አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ለመንግሥት ሠራተኞች የሚሰጥ የወሊድ ፈቃድ
#አለ_ህግ
==================
ለአንድ የመንግስት ሰራተኛ የተለያዩ ዕረፍት ዓይነቶች ያሉ ስሆን በፌደራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010” አንቀጽ 43 ላይ የተደነገገው የወሊድ ፈቃድ ነው።
ነፍሰጡር የሆነች የመንግሥት ሠራተኛ፣ ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ ሐኪም በሚያዘው መሠረት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣታል፤
1. ከመውለዷ በፊት ዕረፍት እንድታደርግ ሐኪም ካዘዘ ደመወዝ የሚከፈልበት ዕረፍት ይሰጣታል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተው ፈቃድ እንደ ህመም ፈቃድ አይቆጠርም፡፡
3. ነፍሰጡር የሆነች የመንግሥት ሠራተኛ መውለጃዋ ሲደርስ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት 30 ተከታታይ ቀናት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ፣ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 90 ተከታታይ ቀናት፣ በአጠቃላይ 120 ተከታታይ ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት የወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት ሠራተኛዋ የተሰጣት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከማለቁ በፊት ከወለደች ያልተጠቀመችበትን ቀሪ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወለደች በኋላ እንድትጠቀምበት ይደረጋል፡፡
5. ሠራተኛዋ የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ያልወለደች እንደሆነ እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት የምትቆይበት ዕረፍት በበጀት ዓመቱ ካላት የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ወይም በበጀት ዓመቱ የዓመት ፈቃድ የሌላት እንደሆነ ከሚቀጥለው የበጀት ዓመት የዕረፍት ፈቃዷ ይተካል፡፡
6. ሠራተኛዋ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) የተወሰነውን የወሊድ ፈቃድ ከጨረሰች በኋላ ብትታመምና ተጨማሪ ፈቃድ የሚያስፈልጋት መሆኑ በሀኪም ከተረጋገጠ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 43(1) በተደነገገው መሠረት የሕመም ፈቃድ መውሰድ ትችላለች፡፡
7. ማንኛዋም ስድስት ወር የሞላት ነፍሰጡር የሆነች የመንግስት ሠራተኛ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከመውሰዷ በፊት ጽንሱ የተቋረጠባት ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የህክምና ማስረጃ ስታቀርብ የ60 ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
8. የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወሰደች በኋላ የጽንስ መቋረጥ ካጋጠማት የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃዷ ተቋርጦ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) የተመለከተው የ90 ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
9. ከሦስት እስከ ስድስት ወር ባለው የእርግዝና ጊዜ ውስጥ የፅንስ መቋረጥ ያጋጠማት የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ የሚከፈልበት 30 ተከታታይ ቀን ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
10. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ የትዳር ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት 10 የሥራ ቀን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
Via Tsegaye Demeke Lawyer

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.com
#አለ_ህግ
ፍርድ ቤት፣
በችሎት ውስጥ መደረግ ያለባቸው ተግባራት


• ዳኞች ወደ ችሎት ሲገቡም ሆነ ሲወጡ ችሎት ውስጥ ያሉ ስዎች ከተቀመጡበት መነሳት፤
• ባለጉዳዮች የተስተካከለና የሰዎችን አትኩሮት ሊሰብ የማይችል አለባበስ ልበስ ይኖርባቸዋል፤
•የዳኞችን ትዕዛዝ ብቻ ጠብቆ መናገር ይኖርባቸዋል፤

• የተጠየቁ ጥያቄዎችን ግልፅና አጭር በሆነ መልኩ መግለፅ አለባቸው!

• ዳኛን ለማናገር የአክብሮት ቃል ማለትም ክቡር ዳኛ/ክብርት ዳኛ የተከበረው ችሎት የሚሉትን በጠቀም መናገር ይኖርባቸዋል፤

• አላስፈላጊ ፍርሃት፣ መጨናነቅ፣ መሸማቀቅና መርበትበትን በማስወገድ ሀሳብን ያለፍርሃት መግፅ ያስፈልጋል፤
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.co
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግል ባንኮች የከፈቷቸው የባንክ ሒሳቦች በሙሉ እንዲዘጉ ታዘዙ
👉ትዕዛዙን ያልፈጸመ መሥሪያ ቤት በጀት አይለቀቅለትም ተብሏል
ሰኞ ሚያዝያ 3 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች በተለያዩ የግል ባንኮች የከፈቷቸውን ሒሳቦች በአስቸኳይ እንዲዘጉ፣ ይህንንም ማድረጋቸውን የሚያረጋግጥ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ታዘዙ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር በግል ባንኮች ውስጥ አካውንት ከፍተው ገንዘብ እያንቀሳቀሱ ነው ለተባሉ መሥሪያ ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ፣ በግል ባንኮች ውስጥ ያላቸውን ሒሳብ ካልዘጉ ዕርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቋል፡፡
በገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተጻፈው ይኸው ደብዳቤ፣ በመንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው የፋይናንስ አስተዳደር ደንብ መሠረት፣ የመንግሥት ገንዘብ ወይም ገቢ የሚደረገው በብሔራዊ ባንክ ወይም ብሔራዊ ባንክ በሚወክለው ባንክ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
በዚህ ድንጋጌ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለጊዜው የሰየመው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ብቻ መሆኑን የሚኒስትር ዴኤታው ደብዳቤ ያመለክታል ሲል ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
ሆኖም በአሁኑ ወቅት በርካታ የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች የመንግሥት ገንዘብ ለማንቀሳቀስ በግል ባንኮች ሒሳብ በመክፈት ላይ መሆናቸውንና ይህንን ማቋረጥ እንደሚኖርባቸው በመታመኑ ዕርምጃው እንደተወሰደ ታውቋል፡፡
_____
አዲስ ማለዳ
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና
👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.co
የሰብዓዊ_መብቶች_ዓለም_አቀፍ_ቃል_ኪዳኖች_በአማርኛ፣_2001_ዓ_ም.pdf
621.5 KB
International Covenant on Civil and Political Rights (የሰብዓዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳኖች) በ2001 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (በቀድሞ አጠራር የአትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን) በአማርኛ የተዘጋጀ
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና
👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
የወራሽነት የምስክር ወረቀትን በተለከተ የሚቀርብ የተቃውሞ አቤቱታ፣ የማስረጃውን ትክክለኛነት እና ህጋዊነት ከማረጋገጥ ያለፈ አንድምታ የሌለው መሆኑ ከተረጋገጠ ማስረጃውን የሰጠው ፍርድ ቤት የማስረጃው ይሰረዝልኝ ጥያቄን ማስተናገድ የሚገባው ስለመሆኑ፣
በሐሰት ለተገኘ የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዝልኝ ጥያቄ ተፈጻሚነት የሚኖረው፣

