አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ማስታወቂያ
ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በዝዉዉር ለመመደብ አመልክታችሁ የጽሁፍ ፈተና ተፈትናችሁ ውጤታችሁ ከተገለጸው ውስጥ፡-
ለሴቶች እና ለአካል ጉዳተኞች 55 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጣችሁ፣
ለወንዶች 60 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጣችሁ፣
ለኢንተርቪው/ቃለ-መጠይቅ የተመረጣችሁ ስለሆነ እራሳችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ይዛችሁ ቅዳሜ በ28/12/2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሠዓት ላይ ሜክሲኮ በሚገኘው አ/አ ፍትህ ቢሮ 5 ፎቅ ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

የዓቃቢያነ ህግ አስተዳደር ጉባዔ
via #ስለ_ህግ
ማስታወቂያ

የህግ መዉጫ ፈተና ለወሰዳችሁ ተፈታኞች በሙሉ

በሰኔ ወር የህግ መዉጫ ፈተና የተሰጠ መሆኑ ይታወቃል በመሆኑም ፈተናዉን ወስዳቹህ ከዉጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ማቅርብ የምትፈልጉ ተፈታኞች ከነሃሴ 23/2014 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 04/2014 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት ብቻ በዩኒቨርሲቲያቹሁ በኩል ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ማንኛዉንም ቅሬታ በትም/ም/ፈ/አገልግሎት በኩል የማይስተናገድ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

ፈተናዎች ምርት ምዘና አገልግሎ
የትም/ም/ፈ/አገልግሎት
ቀን 20/12/2014 ዓ.ም
#የአማካሪ_ምክር_ቤት_ጉባኤ_ተካሄደ
(20/12/2014 ዓ.ም) የአማካሪ ምክር ቤት ጉባኤ ዛሬ በጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ስብሰባውን አካሂዷል፡፡


በጉባኤው ላይ የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም፣ የ2015 ዓ.ም ዕቅድና የክፍያ መመሪያዎችን የሚመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ለውይይት የቀረቡ ሲሆን ከአማካሪ ምክር ቤቱ አባላት በዕቅዱና የክፍያ መመሪያው ላይ ቢስተካከል፣ ቢጨመር አልያም ደግሞ ቢቀነስ የሚሏቸውን ሃሳቦች ሰጥተዋል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የህግ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ላይ ኢንስቲትዩቱ ባለፏት አስር ዓመታት የሰራቸው ስራዎች የሚመሰገን መሆኑን የገለጹት አንድ የአማካሪ ምክር ቤቱ አንድ አባል አሁን ደግሞ የህግ ተማሪዎች መውጫ ስርዓቱ በትምህርት ሚንስቴር የተለያዩ ማሻሻያዎች እንደተደረጉበት በመጥቀስ ኢንስቲትዩቱም ይህንን መነሻ በማድረግ ዕቅዱን እንዲያወጣና እንዲከልስ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩለ፤ ኢንስቲትዩቱ ጠበቆችን፣ ዳኞችን፣ ፖሊሶችንና ሌሎች የፍትህ ዘርፉ መሪ ተዋናዮችን ለማሰልጠን እያደረገ ያለው ጥረት የሚያስመሰግን መሆኑን ከመድረክ የተነገረ ሲሆን በተለያ በ2014 ዓ፣ም የአዲስ አበባ ፍርድ ቤቶች ላይ የሰራው ክፍተትን የመሸፈን ተግባር ሊቀጥል እንደሚገባው ተገልጧል፡፡
በስተመጨረሻም የፌዴራል የፍትህና የህግ ኢንስቱትዩት የተለያዩ ስልጠናዎችን በሚሰጥበት ወቅት ለአሰልጣኞች፣ ለሰልጣኞች ክፍያ፣ ለልዩ ስልጠናዎች ክፍያ፣ የፈተና አገልግሎት ክፍያ፣ ለጥናትና ምርምር ስራዎች ክፍያ፣ ለአስተባባሪዎችና መሰል የተቋሙ ክፍያዎች ላይ የማሻሻያ ረቂቅ መመሪያ ለአማካሪ ምክር ቤቱ ቀርቦ ቢስተካከሉ ይበጃሉ ተብለው የተነሱ ጥያቄዎች የማብራሪያ ሃሳቦችና ጥቆማዎች የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ ተሰጥቶባቸው ጉባዔው ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

