አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት/Legal Immunity/
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ምንነት
ለህዝብ እና ሀገር ጥቅም ሲባል ለተወሰኑ ሰዎች የሚሰጥ በሁኔታ ላይ የተመረኮዘ የህግ ጥበቃ ሲሆን ይሄንን መብት የተጎናጸፉ ሰዎች በህግ የተደነገጉ ሁኔታዎችን እስካልተላለፉ ድረስ ወይም ከለላው እስካልተነሳ ድረስ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት አላቸው፡፡ ይህ ልዩ መብት ወይም (Privilege) ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን የሚሰጥበት አላማ ይህ መብት ወይም ጥበቃ የሚሰጣቸው ሰዎች ባላቸው ሀላፊነት እና ተግባር ምክንያት ስራቸውን በሚያደናቅፍ መልኩ በየምክንያቱ የማሰርና የመክሰስ ተግባር እንዳይኖር በማድረግ የሚያከናውኑትን ተግባር እና የሚወከሉትን ሀላፊነት መጠበቅ ነው፡፡ ይህ ልዩ መብት ጥፋት ወይም ወንጀል ለመፈፀም ፈቃድ ለመስጠት ወይም ተጠያቂነትን ለማስቆም (impunity) እንዲኖር አይደለም፡፡ ልዩ መብቱ የሚሰጣቸው ሰዎች ይታመናሉ ህግንም ያከብራሉ ከሚል እምነት ነው፡፡ ይህ ልዩ መብት የሚሰጠው በልዩ ሁኔታ እንደመሆኑ በጠባቡ የሚተረጎምና አስፈላጊ መሆኑ በታመነ ጊዜ ብቻ በአዋጅ የሚሰጥ መሆኑ ሌላው ባህሪው ነው፡፡ ከለላው የተሰጣቸው ሰዎች ጥፋት ወይም ከባድ ወንጀል ፈፅመው ሲገኙ ግን ይህን ሁኔታ በምርመራ ክፍሉ በቂ ጥርጣሬ ብቻ ሳይሆን ከለላውን በሚከታተለው አካል የጥርጣሬው ትክክለኛነት ተረጋግጦ በህግ እንዲጠየቁ ይደረጋል፡፡

 ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ያላቸው አካላት
1. የምክር ቤት አባላት
ምክር ቤት ማለት የህግ አውጪው የመንግስት አካል ሲሆን የተወሰኑ ሀገራት ባለ አንድ ምክር ቤት (unicameral) ያላቸው ሲሆን ሌሎች ደግሞ ባለ ሁለት ምክር ቤት (bicameral) የሆኑ አሉ፡፡ ስያሜውን ስናይ በኮመን ሎው የህግ ስርዐት የሚከተሉ ሀገራት የላይኛው እና የታችኛው ምክር ቤት እያሉ የሚገልጹት ሲሆን በእንግሊዘኛ አጠራሩ house of lord and house of common ይባላል፡፡

ያለመከሰስ መብት በአብዛኛው ለነዚሁ ለህዝብ እንደራሴዎች የተሰጠ መብት ሲሆን አባላቱ የወከላቸውን ህዝብ ሃሳብ እና ፍላጎት በነጻነት እንዲገልጹ እና በውጤታማነት መወከል እንዲችሉ ለማስቻል ያለመ መብት ነው፡፡

በሀገራችን የስርዐተ-መንግስት አወቃቀር መሰረት በፌዴራል እና በክልል ደረጃ የህግ አውጪ አካላት ያሉ ሲሆን በፌደራል ደረጃ ሁለት ምክር ቤቶች አሉ፡፡ እነሱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌደሬሽን ምክር ቤት ሲሆኑ ክልሎችም የየራሳቸው ምክር ቤቶች አሏቸው፡፡ እነዚህ የምክር ቤት አባላት በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 54 ንኡስ አንቀጽ 4 እና በአንቀጽ 63 መሰረት የሁሉም ህዝብ ተወካይ ናቸው፡፡ በዚሁ መሰረት ማንኛውም የምክር ቤት አባል በምክር ቤቱ ውስጥ በሚሰጠው አስተያየት ምክንያት አይከሰስም፣ አስተዳደራዊ እርምጃም አይወሰድበትም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ማንኛውም የምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም በወ/መ/ስ/ስ/ህግ አንቀጽ 19 እና 20 መሰረት እጅ ከፈንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም በወንጀልም አይከሰስም፡፡ ሆኖም ይህ መብት ፍጹማዊ መብት አይደለም፡፡ ይልቁንም በሁኔታዎች ላይ የተመረኮዘ መብት ነው።

በመሆኑም የምክር ቤት አባላት አባል የሆኑበት ምክር ቤት ሲፈቅድ ወይም የምክር ቤቱ ፈቃድ ሳያስፈልግ ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ከተያዙ የሚያዙበት እና የሚከሰሱበት የህግ አሰራር ያለ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በክልሎች ህገ-መንግስታት እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995(እንደተሻሻለው) አንቀጽ 12 ንኡስ አንቀጽ 3 እና 4 እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ቻርተር መሰረት የክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮቹ ምክር ቤት አባላት ከላይ በተገለጸው መልኩ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ያላቸው ሲሆን ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ከተያዙ ግን የሚያዙበት ሁኔታ በህግ ተደንግጓል፡፡ ለሌላ ወንጀል ጉዳይ ግን የምክር ቤቶቹ ፈቃድ ያስፈልጋል፡፡ እዚህ ላይ ከባድ ወንጀል ምንድን ነው ለሚለው የአገራችንን የወንጀል ህግ ማየት የሚስፈልግ ሲሆን ህጉ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ያስቀመጠው ነገር የለም፡፡ ሆኖም የወንጀል ህጉ አንቀጽ 106 እና 108 ባስቀመጡት አግባብ ቀላል እስራት እና ጽኑ አስራት የሚያስቀጡ ወንጀሎችን እንደየሁኔታው ከባድ ወንጀልን ለመለየት በመስፈርትነት መጠቀም ይቻላል፡፡

2. የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ
በአለምአቀፍ ህግ መሰረት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት የላካቸውን አገር እና አለምአቀፍ ድርጅት ወክለው ባሉበት አገር ፍርድ ቤት በወንጀልም ሆነ በፍትሐብሔር ያለመከሰስ መብት አላቸው፡፡ ይህ ያለመከሰስ መብት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በመኖሪያቸው እና በቢሮዎቻቸው ለሚያደርጓቸው እንቅስቃሴም የሚሰጥ መብት/የህግ ጥበቃ ነው፡፡ ይህ ጥበቃ ሀገራችንም ፈርማ ባፀደቀችው የ1961 የቬና ዲፕሎማሲ ግንኙነት ስምምነት መሰረት የሚሰጥ ሲሆን ለውጭ አገራት አምባሳደሮች፣ ቆንስላዎች እና የኢምባሲቸው ሰራተኞች የሚሰራ ነው፡፡ እንዲሁም ለአለምአቀፍ ድርጅት ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች ከስራቸው ጋር በተገናኘ ሀገራችን በፈረመችው የመቀመጫ ሀገር ስምምነት (host country agreement) የሚሰጥ የህግ ጥበቃ ሲሆን ሆኖም ይህ ያለመከሰስ መብት ፍጹም አይደለም፡፡ ወንጀል በሚፈጸምበት ጊዜ የላካቸውን አገር ወይም አለምአቀፍ ድርጅት የበላይ ሀላፊ ያለመከሰስ መብቱን እንዲያነሳ በመጠየቅ ሲነሳ መያዝ እና መጠየቅ የሚቻል ሲሆን ይሄንን ማድረግ ካልተቻለ ግን ተጠርጣሪውን ከአገር እንዲወጣ ማድረግ (persona non grata) የአንድ ሀገር ሉዓላዊ ስልጣን ነው፡፡

3. ዳኞች
በፌደራል የዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 34 ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት ማንኛውም ዳኛ ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፈንጅ ካልተያዘ ወይም በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ያለመከሰስ መብቱ ካልተነሳ በስተቀር ሊያዝ፣ ሊታሰር እና ክስ ሊቀርብበት አይችልም፡፡ ይህ ህግ ዳኞች በህገመንግስቱ አንቀጽ 79 ንኡስ አንቀጽ 2 እና 3 ላይ የተደነገገውን ዳኞች ከማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን ወይም ሌላ አካል ነጻ ሆነው በህግ ብቻ እየተመሩ የዳኝነት አገልግሎትን ማከናወን እንዳለባቸው የተደነገገውን ለማስፈጸም የወጣ ህግ ነው፡፡ በዚህም ዳኞች በሚወስኑት ውሳኔ ፍትህን ለማስፈን ከየትኛውም አካል መያዝ፣ እስር እና ክስ ሳይደርስባቸው ነጻ ሆነው እንዲሰሩ ለማስቻል ሲሆን በዚህም ፍትህ ፈላጊው ማህበረሰብ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ይህ የህግ ጥበቃ ፍጹም እና ዳኞችም እንደፈለጉት እንዲሰሩ የሚፈቅድ አይደለም፡፡ ዳኞች ከላይ ባነሳነው የወንጀል ህግ እና የወንጀለኛ መቅጫ ስነስርአት ህግ መሰረት ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ከተያዙ ቀጥታ የሚያዙበት፣ የሚታሰሩበት እና የሚከሰሱበት ሁኔታ ያለ ሲሆን ከባድ ወንጀል ባይሆንም ወንጀል ከፈጸሙ በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ተደርጎ ተይዘው ክስም የሚቀርብባቸው መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡
4. የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች
በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 መሰረት አገራዊ ምክክሩን እንዲያመቻች በኮሚሽን ደረጃ የተቋቋመ ህጋዊ ሰውነት ያለው አገራዊ ተቋም ሲሆን ይሄንኑ ኮሚሽን እንዲመሩ በኮሚሸነርነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰየሙ 11 ኮሚሽነሮች እንዳሉት ይታወቃል፡፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 15(1(ሀ) መሰረት እነዚህ ኮሚሽነሮች ያለመከሰስ መብት ያላቸው ሲሆን በዚሁ መሰረት ያለመከሰስ መብታቸው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካልተነሳ ወይም ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ካልተያዙ በስተቀር በኮሚሽነርነት በሚያገለግሉበት ወቅት ያለመከሰስ መብት አላቸው፡፡ እነዚህ ኮሚሽነሮች ከባድ ሀላፊነት ያለባቸው ሲሆን ስራቸውም ከማንም አካል ተጽእኖ ነጻ ሆኖ መከናወን እንዲችል የዚህ አይነቱ ጥበቃ በህግ ተድርጎላቸው ይገኛል፡፡

5. የምርጫ ስራ አመራር ቦርድ አባላት
በምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 4 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሙሉ ጊዜ የሚያገለግሉ 5 አባላት ያሉት ስራ አመራር ቦርድ ያለው ሲሆን በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 15 ንኡስ አንቀጽ 6 መሰረት የስራ አመራር ቦርድ አባላት ሃላፊነት ላይ አስካሉ ድረስ ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ካልተያዙ በስተቀር ያለ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታ ያለመያዝ እና በወንጀል ያለመከሰስ መብት አላቸው፡፡ ይህ መብት ስራ አመራሩ የተጣለበትን ከፍተኛ ሀላፊነት ያለ ተጽኖ በነጻነት አንዲወጣ ለማስቻል ታስቦ የተደነገገ ነው፡፡ ይሄም መብት ጊዜአዊ ሲሆን አባላቱ ሀላፊነታቸውን ሲለቁ ወይም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን ሲያነሳ የሚያበቃ ነው፡፡

