አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር የተጠናቀቀውን የበጀት አመት የግብር አከፋፈል ጋር የተፈጠሩ የአሰራር ችግሮች ጋር በተያያዘ መፍትሄ ለማምጣት እና ዘላቂ የአሰራር ስርአት እንዲኖር ከሀምሌ 01 ቀን 2014ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑ ይታወቃል:: የዚሁ አካል በሆነው 11 አባላት ያሉት ግብረ ሀይል (Task force) አቋቁሞ በርካታ ተግባራትን በየእለቱ ሲያከናውን ቆይቷል::

በዚሁ መሰረት ለአጭርና ለረጅም ጊዜ ስራዎች እቅድ በማውጣት ለአጭር ጊዜ መፍትሄው ቅድሚያ በመስጠት ሲሰራ ቆይቷል::

በዚህም የጠበቆች ማህበሩ በጉዳዩ ላይ ያለውን አቋም ከነማብራሪያው በይፋ ለሚመለከታቸው አካላት በፅሁፍ ከማሳወቅ ጀምሮ አማራጭ መፍትሄዎችን አቅርቧል:: በተመሳሳይ ከሚመለከታቸው የፍትህ ሚ/ር; የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ እና ሌሎች ተቋማት የበላይ ሀላፊዎች ተከታታይ ውይይቶች ሲደረጉ ቆይተዋል:: በዚህም የአጭር ግዜ መፍትሄው በመልካም ውጤት ተጠናቋል::

በመሆኑም ግብር ከፋይ ጠበቆች;
1. ሂሳብ መዝገብ የያዙ ጠበቆች ካሉ በዛው መሰረት እንዲስተናገዱ;
2. በአማራጭ ደረሰኝ የሚስተናገዱ በቆረጡት ደረሰኝ መሰረት ታክሳቸውን አሳውቀው እንዲስተናገዱ;
3. ሁለቱምን ያልያዙ ወይም የሌላቸው ጠበቆች ደግሞ እንደከዚ ቀደሙ በቁርጥ ግብር/ወጪ እንዲስተናገዱ ለሁሉም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ቅርንጫፎች መመሪያ ተላልፏል::
4. በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ጠበቆች በየግብር መክፈያ ቅርንጫፋቸው እየተገኙ ታክሳቸውን መክፈል መቀጠል የሚችሉ ይሆናል::

በዚህ ሂደት አስተዋፅኦ እና ቀና ትብብር ላሳያችሁ ለፍትህ ሚ/ር; የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የበላይ አመራሮችና የስራ ባልደረቦች እንዲሁም በሂደቱ ላይ በቀጥታ ለተሳተፋችሁ ግዜ እና እውቀታችሁን ጭምር አስተዋፅኦ ያደረጋችሁ የማህበሩን የአመራር አባላት እና የግብረሀይሉ አባላት ማህበሩ ምስጋናውን ያቀርባል::

ዘላቂ መፍትሄውን በተመለከተም ከኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር; ከገንዘብ ሚኒስቴር; ከገቢዎች ሚ/ር እና ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የተውጣጣ የጥናትና መፍትሄ አመንጪ ቡድን በማህበሩ አስተባባሪነት ተቋቁሞ ስራውን የሚጀምር መሆኑን እና የሚደረስባቸውን ውጤቶችም የሚያሳውቅ መሆኑን ማህበሩ ይገልፃል::

ከላይ ከተገለፀው በተቃራኒ እክል የሚፈጠርባችሁ ጠበቆች በማህበሩ አድራሻ ስማችሁን; ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱንና tin no በማስመዝገብ መፍትሄ እንድታገኙ የሚደረግ መሆኑን ማህበሩ ያሳስባል::


የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ሀምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
August 3, 2022
August 3, 2022
New_Investment Incentives Regulation_No 517_2022.pdf
4 MB
August 3, 2022
August 4, 2022
Regarding Exemption of Motor Vehicles from Customs Duties.jpg
1.5 MB
August 4, 2022
August 4, 2022
Exit exam guide line.pdf
393.5 KB
August 5, 2022
August 5, 2022
August 5, 2022
የጤና ህግ (Health Law) ትምህርት በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለመክፈት ምክክር ተካሄደ
***
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት የ2014ዓ/ም የስራ ዘመን የስራ አፈጻጸም ግምገማ፣ የ2015 ዓ/ምን የስራ እቅድ ትውውቅና በኽልዝ ሎው ስርዓተ ትምህርት (Health Law curriculum) ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ ሀምሌ 29/2014ዓ/ም በፍሎሪዳ ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ፡፡