ዘገባው፡- የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

https://t.me/lawsocieties
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties/7163
new Criminal procedure research (1).pdf
1.2 MB
https://t.me/lawsocieties/7162
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Forwarded from ሕግ ቤት
2014 ቅሬታ ፎርም.docx
13.8 KB
በexit exam ውጤት ቅሬታ ያላችሁ ቅሬታችሁን ለሚመለከተው አካል ለማመለከት የሚረዳችሁ ቅፅ ነው።
መልካም የእረፍት ቀን እና እሁድ ይሁንላችሁ❗️🙏
የመልካምነት ትንሽ የለውም ሼር/Share በማድረግ ለብዙዎች ተደራሽ እንሁን።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Share
https://t.me/lawsocieties
የዳኞች ዓለም አቀፍ ሕግ ዕውቀት ዝቅተኛ መሆን የባለሥልጣናትን ተጠያቂነት ዝቅተኛ እንዳደረገው ተገለጸ
የአዲስ አበባ የህግ ምሩቃንን ያገለለው የስልጠና እና ስራ ዕድል
የኢትዮጵያ ፍትህ ስርዓት አዳዲስ የህግ ምሩቃንን በዳኝት እና በዐቃቤ ህግነት አሰልጥኖ የሚቀጥር ነው። የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ሰልጣኞች በቀጥታ የፍትህ ስርዓቱን ከመቀላቀላቸው በፊት የተግባር ልምምድ እንዲያገኙ ማስቻል ነው። 

የ አዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ተመራቂዎች  “በአዲስ አበባ የፍትህ አካላት የቅድመ ስራ ስልጠና ተቋም ባለመኖሩ ዓቃቤ ህግ ወይም ዳኛ ሆነው ለመሥራት መቸገራቸውን ይናገራሉ። ወደ ክልልሎች ሲሄዱም ስልጠና ለማግኘት የነዋሪነት መታወቂያና ቋንቋ እንደ ቅድመ ሁኔታ በመቀመጡ ስልጠናውን ማግኘት ሳይችሉ ይቀራሉ።
በተጨማሪም ከክልሉ ነዋሪ ውጪ እድሉን እንደማይሰጡና ቅድሚያ ለክልሎቹ ተመራቂዎች እንደሆነም ይነገራቸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ "አዲስ አበባ የራሷ የሆነ የፍትሕ አካላት ማሰልጠኛ ተቋም ባይኖራትም ከፌደራል የፍትህ እና የህግ ምርምር ተቋም በመቀናጀት ስልጠናው እየሰጠን መጥተናል፣ አሁንም እንሰጣለን። በመሆኑም ተቋም አለመኖሩ ችግር የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም” ባይ ናቸው። ከተማዋ የራሷ የሆነ የፍትህ አካላት የቅድመ ሥራ ማሰልጠኛ ተቋም እንዲኖራት እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ  የህግ ባለሙያ “አንድ የህግ ባለሙያ  ስልጠና ካልወሰደና በዓቃቤ ህግነት ወይም በዳኝነት ተቀጥሮ የመስራት አድሉ ጠባብ ነው ለዚህ ችግር መፍትሄው  አዲስ አበባ የራሷ የሆነ የህግ የቅድመ ስልጠና ማዕከል ማቋቋም ወይም እንኳን አዲስ አበባ የፌደራል መንግስት መቀመጫ እስከሆነች ድረስ ነዋሪዎቿ በፌደራል የፍትህ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ገብተው ስልጠናውን እንዲወስዱ ሊፈቀድላቸው ይገባል" ብለዋል።
አዲስ ዘይቤ
via #tikvahethmagazine
@lawsocieties
👉👉 ስለ ቼክ ይርጋ ጊዜ 👈👈👈
።።።።።።👇👇👇👇👇👇።።።።።።።
ቼክ የወጣበት ቀን ከግምት ሳይገባ በቼክ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በሚከተሉት 6 (ስድስት) ወራት ውስጥ እንዲከፈል ባንክ መቅረብ እንዳለበት በንግድ ሕግ ቁጥር 855 ሥር ተመልክቷል፡፡
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
በንግድ ሕግ ቁጥር ቁጥር 881(1) ሥር ደግሞ በቼክ የሚገደዱ ሰዎች ላይ ቼኩን የተቀበለው ሰው ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼኩን ለክፍያ ባንክ ለማቅረብ የተወሰነው ጊዜ ካለፈ ጀምሮ እስከ (6) ስድስት ወር ድረስ ነው፡፡
በመሆኑም ቼክ የተቀበለ ሰው፣ ቼክ ሰጪው ላይ የፍትሀ-ብሄር ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼኩ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በ 1 (አንድ) ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማይገደቡ መብቶች
።።።።።።።👆👆👆👆።።።።።።።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ሰብአዊ መብቶችን እንደአስፈላጊነቱ የሚገድቡ ህጎችን የማውጣት ስልጣን የሚያገኝበት አዋጅ ነው። የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት በፌዴራል ደረጃ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የሚከተሉትን ሕጋዊ ምክንያቶች አስቀምጧል።