የይርጋ ጊዜ የአስር አመት የይርጋ ጊዜ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000፣
1677 1845 እና 1846
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 እና 359
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና
👇👇👇👇 Join and #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
አለ_ህግ Ale Hig, Ale Law Societies #አለ_ህግባለሙያ፣ ነፃ የህግ ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ የውልና የክስ ቅፆች (ፎርሞች) ፤ የህግ ጉዳዮችን 🔴ሁሉንም ሕጎች በአንድ ላይ ያገኙበታል 🔴 All in one, for All. #አለ_ህግ መሰረታዊ የህግ መረጃና እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው።
ይህን ሊንክ በመጫን በቴሌግራም ተቀላቀሉን https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
email us: lawsocieties@gmail.com
contact us via telegram Bot @LawsocietiesBot

follow us on Facebook page
https://www.facebook.com/lawsocieties/
238_ባንኰች_ባገኙት_ንፋስ_አመጣሽ_ገቢ_ላይ_ግብር_የሚከፈልበትን_ሁኔታ_ለመወሰን_የወጣ_መመሪያ_ቁጥር.pdf
192.5 KB
ባንኮች ባገኙት ንፋስ አመጣሽ ገቢ ላይ ግብር የሚከፈልበትን ሁኔታ
ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 238/2013 #አለ_ህግ #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Entrust🔷ETC)
በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና በአክስዮን ማኅበር መካከል ያላቸዉ መሰረታዊ አንድነት እና ልዩነት
1. አባልነት/Membership: -
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለማቋቋም የሚያስፈልጉ ሁለት/2/ ሰዎች ብቻ ሲሆኑ አክሲዮን ማኅበር ደግሞ ለመጀመር ቢያንስ አምስት/5/ አባላት ያስፈልጋሉ ፡፡
በአክሲዮን ማህበር ውስጥ በከፍተኛው የአባላት ብዛት ላይ ገደብ የለም ፡፡ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ቢበዛ 50 አባላት ብቻ ሊኖሩት ይችላል ፡፡
2. ዳይሬክተሮች/ Directors፡ -
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአንድ ወይም በብዙ ሥራ አስኪያጆች የሚተዳደር ሲሆን አክሲዮን ማኅበሩ ደግሞ አነስተኛ ቁጥራቸው ሦስት በሚሆኑ ዳይሬክተሮች የሚተዳደር ነው ፡፡
3. ፕሮስፔስተስ/ Prospectus: -
አንድ አክሲዮን ማኅበር ለአክሲዮኖቹና ለዕዳ ወረቀቶቹ ደንበኝነት እንዲመዘገብ ህዝቡን መጋበዝ ይችላሉ ፣ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ካፒታሉን ለማሳደግ ወደ ሕዝብ መሄድ አይችልም ፡፡
4. አነስተኛ ምዝገባ /Minimum subscription:-
በአክሲዮን ኩባንያ ውስጥ ሁሉም ካፒታል መፈረም አለባቸው እና ከምዝገባ በፊት የካፒታልው 25% መከፈል አለበት። ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሙሉ በሙሉ በተከፈለ ካፒታል ይመዘገባል ፡፡
5. የማህበሩ ዋና ገንዘብ / capital፡-
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ዋና ገንዘብ ከ15,000 ብር በታች መሆን አይችልም፡፡ በአክሲዮን ኩባንያ ደግሞ መነሻ ካፒታሉ ከ50,000 ብር በታች መሆን አይችልም፡፡
6. የተገደበ ሀላፊነት/Limited liability: -
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሆነ በአክስዮን ማህበር በማህበሩ ባዋጡት/ባላቸዉ ድርሻ ልክ ብቻ ሀላፊነት አላቸዉ፡፡ ማህበርተኞቹም ለማህበሩ ግዴታዎች አላፊ የሚሆኑት ባላቸዉ ድርሻ ልክ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም በተገደበው የኃላፊነት ደንብ መሠረት የኩባንያው አበዳሪዎች በድርጅቱ በራሱ ንብረት ላይ ብቻ የይገባኛል ጥያቄ ለማቅረብ የተገደቡ ሲሆን የድርጅቱ ባለአክሲዮኖች በግል በያዙት ንብረት ላይ ምንም ዓይነት የይገባኛል ጥያቄ የላቸውም ፡፡
7. የህግ ስዉነት/Legal personality፡-
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርም ሆነ አክስዮን ማህበር የራሳቸዉ የሕግ ሰዉነት ያላቸዉ ሲሆን በስማቸዉ የመክሰስ ሆነ የመከሰስ እንዲሁም ማንኛዉንም ስራ የመስራን ሰፊ መብት ተጎናፀፈዋል፡፡
8. የአክስዮኖችን ማስተላለፍን በተመለከተ/Transferable shares፡-
አክስዮን ማህበር ምንም እንኳን በማኅበሩ አንቀጾች ውስጥ የአክሲዮን ነፃ ዝውውርን መገደብ ቢቻልም (አንቀጽ. 333 (1) የአክሲዮን ኩባንያ አጠቃላይ መርሆዎች በነፃነት የሚተላለፉ በመሆናቸው በአክሲዮን ገበያ ሊሸጡ ወይም ሊገዙ ይችላሉ ፡፡ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአባላቱ መካከል በነፃነት የሚተላለፉ ሲሆን ለሌሎች ግን እንደ አክስዮን ማህበር እንደፈለጉ በነፃነት የሚተላለፍ አይደለም ምክንያቱም ሲመሰረትም ቤተሰባዊ እና ቅርርብን መሰረት ተደርጎ የሚመሰረት ማህበር በመሆኑ ነው፡፡
☞ሰናይ ጊዜ
© Yilkal
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Entrust🔷ETC)
የአክስዮን ማህበር መመስረት የሚያስገኙ ጥቅሞች፡-
የአባላቱ ሀላፊነት የተወሰነ መሆኑ፤
የአክስዮን አባላቱ ቢሞቱም በወራሾች በቀላሉ መቀጠል ስለሚችል የማይሞት መሆኑ፤
አክስዮን ማህበር ትልቅ ካፒታል የሚጠይቅ ስለሆነ ግዙፍ ኢንተርፐራይዞች እንዲኖሩ ማድረግ መቻሉ፤
ጠንካራ የገንዘብ አቅም መኖሩ፤
ድርሻዉ በቀላሉ የሚተላለፍበት እና የአባላትም ቁጥር የሚቀያየር መሆኑ፤
ቦንድ/የብድር ሰነድ/መሸጥ የሚችል መሆኑ፤
የተለያየ የአስተዳደር አካላት ማለትም የዳይሬክቶሮች ቦርድ፤ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ እና የዉጪ ኦዲተር ያሉት መሆኑ፤
የመስፋፋት እድል መኖሩ፤
የተበተነ አደጋ መኖሩ/Diffused risk/
ከ50 በላይ አባላት ያሉት ማቋቋም ሲፈለግ፤
መዋጮ ከህዝብ መሰብሰብ መቻሉ ማለትም ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለማቋቋም የአክስዮን ሽያጭ ማስታወቂያ ለህዝብ አስነግሮ ካፒታል መሰብሰብ አይችልም ፡፡ በመሆኑም ብዙ ገንዘብ በሚጠይቁ ዘርፎች ለመሰማራት ካፒታልን ከህዝብ መሰብሰብ የሚያስችል ስለሆነ አክስዮን ማህበር ተመራጭ ያደርገዋል፡፡
ለሶስተኛ ወገኖች የበለጠ አስተማማኝ እና ተቋማዊ ቅርፅ የያዘ መሆኑ፤ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አሰራሩ ቀላል፤ በህግ የሚደረግበት ቁጥጥር የላላ፤ የአስተዳደር ስርዓቱ በአንፃራዊነት የማያስተማምን ስለሆነ 3ኛ ወገኖችን ብዙ አያስተማምንም፡፡ በተቃራኒዉ አክስዮን ማህበር አሰራሩ ዉስብስብ፤ዝርዝር የህግ ቁጥጥር ያለበት፤ አስተዳደሩ በብዙ አካላት የተደራጀ ስለሆነ ለአባላትም ሆነ ከአክስዮኑ ጋር ግኑኙነት የሚፈጥ የ3ኛ ወገኖች መብት ለማስጠበቅ አስተማማኝ ነው፡፡
አንዳንድ የስራ ዘርፎች በህግ በግልጽ በአክስዮን ማህበር ብቻ የሚሰሩ መሆናቸዉ፤ ምሳሌ ባንክ እና ኢንሹራንስ ስራ በሀላፊነቱ የጠወሰነ የግል ማህበራት የማይሰራ መሆኑ፤
ስለሆነም የአክስዮን ማህበር ከላይ ባየናቸዉ ባህሪያት ያሉት ከአባላቱ የተለየ ሀላፊነት ያለበት ራሱን የቻለ የህግ ሰዉነት ያለዉ ድርጅት መሆኑ ተመራጭ የሚያደርገዉ ቢሆንም የራሱ ሆነ ድክመቶች ያሉት ሲሆን እንደሚከተለዉ እናያለን፡፡
የአክስዮን ማህበር መመስረት ያሉት ጉዳቶች፡-
አክስዮን ማህበር ለመመስረት ዉስብስብ እና አስቸጋሪ ስነ ስርዓት መጠየቁ፤
በምስረታ ሂደት የተለያዩ ባለሙያዎች አስፈላጊ መሆናቸዉ ምሳሌ መመስረቻ ፁሁፍን እና መተዳሪያ ደንቡን ለማዘጋጀት የህግ ባለሙያ ማስፈለጉ፤ በአይነት የሚደረገዉን መዋጮ ለመወሰን የሂሳብ ሰራተኛ እና ማህንዲስ አስፈላጊ መሆኑ በምስረታ ሂደትን ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑ፤
በቀጥታ የንብረቱ ባለቤት ያለመሆን፤
የዉሳኔ መዘግየት መኖሩ ምክንያቱም በእያንዳንዱ ወሳኝ ጉዳይ ላይ የጠቅላላ አባላትን እና የተለያዩ አካላትን ዉሳኔን የሚያስፈልግ መሆኑ፤
በጥቂት እጅ የወደቀ እና የተንኮል አስተዳደር የመፈጠር እድሉ ሰፊ ነው ምክንያቱም ባላክስዮኖቹ በየሀገሩ የተበታተኑ እና የማይተዋወቁ በመሆናቸዉ በቀላሉ ለመቆጣጠር እና መብታቸዉን በተደራጀ መልኩ ለማስከበር ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌ፡- የባንክ አባሎች የማይተዋዉ ብዙ ቁጥር ያለቸዉ በመሆኑ ቦርድ እና ስራ አስኪያጆችን በየቀኑ ለመቆጣጠር ያስቸግራል፡፡
ሚስጢር ያለመጠበቅ ችግር