በመርሃ ግብሩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ፣ የአስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት ተወካይ አቶ ልጃለም ጋሻው፣ የህግ ትምህርት ቤት ዲን አቶ አለሙ ታዬ፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተምረው በህግ መምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩና በአሁኑ ሰአት በአሜሪካን ሀገር በሲያትል ዋሽንግተን ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ እዮብ ከበደና ሌሎች የትምህርት ቤቱ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱ ሲሆን፣ በቅድሚያ አቶ እዮብ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የጤና ህግ (Health Law curriculum) ፕሮግራም በዩኒቨርሲቲው በ2ኛ ዲግሪ ለመክፈትና ከዩኒቨርሲቲው ጋር ለመስራት ያላቸውን ፈቃደኝነትንና ተነሳሽነት በዩኒቨርሲቲው፣ በራሳቸውና በህግ ትምህርት ቤቱ ስም አመስግነዋል፡፡ ዶ/ር ካሳሁን አያይዘውም ፕሮግራሙ በዩኒቨርሲቲው መሰጠቱ የሚኖረውን ፋይዳና ተያያዥ ነጥቦችን በማንሳት ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው፣ በሚቀርበው የስራ ሪፖርትና እቅድ ላይ ተሳታፊዎች በንቃት እንዲሳተፉ አሳስበዋል፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኽልዝ ሎው (Health Law curriculum) ፕሮግራምን በ2ኛ ዲግሪ ለማስጀመር ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ እንደቆዩ የሚያነሱት አቶ እዮብ የፕሮግራሙን አስፈላጊነት አስመልክቶ፣ፕሮግራሙ ለዩኒቨርሲቲውና እንደ ሀገርም ያለውን ፋይዳ፣ በአጠቃላይ የፕሮግራሙን ጠቀሜታ እንዲሁም ሊያጋጥሙ በሚችሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ አጭር ገለፃ አድርገዋል፡፡ ገለፃውን ተከትሎ በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመቀጠል የህግ ትምህርት ቤት ዲን በሆኑት በአቶ አለሙ ታዬ የ2014ዓ/ም የስራ ዘመን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችንም በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ የቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰጥተው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ከዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ እቅድ በመነሳት የህግ ትምህርት ቤቱ የ2015 ዓ/ም የስራ እቅድ መታቀዱንና በሚቀጥለው የስራ ዘመን ትኩረት ተሰጥቶ የሚከናወኑ ተግባራትንም አቶ አለሙ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረቡት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዶ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል፡፡
****
ለልህ
ቀት እንተጋለን!
የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሀምሌ 29/2014ዓ.ም
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
August 5, 2022
ኢትዮጵያ በምግብ ዋጋ ንረት ከተመቱ የዓለም ቀዳሚ 10 ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነች።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ኢትዮጵያን ያካተተው የዓለም ባንክ ሪፖርት ይፋ ሆኗል።
በከባድ የምግብ ዋጋ ንረት ተመተዋል በሚል በሪፖርቱ ከተካተቱት ቀዳሚ 10 ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነች።
ኢትዮጵያ ካሳለፍነው ወርሃ መጋቢት ወዲህ እስከ ሰኔ በነበሩት አራት ወራት ከፍተኛ የምግብ ዋጋ ንረት አጋጥሟታል ተብሏል።
ንረቱ 38 በመቶ ሆኖ መመዝገቡም ነው በሪፖርቱ የተጠቀሰው።

በከባድ የብድር ጫና ውስጥ የሚገኙት ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን ለከፋ የምግብ ዋስትና ችግር ሊዳረጉ እንደሚችሉም ተገልጿል።

በሪፖርቱ ሊባኖስ በንረቱ ክፉኛ የተጎዳች ሃገር ነች ተብላለች።


https://am.al-ain.com/article/ethiopia-is-among-the-countries-worst-hit-by-the-food-inflation-crisis-wbg-said

#lawsocieties #AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
August 5, 2022
_የኢትዮጵያ_የንግዴ_ስራ_ፈቃዴ_መስጫ_መዯብ_መመሪያ_ቁጥር_17_201.pdf
3.1 MB
August 6, 2022
August 6, 2022
August 7, 2022
#New#Awash Bank#

▪️1 - Administrative Assistant I
▪️2 - Plumber
▪️3- IT Service Management Officer - Core & Interface
▪️4 - Legal Officer
▪️5 - Mobile & Internet Banking Officer I
▪️6 - Digital Channels Technical Support Officer II
▪️7 - Terminal Management Officer II
▪️8 - Agent Banking Officer II
▪️9 - Branch Manager Class II Branch
▪️Posted On - August 07, 2022
▪️🚩Deadline Date: August 13, 2022
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://bit.ly/3P4CMW3
August 7, 2022
August 7, 2022