አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
መሰረታዊ የሕግ ስህተት በአዲሱ የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አንድ ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ከተሰጠው በኋላ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚባል ከሆነ መሰረታዊ የህግ ስህተቱ ሳይታረም እንዳይቀር በሰበር ለመታየት ዕድል ይሰጠዋል፡፡ ቀደም ሲል መሰረታዊ የህግ ስህተት ምንነት የህግ ትርጉም ያልተሰጠው የነበረ በመሆኑ ጉዳዮች መሰረታዊ የህግ ስህተት አለባቸው በሚል በብዛት ሲቀርቡ ይስተዋል ነበር፡፡ ይህን ለማስቀረት አዲሱ የፍርድ ቤቶች አዋጅ መሰረታዊ የህግ ስህተትን ምንነት ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የመሠረታዊ የሕግ ስህተት ምንነትን እና ተያያዥ ጉዳዮችን እንመለከታለን፡፡

የመሠረታዊ የሕግ ስህተት ምንነት

በአዲሱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 2(4) መሠረት “መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት” ማለት

. የሕገ-መንግሥቱን ድንጋጌዎች የሚቃረን

ለ. ሕግን አላግባብ የሚተረጉም ወይም ለጉዳዩ አግባብነት የሌለውን ሕግ የሚጠቅስ

ሐ. ለክርክሩ አግባብነት ያለው ጭብጥ ያልተያዘበት ወይም ከክርክሩ ጋር የማይዛመድ አግባብነት የሌለው ጭብጥ የተያዘበት

መ. በዳኝነት ታይቶ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ውድቅ የተደረገበት

ሠ. በፍርድ አፈፃፀም ሂደት ከዋናው ፍርድ ጋር የማይገናኝ ትእዛዝ የተሰጠበት

ረ. ጉዳዩን አይቶ የመወሰን የዳኝነት ሥልጣን ሳይኖር ውሳኔ የተሰጠበት

ሰ. የአስተዳደር አካል ወይም ተቋም ከሕግ ውጭ ውሳኔ የሰጠበት

ሸ. የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትን አስገዳጅ ውሳኔ በመቃረን የተወሰነ
እና ፍትህን የሚያዛባ ጉልህ የሕግ ስህተት ያለበት የመጨረሻ ውሳኔ፣ ፍርድ፣ ብይን፣ ትዕዛዝ ሲሆን መሰል ስህተት ያለባቸው ጉዳዮች በዚህ አዋጅ አንቀፅ 10 መሠረት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚታረሙ ይሆናል፡፡ የመጨረሻ ውሳኔ ማለት በፍርድ ቤት፣ በህግ የመዳኘት ስልጣን በተሰጠው አካል፣ በተቋማት ወይም በአማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዴዎች የተሰጠ እና ለጉዳዩ እልባት የሚሰጥ ፍርድ፣ ብይን፣ ትዕዛዝ ውሳኔ ሲሆን የይግባኝ ሂደቶችን የጨረሰ ፍርድ፣ ብይን፣ ትዕዛዝ ወይም ውሳኔን እንደሚጨምር በአዋጁ አንቀፅ 2(5) ትርጓሜ ተሰጥቶታል፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ስልጣን

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ስልጣን የመነጨው ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 80(3)(ሀ) ሲሆን መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትን ማናቸውንም የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችሎት የማየት ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በዚህም በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀፅ 10 መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለባቸውን የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በይግባኝ አይቶ የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸውን ጉዳዮች የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸውን ጉዳዮች የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወይም የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በህገ መንግስቱ በተሰጣቸው የውክልና ስልጣን ፌደራል ጉዳይን አይተው መጨረሻ ውሳኔ የሰጡበት ጉዳይ
የአዲስ አበባ ወይም የድሬደዋ ከተማ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠባቸው የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች እና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎቶች አስገዳጅ ውሳኔ ጋር በተያያዘ የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዳዮች የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ህግን አለአግባብ ከመተርጎም እና ለጉዳዩ አግባብነት የሌለውን ህግ ከመጥቀስ ጋር በተያያዘ የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠባቸው እና ጉዳዮቹ ለህዝብ ጥቅም ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ውሳኔዎች በህግ የመዳኘት ስልጣን ተሰጠው አካል ወይም በሌሎች አካላት የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ አግባብነት ያላቸው የህግ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው በፌደራል ፍርድ ቤት ሊታይ ይችል በነበረ ጉዳይ ላይ በአማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዴዎች መሰረት የተሰጡ የመጨረሻ ውሳኔዎች እንዲሁም በሌሎች ህጎች የተጠቀሱ ጉዳዮች በሰበር አይቶ የማረም ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