6. ለምርጫ የተመዘገቡ እጩዎች
በአትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 42 መሰረት የግልም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩ ተወዳዳሪ /እጩ ተመራጭ/ የሆኑ ሰዎች ከተመዘገቡበት ቀን አንስቶ ምርጫው አልቆ ውጤቱ እስኪገለጽ ድረስ በወንጀል ተጠርጥረው ያለመያዝ መብት አላቸው፡፡ ነገር ግን ከባድ ወንጀል ፈጽመው እጅ ከፈንጅ ከተያዙ ተይዘው ሊከሰሱ ይችላሉ፡፡ የፈጸሙት ወንጀል እጅ ከፈንጅ ባይሆንም የህግ እርምጃ የሚወሰድባቸው ምርጫው አልቆ ውጤቱ ከተገለጸ በኋላ ነው፡፡ ተጠርጣሪው በምርጫው ያሸነፈ ከሆነ በዚሁ ህግ መሰረት ሊያዝ እና ሊታሰር የሚችለው ያለመከሰስ መብቱ በተወከለበት ምክር ቤት ከተነሳ በኋላ ነው፡፡ የዚህ ከለላ ዋነኛ አለማ የምርጫ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግ እና ተወዳዳሪዎች ያለምንም እስር እና ክስ እና ሌሎች እንቅፋቶች የሚወክሉትን መራጭ የህብረተሰብ ክፍል ሀሳብ እና ፍላጎት እንዲገልጹ ወይም እንዲያራምዱ ለማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን ከለላውን ሽፋን በማድረግ ወንጀል ከፈጸሙ ከላይ በተገለጸው አግባብ ከተጠያቂነት አያመልጡም፡፡

7. የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 210/2002 (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) በአንቀጽ 35 መሰረት የኮሚሽኑ ከፍተኛ ሀላፊዎች እና መርማሪዎች ያለመከሰስ መብታቸው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካልተነሳ ወይም ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ካልተያዙ በስተቀር አይከሰሱም፡፡ እነዚህ የስራ ሃላፊዎችም በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 አንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት ዋና ኮሚሽነር፣ ምክትል ዋና ኮሚሽነሮች እና የልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ የተሾሙ ኮሚሽነሮችን ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም በአዋጅ ቁጥር 210/2002 አንቀጽ 2 (10) እና አንቀጽ 35 መሰረት በዋና ኮሚሽነሩ የተሰየሙ የሰብአዊ መብት ጥሰት መርማሪዎችም የዚህ መብት ተጠቃሚ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ የህግ ከለላ ያላቸው ሰዎች ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ከተገኙ በቀጥታ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የሚችሉ መሆኑን አይተናል፡፡ በሌላ በኩል የህግ ከለላ የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስቀር ሳይሆን ከለላው የተሰጣቸው ሰዎች ካለባቸው የስራ ሀላፊነት ልዩ ባህሪ አንጻር ተጽዕኖ እንዳይደርስባቸው ታስቦ የተደነገገ ሲሆን በወንጀል ከተጠረጠሩ ግን ይህ ከለላ በህጋዊ ሂደት ተነስቶ የሚጠየቁ ይሆናል፡፡
በዚህም መሰረት ከባድ ወንጀል ከእጅ ከፈንጅ ውጭ በሆነ ሁኔታ ወይም ቀላል ወንጀል ፈጽመዋል ተብሎ ከተጠረጠሩ በህግ የተሰጣቸው ያለመያዝ እና ያለመከሰስ ከለላቸው እንዲነሳ በሚመለከተው አስፈጻሚ የመንግስት አካል ጥያቄ ሲቀርብ ጉዳዩ የቀረበለት የሚመለከተው ምክር ቤት በምክር ቤቱ አሰራር እና የአባላት የስነ ምግባር ደምብ መሰረት ማመልከቻ የቀረበበትን የምክር ቤት አባል ወይም የስራ ሀላፊ ያለመከሰስ መብት መነሳት አሳማኝ ሆኖ ሲያገኘው ያነሳል፡፡

ተጠርጣሪው ዳኛ ከሆነ በተመሳሳይ ሁኔታ በፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጉዳዩ ታይቶ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብቱ የሚነሳ ይሆናል፡፡ ከለላው በዚህ መልኩ ከተነሳ በ|ላ የሚመለከተው ህግ አስከባሪ መርማሪ አካል ተጠረጣሪውን የሚይዝ ዓቃቤ ህግም ክስ የሚያቀርብበት ሲሆን ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የሚቀጣበት የህግ አሰራር መኖሩን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህም መረዳት እንደሚቻለው የህግ የበላይነት በማንኛውም ሰው ላይ በእኩልነት የሚረጋገጥ እና የሚፈጸም መሆኑን ነው፡፡
በዮሃንስ ግርማ
ከንቃተ ሕግ፣ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
#Share #ሼር #አለ_ህግ #Alehig
#lawsocieties #AleHig
https://t.me/lawsocieties
C_F_N_213835_Cheque_Liability_of_Paying_BankEthiopian_Legal_Brief
3 MB
ሰ/መ/ቁ. 213835
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በቼክ ክፍያ የሚፈጽመ ባንክ በቼኩ ላይ የተመለከተው ፊርማ በዓይን እይታ በሲስተሙ ላይ ካለው የፊርማ ናሙና ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን አረጋግጦ መክፈሉ ከተረጋገጠ ምንም እንኳ ክፍያዉ የተፈጸመዉ ለማይገባዉ ሰው ወይም ተመሳስሎ በቀረበ ፊርማ መነሻነት መሆኑ ቢረጋገጥም ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡


በቼኩ ላይ የተፈረመዉ ፊርማ በእርግጥም ከፊርማ ናሙናዉ ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለመሆኑ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት በማስረጃ መረጋገጥ የሚገባዉ ጭብጥ ነዉ፡፡ ይህን ለማረጋገጥ በአስረጅነት የቀረበዉ እራሱ ክፍያ የተፈጸመበት ቼክ ሲሆን በቼኩ ላይ የተመለከተዉ ፊርማ ከናሙና ፊርማ ጋር የሚመሳሰል መሆን አለመሆኑ ገለልተኛ በሆነ አካል ታይቶ የሚረጋገጥ እንጂ ዳኛዉ እራሳቸዉ አይተዉ ግምት ሊወስዱበት የሚገባ አይደለም፡፡
By abrham yohannes
Mana Murtii Waliigalaa Oromiyaa-
Supreme Court of Oromia
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
The council of lawyers of Oromia (Regional Gumi) held the 199th meeting on 19/11/2014 and discussed the plan of summer work.

Apparently the following issues should be done this summer.

Criminal cases of crime.

✓Crimes against women and children, ✓Crimes concerning youths who are displaced,

Hand and arm crime/RTD

✓ Appointment time, guarantee rights, religious quotes, planning questions (now), We don't give time for the crime of peace and economy of the country and their behavior.

Family matters

Slayer, and a lot of things

Raising and caring for children,

Proof of ownership,

✓Divorce of marriage is provided by agreement,

The protection of the wealthy.

Relationship issues in the middle of nowhere

Relating the issues that are on the date, those that have been agreed upon by reconciliation

Provents presented to avoid looting of

property

Noise free body (habous corpus) ✓Corrections on how the law of social relations are presented by Articles 207 and 208,

✓Investment and economic issues that don't give time,

✓Opening all issues and making

appointments,

If the live link is not open, opening the time is to book your appointment.

The general court of Oromia

Mana Murtii Waliigalaa Oromiyaa-
Supreme Court of Oromia
#Share #ሼር #አለ_ህግ #Alehig
#lawsocieties #AleHig
https://t.me/lawsocieties
የፌዴራል የጠበቆች ማኅበር አስተዳደር ቦርድ ተመሠረተ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
ሐምሌ 22 ቀን 2014(ኢዜአ) በኢትዮጵያ የፍትሕና የጥብቅና ስርዓትን ያዘምናል ተብሎ የታመነበት የፌደራል የጠበቆች ማህበር አስተዳደር ቦርድ ተመሠረተ።

በመሆኑም በህግ እና በሕግ ብቻ የሚመራ የጠበቆች ቦርድ ማቋቋም አስፈልጓል።
#አለህግ
በዚህም በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነው የፌደራል የጠበቆች ማህበር አስተዳደር ቦርድ ተመስርቷል ብለዋል።

ቦርዱ ተጠሪነቱ ለፍትህ ሚኒስቴር እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡

ቦርዱ በዋናነት የፍትህና የጥብቅና ስርዓትን ለማዘመን አላማው አድርጎ የተቋቋመ መሆኑንም አብራርተዋል።

የቦርዱ ስራ አስፈፃሚ አባላት ዛሬ የመጀመሪያውን ውይይት ከሚኒስቴሩ አመራሮች ጋር ያካሄዱ ሲሆን ከነገ ጀምሮ ቦርዱ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል።

በኢትዮጵያ ሁለት የጠበቆች የሙያ ማህበራት ቢኖሩም በቦርድ ደረጃ ሲቋቋም ይህ የመጀመሪያ ነው ።

የኢትዮጵያ የፌደራል ጠበቆች ማህበር በጥር ወር 2014 ዓ.ም ሲሆን ማህበሩ በወቅቱ የምስረታ እና የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን ማድረጉ ይታወሳል።

በሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም በጸደቀው የፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ አማካኝነት ነው ማህበሩ የተቋቋመው።

ማህበሩ በፌደራል ደረጃ በጥብቅና ሙያ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች አባል የሚሆኑበት ነው።

#Share #ሼር #አለ_ህግ #Alehig
#lawsocieties #AleHig
https://t.me/lawsocieties
የቦርዱ ስራ አስፈፃሚ አባላት ዛሬ የመጀመሪያውን ውይይት ከሚኒስቴሩ አመራሮች ጋር ያካሄዱ ሲሆን ከነገ ጀምሮ ቦርዱ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል።
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
ሥራና_ሠራተኛ_አገናኝ_ኤጀንሲዎች_የሥራ_ስምሪት_መመሪያ.pdf
5.2 MB
የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በሀገር ውስጥ የሥራ ስምሪት አገልግሎት ስለሚሰጡበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መመሪያ

የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ሕግና አሠራርን በመከተል ፍትሃዊ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የሥራ ስምሪት አገልግሎት በሀገር ውስጥ የሚሰጡበትን ሁኔታ መወሰን በማስፈለጉ

በኤጀንሲ, አማካኝነት ለሥራ የተሰማራውን ሠራተኛ መብትና ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ ኤጀንሲው እና የአገልግሎት ተጠቃሚው ድርጅት ሊኖራቸው የሚገባውን የጋራና የተናጠል

ኃላፊነት ለይቶ የማመልከቱ ተገቢነት ስለታመነበት፣

መንግሥት በሀገር ውስጥ በግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሚሰጠውን የሥራ ስምሪት አገልግሎት በብቃትና በተገቢው በመከታተል፣ በመቆጣጠርና በመደገፍ፤ በሥራ ላይ የሚሠማሩ ሠራተኞች መብት፣ ደህንነትና ጥቅም የሚጠበቅበትን ሁኔታ መፍጠር እና የኢንዱስትሪ ሠላምን ማስፈን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ!

በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ የሚሰጡ የሥራ ስምሪት አገልግሎቶች በተቀናጀ አግባብ የሚፈጸሙበትን ሁኔታ በመፍጠር ለሀገሪቱ የሥራ ገበያ እድገትና ውጤታማነት ተገቢውን አስተዋጽኦ ማበርከት በማስፈለጉ፤

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በአንቀጽ 171/1/ተ እና በአንቀጽ 174 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
Contract/ውል
Period of limitation/የይርጋ ጊዜ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ውል እንዲፈፀም፤ ውል ባለመፈፀሙ ለደረሰ ጉዳት መፍትሄ ወይም ውል እንዲፈርስ ለመጠየቅ (ውስ የሚሰጠው መብት ከተሰራበት ቀን ወይም ግዴታውን ለመጠየቅ ተገቢ ከነበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር)10 አመት ነው።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

actions for the performance of a contract, actions based on the non-performance and actions for the invalidation of a contract (counted from the date when the obligation is due or the rights under the contract could be exercised) 10 years.
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
የጤና_ባለሙያዎች_ምዝገባና_የሙያ_ሥራ_ፈቃድ_አሰጣጥ፣_አስተዳደርና_ቁጥጥር_መመሪያ_770.pdf
817.4 KB
የጤና ባለሙያዎች ምዝገባና የሙያ ሥራ ፈቃድ አሰጣጥ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር መመሪያ ቁ. 770-2013
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
Succession/ውርስ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ኑዛዜው እንዳይፀና ወይም በአጣሪው የቀረበው የሀብት ክፍፍል ሀሳብ እንዳይፀና ለመቃወም ኑዛዜው - ከተነበበበት ቀን ጀምሮ ወይም አጣሪው ስለክፍፍል ሀሳቡ ካሳወቃቸው ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 15 ቀናት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

to apply for the nullity of a will or to impugn the order of partition proposed (counted from the opening of the will or from the day the person was told about the proposed partition) 15 days.
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
ለመንግሥት ሠራተኞች የሚሰጥ የወሊድ ፈቃድ፣
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
https://t.me/lawsocieties

ለአንድ የመንግስት ሰራተኛ የተለያዩ ዕረፍት ዓይነቶች ያሉ ስሆን በፌደራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010” አንቀጽ 43 ላይ የተደነገገው የወሊድ ፈቃድ ነው።
ነፍሰጡር የሆነች የመንግሥት ሠራተኛ፣ ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ ሐኪም በሚያዘው መሠረት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣታል፤

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

1. ከመውለዷ በፊት ዕረፍት እንድታደርግ ሐኪም ካዘዘ ደመወዝ የሚከፈልበት ዕረፍት ይሰጣታል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተው ፈቃድ እንደ ህመም ፈቃድ አይቆጠርም፡፡
3. ነፍሰጡር የሆነች የመንግሥት ሠራተኛ መውለጃዋ ሲደርስ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት 30 ተከታታይ ቀናት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ፣ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 90 ተከታታይ ቀናት፣ በአጠቃላይ 120 ተከታታይ ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት የወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት ሠራተኛዋ የተሰጣት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከማለቁ በፊት ከወለደች ያልተጠቀመችበትን ቀሪ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወለደች በኋላ እንድትጠቀምበት ይደረጋል፡፡
5. ሠራተኛዋ የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ያልወለደች እንደሆነ እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት የምትቆይበት ዕረፍት በበጀት ዓመቱ ካላት የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ወይም በበጀት ዓመቱ የዓመት ፈቃድ የሌላት እንደሆነ ከሚቀጥለው የበጀት ዓመት የዕረፍት ፈቃዷ ይተካል፡፡
6. ሠራተኛዋ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) የተወሰነውን የወሊድ ፈቃድ ከጨረሰች በኋላ ብትታመምና ተጨማሪ ፈቃድ የሚያስፈልጋት መሆኑ በሀኪም ከተረጋገጠ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 43(1) በተደነገገው መሠረት የሕመም ፈቃድ መውሰድ ትችላለች፡፡
7. ማንኛዋም ስድስት ወር የሞላት ነፍሰጡር የሆነች የመንግስት ሠራተኛ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከመውሰዷ በፊት ጽንሱ የተቋረጠባት ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የህክምና ማስረጃ ስታቀርብ የ60 ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
8. የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወሰደች በኋላ የጽንስ መቋረጥ ካጋጠማት የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃዷ ተቋርጦ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) የተመለከተው የ90 ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
9. ከሦስት እስከ ስድስት ወር ባለው የእርግዝና ጊዜ ውስጥ የፅንስ መቋረጥ ያጋጠማት የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ የሚከፈልበት 30 ተከታታይ ቀን ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
10. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ የትዳር ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት 10 የሥራ ቀን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡

ምንጭ: Tsegaye Demeke - Lawyer
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ ያውቃሉ ?
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
የህግ ምንነት
ህግ የሚለው ቃል በማህበረሰቡ ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ቃል ነው፡፡
በተለይ ህግ አስገዳጅ መሆኑን የሚረዳው ለመሆኑ ቀደም ባለው ጊዜ በየዕለት ኑሮ ፀብ ሲገጥመው እንኳን “በህግ አምላክ” ብሎ ፀብ የማብረድ ልምድ የነበረው መሆኑ ማሳያ ነው፡፡ ሆኖም ማህበረሰቡ ህግን የሚረዳው በተለምዶአዊው አረዳድ እንጂ የዘርፉ ባለሞያዎች በሚረዱበት መልኩ አይደለም፡፡