ሰናይ ጊዜ 👏
YilkalG.
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
ስለወጭና ስለኪሳራ /በክርክሩ ምክንያት የወጡ ወጪዎች የሚመለከተው ወገን
#አለ_ህግ
#ስለ ፍርድ ቤቱ ሥልጣን
በሌላ አኳኋን እንዲፈጸም በግልጽ ካልተደነገገ በቀር በክስ ምክንያት ስለሚከፈለው ስለማናቸውም ወጭና ኪሳራ፣ የሚከፈለውን ወገን የወጭንና የኪሳራውን ልክ የሚከፈልበትን የሃብት ምንጭ የአከፋፈሉን ሁኔታ ሌላውንም ተገቢ መስሎ የታየውን ውሳኔ ወይም ትእዛዝ ፍርድ ቤቱ ትክክል በስሎ በሚገመተው ሁኔታ ሊሰጥ ይችላል፡፡
#ስለወጭና ስለኪሳራ ዝርዝር
ተረቺው ለረቺው ኪሳራና ማናቸውንም ወጭ እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ሲያዝ፣ ወጭ ያደረገው ወገን የወጭውን ልክ የሚያሳይ ዝርዝር አዘጋጀቶ ማቅረብ አለበት፡፡
ዝርዝር የሚቀርበው ፍርዱን ለፈረደው ፍርድ ቤት ሲሆን አንዱ ግልባጭ ለከፋዩ ወገን ይሰጣል፡፡
#የወጭው ሂሳብ ስለሚመረመርበት ሁኔታ
የወጭው ሂሳብ ዝርዝር ለፍርድ ቤቱ ከቀረበ በኋላ ትክክለኛነቱ የሚመለመርበትን ቀን ቀጠሮ ወስኖ ባለጉዳዮቹ እንዲቀርቡ ያዛል፡፡
ሂሳቡን መርምሮና ተከራካሪዎቹ ወገኖች የሚያቀርቡትን ሃሳብ ተቀብሎ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን ይፈጽማል፡፡
በቀረበው የሂሳብ ዝርዝር ውስጥ በቂ ባልሆነ ምክንያት ከፍ ብሎ የሚታየውን ገንዘብ ይቀንሳል፡፡ ወይም
በዝርዝሩ ውስጥ የክሱን ጉዳይ ለማስፈጽም ወይም አስፈላጊውን ዳኝነት ለመከታተል ተገቢ ያልሆነ ወጭ ተመልክቶበት የተገኘ እንደ ሆነ ፍርድ ቤቱ ሊቀንሰው ወይም ሊያስቀረው ይችላል፡፡
ወጭው ወይም ኪሳራው ሊከፍለው የሚገባው ወገን የሚጠይቀውን የወጭ ዝርዝር ያላቀረበ እንደ ሆነ ፍርድ ቤቱ ይህንኑ መዝግቦ ሌሎች ወገኖች ያደረጉትን ወጭ መርምሮ ያረጋግጥላቸዋል፡፡ ወይም የሂሳቡን ዝርዝር አንዱ ወገን ባለማቅረቡ ምክንያት ሌሎች ወገኖች እንዳይጎዱ ላላቀረበው ወገን ተገቢ ግምት ያለው ኪሳር ይወስንለታል፡፡
ማንኛውም የወጭ ወይም የኪሳራ ገንዘብ በፍርዱ መሰረት እስኪፈጸም ድረስ ዋናው ፍርድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በሕግ የተወሰነ ወለድ ይታሰብበታል፡፡
ፍርድ ቤቱ በኪሳራና በወጭ አከፋፈል ምክንያት ለተነሳው ክርክር ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት የፍርድ ቤቱ ሬዢስትራር ወይም የምግብ ቤቱ ሹም የቀረበውን ዝርዝር መርምሮና ተከራካሪዎቹ ወገኖች የሚያቀርቡትን አሳብ ተቀብሎ የተጣራውን ሂሳብ እንዲያቀርብለት ከማዘዝ የዚህ ቁጥር ድንጋጌ አያግደውም፡፡
#ካሳ ስለሚከፈልበት ምክንያት
በማንኛውም ክስ ወይም ክርከር ላይ በክስ ወይም በመከላከያ መልክ ከሳሹ ወይም ተከሳሹ ያቀረበው የመከራከሪያ ወይም የመከላከያ ማስረጃ ወይም ክርክሩ ራሱ ወይም ማስረጃው አሰተኛ ነው ወይም መከራከሪያውንና አሰተኛ ማስረጃ ያቀረበው ወገን በሐሰት የተከራካሪውና አሰተኛ ማስረጃ ያቀረበው ክርክሩን ለማሰናከል፣ ጊዜ ለመፍጀት ወይም አንደኛውን ወገን ለመበደል ወይም ለማጉላላተር ሆነ ብሎ ያደረገው ነው በማለት ወይም የክርክሩንና የማስረጃውን አሰተኛነት እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው ሆን ብሎ ማቅረቡን ሲያመለክትና ፍርድ ቤቱም ተቃዋሚው ወገን ያቀረበውን ነገር እርግጠኛነት ሲረዳው ይህንኑ በመዝገቡ ላይ አስፍሮ አሰተኛ ማስረጃ ወይም ክስ ወይም መከላከያ ያቀረበው ወገን ላቀረበው ለእያንዳንዱ ሀሰተኛ ማስረጃአንዱን ወገን ለመበደል፣ ለማጉላላት ወይም ጊዜ ለመፍጀት ላቀረበው አሰተኛ ክርክር ከማናቸውም ኪሳራና ከሌላው ወጭ በቀር ከ500 ብር የማይበልጥ ካሳ ለተበዳዩ እንዲከፈል ሊወስንበት ይችላል፡፡
#ይህም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በቁጥር 446 በተመለከተው መሰረት ሃሰተኛ ማስረጃና ክርክር በማቅረቡ ከመከሰስና ከመቀጣት ነፃ ሊሆን ይችላል፡፡
ካሳ የተወሰነለት ወገን በሀሰት በመከሰሱ ወይም ሃሰተኛ መከላከያ ወይም ክስ የቀረበበት በመሆኑ ካሳና ኪሳራ ይገባኛል ሲል ሌላ ክስ አቅርቦ ካሳ ወይም ኪሳራ የተወሰነለት እንደሆነ በመጀመሪያው ክስ ላይ ከሚወስንለት ኪሳራና ካሳ ላይ ይቀነስበታል፡፡
#ስለ ይግባኝ
ማንኛውም ተከራካሪ ወገን በስረ ነገሩ ላይ ይግባኝ ባያቀርብም፣ በተወሰነበት የወጭ ወይም የኪሳራ አከፋፈል ብይን ላይ ይግባኝ ለማለት ይችላል፡፡ በዚህም ነገር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡
ፀጋዬ ደመቀ ሎየር
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
ቀጠሮ ሳናከብር በመቅረታችን ይቅርታ እንጠይቃለን❗️❗️🙏🙏