አንድ ጉዳይ በሰበር ሲታይ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ሊሰየሙ እንደሚገባ በአዋጁ አንቀፅ 25(2) ተደንግጓል፡፡ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የሚሰጠው የሕግ ትርጉም በየትኛውም ደረጃ ላይ በሚገኝ የፌዴራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት ላይ አስገዳጅነት እንደሚኖረው ከአንቀፅ 10(2) መረዳት ይቻላል፡፡

ይህን አምስት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ ሰባት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት በድጋሚ ሊታይ ይችላል፡፡ ይህ የሚሆነው በባለጉዳዮች አመልካችነት ወይም በችሎቱ በራሱ አነሳሽነት ቀድሞ የሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በተለያዩ ምክንያቶች ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በሰባት ዳኞች ችሎት እንዲታ በቂ እና አሳማኝ ምክንያቶችን ተንትኖ በመግለፅ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሲያቀርብ እንደሆነ ከአንቀፅ 26(1) መረዳት ይቻላል፡፡ በዚህ መልኩ ጥያቄ ሲቀርብ ፕሬዝዳንቱ ጉዳዩ ሰባት ዳኞች በሚሰየሙበት ችሎት እንዲታይ የሚያደርግ ሲሆን በችሎቱ የሚሰጠው ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በማንኛውም ደረጃ ፍርድ ቤት አስገጃጅ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት ቀድሞ የሰጠውን የህግ ትርጉም ከሰባት ባላነሱ ዳኞች በተመሳሳይ ጭብጥ በሌላ ጊዜ ሊሻሻል ይችላል፡፡

ማጠቃለያ

በአጠቃላይ የሰበር ሥርዓት መሰረታዊ ህግ ስህተት ያለበት የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠበት ጉዳይ ለመጨረሻ ጊዜ የሚታይበትና እና የሚታረምበት የዳኝነት ሂደት ነው፡፡ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ምንነት ደግሞ በአዋጁ የተገለፀ በመሆኑ ለሰበር የሚቀርቡ ጉዳዮች ይህንን ተከትለው መቅረብ አለባቸው፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
#አለ_ህግ #ale_hig #lawsocieties #law https://t.me/lawsocieties
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ማለት
ሠራተኛው ካለፈው፣ አሁን ካለው ወይም ወደፊት ከሚመጣው የቅጥር ውል ጋር በተያያዘ የሚያገኘው ደመወዝ/ምንዳ፣ አበል፣ ጉርሻ፣ ኮሚሽን፣ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማበረታቻ ስጦታ ወይም ሌላ የአገልግሎት ዋጋ ክፍያ፣ ተቀጣሪው ከስራ ሲቀነስ ወይም ከስራ ሲለቅ ወይም ስራን እንዲለቅ ለማግባባት የሚከፈል ገንዘብ ወይም የስራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በፈቃደኝነት፣ በስምምነት፣ በዳኝነት ውሳኔ መሠረት በጥሬ ገንዘብ (በዓይነት) የተቀበለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን ከታክስ ነጻ ከተደረገው ውጪ እንደ ገቢ ተቆጥሮ ታክስ የሚሰላበት ይሆናል፡፡
* አንድ ተቀጣሪ ከመቀጠር የሚያገኘው ገቢ በኢትዮጵያ የመነጨ ነው የሚባለው፡-
1. ክፍያው የሚፈፀመው ስፍራ ግምት ውስጥ ሳይገባ ኢትዮጵያ ውሰጥ ከሚከናወነው የቅጥር አገልግሎት የተገኘ ገቢ ከሆነ ወይም
2. የቅጥር አገልግሎቱ የትም ቢከናወን በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ስም ክፍያው ለተቀጣሪው ከተፈፀመ ነው፡፡
* ተቀጣሪው ከመቀጠር በሚያገኘው ገቢ የሚያወጣው ማንኛውም ወጪ በተቀናሽ ሊያዝለት አይችልም፡፡
#አለ_ህግ #ale_hig #lawsocieties #law https://t.me/lawsocieties
Federal_Supreme_Court_Cassation_Decisions_Table_of_content_Volume.pdf
6.6 MB
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሕግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ዝርዝር ማውጫ ሰንጠረዥ ከቅጽ 1 እስከ 25

በ፦ ዋስይሁን ኃይለማርያም እና የኋላሸት ታምሩ

አዘጋጆቹ በዚህ ጊዜ በመስፍን ታፈሰ እና ጓዶቹ (MTA) የሕግ ቢሮ በአሶሲየትነት በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆኑ ይህን ስራ አዘጋጆቹ በግላቸው የሰሩት እና የሚሰሩበትን ተቋም ያካተተ ወይም የሚወክል አይደለም። ይህ ማውጫ የሚያገለግለው ለትምህርት እና ለመረጃ ምንጭነት ብቻ ነው። በዚህ ማውጫ ዝግጅት ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያዘጋጀው ከ ቅጽ 1 እስከ 16 ማውጫን በመጠቀም የቀሩትን ቅጾች አጠቃለን አዘጋጅተናል።