1. የውጭ ወረራ ሲኖር

11. ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል እና በመደበኛው ህግ የማስከበር ስርዓት መቆጣጠር የማይቻል የሕግና የሥርዓት መፈራረስ ሲኖር

III. የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም

V. ተላላፊ በሽታ ሲመጣ ከላይ በተገለጹት ሁኔታዎች ውስጥ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥቶ የዜጎችን መብት ይገድባል። ነገር ግን እንደየቦታው አንዳንድ ሰብአዊ መብቶች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ እንኳን በፍፁም ሊጣሱ አይችሉም።

Non-Derogable Rights in a State of Emergency

A state of emergency is a circumstance in which a government is given the authority to enact laws that would limit essential human rights to ensure the safety and security of its citizens. The FDRE Constitution provides the following legitimate reasons to declare a state of emergency at the federal level:

I. external invasion
II. a breakdown of law and order which endangers the Constitutional order and which

be controlled by the regular law enforcement agencies and personnel,

III. a natural disaster

IV. an epidemic

In the above circumstances, the government enacts a state of emergency and it will derogate or limit its citizens' rights. However, depending on the jurisdiction, some human rights cannot be derogated even in a state of emergency.
#AleHig.... #lawsocieties #Share
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ዳኛ ከስራ የሚነሳበት አግባብ በሕግ ተቀምጧል።

አብዛኛዉ ዳኛ ፕሮፈሽናል ፤ ስራዉን አክብሮ የሚሰራ ነዉ። ዳኞች የችግር አካል ናቸዉ ብሎ በሙሉ መፈረጅ ትክክል አይደለም። ዳኞ ከሥራ የሚነሳበት አግባብ በሕግ ተቀምጧል። ዳኛ አንዴ ከተሾመ በኋላ የሕግ ጥበቃ አለዉ። ይኸ የዓለም አቀፍ መርህ አካል ነዉ።

በስሜት ተነሳስቶ ዳኛን ከሥራ ማስነሳት ትክክል አይደለም።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክብርት ወ/ሮ መኣዛ አሸናፊ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም በፋና ቴሌቪዥን ከሰጡት ቃለ-መጠይቅ የተወሰደ
በደሳለኝ ከበደ
https://t.me/lawsocieties
Nigeria Becomes First Country To Ban Foreign Models in Advertisments

Nigeria’s advertising regulator has announced a ban on using foreign models and voice-over artists in television commercials made in the country.

The move, which is the first of its kind, will take effect in October and follows the Federal Government’s pledge that promises to develop local talent, drive inclusive economic growth, and promote the advertising industry in Nigeria.

Via #Ethiopian Business Daily
https://t.me/lawsocieties