ውድ የ አለ_ህግ ቤተሰቦች
@lawsocieties
ሁሉንም የ #አለ_ህግ አባላትን በሚያሳትፍ መልኩ በወቅታዊ ጉዳይ ስለ ህጎች፣ ሁሌም እሁድ እሁድ የቀጥታ (Live stream) የድምፅ ውይይት መጀመራችን ይታወቃል።
ሆኖም፣
#የህግ ጉዳይ የመወያያ እርዕስ አስቀድማችሁ እንድትመረጡ አሳሰብን ነበር፣
ምክንያቱም፣ ከወዲሁ ተዘጋጅተው ለውይይቱ እንዲመጡና ጠቃሚና ፍሬአማ ሀሳቦችን እንድንለዋወጥ ይረዳናል።
1. የመወያያ አጀንዳ ይምረጡ
2. ተዘጋጅተው የውይይቱ ተሳታፊ ይሁኑ
3. Share and add ማድረግን አትርሱ
#Ale_Lawsocieties
#አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
አለ_ህግ Ale Hig, Ale Law Societies #አለ_ህግባለሙያ፣ ነፃ የህግ ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ የውልና የክስ ቅፆች (ፎርሞች) ፤ የህግ ጉዳዮችን 🔴ሁሉንም ሕጎች በአንድ ላይ ያገኙበታል 🔴 All in one, for All. #አለ_ህግ መሰረታዊ የህግ መረጃና እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው።
ይህን ሊንክ በመጫን በቴሌግራም ተቀላቀሉን https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
email us: lawsocieties@gmail.com
contact us via telegram Bot @LawsocietiesBot

follow us on Facebook page
https://www.facebook.com/lawsocieties/
የብድር ውል የፍትሐብሔር ሕግ ከቁጥር 2471-2489፣
#አለ_ህግ
የብድር ውል ምንነት፡- የተለያዩ ፅሑፎች እንደሚያስረዱት ብድርን በተመለከተ ሁሉንም ሊያግባባ የሚችል አንድ ወጥ የሆነ ትርጉም አናገኝለትም፡፡ የፍትሐብሔር ሕጋችን የሚከተለውን ትርጉም ሰጥቶታል፡- “የሚያልቅ ነገር ብድር ማለት ከተዋዋዮቹ አንዱ ወገን አበዳሪው ሌላውን ተበዳሪ ሰው የተበደረውን ነገር በዓይነቱ ለመመለስ ተገዳጅ በማደረግ ገንዘብ ወይም በማገልገል የሚያልቅ ሌላ ነገር ለተበዳሪው ለመስጠትና ሀብትነቱን ለማስተላለፍ የሚገደድበት ውል ነው” ይላል፡፡ ከዚህ ትርጓሜ መረዳት እንደሚቻለው ብድርን በሚመለከት ሕጉ በሚያልቅ ነገር ላይ ብቻ እንጂ ከዛ ባለፈ ማለትም በማያልቅ ነገር ወይም ቋሚ የሆነ ንብረትን የማያካትት መሆኑን ነው፡፡ የድንጋጌውን አጠቃላይ ይዘት ስናይ አመላለሱ በዓይነት ወይም በአገልግሎት ሊሆን እንደሚችል እና ውሉ አስገዳጅ መሆኑንም ያሳያል፡፡
የዉል አመሠራረት፡- የብድር ውል የውል አንድ አካል እንደመሆኑ መጠን አመሰራረቱም ሆነ አፈፃፀሙ በጠቅላላው የውል ሕግ መርሆች የሚገዛ በመሆኑ የብድር ውልን ዝርዝር ድንጋጌዎች ከማየታችን በፊት ስለውል አመሰራረት ባጭሩ አይተን ብናልፍ የተሻለ ግንዘቤን ይፈጥራል፡፡ ዉል ስምምነት ቢሆንም ከሌሎች ስምምነቶች የሚለየዉ በአፈፃፀሙ ከበስተጀርባዉ የሕግ ድጋፍ ያለዉ ስምምነት መሆኑ ላይ ነዉ፡፡

አንድ ውል የሚፀና ውል ነው ለማለት የሚከተሉትን መርሆች ማሟላት አለበት፡- 1ኛ ዉል የሚፈፀመዉ ለመዋዋል ችሎታ ባላቸዉ ሰዎች መካከል ብቻ መሆኑ (እድሜዉ ለአቅመ አዳም/ሄዋን ያልደረሰ ወይም አይምሮዉ ህመም ያለበት ሰዉ ወይም በፍርድ ቤት የተከለከለ ሰዉ ችሎታ እንደሌለዉ ይቆጠራል፡፡) 2ኛ ዉል የሚደረገው በተወያያቹ ነፃ ፍቃድ ብቻ የሚደረግ መሆኑ፡፡ 3ኛ ተወያይ ወገኖች የሚዋዋሉበት ጉዳይ በእርግጠኝነት የሚቻል እና ህጋዊና ሞራላዊ ጉዳይ ላይ መሆን የሚገባው መሆኑ፡፡ 4ኛ የዉል አቀራረጹ ወይም አፃፃፉ (ፎርም) በህግ ተለይተዉ የተቀመጡ ወይም ተዋዋይ ወገኖች ተለይቶ እንዲቀመጥ ከተስማሙበት የዉል ጉዳይ በቀር የተለየ የዉል ፎርም አያስፈልግም፡፡