በመሰረቱ ህግ ለሚለው ቃል ትርጓሜ መስጠት ቀላል አይደለም፡፡ ምክንያቱም የተለያዩ ምሁራን ቃሉን በተለያየ መንገድ የሚገልፁት በመሆኑ ነው፡፡ እንዲሁም የቃሉ ፍቺ ሊደረስባቸው በሚፈለጉት የተለያዩ ዓላማዎች ምክንያት ሊለያይ ይችላል።
ለህግ ቃላት ትርጉም በመስጠት የሚታወቀው ብላክስ ሎው የህግ መዝገበ ቃላት በተሻሻለው ስድስተኛ እትሙ (Black’s Law Dictionary, 6th ed.,) ለህግ ትርጉም ሲሰጥ law is “a body of rules of action or conduct prescribed by controlling authority, and having binding legal force, which must be obeyed and followed by citizens subject to sanctions or legal consequence is a law.” ወደ አማርኛ በግርድፉ ሲመለስ ስልጣን ባለው አካል የተደነገገ የተግባር ወይም የምግባር ደንብ እና አስገዳጅ የህግ ኃይል ያለው አካል ነው። ይህንንም ዜጎች ሊታዘዙት እና ሊከተሉት የሚገባ ሆኖ ማዕቀብ ወይም ህጋዊ ውጤት የሚጥል ህግ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

በመሆኑም የአንድ ሀገር ሕግ፡- ሰላምን ለማስጠበቅ፣ ነባራዊ ሁኔታውን ለማስጠበቅ (maintain the status quo)፣ የግለሰብ መብቶችን ለማስጠበቅ፣ አናሳዎችን ከብዙኃን ለመከላከል ( protect minorities against majorities)፣ ማኅበራዊ ፍትህን ለማስፈን( promote social justice) እና ሥርዓት ያለው ማህበራዊ ለውጥ እንዲኖር ለማድረግ( provide for orderly social change) ያገለግላል።

• የህግ መሰረታዊ ባህሪያት
የህጎችን የተለመዱ ባህሪያት እና ተፈጥሮ መፈተሽ የህግ ጽንሰ-ሀሳብን ለመገንዘብ የሚረዳ ሲሆን ከእነዚህ ባህሪያት እና ተፈጥሮዎች መካከል እንደ ወሰኝ ወይም አስፈላጊ የሚታሰቡት አጠቃላይነት(ህግ በሁሉም ሰው ላይ በተመሳሳይነት (uniformity) እና እኩልነትን (Equality) የሚፈፀም መሆኑ)፣ መደበኛነት (ህግ ማህበራዊ ባህሪን በመፍቀድ፣ በማዘዝ ወይም በመከልከል ልማዶችን የሚፈጥር መሆኑ) እና ማዕቀብ ወይም ቅጣትን (ህግን ያላከበረ ቅጣት የሚጠብቀው መሆኑን) ያካትታሉ፡፡

• ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ
በወንጀልም ሆነ በፍትሐ ብሄር ጉዳይ ህጎቹ ስልጣን ባለው የህግ አውጪ አካል ወጥተው ከፀደቁበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንደሚውሉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ዜጎች የህጎቹን መኖር ወይም መውጣት የማወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይኸውም ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም የሚለው የህግ መርህ በላቲን Ignorantia juris non excusat ወይም በእንግሊዘኛ "ignorance of the law excuses not" ከሮማውያን ህግ የተወሰደ ሲሆን ህግን የማያውቅ ሰው ይዘቱን ባለማወቅ ብቻ ህጉን በመተላለፍ ከተጠያቂነት ሊያመልጥ እንደማይችል የሚገልጽ የህግ መርህ ነው። እንዲሁም የህግ ስህተት (mistake of law) ሰዎች በአንድ ጉዳይ ላይ ተፈጻሚነት ያለው ሕግ እንዴት እንደሚተገበር የሚይዙትን የአረዳድ ስህተቶችን የሚያመለክት የሕግ መርህ ነው። ‘ህግን አለማወቅ’ እና ‘የህግ ስህተት’ የሚሉት ቃላቶች በህጋዊ እይታ ውስጥ ተመሳሳይ ትርጉም የማይሰጡ ሲሆን አለማወቅ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አጠቃላይ የእውቀት ያለመኖርን ያመለክታል። ማሳሳት ግን እውቀትን ተቀብሎ ወይም እውቀት እንዳለ አምኖ ነገር ግን የተሳሳተ መደምደሚያን ላይ መድረስን ያሳያል። ይሁንና ህግን አለማወቅም ሆነ የህግ ስህተት ከተጠያቂነት እንደማያድን እንደ አንድ የህግ መርህ ይወሰዳል፡፡

• ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ መርህ ምክንያት (rationale for "ignorance of the law excuses not" principle)
በመሠረቱ አንድ ሰው ህግን ከጣሰ ህጉን ስለመጣሱ ምንም እውቀት ባይኖረውም ተጠያቂ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ሰዎች ህጉን አላውቀውም በማለት ድርጊታቸውን ሊከላከሉ እንደማይችሉ ያመለክታል፡፡ የዚህ ህግ መርህ ምክንያት( rationale) አለማወቅ ሰበብ ቢሆን ኖሮ ምንም እንኳን ያ ሰው ህጉ መኖሩን ቢያውቅም በወንጀል ህግ ወይም በፍትሐ ብሄር ጉዳይ ቢከሰስ ህጉን አላወኩም በማለት ከተጠያቂነት ማምለጫ እንዳይሆን በሚል ነው፡፡ በመሆኑም ከመርህ በስተጀርባ ያለው ምክንያት አለማወቅ ሰበብ ከሆነ ማንኛውም በወንጀል ወይም በፍትሐ ብሄር የተከሰሰ ሰው ተጠያቂነትን ለማስወገድ አላዋቂ ነኝ ሊል ይችላል የሚል ነው። ስለዚህ ህጉ የቱንም ያህል አጭር ጊዜ ቢቆይ ሁሉም ህጎች በስልጣኑ ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ ሰው ተፈፃሚ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

በኢትዮጵያም ህግን አለማወቅ ወይም የህግ ስህተት ከተጠያቂነት እንደማያድን በወንጀል ህጉ አንቀፅ 81 ስር ተደንግጓል፡፡ በዚሁ መሰረት ሕግን አለማወቅ ወይም በህግ ላይ መሳሳት መከላከያ ሊሆን እንደማይችል ያስቀምጣል፡፡ በሌላ በኩል በፍትሐ ብሄር ህግ አንቀፅ 2035/1 እና 2 ስር አንድ ሰው በህግ ላይ በትክክል የተገለፀውን ድንጋጌ፣ ልዩ ደንብና ሥርዓት የጣሰ እንደሆነ ጥፋተኛ እንደሆነ እና ህግን አለማወቅ ይቅርታ ሊያስገኝ የማይችል መሆኑ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

• የህግ መኖር ማወቅ የሚቻልበት መንገድ
ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም የሚል የህግ መርህ ተቀባይነት አለው ማለት ሁሉም ሰው ህግ የማወቅ ግዴታ እንዳለበት እና የህግን መኖር ያውቃል የሚል ግምት እንደሚወሰድ ያመለክታል፡፡ ታዲያ ሁሉም ሰው ህግን የተማረ ሊሆን የማይችል በመሆኑ እንዲሁም ህግን ቢማር እንኳ ሁሉን ህግ በተገቢው ሁኔታ ያውቃል ማለት ተጨባጭ (realistic) የማይመስል በመሆኑ የህግን መኖር እንዴት ማወቅ ይቻላል የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡

የህግን መኖር በተለያዩ መንገዶች ማወቅ ይቻላል፡፡ ይኸም በዋናነት ህጎች የሚፀኑበትን ጊዜ ከሚገነግጉ ድንጋጌዎች ሲሆን ህግ የሚፀናበት ጊዜ በተለያዩ ህጎች ላይ በተለያየ ሁኔታ ተገልፆ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ህጉ ወይም አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ የሚፀና ይሆናል፣ ህጉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል እና የተወሰነ ቀን በማስቀመጥ ከዛ ቀን ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን ሊደነገግ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት በህዳር 29/1987 የፀደቀ ሲሆን ከነሐሴ 15/1987 ጀምሮ በሥራ ላይ እንደሚውል እና የፀና እንደሚሆን በመደንገግ ህጉ የሚፀናበትን ጊዜ በዚህ መልኩ አውጇል ፡፡ በመሆኑም ህጎቹ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታውጀው ከፀደቁበት ቀን ጀምሮ ወይም በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ በህብረተሰቡ ይታወቃሉ ተብሎ ይገመታል፡፡
ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ መርህ የማይፈፀምበት ልዩ ሁኔታ
ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ መርህ የማይፈፀምበት ልዩ ሁኔታ የተፈጠረው በዓለም አቀፍ ደረጃ በፍርድ ቤቶች በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ነው።
ፍርድ ቤቶች የህግ አለማወቅ እንደ ሰበብ የተቀበሉት የህግ ጥሰት ሆን ተብሎ ያልተፈፀመ ወይም ያለጥፋት ሲጣስ ሆኖ በዚህ ጊዜ ቅጣት ለመጣል ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ስለሆነም የሕግ ስህተት እንደ መከላከያ የሚሠራው የሕግ ስህተቱ ሐቀኛ ሆኖ በቅን ልቦና ሲሠራ ነው። እንዲሁም የተከሳሽ ህግን አለማወቅና ስህተት ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ አጠቃላይ ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት አያድንም የሚለው መርህ ተፈፃሚ አይሆንም ማለት ነው፡፡

በተመሳሳይ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ወንጀል ህግ አንቀፅ 81/2 ስር እንደተደነገገው ድርጊቱን ለመፈፀም መብት ያለው መሆኑን በቅን ልቦና ለማመንና እንደዚህ ባለ የተሳሳተ እምነት ላይ ለመገኘት በቂና እርግጠኛ ምክንያት ያለው ሆኖ ለተገኘ ወንጀለኛ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን ሊያቀልለት እንደሚችል ያስቀምጣል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን የሚወስነው ከስህተት የደረሰበትን ምክንያት በተለይም የስህተትና የነገሩን ሁኔታ በመገመት ነው፡፡ በተጨማሪ ምክንያት ሊገኝበት በሚችልና ፍፁም በሆነ አለማወቅና ቅን ልቦና እንዲሁም ወንጀሉን የማድረግ አሳብ መኖሩን በግልፅ በማይታይባቸው የተለዩ ሁኔታዎች ፍርድ ቤት ከቅጣት ነፃ ለማድረግ እንደሚችል የወንጀል ህጉ ይደነግጋል፡፡

በአጠቃላይ ህግ የሰዎችን የእለት ተዕለት ተግባር በመግዛት ሰላማዊ ኖሮ እንዲኖሩ የሚያስችል አንዱ መሳሪያ በመሆኑ ሰዎች ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት እንደማያድን እና መከላከያ ሊሆን እንደማይችል በማወቅ በተቻለ መጠን ህገ ወጥ ከሆኑ ተግባራት እራሳቸውን በማረቅ ይኖርባቸዋል፡፡
በእፁብ ደጀኔ
በንቃተ ህግ፣ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በነሐሴ ወር መደበኛ ሥራቸውን ይቀጥላሉ