አዘጋጆቹ ይህን ማውጫ በሚያዘጋጁበት ጊዜ በውስጡ ያሉትን መረጃዎች እውነታነት ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ጥረት አድርገዋል፡፡ ይህ ማውጫ ሲዘጋጅም ትክክለኛ መረጃ እንዲይዝ በማሰብ ነው፡፡ ሆኖም ግን በዚህ ማውጫ ላይ ሊኖሩ በሚችሉ ስህተቶች፣ ግድፈቶች፣ ጉድለቶች እንዲሁም አለመስማማቶች ሊከሰቱ ለሚችሉ ጉዳቶችም ሆነ ኪሳራ አዘጋጆቹ ምንም አይነት ኃላፊነት እንደማይወስዱ ያሳውቃሉ።

ይህ ማውጫ በዋነኛነት የመረጃ ምንጭ እንዲሆን እና ለሕግ ማህበረሰቡ ቀላል እና ፈጣን ማጣቀሻ እንዲሆን የተዘጋጀ ቢሆንም ቀጥታ የባለሞያ ምክር ወይም ድጋፍ አይተካም። ይህን አይነት አገልግሎት ከተፈለገ ከባለሞያ መጠየቅ አለበት፡፡

አዘጋጆቹን አቢሲኒያሎውን ከልብ ያመሰግናል!
#አለ_ህግ #ale_hig #lawsocieties #law https://t.me/lawsocieties
የዘንድሮ 12ኛ ክፍል የተማሪዎች አማካይ ውጤት በየትምህርት አይነቱ፤

አጠቃላይ መረጃ፡-  ፈተና የተፈተኑ ብዛት-----908,256 ናቸው፡፡

  አማራ………..30.37%
  ኦሮሚያ…..…27.96%
  ደቡብ………..28.17%
  ሀረሪ…………32.88%
  አዲስ አበባ----38.46%
  ደሬደዋ--------31.42%
  ሲዳማ---------28.34%

2. ከ50% እና በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት ከተፈተኑ መካከል

(እንደ ሀገር ያለፉ 29909 (3.3%) ናቸው

  አማራ………ከ246,675 መካከል 8,810 ((3.6%)
  ኦሮሚያ…..…327,737 መካከል 6,407 (2.0%)
  ደቡብ………..ከ127,345 መካል 2,533 (2.0%)
  ሀረሪ…………ከ1,849 መካከል 194 (10.5%)
  አዲስ አበባ----ከ47,980 መካከል 9,491 (19.8%)
  ደሬደዋ-------- ከ3,726 መካከል 250 (6.7%)
  ሲዳማ---------ከ53,478 መካከል 1247 (2.3%)

3. ተፈጥሮ ሳይንስ  ከ600 እና በላይ እንደ ሀገር 263 ተማሪዎች ያስመዘገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ

  አማራ………70 ተማሪዎች
  ኦሮሚያ…..…51 ተማሪዎች
  ደቡብ………..10 ተማሪዎች
  ሀረሪ…………1 ተማሪዎች
  አዲስ አበባ----117 ተማሪዎች
  ደሬደዋ-------- 2 ተማሪዎች
  ሲዳማ---------8 ተማሪዎች

4. ማህበራዊ ሳይንስ  ከ500 እና በላይ እንደሀገር 10 ተማሪዎች ያስመዘገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ

  አማራ………1ተማሪ
  አዲስ አበባ----8 ተማሪዎች
  ደሬደዋ-------- 1 ተማሪ

5. ሁሉንም ተማሪዎች 100% ያሳለፉ ት/ቤቶች 7 ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ

  ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት
  ባሕር ዳር ስቲም ት/ቤት
  ጎንደር ኮሙኒቲ ስኩል
  ወላይታ ሶዶ ሊቃ ት/ ቤት
  አዳማ ኦዳ አዳሪ ት/ ቤት
ናቸው።

6. ከፍተኛ ውጤት (የዓመቱ ሰቃይ)