የአበዳሪና ተበዳሪ ግዴታዎች፡- አበዳሪና ተበዳሪ የራሳቸው የሆኑ ሊያከብሯቸው የሚገቡ ግዴታዎች አሉባቸው፡፡ በቅድሚያ የአበዳሪው ግዴታዎችን ስናይ ሕጉ የአበዳሪውን ግዴታዎች በተመለከተ የሽያጭ ውልን በሚደነግገው ክፍል ላይ የሻጩ ግዴታዎች ተብለው የተገለፁት ደንቦች በአበዳሪ ላይ ተግባራዊ ይሆናሉ ይላል፡፡ በፍትሐብሔር ሕጉ የሻጭ ግዴታዎች ናቸው የተባሉት ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1ኛ ዕቃ የማስረከብ ግዴታ፡- የሽያጭ ውል ከተከናወነ በኋላ ሻጭ የግብይት ምክንያት የሆንውን ዕቃ/ንብረት ለገዥ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡ 2ኛ ስመ-ሀብት የማስተላለፍ ግዴታ፡- ከላይ ለማንሳት እንደተሞከረው የሽያጭ ውል ልዩ መገልጫ ከሆኑት ጉዳዮች ውስጥ ሻጩ የሽጭ ምክንያት የሆነውን ንብረት ስመ-ሀብትን የማስተላለፍ ግዴታ ያለበት መሆኑ ነው፡፡ የባለቤትነት መብት መተላለፍን በተመለከተ የብድር ውል ከሽያጭ ውል ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር የብድር ውሉ በትርጉም ክፍሉ ላይ እንደሰፈረው አላቂ ዕቃን ብቻ የሚመለከት በመሆኑ ዕቃውን ለተበዳሪው በሚያስረክብበት ወቅት የባለቤትነት መብትም አብሮ መተላለፍ መቻሉ ነው፡፡ 3ኛ ዋስትና የመስጠት ግዴታ፡- ሌላኛው የሻጭ ግዴታ ከተሸጠው ዕቃ ጋር በተገናኘ ለሚፈጠሩ ችግሮች ለገዥው ዋስትና የመስጠት ግዴታ ነው፡፡

የተበዳሪውን ግዴታዎች በተመለከተ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ዕዳውን መልሶ ከመክፈል ጋር የሚገናኝ ነው፡፡ ተበዳሪ የብድር ውል ውስጥ ሲገባ የተበደረውን ነገር በዓይነቱ ለመመለስ ወይም በገንዘብ የሚመለስ ሲሆን እነዚህን በወቅቱ የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡ የብድሩ አመላለስ በማገልገል የሚያልቅ ሲሆን ደግሞ ለአበዳሪው ተገቢውን)
የብድር ማስረጃ፡- ማስረጃ ማለት አንድ በፍርድ ቤት ምርመራ ላይ ያለ በጭብጥ የተያዘ አከራካሪ ጉዳይ እውነት መሆንና አለመሆኑን በሚያሳምን ሁኔታ ማረጋገጥ እንዲያስችል በግብአት የሚቀርብ ፍሬ ነገር ስለመሆኑ ብ/ጀነራል ታጠቅ ታደሰ “የማስረጃ ሕግ መሰረተ ሀሳቦች” በሚለው መፅሐፋቸው ገልፀውታል፡፡ ማስረጃ ማለት ይህ ከሆነ በሁለት ሰዎች መካከል የብድር ውል ተደርጓል ወይስ አልተደረገም የሚለውን ጥያቄ በምን ማረጋገጥ እንችላለን? የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ ቀጥለን እናያለን፡፡ የፍ/ሕጋችን በአን. 2472 ስር የብድር ማስረጃ በሚል ርእስ የሚከተለውን ደንግጓል፡-
(1) በብድር የተሰጠው ገንዘብ ከብር 500 በላይ ሲሆን የብድሩን ውል በፅሑፍ ወይም በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም መሐላ ካልሆነ በስተቀር ለማስረዳት አይቻልም፡፡
(2) ለብድር ውል ማናቸውም ሌላ ዓይነት ማስረጃ ለማቅረብ አይቻልም ፡፡ (3) እንዲሁም ከብር 500 የበለጠ ገንዘብ የመክፈል ነገር በዚህ ዓይነት ይፈፀማል፡፡ በዚህም መሰረት የብድሩ መጠን ብር 500 እና ከዛ በታች ከሆነ በማንኛውም ዓይነት ማስረጃ ለምሳሌ በቦታው የነበረ የሰው ምስክር በመስማት ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑን እና መጠኑ ከዛ በላይ ከሆነ ግን ከሦስቱ የማስጃ ዓይነቶች መካከል በአንዱ ካልሆነ በስተቀር በሌላ በምንም መንገድ ማረጋገጥ የመማይቻል መሆኑን ነው መረዳት የሚቻለው፡፡ እነዚህን ሦስት የማስረጃ ዓይነቶች ቀጥለን እንመልከት፡፡
የመጀመሪያውና የበለጠ አስተማማኝ የሆነው ማስረጃ የፅሑፍ ማስረጃ ነው፡፡ ይህም ማለት ገና ከጅምሩ የብድር ውሉ ሲደረግ በፅሑፍ የተደረገ ሲሆን ያንን ፅሑፍ ለፍርድ ቤት በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል፡፡ በሌላ አነጋገር ከብር 500 በላይ የሆነ የብድር ውል በፅሑፍ እንዲሆን ሕጉ አስገዳጅ የሚመስል ድንጋጌ ያስቀመጠ በመሆኑ ከላይ ካነሳነው የውል አመሰራረት መርሆች መካከል የተለየ ፎርም የሚፈልግ መሆኑን ማየት ይቻላል፡፡ ሁለተኛው የማረጋገጫ መንገድ በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ነው፡፡ ይህም ማለት ተበዳሪው በፍርድ ቤት ቀርቦ በከሳሹ የቀረበበትን ክስ ማለትም ከከሳሹ ገንዘብ የተበደረ መሆኑን፣ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ በማያሻማ መንገድ ካመነ በቀላሉ የብድሩ መኖር የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡ ሦስተኛውና የመጨረሻው የማረጋገጫ መንገድ በመሐላ የማረጋገጥ ሂደት ነው፡፡ መሐላ ማለት በክርክር ወቅት አንድ ተከራካሪ ወገን በሚያቀርበው ማስረጃ ወይም በሚናገረው ፍሬ ነገር እውነትነትን ለማረጋገጥ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ቅፅ ላይ የሚሰጡት ማረጋገጫ ነው፡፡

የብድር መመለሻ ጊዜ፡- ብድር ውል እንደመሆኑ መጠን ለተዋዋይ ወገኖች ሰፊ ነፃነት መሰጠት አለበት፡፡ በመሆኑም ሕጉ ስለብድር መመለሻ ጊዜ በተዋዋይ ወገኖች የተወሰነ ጊዜ በሚኖርበት ወቅት ይህንኑ ዕውቅና በመስጠት ክፍያው በዛ ጊዜ መሆን እንደሚገባው ሕጉ አፅንኦት ሰጥቶበታል፡፡ ከዚህም ባለፈ ብድሩ ወለድ የሌለበት ከሆነ የተበደረውን ገንዘብ ለመመለስ ማሰቡን ለአበዳሪው ከአንድ ወር በፊት አስታውቆ የመመለሻ ጊዜው ከመድረሱ በፊት ሊመልስለት እንደሚችልም ሕጉ ይደነግጋል፡፡ የብድሩ መመለሻ ጊዜ በተዋዋይ ወገኖች ያልተወሰ በሚሆን ጊዜ ሕጉ ብድሩ በምን ያክል ጊዜ ውስጥ ሊከፈል እንደሚገባው ደንግጓል፡፡ ይኼውም አበዳሪው መልስልኝ ሲል ከጠየቀበት ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መመለስ እንዳለበት ተደንግጓል፡፡.........ይቀጥላል...
#አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
.......................ተበዳሪውም በአበዳሪው ሳይጠየቅ መክፈል ቢፈልግ ለመክፈል ያለውን ሀሳብ ከአንድ ወር በፊት ካስታወቀ በኋላ ዕዳውን መመለስ እንደሚችል እንዲሁ ተደንግጓል፡፡

