ሁኔታዎች
በፍሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 475 መሰረት የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ መከራከር ማስረጃ ዋጋ ሊያጣ የሚችል ሲሆን ይኸውም
ክርክሩ እንዲሰማ በተቀጠረው ቀነ ቀጠሮ የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ልከራከር ባይ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ ወይም የማወክ፣ የማስቸገርና የተንኮለኛነት ጠባይ ያሳየ እንደሆነ፣
ክርክሩ በሚቀጥልበት ጊዜ ሀብት ያለው መሆኑ የተገለፀበት እንደሆነና በነጻ ዳኝነት መጠቀም ወይም በዚህ መቀጠል የማይገባው መሆኑን ፍርድ ቤቱ የተረዳ እንደሆነ፤
ለክርክሩ መነሻ በሆነው ሀብት ላይ ሌላ ሶስተኛ ወገን ጥቅም እንዲያገኝ ስምምነት አድርጎ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡
ሀብት ያለው መሆኑ ተገልፆበት ወይም ለክርክሩ መነሻ በሆነው ሀብት ላይ ሌላ ሶስተኛ ወገን ጥቅም እንዲያገኝ ስምምነት አድርጎ በመገኘቱ በነፃ መከራከር መብቱ የተሰረዘበት ሰው ተገቢውን የዳኝነትና ማናቸውንም ለፍርድ ቤት የሚከፈለውን ገንዘብ እንዲከፍል ይታዘዛል፡፡
በነፃ እንዲከራከር የተፈቀደለት ድሀ በክርክሩ የመርታት ወይም ሀብት የማግኘት ውጤት
በነፃ እንዲከራከር የተፈቀደለት ሰው የዳኝነት ሳይከፍል የሚከራከርበትን ጉዳይ ራሱ በፍርድ አፈፃፀም የረታ እንደሆነ ፍርድ አስፈፃሚው በፍሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 476 መሰረት ለመንግስት የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብና ማናቸውንም ወጪ ከረታው ሀብት ላይ ተቀናሽ በማድረግ ገቢ ካደረገ በኋላ ቀሪው ሀብት ረቺው እንደ ፍርዱ እንዲረከብ ማድረግ እንዳለበት ተደንግጎአል፡፡ ሌሎች በነፃ ለመዳኘት የሚቀርቡ ማመልከቻዎችና ይህንን ለመመርመር የሚያስፈልጉ ማናቸውም ወጭዎች ሁሉ ለዳኝነት ከሚከፈል ገንዘብ ጋር የሚታሰቡ እንደሆኑ ከፍሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 479 መረዳት ይቻላል፡፡
በተጨማሪም የዳኝነት ሳይከፍል የሚከራከር ወገን ማስረጃው በተሰጠው በአስር አመት ግዜ ውስጥ ወይም ክርክሩ በሚቀጥልበት ጊዜ ሀብት ካገኘ ይህንኑ አስታውቆ ዳኝነቱን መክፈል እንዳለበት በፍሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 478 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ገንዘብ አግኝቶ እያለ ይህንን የማያስታወቅ ወይም የመክፈል ግዴታውን ባይወጣ በአታላይነት ወንጀል እንደሚጠየቅ በድንጋጌው ተመልክቷል፡፡
ዳኝነት ሳይከፈልበት በነፃ የሚቀርብ ክስ የዳኝነት ለመክፈል አቅም ያጡ ሰዎች ገንዘብ በማጣት መብቶቻቸውን እንዳያጡ ለማድረግ በህጉ የተቀመጠ መፍትሄ ሲሆን በዚሁ መልኩ የተከራከረ ሰው ሀብት ሲያገኝ በአግባቡ አስታውቆ የዳኝነት መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ስለሆነም ገንዘብ ሲያገኙ መክፍል እንደተጠበቀ ሆኖ የዳኝነት ለመክፈል አቅም የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ገንዘብ ማጣታቸው ዳኝነት እንዳያገኙ እንደማይከለክላቸው አውቀው ተገቢውን ማስረጃ በማቅረብ በህጉ በተቀመጠው መልኩ መስተናገድ ይችላሉ፡፡
መረጃው፡- ከፍትሕ ሚኒስቴር የተገኘ ነው!
Federal Justice and Law Institute
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/