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 እስከ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ መደበኛውን የዳኝነት አገልግሎት መስጠታቸውን የሚቀጥሉ እንደሚቀጥሉ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በመግለጫው ወደ 2015 ዓ.ም የሚያልፉ መዝገቦችን ቁጥር ለመቀነስ፣ የበሰሉ መዝገቦችን እልባት ለመስጠት፣ እስረኛ ያለባቸውን መዝገቦች ቅድሚያ ሰጥቶ ለመስራት እንዲያስችል በዳኞች ፈቃደኝነት ላይ በመመስረት የፌዴራል ፍርድ ቤቶቹ ከነሐሴ 1-30/2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ መደበኛውን የዳኝነት አገልግሎት መስጠታቸውን የሚቀጥሉ ይሆናል ሲል አስታውቋል።
(የፌ/ጠ/ፍርድቤት)
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#New#Cooperative Bank Of Oromia#

▪️1 - Digital Banking Officer
▪️2 - Attorney
▪️3 - Legal Aid
▪️4 - Corporate Strategy Management Officer
▪️5 - Corporate Strategy Management Expert
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://bit.ly/3d0PAiX

▪️Deadline - August 08/2022
ጉባዔው በ26 የሕገ መንግሥት ትርጉም ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።
------------------------------------------------------------------------------------------------------
የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ረቡእ ሚያዝያ 05 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ 26 ጉዳዮች ላይ በመወያየት 25ቱ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት እንዲዘጉ የወሰነ ሲሆን፤ በአንድ ጉዳይ ላይ በሰፊው በመወያየት ጉዳዩ ተጨማሪ ጥናት እንዲደረግበት በይደር እንዲያልፍ ወስኗል።
ሰፊ ውይይት የተደረገበትና ተጨማሪ ጥናት እንዲደረግበት የተወሰነው ጉዳይ የንብረት ክርክር ጉዳይ ሲሆን ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የስምንት ሰዎች ይዞታ የተመዘገበ ሆኖ እያለ ፍ/ቤቱ ከስምንቱ አመልካች አንዱ ሆነው የቀረቡትን የተከሳሽ ሚስትንና ተከሳሽ ሆነው የቀረቡትን ባል በማከራከር የከሣሽ እና ተከሣሽ የጋራ ሀብት ነው በማለት ይወስናል፡፡ የተቀሩት ሰባቱ ባለይዞታዎችም ውሳኔውን በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 358 በመቃወም ጣልቃ ገብ አመልካች ሆነው ወደ ክርክሩ ቢገቡም ፍ/ቤቱ በክርክሩ ሂደት ወቅት ግማሾቹ በምስክርነት የቀረቡ ሌሎቹ ደግሞ ችሎት እየገቡ ሲከታተሉ የነበሩ በመሆኑ መብታቸውን ለማስከበር ጣልቃ በመግባት መከራከር እየቻሉ የክርክሩን ውጤት ጠብቀው መብታቸውን የሚነካ ውሣኔ ሲሰጥ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 358 መሠረት ያቀረቡት ተቃውሞ ተቀባይነት የለውም በማለት ብይን ይሰጣል፡፡ የይግባኝ አቤቱታቸውን ለፌ/ከ/ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ፍ/ቤቱ አስቀርቦ በማከራከር የስር ፍ/ቤት ውሣኔን አፅንቷል፡፡ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም አያስቀርብም በማለት ጉዳዩን በመዝጋቱ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መ.ቁ. 201187 እና 187023 የሰጣቸው ውሣኔዎች በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40/1፣ 2፣ 7 እና 81 ስር የተደነገጉትን የንብረት መብቶች እና በአንቀጽ 9/1/ የተደነገገውን የሕገ መንግሥት የበላይነት ድንጋጌን ስለሚቃረን የሕገ መንግሥት ትርጉም ይሰጠን በማለት ጠይቀዋል፡፡
ጉባዔውም በጉዳዩ ላይ በስፋት የተከራከረ ሲሆን በአንድ በኩል ከላይ ፀንተው ያሉት ሁለቱ ውሣኔዎች ለሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታ የቀረቡ ቢሆንም ሁለቱም የፍ/ቤቶቹ ውሣኔዎች ማስረጃን በመመዘን እና ሕግን በመተርጎም የተወሰኑ በመሆናቸው የአመልካቾችን የትኛውንም ሕገ መንግሥታዊ መብት የሚፃረሩ አይደሉም የሚል ሀሳብ ቀርቧል፡፡
በሌላ በኩል የፍ/ስ/ስ/ህጉ ቁ. 358 ድንጋጌ ይዘት ሲመረመር በዋና ክርክር ወቅት ተካፋይ መሆን ሲገባው በክርክሩ ተካፋይ ያልሆነና ወይም በክርክሩ መብት ያለው እና ተካፋይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ፍርድ መብቱ የተነካበት ሰው ፍርዱ ከመፈጸሙ በፊት የመቃወም አቤቱታ አቅርቦ መከራከር እንደሚችል በግልጽ ስለሚገነግግ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 56795 ላይ አንድ ክርክር መጀመሩን ያወቀ ወገን የክርክሩን ውጤት ጠብቆ መብቱን የሚነካበት ሆኖ ባገኘው ጊዜ ከውሳኔው በኋላ የሚያቀርበው አቤቱታ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 358 መሰረት ተቀባይነት የለውም ብሎ የሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ህግን ከመተርጎም ስልጣኑ ያለፈና የአመልካቾችን ንብረት የማፍራት መብት የሚጻረረር በመሆኑ ውሳኔው የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 37፣ 40 እና 79(1) ድንጋጌ ስለሚቃረን የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልገዋል የሚል ሀሳብ ቀርቧል፡፡ ጉባዔውም በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ጥናት እንዲደረግበትና ለቀጣይ ውይይት እንዲቀርብ ወስኗል፡፡
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