በብድር ላይ ሊኖር ስለሚችል ወለድ፡- በብድር ውል ላይ ሊኖር ስለሚችል ወለድም ለተዋዋይ ወገኖች ነፃ ፈቃድ የተተወ ጉዳይ ነው፡፡ ብድሩ ወለድ የሚከፈልበት ስለመሆኑ በውሉ በግልፅ ካልተገለፀ ግን ተበዳሪው በምንም መልኩ ወለድ እንዳይከፍል ሕጉ ጥበቃ ያደርግለታል፡፡ ሕጉ በብድር ውሉ ላይ ወለድ ይኑር አይኑር የሚለውን ጉዳይ በተዋዋይ ወገኖች እንዲወሰን ነፃነት የሰጠ ቢሆንም በወለድ መጠኑ ልክ ላይና ስለሚከፈልበት ጊዜ ወይም ወለዱ ስለሚሰላበት ጊዜ ግን ገደብ አስቀምጧል፡፡ በዚህም መሰረት ተዋዋይ ወገኖች የወለዱን መጠን በዓመት ከ12 በመቶ በላይ ማድረግ እንደማይችሉ ገደብ ጥሏል፡፡ እንዲሁም የወለዱ መጠን በውሉ ላይ ካልተገለፀ እና ወለድ የሚከፈልበት ብድር መሆኑ ብቻ ተገልፆ ከሆነ ወይም ወለዱ ከ12 በመቶ በላይ ይሆናል የሚል የውል ቃል ካለ መከፈል የሚችለው የወለድ መጠን በዓመት 9 በመቶ ብቻ እንደሚሆንና የሚሰላውም ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ ብድሩ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር በየዓመቱ መጨረሻ ላይ መሆን ይገባዋል ይላል ሕጉ ፡፡

የብድር አከፋፈል (የሚከፈለው ነገር)፡- በብድር አመላለስ ወቅት ሌላው ግለፅ መሆን ያለበት ጉዳይ ብድሩ በየትኛው ሀገር የገንዘብ ዓይነት ነው? ከብድሩ በኋላ የምንዛሬ ዋጋ መለዋወጥ ቢያጋጥምስ ምን ይሆናል? የሚለው ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የፍትሐብሔር ሕጉ ግልፅ ድንጋጌዎች አሉት፡፡ በዚህም መሰረት የብድር ውሉ የተደረገው በኢትዮጵያ ብር ከሆነ ብድሩ በሚመለስበት ወቅት ባለው ሕጋዊ የኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ ወይም ለዚህ የገንዘብ መጠን የሚተካ የውጭ ምንዛሬ በማቅረብ ከዕዳው ነፃ እንደሚሆን ተደንግጓል፡፡ የሚከፈለውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ የብድር ውሉ በሚከናወንበት ጊዜ በትክክል የተበደረውን ያክል እንጂ ሌላ ነገር እንደማያካትትና በመሀል ሊያጋጥም የሚችለውን ወይም ያገጠመውን የገንዘቡ ዋጋ መለዋወጥ ግምት ውስጥ መግባት እንደሌለበትም ሕጉ አያይዞ ይገልፃል፡፡ ብድሩ በውጭ አገር ገንዘብ ተደርጎ ከነበረ ደግሞ ብድሩ በሚከፈልበት ጊዜ በዛ አገር ሕጋዊ መገበያያ በሆነው የገንዘብ ኖት መከፈል ያለበት ሲሆን መጠኑም የተበደረውን ያክል ብቻ መሆን እንዳለበት ሕጉ አመልክቷል፡፡ የብድር ውሉ የተደረገው ከገንዘብ ውጪ ባሉ የሀብት ዓይነቶች በሚሆንበት ጊዜ ለምሳሌ፡- ለምግብ የሚሆኑ ነገሮች፣ ሸቀጦች ወይም መአድናት ሲሆኑ ተበዳሪው በተበደረው ልክ ብዛቱንና ዓይነቱን በመክፈል ከዕዳው ነፃ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ከብድሩ በኋላ በሚኖር የዋጋ መለዋወጥ የብድድር አመላለሱን መጠንና ዓይነት ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ የለም።

federal attorney general
You shall Share......
ሼር አድረጉት
ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ አጋሩት፣
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
ያለመናገር መብት
መግቢያ

