አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#United Insurance Company#

▪️1: Trainee Underwriting/Trainee Claims Officer
▪️2: Property Administration Officer
▪️3: Human Resource Officer/Personnel Officer
▪️4: Attorney
▪️5: Driver II/CEO Driver
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://bit.ly/3KNs5qg

▪️Deadline - September 11/22
#Enat Bank SC#

▪️1: Business Development Officer
▪️2: Legal Aid
▪️3: Senior Business Research Management Officer
▪️4: Senior IS Auditor
▪️5: Branch Manager Grade B
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://bit.ly/3TWvw2j

▪️Deadline - September 10/22
NBE Directive (1).pdf
1.8 MB
New directive Alert📍📍📍The National Bank of Ethiopia isused a directive that requires every person residing in Ethiopia (includes Ethiopians and foreigners having a permanent or temporary residence permit) to convert all of their foreign currency into Birr within 30 days of their entry in to Ethiopia. Those acquiring #forex through gift or donation before September 5 are also required to convert the same within 30 days as of today. The directive entered into force as of today.
Religious Radio and TV Licensing Directive_899.pdf
437.2 KB
የሃይማኖት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 899/2014
ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶች
***

* ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ በተወሰኑ የፍትሐ ብሔር እና የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።

* የመጀመሪያውን ማሻሻያ ያደረገው አዋጅ ቁጥር 65/89 ነው።
* ይህ አዋጅ በፍ/ሕ/ቁ 2851 እና 3ዐ6ዐ ላይ ማሻሻያ አድርጎባቸዋል።
* ማሻሻያው የሚመለከተው ባንክ በመያዣ የተያዙ ንብረቶች አሻሻጥ ሥርዓትን ነው።
* ባንክ በመያዣ የያዘውን ንብረት ወደ ፍ/ቤት መምጣት ሳያስፈልገው ራሱ እንዲሸጥ።
* የሚያደርገ ስምምነት ሕጋዊ ውጤት እንዲኖረው ተደርጓል።
* አዋጅ ቁጥር 97/9ዐ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን አዋጅ ሽሮታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለባንክ በመያዣ የተሰጠ የንግድ መደብርን በተመለከተ አዋጅ ቁጥር 98/98 በቀድሞው የንግድ ሕጉ ላይ ማሻሻያ አድርጓል።
* እነዚህ አዋጆች ባንክ በመያዣ የያዛቸውን ንብረቶች ራሱ የውል ጊዜው ተጠናቆ ብድር ካልተመለሰ እንዲሸጥ የሚያደርገውን ስምምነት ህጋዊነት ይቀበላሉ።
* አዋጆቹ ከመውጣታቸው በፊት እና በኋላ በመያዣ በተሰጡ ንብረቶች ላይ ልዩነት አድርገዋል።
* አዋጆቹ ከመውጣታቸው በፊት ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ ባንኩ የተዋዋዮቹ ስምምነት ሳያስፈልገው ንብረቶቹን ራሱ ለመሸጥ ህጉ መብት ሰጥቶታል።
* አዋጆቹ ከወጡ በኋላ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ ራሱ ለመሸጥ ግን ስምምነት ያስፈልገዋል።
* ባንኩ ንብረቶቹን ራሱ ለመሸጥ ስምምነት ካላደረገ የፍትሐብሔር ህጉ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ።
* በአሻሻጥ ሥርዓቱ ላይ ከተደረገው ለውጥ በቀር የፍትሐብሔር ህጉ ሆነ የንግድ ህጉ ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል።
* በአዲሱ የንግድ ሕግ በአንቀጽ 654 ሥር የተቀመጡ ድንጋጌዎች ንግድ ባንኮች በአዋጁ የተሰጠንን መብት የሚሸረሽር ነው በሚል ቅሬታ እያቀረቡበት ነው ።
📌* በዚህ አንቀጽ ሥር የተቀመጠው መሠረታዊ ድንዳጌ፣ ‹‹…የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ፣ የንብረት ዋስትና ያላቸውን፣ የቅድሚያ መብት ያላቸውን፣ እንዲሁም ባለሀብትነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የተደረጉ የሽያጭ ውሎች ያሏቸው ገንዘብ ጠያቂዎችን ጨምሮ፣ በማናቸውም ገንዘብ ጠያቂዎች ክፍያ ለማስፈጸም በተናጠል የሚደረጉ ክርክሮች፣ በሙሉ ባለ ዕዳው ወይም በመልሶ የማደራጀት ኃላፊው በተናጠል ክፍያ ለማስፈጸም የሚደረጉ ክርክሮች እንዲቋረጡላቸው ጥያቄ ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው በመጠባበቂያ ጊዜው ወቅት በሕግ ተቋርጠው ይቆያሉ፤›› የሚል ነው፡፡
📌* በዚህ የአዲሱ ህግ ድንጋጌ እና በጠቅላላው ምዕራፍ 3 ላይ የተካተቱ ድንጋጌዎች መሰረት አንድ ተበዳሪ ያለበት ብድር ተበላሽቷል ( bad debit) ሆኗል ከመባሉ አስቀድሞ ብድሩን ሊከፍል የሚችልበት አማራጭ እድል ይሰጠዋል።
📌* ይህም በብዙዎች ኢ- ህገመንግስታዊ እና ኢ-ፍትሃዊ ነው ተብሎ ከተረቀቀበት ጊዜ አንስቶ ሲተች የነበረውን አዋጅ ቁ. 90/97 እና አዋጅ ቁጥር 98/98 የማሻሻል የህግ ውጤት ስላላቸው የንግድ ህጉ አካሄድ ይበል እሚባል ነው ።