👉ከአማራ ክልል ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪ ሚኪያስ አዳነ 666 አስመዝግቧል።

https://t.me/lawsocieties
#housinginaddisababa
#አለ_ህግ #ale_hig #lawsocieties #law https://t.me/lawsocieties
Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር:
ሀብትን በማስተላለፍ የሚገኝ ገቢ
1. አንድ ሰው አንድን ሀብት ሲያስተላልፍ ከዚህ ሀብት የተገኘ ገቢ ሆኖ የሚወሰደው ሀብቱን ሲያስተላልፍ የተቀበለው ወይም የሚቀበለው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን ሲሆን፣ ሀብቱ በተላለፈበት ጊዜ በዓይነት የተገኘውን ማንኛውንም ጥቅም ትክክለኛ የገበያ ዋጋ ይጨምራል፡፡
2. ለኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ደርጅት ወይም የኢትዮጵያ ማህበር የሚሰጥን እርዳታ ሳይጨምር ሀብት በስጦታ የተላለፈ እንደሆነ በተላለፈበት ጊዜ ያለው ትክክለኛ የገበያ ዋጋ ከሀብቱ የተገኘ ገቢ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
3. አንድ ሰው ሀብቱን በማስተላለፍ ያገኘው ገቢ ሀብቱን ከማስተላለፍ ጋር በተያያዘ ከቀረበለት ምርጫ ያገኘውን ጥቅም ይጨምራል፡፡ ሆኖም ይህ ጥቅም እንደገቢ ተደርጐ የሚወሰደው ከቀረበለት ምርጫ ጋር በተያያዘ ባገኘው ጥቅም ላይ ግብር ያልከፈለ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
4. አንድ ሀብት የጠፋ ወይም የወደመ እንደሆነ፣ የዚህ ሀብት ዋጋ ነው የሚባለው ባለሀብቱ ሀብቱ በመጥፋቱ ወይም በመውደሙ ምክንያት የተቀበለው ወይም የሚቀበለው የካሳ መጠን ሲሆን የሚከተሉትን ይጨምራል፡-
   ሀ) በመድን ፖሊሲ መሠረት፣ በካሳ ወይም በሌላ ስምምነት ምክንያት የተቀበለውን ወይም የሚቀበለውን የገንዘብ መጠን፤
   ለ) በድርድር ምክንያት የሚቀበለውን የገንዘብ መጠን፤ ወይም
   ሐ) የፍርድ ቤት ውሳኔን ተከትሎ የተቀበለውን ወይም የሚቀበለውን የገንዘብ መጠን፤
5. አንድ ሰው በአንድ ግብይት ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሀብቶችን ያስተላለፈ እንደሆነና የእያንዳንዱ ሀብት ዋጋ ተለይቶ ያልታወቀ እንደሆነ፣ ሀብቶቹ በተላለፉበት ጊዜ ባለው ትክክለኛ የገበያ ዋጋ መሠረት በማስተላለፉ ምክንያት የተቀበለው የገንዘብ መጠን ለተላለፉት ሀብቶች እንደየድርሻቸው ይደለደላል፡፡
6. አንድ ግብር ከፋይ የተላለፈውን ሀብት ዋጋ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ያልቻለ እንደሆነ ሀብቱ በተላለፈበት ጊዜ የነበረው ትክክለኛ የገበያ ዋጋ የሀብቱ ዋጋ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
https://t.me/lawsocieties
#housinginaddisababa
#አለ_ህግ #ale_hig #lawsocieties #law https://t.me/lawsocieties
Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር:
ሀብትን በማስተላለፍ የሚገኝ ገቢ
https://t.me/lawsocieties
#housinginaddisababa
#አለ_ህግ #ale_hig #lawsocieties #law https://t.me/lawsocieties
እሁድ እሁድ ስናካሂድ የነበረውን ከምሽቱ 2:30 የእሁድ ችሎት ነፃ ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ የተቋረጠ ሲሆን ውይይቱን ስንጀምር የምናሳውቅ ይሆናል‼️

#የእለቱ_ችሎት

#የችሎቱ_ጭብጥ

ፕሮግራም ለአልተወሰነ ጊዜ የተቋረጠ መሆኑን ስለማሳወቅ‼️

#ውሳኔ
ችሎቱ ቢያመልጥዎት በሌሉበት የሚሰማ ይሆናል።

ቀጠሮው እሁድ ማታ በስልክዎት በ @lawsocieties የቴሌግራም ቻናል በመዝገብ ስዓት ቁጥር 2:30 የመገኘት መብትዎ የተከበረ ሆኖ ተራዝሟል።

ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይመለሱ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
#የሚነበብ#አለ_ህግ ስም አለበት
https://t.me/lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
የጋብቻ መፈፀም የሚያስከትለው ውጤት
#ጋብቻ አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት በሁለት ሰዎች (ባልና ሚስት) መካከል የሚፈጠም ህብረት እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ የሀገራችን ቤተሰብ ህግ ለጋብቻ ትርጉም ያልሰጠ ሲሆን ጋብቻ ለማቋቋም ሊሟሉ የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን እና ጋብቻ የሚፈፀመው በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡

በህግ ፊት የፀና ጋብቻ ለመፈጸም የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው፡፡ በዚህ መሰረት የሁለቱ ሰዎች ፈቃድ መኖር፣ በህጉ የተቀመጠው ዝቅተኛ እድሜ መሟላት፣ የዝድና አለመኖር፣ በጋብቻ ላይ ጋብቻ አለመኖር መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

ጋብቻ በተለያዩ ሶስት መንገዶች ሊፈጸም ይችላል፡፡
እነዚህም በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈፀም፣ የሀይማኖት ጋብቻ እና የባህል ጋብቻ ናቸው፡፡ በእነዚህ መንገዶች የተፈፀመ ጋብቻ ተመሳሳይ ውጤት ያለው ሲሆን በእነዚህ መንገዶች አስፈላጊውን ሁኔታ በማሟላት የተፈጸመ ጋብቻ የሚያስከትለው ውጤቶች እንደሚከተለው ተብራርተዋል፡፡

1. ጋብቻ በተጋቢዎች ግላዊ ግንኙነት ላይ የሚያስከትለው ውጤት

i. አብሮ መኖር
ባልና ሚስት ጋብቻ ከፈፀሙ በኋላ አብረው እንዲኖሩ በህግ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ የመኖሪያ ቦታቸውንም አብረው የሚወስኑ ይሆናል፡፡ ሆኖም ባልና ሚስቱ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ተለያይተው ለመኖር መስማማት አይከለከሉም፡፡ ይህ ስምምነት መቀየሩ አግባብ ካልሆነ በስተቀርም ተጋቢዎች ወይም ከሁለት አንዳቸው አስበው ሊቀይሩትም ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ የባልና ሚስቱ የሥራ ቦታ ሊለያይ የሚችልበት አጋጣሚ ሲፈጠር ሁለቱም በያሉበት ሆነው ሥራቸውን ለመሥራት ሊስማሙ የሚችሉ ሲሆን አመቺ ሆኖ ካላገኙትም ሀሳባቸውን መቀየር ይችላሉ፡፡

ይህ ብቻ ሳይሆን ተጋቢዎች ጋብቻ ተሳስረው ሲኖሩ ለጤናቸው አደገኛ ካልሆነ በስተቀር ከጋብቻ የሚጠበቀውን መደበኛ የሩካቤ ሥጋ መፈፀምም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን የሚቃረን ስምምነት ውጤት አይኖረውም፡፡ በተጨማሪም በማንኛውም ሁኔታ አንዳቸው ለሌላኛው ታማኝ የመሆን ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ አንዳቸው ሳይታመኑ የአመንዝራነት ድርጊት ቢፈፅሙ በተበደለው ተጋቢ አቤቱታ አቅራቢነት በእስራት ወይም በመቀጮ ሊያስቀጣ የሚችል የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል ነው፡፡

ii. መከባበር፣ መተጋገዝና መደጋገፍ

ባልና ሚስት በትዳር በሚኖሩበት ጊዜ አንዳቸው ሌላኛውን የማገዝና የመደገፍ እንዲሁም ተከባብሮ የመኖር ሀላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ይህንን ሀላፊነት በስምምነት ፈፅሞ ሊያስቀሩት እንደማይችሉ በህግ ተደንግጓል፡፡

iii. ቤተሰብን በጋራ መምራት

ጋብቻ በሁለቱ ተጋቢዎች ተወስኖ የማይቀርና ልጆችን የሚፈጥርና የቤተሰብ መሰረት የሚሆን ተቋም ነው፡፡ በዚህም የልጆች አስተዳደግ፣ ትምህርት፣ ጤና ወዘተ የመሳሰሉ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች በተጋቢዎች እንዲሟሉ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ አንፃር ባልና ሚስት እኩል መብት እንዳላቸው በቤተሰብ ህግ ደንግጓል፡፡ በዚህም በማናቸውም ረገድ የቤተሰቡን ደህንነትና ጥቅም ለማስጠበቅ፣ ልጆቻቸው በመልካም ሥነ ምግባር እንዲታነፁ፣ ተገቢ ትምህርት እንዲቀርሙና ሀላፊነት የሚሰማቸው ዜጎች ሆነው እንዲያድጉ ለማድረግ ባልና ሚስቱ መተባበር ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ጋብቻ በንብረት ረገድ የሚያስከትለው ውጤት

ጋብቻ በተጋቢዎች ግላዊ ግንኙነት ላይ ውጤት እንዳለው ሁሉ በንብረት ረገድም የራሱ የሆነ ውጤት የሚያስከትል ነው፡፡ ንብረትን በተመለከተ ጋብቻ የግል እና የጋራ ንብረት ውጤት የሚስከትል ነው፡፡

i. የግል ንብረት ምንነትና አስተዳደር

የግል ንብረት የምንለው ሁለቱ ተጋቢዎች ከጋብቻው በፊት በየግል የነበሯቸው ንብረቶች ወይም ከጋብቻው በኋላ በውርስ ወይም በየግላቸው በስጦታ ያገኟቸው ንብረቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ንብረቶች በጋብቻውም ዘመን የግላቸው ሆነው ይቀጥላሉ፡፡ እነዚህን ንብረቶች ሸጦ የሚገዛው ንብረት የራሱ የሚሆን ሲሆን ይህ የሚሆነው ግን በፍርድ ቤት የግሌ ይባልልኝ ብሎ ሲጠይቅና ሲፀድቅለት ነው፡፡

የግል ንብረት አስተዳደርን በተመለከተ የግል ንብረቱ ባለቤት የሆነው ተጋቢ ሊያዝበት የሚችል ሲሆን ሌላኛው ተጋቢ እንዲያስተዳድረው በጋብቻ ውል ሊስማሙ የሚችሉ ከመሆኑም በላይ ውክልና በመስጠት ሌላኛው ተጋቢ እንዲያስተዳደር ሊያደርግ ይችላል፡፡

ii. የጋራ ንብረት ምንነትና አስተዳደር

የጋራ ንብረትን በተመለከተ የጋራ ንብረት የሚባለው ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ በግብይት የሚያገኟቸው ንብረቶች፣ ባልና ሚስት በግል ጥረታቸው የሚገኝ ገቢ፣ ከግል እና ከጋራ ንብረታቸው የሚገኟቸው ገቢዎች ሁሉ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በስጦታ ወይም በኑዛዜ በጋራ የተሰጧቸው ንብረቶች የጋራ ንብረቶች ናቸው፡፡ እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን ካላስረዳ በስተቀር በአንደኛው ተጋቢ ስም የተመዘገበ ሀብትም ቢሆን እንኳን የተጋቢዎች የጋራ ሀብት እንደሆነ የህግ ግምት የሚወሰድበት መሆኑ ነው፡፡

በንብረት አስተዳደር ረገድ የጋራ ንብረታቸውን አንደኛው ተጋቢ እንዲያስተዳድረው ካልተስማሙ፣ ችሎታ የለውም በሚል ካልተወሰነ፣ ንብረት የማስተዳደር መብቱ ካልተገፈፈ፣ ወይም በማናቸውም ምክንያት ንብረታቸውን ማስተዳደር የማይችል ሆኖ ካልተገኘ በስተቀር የጋራ ንብረታቸውን በጋራ ያስተዳድራሉ፡፡ ሆኖም በተጠቀሱት ምክንያቶች አንደኛው ተጋቢ ብቻውን ንብረቱን የሚያስተዳድር ከሆነ ለሌላኛው ተጋቢ መረጃ የመስጠት ሃላፊነት አለበት፡፡

በገቢ ረገድ ሁለቱም ተጋቢዎች ገቢያቸውን በየራሳቸው መቀበል የሚችሉ እንዲሁም በግል ወይም በጋራ የባንክ ሂሰብ ከፍተው ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡ ይህ ማለት ግን አንደኛው ተጋቢ ሌላኛው ተጋቢ እንዲቀበልለት ስልጣን ለመስጠት የሚከለክለው ነገር የለም፡፡ በየግል የሚያገኙትንም ገቢ ሌላኛው ተገቢ ሲጠይቅ ማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡

ከንብረት በተጨማሪ በጋብቻ ውስጥ እዳ ሊኖር እንደሚችል የሚጠበቅ ነው፡፡ ልክ እንደንብረት ሁሉ እዳም የግል ወይም የጋራ ተብሎ የሚከፈል ነው፡፡ እዳው ለባልና ሚስት እና ለልጆቻቸው የዕለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማሟላት ወይም ባል ወይም ሚስት ቀለብ የመስጠት ግዴታቸውን ለመወጣት የተገቡ እዳዎች እንዲሁም ከባልና ሚስት በአንደኛው ወይም በዕዳ ጠያቂው አመልካችነት ለትዳር ጥቅም ስለመሆኑ ፍርድ ቤት የተቀበለው እዳ በጋራ የሚከፍሉት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የሚኖረው እዳ የግል ይሆናል ማለት ነው፡፡ አከፋፈሉ ሲታይ የጋራ እዳ ከባልና ሚስቱ የጋራ ሀብት የሚከፈል ሲሆን ዕዳውን ለመሸፈን በቂ በማይሆን ጊዜ ከባል ወይም ከሚስት የግል ሀብት የሚከፈል ይሆናል፡፡

በአንፃሩ የግል ዕዳ ከባለዕዳው ተጋቢ የግል ሀብት የሚከፈል ሲሆን ዕዳው ለመሸፈን በቂ በማይሆንበት ጊዜ ከጋራ ሀብት የሚከፈል ይሆናል፡፡ እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ከጋራ ሀብት ሲባል በድርሻው ልክ እንጂ የሌላኛውን ተጋቢ ጥቅም በሚነካ መልኩ ሊሆን እንደማይችል ነው፡፡
የንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
#አለ_ህግ #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share #lawsocieties
..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
#Vacancy for Lawyers
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ምስረታ  አንደኛ ዓመት መታሰቢያ በማህበሩ መ/ቤት ታስቦ ውሏል!!
***
በኢትዮጵያ የህግ ስርዓት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው የሆነውና ለአስርት ዓመታት በተከታታይ የህግ ሙያ ትውልዶች ትግል ሲደረግበት የቆየው በርካታ ባለሙያዎች በየወቅቶቻቸው አስተዋፅኦ ያደረጉበት የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር በአዋጅ ቁጥር 1249/13 ከአንድ አመት በፊት ጥር 15 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ኢንተርሌግዥሪ (ኢንተርኮቲነንታል) ሆቴል ከ ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ (1600) በላይ ጠበቆች ፣ ሚኒስትሮች ፣ የፌደራልና የክልል የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንቶች ፣ የክልል ጠቅላይ ዐቃቢያነ ህግ እና ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት በታሪክ የመጀመሪያው የሆነውን ታሪካዊ ጠቅላላ ጉባኤውን አደረገ::

ማህበሩ በህግ ከተቋቋመበት የመጀመሪያ መስራች ጉባኤው ጀምሮ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች እያደረገ ሲሆን የተቋም መሰረት የመጣልና ተቋም የመፍጠር ስራው ቅድሚያ ተሰጥቶት እየተሰራበት ያለ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሀገር የህግ ስርአት ላይ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት በርካታ ጥረቶችን እያደረገ ይገኛል:: ተቋሙ እያሳያቸው ያሉ ጅምሮች ተጠናክረው በመቀጠል  ለሀገርና ለህዝብ እንዲተርፍ ለማስቻል ዘንድ የመላው አባላቱ ፣ የህግ ማህበረሰቡ እና የባለድርሻ አካላት ድጋፍ የሚያስፈልግ ነው::

በዛሬው እለትም የማህበሩ መሪዎች በተገኙበት በማህበሩ መ/ቤት የታሪካዉን ምስረታ አንደኛ አመት ያከበረ ሲሆን በእለቱም በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይቶች ተደርገዋል::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ጥር 15 2015ዓ.ም
አዲስ አበባ
#አለ_ህግ  #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share
https://t.me/lawsocieties
ኢትዮጵያ በ2022ቱ የሀገራት የሙስና ደረጃ ስንተኛ ላይ ተቀመጠች?

ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የ2022 የሀገራት የሙስና ተጋላጭነት ደረጃን ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያም 38 ነጥብ በማምጣት ከ180 ሀገራት 94ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት አመላክቷል።

ተቋሙ "በሙስና የተደናቀፉ መንግስታት ህዝባቸውን የመጠበቅ አቅም የላቸውም፤ የህዝቡ ቅሬታም ወደ ብጥብጥ የመቀየር እድሉ ከፍተኛ ነው" ብሏል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ https://am.al-ain.com/article/corruption-perceptions-index-2022
#አለ_ህግ  #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share
https://t.me/lawsocieties
የሂሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ላይ የተደረጉ ማሻሻያያዎች
ሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 152/2011 ተሽሮ በመመሪያ ቁጥር 176/2014 ተተክቷል፡
መመሪያውን ማሻሻል ካስፈለገባቸው ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡-
1. የታክስ ሒሳብ መዝገብ ሲዘጋጅ ሊሟሉ የሚገባቸው ዝርዝር ሁኔታዎች በነባሩ መመሪያ በግልጽ ስላለተገለፁ፣
2. በታክስ ባለስልጣኑ ቅ/ጽ/ቤቶች ተመሳሳይ አተረጓጎም ወይም አፈጻጸም እንዲኖር እና አገልግሎት አሰጣጡን የተቀላጠፈ ለማድረግ፤
3. የነባሩ መመሪያ አቀራረጽ ከታክስ ህግ ያለፈ እይታ ያለው ይመስል ስለነበር ይሕን ብዥታ ለመቅረፍ፣
4. ግብይት ሳይኖር ወይም ሕገ-ወጥ ደረሰኞች ሲቀርቡ ተቀባይነት እንደሌላችው በግልጽ ማመላከት በማስፈለጉ ምክንያት መመሪያውን ማሻሻል አስፈልጓል፡፡

በዚህም መሰረት በአዲሱ መመሪያ ውስጥ እንዲካተቱ ከተደረጉት ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡-
1. የውጪ ምንዛሬ ትርፍ ወይም ኪሳራ መቼ መመዝገብ እንዳለበት፤
2. የብድር ውል ሰነድን የመመዝገብ ስልጣን ባለው አካል ቀሪ ሆኖ ነገር ግን ብድሩ በባንክ የተከፈለ ስለመሆኑ የሚያሳይ ሰነድ መቅረብ እንዳለበት፤
3. የቴምብር ቀረጥ በብድሩ ላይም ሆነ ሰራተኛ ሲቀጠር መከፈል እንዳለበት እና
4. ለወጪም ሆነ ለገቢ የሚቀርቡ ማስረጃዎች ህጋዊ ብቻ እንዲሆኑ ሲባል በመመሪያው እንዲካተት ተደርጓል፡፡
በአጠቃላይ የተሻሻለው የሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 176/2014 ታክስ ከፋዩ የተቀላጠፈ አገልግሎት አግኝቶ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴውን እንዲያከናውን በሚያመች ሁኔታ የተዘጋጀ መመሪያ ነው፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር
#አለ_ህግ #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share #lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ቻይና በኦሮሚያ የዜጋዋን ግድያ ተከትሎ ለዜጎቿ ማስጠንቀቂያ አወጣች! //BBC//

አንድ ቻይናዊ በኦሮሚያ ክልል ገብረ ጉራቻ ከተማ ከተገደለ በኋላ ቻይና በክልሉ ለሚንቀሳቀሱ ዜጎቿ ማስጠንቀቂያ ሰጠች።

ኤአፍፒ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲን ጠቅሶ እንደዘገበው ሰኞ ጥር 22/2015 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ በሰሜን አቅጣጫ ገብረ ጉራቻ ከተማ 9 የቻይና ዜጎች በታጣቂ ቡድኖች ተኩስ ተከፍቶባቸው ነበር።

ተኩስ ከተከፈተባቸው ቻይናውያን መካከል አንዱ ሕይወቱ ማለፉን ሮይተርስ እና ኤኤፍፒ የዜና ወኪሎች በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲን ዋቢ አድርገው ዘግበዋል።

ኤምባሲው የዜጋውን መገደል ይፋ ባደረገበት መግለጫው፤ ጥቃቱን ያደረሰው ታጣቂ ቡድን ማን እንደሆነ እንዲሁም የጥቃቱ ዒላማ የሆኑት ቻይናውያን ማንነትንም አልገለፀም።

የቻይኛ ኤምባሲ መግለጫ አንድ ቻይናዊ መገደሉን ከመጥቀስ ውጪ፣ በሌሎች ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ያለው ነገር የለም።

ከአዲስ አበባ 163 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ከተማ በቻይናውያኑ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ኤምባሲው ባወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ ላይ፤ “ከፍተኛ የአደጋ ስጋት ባለበት አካባቢ ከሆናችሁ፤ በአስቸኳይ ደኅንነቱ ወደ ተጠበቀ አካባቢ መውጣት አለባችሁ” ብሏል።

ኤምባሲው በኦሮሚያ ክልል እና በአጎራባች ክልሎች በጦር መሳሪያ የታገዘ ጥቃት፣ አፈና እና ዘረፋ የተስፋፋ ነው ብሏል።

ዘገባው ፦ የቢቢሲ ነው!
Do you find it easy or difficult to live peacefully with others?
Anonymous Poll
46%
easy
47%
difficult
12%
None ⁉️
ለእጩ ዐቃቤ ሕግነት መደብ ላይ ለመቀጠር የ2ኛ ዙር ፈተና ለወሰዳችሁ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፤
ተቋማችን እጩ ዐቃብየነ ህግን ለመቅጠር መስከረም 06 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሰረት የውድድር መስፈርቱን አሟላልታችሁ ከነበራችሁ ተወዳዳሪዎች መካከል የመጀመሪያ ዙር ፈተናውን ያለፋችሁ ተወዳዳሪዎች የሁለኛ ዙር ፈተና የተሰጣችሁ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሰረት በሁለተኛ ዙር ፈተናው ያገኛችሁት ውጤት ከዚህ በታች የተገለፀ ሲሆን በፈተናው ውጤት ላይ ያላችሁን ቅሬታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበቅ ቀን ጀምሮ ባሉት 4 (አራት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለዐቃብየነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ፅ/ቤት በፅሁፍ እንድታቀርቡ እየገለፅን የፈተና ውጤታችሁ 60 (ስልሳ) እና ከዛ በላይ የሆነ ተወዳዳሪዎች ፈተናውን ያለፋችሁ ሲሆን የካቲት 01 ቀን 2015 ዓ.ም ቀን የዐቃብየነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ ሪፖረት እንድታደርጉ እያገለፅን ውጤታችሁ ከ55-59 የሆናችሁ ተጠባባቂ መሆናችሁን እናሳውቃለን፡፡
የዐቃብየነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባዔ ጽ/ቤት
#አለ_ህግ  #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share #lawsocieties
https://t.me/lawsocieties