።።።።።።።።።🙏 #አለ_ህግ
በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ስርአት ውስጥ የተያዙ ወይም የተከሰሱ ሰዎች
ያለመናገር መብት (the right to remain silent) አላቸው፡፡ ይህ መብት
የተጠረጠሩበትን ወይም የተከሰሱበትን ወንጀል እንዲያምኑ ያለመገደድ
ወይም ቃል እንዲሰጡ በሚጠየቁበት ወቅት ቃላቸውን ላለመስጠት መብት
ያላቸው መሆኑን የሚመለከት ነው፡፡ ለዚህም ሲባል ተጠርጣሪዎች በሚያዙበት
ወቅት የሚናገሩት ነገር የእምነት ቃል ሆኖ በፍርድ ሂደት በማስረጃነት
ሊቀርብባቸው ስለሚችል ላለመናገር መብት ያላቸው መሆኑን የሚጠብቅ
ነው፡፡ ይህ መብት የሚመነጨው መሰረታዊ ከሆነ የወንጀል ህግ እና የሰብአዊ
መብት መርሆች ከሆኑት እራስ ላይ ያለመመስከር ወይም ያለመወንጀል
መርህን (protection against self-incrimination) እና በፍርድ
እስኪረጋገጥ ድረስ ነፃ ሆኖ የመገመት (presumption of innocence
until proven guilty) መሰረት አድርጎ ነው፡፡
መብቱን የማክበርና የማስከበር ግዴታ
ይህ ያለመናገር መብት ለማን የተገባ ወይም የእነማን መብት ነው የሚለውን
ስንመለከት ማናቸውም በፖሊስ ተጠርጥሮ የሚያዝ፣ የተያዘ፣ የሚከሰስ
ወይም የተከሰሱ ሰዎችን የሚመለከት ነው፡፡ ይህን መብት ለማስከበር ግዴታ
ያለባቸው ደግሞ ማናቸውም የወንጀል ምርመራ እንዲሁም የመያዝ ተግባር
የሚፈፅሙ ፖሊሶችና ውሳኔ የሚሰጡ ዓቃቤ ህጎችንም እንዲሁም በፍርድ
ሂደት የሚሳተፉ ዳኞችንም ይጨምራል፡፡ እነዚህ አካላት የምርመራ፣ ውሳኔ
አሰጣጥና ፍርድ ሂደት መብቱን ማክበርና የማስከበር ሀላፊነት አለባቸው፡፡
መብቱ መከበር ያለበት ጊዜና ሂደት
ይህ መብት መቼ የሚፈፀም ወይም መከበር ያለበት እንደሆነ ስንመለከት
በመያዝ፣ በምርመራ፣ በውሳኔ አሰጣጥና በፍርድ ሂደት በአጠቃላይ
በማናቸውም የወንጀል ፍትህ አስተደደር ሂደት ሊከበር የሚገባ መብት ነው፡፡
በዋናነት ተጠርጣሪዎች በሚያዙበት ጊዜ ፖሊሶች መብቱን ማክበርና
ግዴታቸውንም መወጣት ይጠበቅባቸው፡፡ ከዚህ በመቀጠል ባሉ የወንጀል
ፍትህ ሂደቶችም ውስጥ ማለትም የወንጀል ምርመራ፣ የውሳኔ አሰጣጥና
የፍርድ ሂደት ወቅት ሊከበርና ሊጠበቅ ይገባል፡፡
የመብቱ ይዘት
ያለመናገር መብት ተጠርጣሪዎች በሚያዙበት ጊዜ ለሚይዛቸው አካል
ላለመናገር፣ ቃል እንዲሰጡ በሚጠየቁበት ወቅት ላለመናገር እንዲሁም
በፍርድ ሂደት እንዲመሰክሩ ያለመገደድ ናቸው፡፡ ይህ መብት በህገ
መንግስታችን አንቀፅ 19(3) እንደተደነገገው የሚያዙ ሰዎች በሚያዙበት
ወቅት ወዲያውኑ በሚገባቸው ቋንቋ ያለመናገር መብት እንዳላቸውና
የሚሰጡት ማንኛውም ቃል ፍርድ ቤት በማስረጃነት ሊቀርብባቸው
እንደሚችል መረዳት በሚችሉት ቋንቋ እንደተያዙ ወዲያውኑ ማስገንዘቢያ
እንዲሰጣቸው መብት አላቸው፡፡ በተጨማሪም በአንቀፅ 19(5) መሰረት
የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል የእምነት ቃል
እንዲሰጡ ወይም ማናቸውም ማስረጃ እንዲያምኑ ሊገደዱ እንደማይገባ እና
በማስገደድ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት እንደሌለው ይደነግጋል፡፡ በአንቀፅ
20(3) በፍርድ ሂደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ
ያለመቆጠር፣ በምስክርነት እንዲቀርቡ ያለመገደድ መብት አላቸው፡፡ ይህን
መብት ተፈፃሚ ለማድረግ በወንጀል ስነ ስርአት ህግ አንቀፅ 27(2) መሰረት
መርማሪው ፖሊስ የተጠረጠረውን ሰው ቃሉን ለመስጠት ነፃ እንደሆነ እና
ፈቅዶ የሚሰጠው ማናቸውም ቃል በማስረጃነት የሚቀርብ መሆን አስቀድሞ
መንገር እንደሚገባ ይደነግጋል፡፡
በተጨማሪም የምርመራ ስራ በሚከናወንበት ወቅት የምርመራ ቃል መቀበያ
ፎርሞች ይህው ማስገንዘቢያ ተገልጾ እንዲታተሙ የሚደረግ ሲሆን ህጉ
በሚያዘውና በፎርሞቹ ላይ በተቀመጠው መንገድ መብቱን ተግባራዊ ማድረግ
እና ይህን ተግባራዊ ከማድረግና መብቱ ሳይነገር ወደ ጥያቄ ከመግባት
አንፃር ያለውን ክፍተት ማስተካከል ይጠበቃል፡፡
ይህ መብት በተመሳሳይ መልኩ ሀገራችን በተቀበለቻቸው አለም አቀፍ
የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች በግልፅ እና በትርጉም የተካተተ ነው፡፡
በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ አንቀፅ 10 በፍትሀዊ የፍርድ
ሂደት መብት (fair trial) ትርጓሜ እና አንቀፅ 11 ነፃ ሆኖ የመገመት መብት
እውቅና የተሰጠው ነው፡፡ በአለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች
ስምምነት አንቀፅ 14/3/g/ መሰረት በራስ ላይ ለመመስከር ከመገደድ
መጠበቅ እና በአንቀፅ 14/2/ ነፃ ሆኖ የመገመት መብት ተካቶ ይገኛል፡፡
በተመሳሳይ በሌሎች ሀገራትም ይህ መብት እውቅና የተሰጠውና ተግባራዊ
የሚደረግ ስርአት እና የአሰራር ደረጃ (standard) ነው፡፡ ሆኖም ይህ
ያለመናገር መብት ለህግ አስከባሪ አካላት ማንነትን እና አድራሻን ከማሳወቅ
ግዴታ የሚጠብቅ ሳይሆን ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር በተያያዘ ያለመናገር
መብትን የሚመለከት ነው፡፡
በዚህም መሰረት መብቱን ተፈፃሚ ለማድረግ አንድ ተጠርጣሪ በሚያዝበት
ወቅት በተመሳሳይ ፆታ ሆኖ ማንነትን ወይም ህግ አስከባሪ አካል መሆንን
ማሳወቅ፣ የሚያዘው በፍርድ ቤት ትእዛዝ መሰረት ከሆነ ይህንኑ ማሳየት
ወይም እንደ እጅ ከፍንጅ ባለ ሁኔታ የሚያዝ ከሆነም የመያዙን ህጋዊነት
ማረጋገጥ፣ ቀጥሎም በቁጥጥር ስር የዋለ መሆኑን መንገር፣ የሚያዝበትን
ምክንያት ወይም የተጠረጠረበትን ወንጀል መንገር፣ ያለመናገር መብት
እንዳለው እና የሚናገር ነገር በፍርድ ቤት በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል
መሆኑን ማስገንዘብ፣ በጠበቃ የመወከል መብት እንዳለውም መግለፅና
ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህንም በሚገባው ቋንቋ መንገር
ያስፈልጋል፡፡
በአጠቃላይ የዜጎችን መብቶች ተፈፃሚ ለማድረግና አለማአቀፍ የወንጀል
ምርመራ አሰራር ደንቦችን ተግባራዊ ለማድረግ የህግ አስከባሪ አካላት
የተጠርጣሪዎችና የተከሰሱ ሰዎችን መብቶች ማወቅና ተግባራዊ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንፃር በህገ መንግስታችን እና በሌሎች ህጎች እውቅና
የተሰጠውን የሚያዙና ቃል የሚሰጡ ሰዎችን ያለመናገር መብት እንዳላቸው
እና የሚሰጡት ቃል በፍርድ ቤት በማስረጃነት ሊቀርብ እንደሚችል
በሚያዙበት ጊዜና ቃል እንዲሰጡ በሚጠየቁበት ጊዜ አስቀድሞ ማስገንዘብ
ያስፈልጋል፡፡ ዜጎችም ይህን መብታቸውን አውቀውና ተገንዝበው ይጠቅመናል
በሚሉት መንገድ መጠቀም ይገባል፡፡
ምንጭ የፍትህ ሚኒሥቴር ማህበራዊ ገጽ
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
#1-
ደሀ ደንብ
ዳኝነት ሳይከፈል፣ በነፃ መዝገብ ማስከፈት