💼#ዳንኤል ፍቃዱ (ጠበቃና የህግ አማካሪ)
https://t.me/lawsocieties
የመድን ህግ -ቅሪት ሰ/መ/ቁጥር 204256

በመኪና ላይ ለደረሰ ጉዳት ለማስጠገኛ ወጪ ክፍያ የሚቀበል የመኪና ባለቤት ከጥገና የሚቀሩ ቅሪቶችን በዓይነት ወይም ግምታቸውን በገንዘብ ለመድን ሰጪው ድርጅት ሊመልስ ይገባል፡፡

የጉዳት ካሳ የመክፈል ሀላፊነት ያለበት የመድን ድርጅት ከጉዳት የተረፉ ቅሪቶች በዓይነት እንዲሰጠው ወይም በዋጋቸው ልክ ከሚከፍለው ላይ እንዲቀነስለት ለመጠየቅ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ማቅረብ ሳይኖርበት በመከላከያ መልሱ ላይ ጥያቄውን ማቅረብ ይችላል፡፡
#Abrham_Yohanes
የአዲስ አበባ የህግ ምሩቃንን ያገለለው የስልጠና እና ስራ ዕድል
የኢትዮጵያ ፍትህ ስርዓት አዳዲስ የህግ ምሩቃንን በዳኝት እና በዐቃቤ ህግነት አሰልጥኖ የሚቀጥር ነው።


የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ሰልጣኞች በቀጥታ የፍትህ ስርዓቱን ከመቀላቀላቸው በፊት የተግባር ልምምድ እንዲያገኙ ማስቻል ነው። 

የ አዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ተመራቂዎች  “በአዲስ አበባ የፍትህ አካላት የቅድመ ስራ ስልጠና ተቋም ባለመኖሩ ዓቃቤ ህግ ወይም ዳኛ ሆነው ለመሥራት መቸገራቸውን ይናገራሉ። ወደ ክልልሎች ሲሄዱም ስልጠና ለማግኘት የነዋሪነት መታወቂያና ቋንቋ እንደ ቅድመ ሁኔታ በመቀመጡ ስልጠናውን ማግኘት ሳይችሉ ይቀራሉ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ የህግ ተመራቂ ተማሪዎች በየአከባቢያቸው የመሰልጠንና የመስራት ህገመንግስታዊ መብታቸው ተገፎ በማያውቁት አከባቢ ተገደው ሄደው እንዲሰለጥኑ እና እንዲሰሩ ሆኗል በዚህም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየገጠው ይገኛል ተማሪዎቹም በየአከባቢአቸው ስልጠናውና የስራ እድል እንዲሰጣቸው ይጠይቃል ።
የአዲስ አበባ ነዋሪ የህግ ተመራቂ ተማሪዎች!!
Justice for addis ababa dweller law graduate student!!
Via Santa
#share for Justice
ፍትህ እንድናገኝ ሼር በማድረግ ድምፅ ይሁኑን🙏🙏
#መረጃ

"ለግል መገልገያ እንዲውሉ ወደ ሀገር የሚገቡ/የሚወጡ ዕቃዎች ሁኔታን የሚወስነው በሥራ ላይ ያለው መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 51/2010) ለሕገ ወጥ ንግድ በር የከፈተ እና አገልግሎት አሰጣጡ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ በመሆኑ ዓለምአቀፍ አሠራሮችን በተከተለ አኳኋን መመሪያውን አሻሽል ማውጣት በማስፈለጉ" በሚል ምክንያት ለግል መገልገያ እንዲውሉ ወደ አገር የሚገቡ ወይም ከአገር የሚወጡ ዕቃዎችን ለመወሰን መመሪያ ቁጥር 923/2014 ከነሀሴ 12/2014 ጀምሮ ተፈፃሚ እንዲሆን በገንዘብ ሚኒስቴር የተሻሻለው መመሪያ ይፋ ወጥቷል፡፡

በቀደመው መመሪያ በርካታ የቁሳቁስ አይነቶች ወደ ሀገር ውስጥ ከቀረጥ ነጻ ለማስገባት የሚፈቅደው መመሪያ በተሻሻለው አዲሱ መመሪያ መጠኑን ወደሚከተለው ሰንጠረዥ አሳጥሯል፡፡ ሙሉ መመሪያውን ማንበብ ለምትፈልጉ ከታች ይመለከቱ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የኪራይ ቤቶችን ዋጋ ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በዚህ አመት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል!

ለኪራይ የሚዘጋጁ ቤቶችን ዋጋ ደረጃ ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በዚህ አመት ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ተናገሩ።በተለይ በከተሞች ያለው የመኖሪያ ቤት ከራይ መወደድና የአከራይና ተከራይ ጭቅጭቅ መላ ሊበጅለት እንደሚገባ በርካቶች ያምናሉ።

ለችግሩ እልባት ለመስጠት ተዘጋጅቶ ሚኒስትሮች ምክር ቤት የደረሰው ረቂቅ አዋጅ፥ የኪራይ ውል ጊዜን ከመወሰን ባለፈ ለኪራይ የሚዘጋጁ ቤቶች ሊያሟሏቸው የሚገቧቸውን መሰረተ ልማቶች በግልጽ ያስቀምጣል ብለዋል።በረቂቅ አዋጁ እንደተቀመጠውም አከራዮች የኪራይ ዋጋ መጨመር ሲፈልጉ በምን ያህል ጊዜና ምን ያህል የሚለውም ተለይቷል።ተከራዮችም በኪራይ የወሰዷቸውን ቤቶች በአግባቡ መያዝ እንደሚገባቸውና ሌሎች ግዴታዎቻቸውንም አስፍሯል ነው የተባለው።

ረቂቅ አዋጁ በደላሎች የሚዘወረውን የኪራይ ቤቶች ዋጋና አቅርቦት በማስተካከል አከራይንና ተከራይን ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ይታደጋልም ተብሎ ታምኖበታል።የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒም ረቂቅ አዋጁ በዚህ አመት ፀድቆ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው የተናገሩት።
Via #EthiopiaBusinessDaily
ቂሙን በፍየሎቹ ላይ የተወጣው ግለሰብ።

አንድ ግለሰብ ከወንድሙ ሚስት ጋር በመጣላቱ የተነሳ በፖሊስ ተይዞ ይታሰራል። ነገር ግን ግለሰቡ ለካ ለምን ታሰርኩ ብሎ ቂም በመያዝ በዋስ ከተፈታ በኋላ በመገስገስ ወደ ወንድሙ ሚስት ቤት ይሄዳል።

ሲደርስ ያጣታል፥ ይበሳጭና በሰፈር ውስጥ ታስረው ይግጡ የነበሩትን ንብረትነቱ ተጣላኋት ያላት የወንድም ሚስት የሆኑትን ሁለት ፍየሎች አርዶ ሄዷል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በሀረር ከተማ ሶፊ ወረዳ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መሆኑንና ግለሰቡም በድጋሚ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው አዛዥ ምክትል ኮማንደር መሀመድ ሳፊ ገልጸዋል።
#tikvahethmagazine
https://t.me/lawsocieties
የቤት ኪራይ ሕግ ሊወጣ ነው ሲባል ሰማሁ!  ሕጉ ምን ምን መያዝ እንዳለበት ሁላችንም ሐሳብ እንስጥበት፦

የእኔን እነሆ!
                ===
1. ለምሳሌ ቤቱን ተከራይተህ ምግብ መሸጥ ትጀምርና ቤትህ ታዋቂ ይሆናል። ባለቤት ሆዬ ውጣ ይልህና አንተ ባመጣኸው ዝና good will ይነግዳል። ውጣ ብሎ ካስወጣህ በዚያ ተመሳሳይ  ሥራ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት መሥራት የለበትም።

2. ኪራይም ተመን ሊኖረው ይገባል። አንድ ቤድ ሩም፣ ሁለት ቤድ ሩም፣ ሶስት ቤድ ሩም እና ሊፍት ያለው የሌለው እንዲሁም አካባቢው አንደኛ ሁለተኛ ደረጃ ተብሎ የመነሻ እና የመዳረሻ Range ተመን ሊወጣለት ይገባል።

3. ባለፎቆች ገንዘብ ስላላቸው ለዓመታት ቤቱ ባይከራይ ጉዳያቸው አይደለም። ከሦስት ወራት በላይ ባልተከራየ ቤት እንደተከራየ ተደርጎ ግብር የሚከፍሉበት ሥርዓት ቢኖር መልካም ነው።

4. ኪራይ በዶላር መተመን በሕግ መከልከል አለበት።

5. ለረጅም ጊዜ ኪራይ ላልጨመሩ፣ የተጋነነ ኪራይ ላልጠየቁ፣ ከተሰጣቸው range በሚኒመም ላከራዩ፣ ለብዙ ዓመታት አንድ ቤተስብ ተከራይ ያላስወጡ ኢንሴንቲቭ ሊሰጣቸው ይገባል።

5. በአከራዮች ላይ የሚጣለው ግብር ገቢያቸው ከፍ ሲል የግብር መጠኑ ከፍ የሚልበት Marginal progressive taxation system ቢሆን፣ አንዳንዴም ከአነስተኛው እርከን ያገኘውን በታክስ የሚወስድበት ቢሆን መልካም ነው።

6. የመንግሥት መኖርያ ቤት ጠቅላላውን ለመንግሥት ሰራተኞችና ለጡረተኞች ብቻ ቢከራይ፣ የግል ፎቆች ላይ ነጋዴ ቢሆን ያስኬዳል፤  ነጋዴ ለነጋዴ ብቻ እርስ በርሱ ይሞሸላለቃል።

7. የራሳቸውን ቤት አከራይተው በመንግሥት ቤት የሚኖሩ ተለቅመው ሊነጠቁ ይገባል።

8. የመንግሥት መ/ቤቶች ለሠራተኞቻቸው መጠነኛ ኪራይ አስከፍለው የሚያከራዩት ቤት ቢኖራቸው ይደገፋል። አ.አ.ዩ አራት ኪሎ ሁለት ፎቅ ይዞ ቤት ለሌላቸው መምህራን ያከራያል።

9. ውል ለማቋረጥ ተከራይ ማስጠንቀቂያ መስጠት አያስፈልገውም። አከራይ ግን ለአንድ ዓመት ውል ሁለት ወር፣ ለሁለት ዓመት ውል አራት ወር፣ ለሶስት ዓመት ውል ስድስት ወር ቢሆን ከዚያ በላይ ላለው ስድስት ወር ቢሆን መልካም ነው።

10. የንግድ ቤት የኪራይ ውል ተከራይ በማናቸውም ጊዜ በማስጠንቀቂያ የማቋረጥ መብቱ ተጠብቆ ትንሹ የኪራይ ዘመን አምስት ዓመት መሆን አለበት።

11. ቤት ሲለቀቅ በጥንቃቄ ጉድለት የተበላሸ እንጂ እርጅና ብልሽት የማስተካከል ግዴታ መኖር የለበትም።

12. አከራይ ከተከራይ ጋር አንድ ግቢ የሚኖር ከሆነ የኪራይ ተመኑ ዝቅ ማለት አለበት።

13. የመንግስት ቤት የተከራዩ በኪራይ ማዳበል ቢፈቀድላቸው እጥረት ይቀርፋል።

14. ማናቸውም ቀጣሪ የግልም የመንግስትም ለሰራተኞቻቸው የኪራዩን እስከ 25% የኪራይ አበል መክፈል አለባቸው።

15. ቤት ለሌላቸው መንግስት መ/ቤት ላገለገሉ ጡረተኞች እንደ አገልግሎታቸው መጠን የቤት ኪራይ አበል ሊከፈላቸው ይገባል። ጡረተኛ እንደ ውዳቂ የማየት በመለስ ዜናዊ ለጡረተኛ ብር መስጠት ጉቶ ውኃ ማጠጣት ነው የሚለው የዱርዬ ፖሊሲ መሻር አለበት።
Guagule Teshager J
#Ministry of Finance

የታክሲ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥና ታክስ ነጻ በሚመለከት የተሰጠ ማብራሪያ


መስከረም 4/ 2015 ዓ.ም - መንግስት የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን እንዲሁም ለረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ በተለምዶ ላዳ ታክሲ በመባል የሚታወቁ ተሸከርካሪዎች በአዲስ ተሸከርካሪዎች የሚተኩበት መመሪያ ቁጥር 70/2013 አውጥቶ ስራ ላይ ማዋሉ ይታወሳል፡፡

ያገለገሉ ላዳ ታክሲዎችን የሚተኩ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ተበትነው ወደ ሀገር ገብተውና በአገር ውስጥ ተገጣጥመው ለዚሁ ዓላማ ሲቀርቡ እንዲሁም አዲስ የታክሲ ማህበራት በሚመለከት ሙሉ ለሙሉ ተበትነው የገቡና በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ ሲሆን ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ መደረጉን በገንዘብ ሚኒስቴር ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ሚኒስቴሩ በሰጠው ማብራሪያ በአዲስ አበባ ከተማ ለረጅም ዓመታት በማገልገል ላይ የሚገኙ በተለምዶ የላዳ ታክሲዎች በመባል የሚታወቁ ተሽከርካሪዎች በአዲስ እንዲተኩ በማድረግ ባለንብረቶቹን በተሸከርካሪዎቹ እርጅና ምክንያት ከሚደርስባቸው ከፍተኛ የነዳጅና የመለዋወጫ ወጪ ለማዳን፣ በገበያ ላይ ተወዳዳሪ ሆነው በመስራት ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል፣ የአከባቢ ብክለትን ለመቀነስ፣ የከተማዋን ገፅታ ለማሻሻል እንዲሁም የከተማዋን የትራንስፖርት ዘርፍ ለማዘመን ሲባል ያገለገሉ ላዳዎችን የሚተኩ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ መደረጉ ተገልጽዋል፡፡

ይህን ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት ያስፈለገው የታክሲ ተሽከርካሪዎች የቀረጥና ታክስ ነጻ ጥያቄዎች አቀራረብና አፈቃቀድ በተመለከተ የወጣውን መመሪያ በአግባቡ የመገንዘብ ችግር ስላለ መሆኑን በመጥቀስ በመመሪያ 70/2013 በተደነገገው መሠረት የታክሲ ተሽከርካሪዎች ቀረጥና ታክስ ነጻ ጥያቄዎች የሚስተናገዱት ያገለገሉ ላዳ ታክሲዎችን የሚተኩት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ተበትነው ወደ ሀገር ገብተው በአገር ውስጥ ተገጣጥመው ሲቀርቡ ብቻ ሲሆን አዲስ የታክሲ ማህበራትን በሚመለከት ትኩረት የሚያደርገውም የትራንስፖርት ዘርፉን ፍላጎት ሆኖ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በሚያዘጋጀው ሀገር-አቀፍ የትራንስፖርት ፖሊሲና ስትራቴጂ ብቻ የሚወሰን መሆኑንም አስረድቷል፡፡

በዚህም መሰረት የሚቀርቡ ጥያቄዎች የሚስተናገዱት ለዚሁ ዓላማ በወጣው መመሪያ ቁጥር 70/2013 መሰረት በማድረግ ብቻ ሲሆን በዚህ መመሪያ ግልፅ የጥያቄ አቀራረብና የአፈቃቀድ ስርዓት መደንገጉንና በተለይም በመመሪያው አንቀፅ 10 መሰረት ለታክሲ አገልግሎት የሚውሉ የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ ነጻ ጥያቄዎች መቅረብ የሚችሉት በሚከተለው መንገድ ብቻ ማለትም ፡-

የክልል መንግስታት፣ የከተማ አስተዳደሮች እና የፌዴራልና የመንግስት መ/ቤቶች ለታክሲ አገልግሎት የሚውሉ ተሸከርካሪዎች ከቀረጥና ታክስ ነፃ የሚገዙትን ተሽከርካሪዎች የሚፈልጉ የታክሲ አገልግሎት ሰጪ ማህበራት ጥያቄ ከድጋፍ ደብዳቤ ጋር ለትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ሲላክ፤

የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የታክሲ ማህበሩን የግብር ከፋይ መለያ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርፊኬት፣ የተሽከርካሪዎቹን ሊብሬ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝ ለገንዘብ ሚኒሰቴር ሲልክ፤

የገንዘብ ሚኒሰቴርም የቀረበውን ጥያቄ አግባብነት እና ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ የቀረጥ ነፃ መብቱን በመስጠት ለጉምሩክ ኮሚሽን ሲልክ መሆኑን ተብራርቷል፡፡

ከዚህ መመሪያ ውጭ የሚቀርቡ ጥያቄዎች የህግ መሰረት የሌላቸው በመሆኑ ተቀባይነት የሌላቸውና ከመመሪያው ውጪ የሚቀርቡ የታክሲ ተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ ነጻ ጥያቄዎች ከገንዘብ ሚኒስቴር እውቅና ውጭ መሆናቸውን በማወቅ ህብረተሰቡ ከተጠቀሰው ህጋዊ አሰራር ውጪ ማህበር እናደራጃለን፣ ቀረጥና ታክስ ነጻ አስፈቅደናል ወይም እናስፈቅዳለን ከሚሉ አካላት ራሱን መጠበቅ እንዳለበት የገንዘብ ሚኒስቴር ያሳስባል፡፡
ከቅርቡ ጊዜ ወዲህ የገንዘብ መግዛት አቅም እየወደቀ ነው ከሚል Speculation በመነሳት ያልተጠበቀና የናረ ፍላጎት በመፈጠሩ ምክንያት በተሽከርካሪና ቋሚ ንበረቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ተከስቷል።

የተከሰተውን ከፍተኛ ጭማሪ ለማርገብ በተለይ በኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ ሁሉም የታክስ አይነቶች ሱር ታክስ፣ ኤክሳይዝ ታክስ ወዘተን በማንሳት 15 % ብቻ ተቀርጠው እንዲገቡ መፈቀዱ ትልቅ እርምጃ ነው። በተሽከርካሪ ላይ የተወሰደው ዋጋ የማረጋጋት ውሳኔ በተጠና መልኩ በሌሎቹም ዘርፉች ቢቀጥል ሌሎች መፍትሔጨ የሚሹ ችግሮች እንደተጠበቁ ሆነው ኢኮኖሚያችን ላይ ትልቅ እመርታ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ።

በነጻ ገበያ ስርዓት፣ ዜጎች ግብይታቸውንና አገልግሎታቸውን በሚያዋጣቸውና በሚጠቅማቸው መንገድ የማካሄድና እውቀታቸውን የመሸጥ መብት አላቸው። ይህ ማለት ግን ሕግ፣ ስርዓት የማይገድባቸውና የዜጎች የጋራ ጥቅም የማይገዛቸውና ኋላፊነት የሌለባቸው ናቸው ማለት አይደለም። አገልግሎታቸውን በተገቢው መንገድ የመስጠት፣ የትርፍ ሕዳጋቸውን ተመጣጣኝ የማድረግና ላተረፉት ትርፍ ተገቢውን መረጃ የማቅረብ፣ ተገቢውን ግብር እና መንግስታዊ ግዴታ መወጣት ይጠበቅባቸዋል። ይህ ካልሆነ መንግስት ጣልቃ ገብቶ ማረጋጋቱ የሚጠበቅ ነው። የዜጎችን የመግዛት አቅም በገንዘብ ከመደገፍ ጀምሮ፣ ሞኖፖሊንና ኦሊጎፖሊን በመቆጣጠርና ገበያው በምርት እስከ ማጥለቅለቅ የደረሰ እርምጃዎችን መውሰድ በምዕራባውያን ዘንድ የተለመደ አሰራር ነው።

የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አደጋና ስጋት ሲደቀንበት አደጋውን ለመቀልበስ ሲባልና ከጥቂት ነጋዴዎች ትርፍና ሐብት ማከማቸት ፍላጎት በላይ የሀገርና የሕዝብ ደህንነት በማስቀደም መንግስት ጣልቃ መግባታቸው የተለመደ ነው። መንግስት በሕግ የተሰጡት ኢኮኖሚው ማቃኛ መንገዶች ተጠቅም የእርምት ይወስዳል።

ከተለመዱት የዋጋ ማረጋጊያ እርምጃ መካከል አንዱ የአቅርቦት ወይም የምርት ዋጋ ከመጠን በላይ ሲንር ተጓዳኝ እና ተመሳሳይ (Complementary, Supplementary ) ምርቶች ላይ የግብር ቅናሽ ማድረግ ነው ። ለኑሮ እጅግ በጣም አስፈላጊ ምርት ሲሆኑ ደግሞ ተጓዳኝ ወይም ተመሳሳይ ምርቶችን አስመጥቶ ያለ ትርፍ ሕዳግና ያለ ተጨማሪ ወጭ ማከፋፈልና መሸጥም ሌላው ግሽበትንና ዋጋ ማረጋግያ መንገድ ነው።

በነዳጅ ከሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ጋር ሲወዳደር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ዋጋ ከ50% በላይ ቅናሽ ይኖረዋል። ውሳኔው የአየር ብክለት ከመቀነስ፣ በርካታ መለዋመጫን ከማስቀረትና ከዘይትና ከነዳጅ ግዢ ከመታደጉም በላይ ያበጠውን የተሽከርካሪ ዋጋ እንደሚያስተነፍሰው ጥርጥር የለው። ይበል የሚያሰኝ ትልቅ እርምጃ ነው።

ሌላው ሊታሰብበት የሚገባው ጉዳይ (Windfall gain) ነው አብዛኛው የተሽከርካሪ ነጋዴ ሕጋዊ ደረሰኝ እየሰጠና ትርፉን እያሳወቀ አይደለም። ለምሳሌ ዛሬ ላይ አንድ ሲዙኪ ዲዛየርን ስም ለማዞር መንገድ ትራንስፖርት የሚገምተው ከ750 ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር ነው። ተጨማሪ ወጭዎች ተደማምረው የተሽከርካሪው የሽያጭ ዋጋው በአማካይ እስከ ከ1.2 ሚሊየን ብር ቢደርስ፣ ተሽከርካሪው ገበያ ላይ አሁን የሚሸጥበት ዋጋ 2 ሚሊየን 100 ሺህ ሰለደረሰ ሻጩ ከአንድ ሚሊየን እስከ አንድ ሚሊየን አንድ መቶ ሺህ ብር ድረስ ትርፍ እያገኙ በመሸጥ ላይ ናቸው። በነጻ ገበያ ስርዓት በፈለጉት ዋጋ መሸጥ መብት የመሆኑን ያህል አብረውት የሚመጡ ግዴታዎች ስላሉት ለተገኘው ገቢ የትርፍ ግብርና ለተፈጠረው እሴት ደግሞ ተ.እ.ት መክፈል የዜግነት ግዴታ ነው።

የኑሮ ውድነት አናቱ ላይ እያናጠረበት ከሚያገኛት ደሞዝና ጥቅማጥቅ ላይ እግር በእግር እየተከታተለ እስከ 35% የገቢ ግብር የሚያስከፍል መንግስት ከ50 % እስከ 100% እያተረፉ ገቢን በመሰወርና ደረሰኝ በመከልከል ግዴታቸውን የማይወጡት ዜጎችን ቸል ሊል አይገባም። የትርፍ ግብር እና ተ.እ.ት ክፍናን ላላሳወቁና በሰወሩ ላይ አስተማሪ በሆነ መልኩ ትርፍ ግብር ከነመቀጫው ማስከፈል አለበት። ሁሉም ሰው በሀገሩ ላይ በዜግነቱ እኩል ነው። ተጠቃሚ በሆነበትና ሐብት በአፈራበት ልክ ትርፉን በማሳወቅና ግብር በመከፍል የዜግነት ግዴታውን በአግባቡ መወጣት ለድርድር የሚቀርብ አይደለም።
Mushe Semu
ቅድመ ጭነት የዉጭ ንግድ ብድር ( Pre- shipment Export Credit):-

ባንኮች የዉጭ ንግድ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ነጋዴዎች የሚሰጡ ቅድመ ጭነት ብድር አይነት ነው ።

እንዲሁም የውጭ ንግድ ላኪነት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ለውጭ ጭነት የተዘጋጁ እቃዎች እስከ መዳረሻቸዉ ድረስ የሉትን የተለያዩ ወጪዎችን ለመሸፈን የሚያገለግል ቅድመ ጭነት ብድር የሚወስዱት ብድር አይነት ነዉ ።

ቅድመ ጭነት ብድር ብዙ ጊዜ ባንኮች ከሌሎች ብድር አይነት የተለየ ትኩረት ይሰጣለሁ እንዲሁም ለብድሩ ምስመለሻ ዝቅተኛ ወልድ ተመን ያስከፍላሉ ። ለዚህም ትልቁ ሚክንያት ባንኮች ለሰጡት ብድር ማስመለሻ እና አከፋፈል ላኪዎች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሪ ላይ ብድሩን እንዲከፍሉ በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ክምችታቸዉን አሳድጋለሁ ። ይሁንና ባንኮች ለብድሩ ማስመለሻ የሚሆን ቋዋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረት የሚጠየቁ ሲሆን በተጨማሪም ላኪው  ( ተበዳሪዉ) ከባህር ማዶ ገዢ ጋር የተዋዋሉትን የሽያጭ ዉል ( Sales Contract ) መኖሩን ያረጋግጣለሁ ። እንዲሁም አንዳንድ ባንኮች ለብድሩ ማስመለሻ የሚሆን ንብረት እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠይቁም ላይጠየቁም የሚችሉበት ሁኔታ ይኖራል ነገር ግን የተረጋገጠ እና አስተማማኝ ሰንድ ከሚመለከተዉ የጉምሩክ መስሪያ ቤት በላኪ አማካኝነት በሚቀርብ  የውጭ ጭነት እደት መሟላቱን አረጋግጦ ብድር አገልግሎት ይሰጣለሁ  ።

ብዙአየሁ ኃይለማርያም አስፋዉ

የቅርንጫፍ ባንክ ሥራ አስኪያጅና የባንክ አገልግሎት ዘርፍ አማካሪ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
https://t.me/lawsocieties
#Nile Insurance SC#🚩For Fresh & Exp

https://bit.ly/3BpaYHc👈👈👈

▪️ 1 - Attorney I
▪️ 2 - Human Resource Officer
▪️ 3 - Senior Procurement Officer
▪️ 4 - Branch Manger (Grade V Branch)
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧

https://bit.ly/3BpaYHc

▪️Deadline: Sept 23, 2022
Limits of Birr holding (2).pdf
487.3 KB
የ ኢ ት ዮ ጵ ያ ብ ሔ ራ ዊ ባ ን ክ NATIONAL BANK OF ETHIOPIA ADDIS ABABA


Directives No. FXD/49/2017

Limits on the Birr and Foreign Currency Holding

in the Territory of Ethiopia

Whereas, it has become necessary to limit the Birr holding amount for persons entering into and departing from Ethiopia:

Whereas, it has also become necessary to set the conditions, limitations and circumstances under which Ethiopians, residents of Ethiopia, and non-residents or any other person who may possess and utilize foreign currency:

Now, therefore, pursuant to Articles 18(6) 20 (2) and 27(2) of the National Bank of Ethiopia

Establishment (as Amended) Proclamation No. 591/2008, these directives are hereby issued as follows:

Short Title
These directives may be cited as "Limits on Birr and Foreign Currency Holding Directives No. FXD/49/2017