ክስ ለማቅረብ የፈለገ ወገን ከፍርዱ ለሚያገኘው የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል የገንዘብ አቅም የሌለው ከሆነ ክሱን ያለዳኝነት ገንዘብ በደሀ ደንብ መሠረት የማቅረብ መብት እንዳለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 215 ተደንግጓል፡፡ ክሱን የሚያቀርበው ወገን ድሀ በመሆኑ ምክንያት የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍል ክሱን አቅርቦ እንዲያሰማ ሊፈቅድለት ይገባል? የሚለው ጉዳይ ሊለይ የሚችልበት ዝርዝር አፈፃፀም ደንቡም ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 እና ተከታዩ ድንጋጌዎች ተመልክቷል፡፡ እነዚህ ደንቦች ተፈፃሚነታቸው ክስ ለማቅረብ በፈለገ የተፈጥሮ ሰውም ሆነ በሕግ ሰውነት ያላቸው ወገኖችም ጭምር ነው፡፡
በዚህም መሠረት ድሀ ነኝ፤ መብቴን ለማስከበር ያለኝ ፍላጐቴ በዳኝነት ገንዘብ እንቅፋት ምክንያት ሊሰናከል አይገባም፡፡ ስለሆነም በድሀ ደንብ መሠረት ክሱን በነፃ እንዳሰማ ይፈቀድልኝ የሚል ማናቸውም ከሳሽ ድሀ መሆኑን ሊያመለክት የሚችል የሚገኝበትን የገንዘብ አቋም ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ ይህም ከሳሹ የሚገኝበት የገንዘብ አቋም ከተረጋገጠ በኋላ ለክሱ ሊከፈል የሚገባው የዳኝነት ገንዘብ መጠን ከሳሹ ከሚገኝበት የገንዘብ አቋም አኳያ ተገናዝቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 መሠረት ድሀ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ሊለይ ይገባል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 79555 ቅጽ 14፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467
አንድ ሰው በፍርድ ሊያልቅ የሚገባው ጉዳይን ፍርድ ቤት ይዞ ሲቀርብ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ መክፈል ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 215፣ ከ467 እስከ 479 ድረስ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ያሳያሉ፡፡ የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የማይችል ሰው ክስ ለማቅረብ የሚችልበት አግባብ ስለመኖሩም ተጠቃሽ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡ አንድ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመክፈል የማይችል ሰው በደሃ ደንብ ክስ ለማቅረብ የሚችል ሲሆን ለመክፈል አቅም እያለው ክስ ያቀረበ መሆኑ ከተረጋገጠ ግን መዝገቡ እንደሚዘጋ፣ የተዘጋ መዝገብ ደግሞ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ /ገንዘቡን/ ለመክፈል ዝግጁ እስከሆነ ድረስ የሚንቀሳቀስለት መሆኑን የሥነ ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች መንፈስና ይዘት ያስገነዝባሉ።
ሰ/መ/ቁ. 52942 ቅጽ 12፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467-479 ....ይቀጥላል --- source ፦Amharic Legal Glossary Abrham Yohanes
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
የብድር ውል
የብድር ውል (በኢትየጵያ የፍትሐብሔር ሕግ ከቁጥር 2471-2489) ከዚህ እንደሚከተለው ብድር የሚለውን ቃል ፍቺ ይሰጣል፡፡
“የሚያልቅ ነገር ብድር ማለት ከተዋዋዮቹ አንዱ ወገን አበዳሪው ሌላውን ተበዳሪ ሰው የተበደረውን ነገር በዓይነቱ ለመመለስ ተገዳጅ በማደረግ ገንዘብ ወይም በማገልገል የሚያልቅ ሌላ ነገር ለተበዳሪው ለመስጠትና ሀብትነቱን ለማስተላለፍ የሚገደድበት ውል ነው” ይላል፡፡
በተቋማችን የብድር ውል ለመዋዋል ሁለቱም ወገኖች ሊያሟላቸው የሚገባቸውን ዝርዝር ቅድመ ሁኔታዎች ከዚህ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
. በተቋሙ የDARIS ስርዓት የተዘጋጀ ሰነድና የአገልግሎት ቁጥር፤
. ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጫ ሰነድ፤
. የተዋዋዮች በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤
. የተዋዋዮች የጋብቻ ማስረጃ ወይም የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፤
. ተበዳሪው የንግድ ማህበር ከሆነ መመስረቻ ጽሑፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ የንግድ ዋና ምዝገባ እና እንደ አስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባኤ፤
. ገንዘቡ የተላለፈበት (የባንክ ስቴትመንት ስሊፕ) እና የባንክ ደብዳቤ፤
. በተቋማችን ተገልጋዮች ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ ለአገልግሎቱ የሚወስደው ጊዜ 30 ደቂቃ ነው፡፡
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ( share ) በማድረግ ብልሹ አሰራር እና ሙስናን ይከላከሉ፡፡

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
#የሚንቀሳቀስ ወይንም የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውል

“የመያዣ ውል ማለት አንድ ባለዕዳ በባለገንዘቡ በኩል የሚገባውን ግዴታ ለመፈጸም መቻሉን ለማረጋገጥ መያዣ ተብሎ የሚጠራውን ዕቃ ለመስጠት የሚገደድበት ውል ነው፡፡” በማለት በፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2825 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

“ዋስትና የተሰጠበት ግዴታ ከፍተኛው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ በማንኛቸውም ሁኔታ ቢሆን በግልጽ ተጠንቅቆ በመያዣው ውል ውስጥ መመልከት ይገባዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ውሉ ፈራሽ ይሆናል” በማለት በፍ/ብ. ቁ 2828(1) ተጠቅሷል፡፡

“የመያዣው ውል ከ500 የኢትዮጵያ ብር በላይ የሆነ እንደሆነ ውሉ በጽሁፍ ካልተደረገና ይኸውም ጽሁፍ እርግጠኛ ቀን ካገኘበት ዘመን ጀምሮ ካልሆነ በቀር አይጸናም፡፡ ይላል፡፡” በፍ/ብ. ቁ 2828 (2)፡፡

“የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣን የሚያቋቁም ውል ወይም ህጋዊ ሰነድ በጽሁፍ ካልተደረገ በቀር ዋጋ የለውም፡፡ በማለት በፍ/ብ.ቁ 3045 (1) ላይ ተጠቅሷል፡፡

በፍ/ብ. ቁ 3045 (2) መሰረት መያዣ የተሰጠበት ገንዘብ ልክ በኢትዮጵያ ገንዘብ ካልተመለከተ በቀር ፈራሽ ነው ::

በዚህም መሰረት በፍ/ብ. ቁ 2825 እና 3041 መሠረት የመያዣ ውል ለመዋዋል ወደ መስሪያ ቤታችን ሲመጡ ተገልጋዮች ማሟላት ያለባቸው ጉዳዮች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡

.በተቋሙ የDARIS ስርዓት የተዘጋጀ ሰነድና የአገልግሎት ቁጥር

.የተዋዋዮ በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤

.የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሆነ ሁለት የሰው ምስክሮችና መታወቂያ፤

.ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጫ ሰነድ፤

.የተዋዋዮች የጋብቻ ማስረጃ ወይም የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፤

.በመያዣነት የቀረበው ንብረት የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ፤

.የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፤ መተዳደሪያ ደንብ እና ቃለጉባኤ እንደአስፈላጊነቱ ዋና የንግድ ምዝገባ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተገልጋዮች የተባሉትን ነገሮች አሟልተው ሲቀርቡ ለዚህ አገልግሎት የሚወስደው ጊዜ 25 ደቂቃ ነው፡፡

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
#የውል ማሻሻያ

ተዋዋይ ወገኖች በተለያየ ጊዜና በተለያዩ ምክንያቶች ለህግና ለሞራል ተቃራኒ ካልሆነ፣ ሊተገበር የሚችል ከሆነ እና ተያያዥ ምክንያቶች ቀድሞ የነበረው ውል በመለወጥ ማሻሻል ይችላሉ፡፡
መረጃውን ለሌሎች እንዲደርስ በማድረግ ተቋሙ አላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት እንዲሁም ብልሹ አሰራር ለማስቀረት እያደረገ ያለውን ጥረት ያግዙ ፡፡
በመሆኑም ተዋዋይ ወገኖች ውል ለማሻሻል ወደመስሪያቤታችን ሲመጡ ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡


. በተቋሙ የDARIS ስርዓት የተዘጋጀ እና የሚሞላ ሰነድ ወይም የአገልግሎት ቁጥር፤
• ቀደም ሲል የተመዘገበው ወይም የሚሻሻለው የውል ሰነድ፤
• ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን(ውክልና) ፤
• የተዋዋዮች ጊዜው ያላለፈበት ወይም በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤
• ውሉ የሚሻሻለው የማይንቀሳቀስ ንብረት ማስተላለፍ ውልን በሚመለከት ሲሆን ሁለት ምስክሮች ፤
• የተዋዋዮች ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፣
• የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ እና ቀደም ሲል የተመዘገበው ወይም የሚሻሻለው ቃለ-ጉባኤ ወይም የውል ሰነድ፤
ተገልጋዮች ከላይ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች(መረጃዎች) ሙሉ በሙሉ አሟልተው ሲመጡ ውሉን ለማጠናቀቅ 25 ደቂቃ ብቻ ነው፡፡
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties