አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
ኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር EWLA

የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በፌደራል ደረጃ በ1987 ዓ.ም በሴት የህግ ባለሙያዎች የተቋቋመ ፤ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተመዘገበ ሃገር በቀል የሲቪክ ማህበር ሲሆን ላለፉት ከ25 ዓመታት በላይ የሴቶችን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ሕጋዊ መብቶች እንዲታወቁ በማድረግ ሴቶች በሕገ-መንግስቱ እና በሌሎች ሕጎች በተመላከቱ መብቶቻቸዉ እንዲጠቀሙ የሚያግዙ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ፡፡

የማህበሩ ግብ ሴቶች በሁለንተናዊ ዘርፍ እኩል ተጠቃሚና ተሳታፊ እንዲሆኑ አስተዋፅኦ ማድረግ ሲሆን በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን መከላከልና ለሴቶች ከጥቃት የፀዳ አከባቢን መፍጠር አላማዉ አድርጎ በሶስት ፕሮግራሞቹ ማለትም የህግ ምርምር እና ጥናት፣ የህዝብ ማስተማርና አቅም ግንባታ እንዲሁም ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት በመስጠት ይሰራል፡፡  👍👍👍👇👇👇👇👇👇👇
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ልዩልዩ #አለ_ችሎት #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Legal Trainee
Commercial Bank of Ethiopia
Addis Ababa

Full–time

Required Education, Qualification and Experience:................................................LLB Degree in Law with zero year of work experience Salary : ...................................................... As per the Bank’s salary scale Term of Employment: ............................. Permanent Place of Work: .......................................... All Districts Year of Graduation:...................................Only 2020/21 Graduates CGPA:......................................................... 3.0 and above Application Date:.......................................March 21, 2022 – March 31, 2022 Age: ............................................................ 35 and Below Note: Interested and qualified applicants should apply through CBE career website https://vacancy.cbe.com.et, and required to attach Degree document, curriculum vitae, work experience, 8th grade certificate document and other necessary credentials within ten consecutive working days from the date of this announcement. However, the bank has full right to cancel or take any other alternative in this regard.
• Only shortlisted applicants will be communicated for exam and interview.
• All documents should be scanned in pdf or docx formats only and the size of the documents should be less than 2MB. You can use the following link to learn how to apply on CBE’s Career Website

Report this listing

Commercial Bank of Ethiopia
#በነፃ የስልክ ጥሪ ማዕከል #7711 በመደወል በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ይጠቁሙ ፤ ድምፅዎት እንዲሰማ ያድርጉ
#Let your voices be heard and report incidences of violence against women in the election by calling toll free#7711
#Yeroo filaannoo dhiibbaa dubartoota irra gahuu karaa lakkooffsaa bilbilaa tolaa #7711 irratti bilbiluudhan odeeffaannoo nuu biraan gahaa sagaleen isaani akka dhaga’aamuu ga’ee keessaan ba’aa
#Dooroh uddur sayyot yakkeh Yan bood currik yan telephone nebroh fateena, #7711 ah haak ascossa aba. Isinni xongolo kah tantaabbime innah aba
Corruption is a human rights issue, which ought to be recognized as such by States, the business community and civil society. Those who peacefully work for the rights of others against corruption should be recognized, celebrated and protected as human rights defenders.
https://t.me/TransparencyEthiopia
በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረታዊ ነጥቦች
በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረታዊ ነጥቦች

ይህ አጭር ጽሁፍ ስለ ሀገራዊ ምክክር ምንነት፣ ጥቅሞችና ዓላማዎች፣ መርሆች እና ምክክሩን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ የሚያትት ሲሆን የሀገራዊ ምክክር ጽንሰ ሃሳብን ከአዋጅ ቁጥር 1265/2014 አንፃርም አጭር ትንተና ያቀርባል፡፡
መልካም ንባብ

1. ስለ አገራዊ ምክክር
ሀገራዊ ምክክር ስር የሰደዱ ሀገራዊ አለመግባባቶችን፣ ግጭቶችን ለመፍታት ጥቅም ላይ የሚውል አንድ አይነት የግጭት መፍቻ ዘዴ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ድርድር (negotiation) የተለያየ ጥቅምና ፍላጎት የሚወክሉ አካላት በሰጥቶ መቀበል መርህ ልዩነቶቻቸውን የሚፈቱበት ዘዴ ነው፡፡ ሌላው ዘዴ እርቅ (reconciliation) ሲሆን የደረሰ በደል ላይ ጥልቅ ውይይት ማድረግና በመተማመን ይቅር በመባባል ስምምነትን ማስፈኛ ዘዴ ነው፡፡ በመጨረሻም የማስማማት (mediation) የግጭት መፍቻ ዘዴ በሶስተኛ ወገን አማካኝነት ልዩነትን ለማስወገድ ጥቅም ላይ የሚውል ነው፡፡

2. የሀገራዊ ምክክር ከአዋጅ ቁጥር 1265/2014 አንፃር
ከግጭት መፍቻ ዘዴዎች መካከል አንዱ የሆነውን አገራዊ ምክክር (national dialogue) ለማድረግ እንዲቻል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 አውጥቷል፡፡ የአዋጁን አላማ እና ይዘት እንደሚከተለው ለማብራራት ተሞክሯል፡፡

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋያ አዋጅ ተግባራዊ ያደረገው ዘዴ አካታች አገራዊ ምክክርን ነው፡፡ አገራዊ ምክክር በአገራችን ወቅታዊና ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ተመራጭ ግጭት መፍቻ ዘዴ ነው፡፡ አገራዊ ምክክር አንድ ወጥ ሀሳብ እና አንድ ወገን ብቻውን የሚመክርበት ሳይሆን በየአጀንዳው የተለያዩ ሀሳቦች፣ ጥቅሞች፣ ፍላጎቶችና መብቶች የሚወከሉበትና ምክክር የሚደረግበት፣ እነዚህን ሀሳቦች የሚወክሉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚወከሉበት ብዝሀነት ያለው መድረክ ነው፡፡ በዚህም በሀገራችን የሚስተዋሉ መሰረታዊ ችግሮችን እና ልዩነቶችን ወደ ጠረጴዛ በማምጣት፣ የተለያዩ ጥቅሞችና የህብረተሰብ ክፍሎች በሚሳተፉበት ምክክር የጋራ መፍትሄ ለማምጣት የተመረጠና ጥቅም ላይ የሚውል ዘዴ ነው፡፡

2.1. የአገራዊ ምክክር ጥቅሞችና ዓላማዎች
የአገራዊ ምክክር ጥቅም በዋናነት ግጭትን ለማስወገድ (peace building)፣ የፖለቲካና ዴሞክራሲ ሽግግርን ለማሳለጥ የሚጠቅም ነው፡፡ በተለይም ግጭቶችን ለመከላከል፣ ለማስተዳደር (conflict management) እና ለመፍታት አይነተኛ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃም በበርካታ ሀገራት በተለየዩ ጊዜያት በተለያየ መነሻ ምክንያቶች ሀገራዊ ምክክሮችን አካሂደዋል፡፡ የተወሰኑት የተሳካለቸው ሲሆን በተወሰኑት የሚፈለገውን ግብ ሳያሳካ ቀርቷል፡፡

የሀገራዊ ምክክር አላማዎች መሰረታዊ የሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ያሉ ልዩነቶችን በማጥበብ መግባባትን ለመፍጠር፣ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከልና ከመንግስት ጋር ያለን ግንኙነት ለማሻሻል፣ መተማመንን ለማጎልበት፣ የመነጋገር የፖለቲካ ባህልን ለማጎልበት፣ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት፣ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው አገረ መንግስት በጋራ ለመገንባት፣ ልዩነቶችን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመፍታት፣ የዴሞክራሲና የፖለቲካ ሽግግር (transformation) ለማስቻል፣ ልማትን ለማፋጠን የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በተጨማሪም የሀገራዊ ምክክር አላማ መሰረታዊ አለመግባባቶች፣ ልዩነቶችና ግጭቶች ምን እንደሆኑ መለየት፣ መሰረታዊ ምክንያታቸውን (root cause) መለየት እና በእነዚህ ላይ ልዩነቶችን በምክንያታዊ፣ በሰለጠነ፣ በመቻቻል መንገድ የጋራ መግባባቶች ላይ ለመድረስ እና የግጭቶቹ መንስኤ የሆኑ ልዩነቶችን ለማጥበብ ካልሆነም በልዩነቶች ላይ በመስማማት በሀሳብ ለመለያየት ብሎም ይህን የሀሳብ ልዩነት በዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊና ህጋዊ መንገድ መፍታት የሚቻልበትን ዘዴ በጋራ በመቀየስ ተግባራዊ ለማድረግ ለመግባባት የጋራ ጥረት የሚደረግበት መድረክ ነው፡፡

2.2. የአገራዊ ምክክር መርሆች
አገራዊ ምክክር ዓላማን ለማሳካት ምክክሩ ሊከተላቸው የሚገቡ መርሆች ውስጥ አካታችነት፣ ግልፅነት፣ ተአማኒነት፣ መቻቻልና እና መከባበር፣ ምክንያታዊነት፣ የምክረ ሀሳቦች ተግባራዊነት እና አውድ ተኮርነት፣ ገለልተኛ አመቻች፣ የአጀንዳ ጥልቀትና አግባብነት፣ ዴሞክሲያዊነት፣ የህግ የበላይነት በአዋጁ የተጠቀሱ ናቸው፡፡ ከነዚህ በተጨማሪነት ኮሚሽኑ አስፈላጊ የሚላቸውን መርሆች ሊያካትት እንደሚችል ተመልክቷል፡፡ ከዚህ አንፃር ኮሚሽኑ ተሳታፊዎች በቅን ልቦና እንዲሳተፉ እና ፍትሀዊነት መርሆችን ሊያካትት ይችላል፡፡

እነዚህን መርሆች በዝርዝር ስንመለከት በመጀመሪያ የምናገኘው አካታችነትን ይሆናል፡፡ አካታችነት ከህጉ ዝግጅት እና ኮሚሽነሮች ምርጫ ጀምሮ በተቻለ መጠን ሰፊ ተሳትፎን ለማረጋገጥ ጥረት የተደረገበት ነው፡፡ በምክክር ሂደትም መሰረታዊ አገራዊ ጉዳዮችን በሙሉ እንደሚያካትት፣ እነዚህ ሀሳቦችና ጥቅሞችን የሚወክሉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በየደረጃው እንዲሳተፉበት እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡ ስራዎቹንም በግልፅነት ለህብረተሰቡ የደረሰበትን ደረጃ በማሳወቅ እንደሚከውን ይጠበቃል፡፡ ኮሚሽኑ ስራዎቹን በተአማኒነት ለአገር፣ ለህዝብ፣ ለህግ፣ ለመርህ እና ለስነምግባር ተገዢ ሆኖ እንደሚፈፅሙ ይጠበቃል፡፡ ተወያዮችም በመቻቻልና በመከባበር መንፈስ በሰከነና በሰለጠነ መንገድ ምክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ ሌላው መርህ ምክንያታዊነት ሲሆን ይህም በማስረጃ እና በእውነት ላይ የተመሰረት የሀሳብ መግለፅ እንደሚኖር እና ሀሳቦችን በምክንያታዊነት የመቀበልና የመቃወም አካሄድ እንደሚኖር ህጉ ይጠብቃል፡፡ ከሂደቱ ውጤት ስምምነት የሚደረስባቸው የትግበራ አቅጣጫዎችን መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ይተገብራሉ ተብሎም እምነት ተይዟል፡፡ በተለይም ልዩነቶች የሚፈቱበት ህጋዊ አካሄድ አቅጣጫ በሚቀመጥበት ወቅት ተግባራዊ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

2.3. የሀገራዊ ምክክር ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራት
አገራዊ ምክክር ከሚያልፍባቸው ሂደቶች ውስጥ መነሻ (initiation)፣ ዝግጅት፣ ምክክር እና ትግበራ (implementation) ናቸው፡፡ አሁን ባለንበት የዝግጅት ምእራፍ ሲሆን ከዚህ አንፃር አዋጁ ያካተተው ጉዳይ የኮሚሽኑን ተግባርና ሀላፊነት በሚመለከት ኮሚሽኑ በአላማ የተመለከተውን ጉዳይ ለማሳካት በገለልተኛነት እና በነፃነት መስራት እንደሚጠበቅበት ያስቀምጣል፡፡ በዝርዝርም የምክክር አጀንዳዎችን፣ አወያዮች አመራረጥን፣ የምክክር ስነ ስርአትን፣ የተወያዮች አመራረጥን እና ሌሎች መሰል ጉዳዮችን በነፃነትና በገለልተኝነት በራሱ እንደሚወስን ይጠበቃል፡፡ ምክክር የሚደረግባቸው ደረጃዎች፣ ሂደቶች፣ አካባቢዎችን መወሰን እና ምክክሩንም በአመቻችነት መምራት ይጠበቃል፡፡ ለዚህ አላማ ኮሚሽኑ በአጠቃላይ አስራ አንድ ኮሚሽነሮች ያሉት ሲሆን ከነዚህ ውስጥም አንድ ዋና ኮሚሽነር እና ምክትል ዋና ኮሚሽነር አለው፡፡ ኮሚሽኑ ፅሀፈት ቤት፣ አስፈላጊ ኮሚቴዎች እና አስፈላጊ ሰራተኞች እንደሚኖሩት አዋጁ ይገልፃል፡፡ ይህን የማደራጀት ተግባሩም የሚጠበቅ ነው፡፡ ይህን ለመፈፀም የሚያስችለው የፋይናንስ ነፃነቱንም ለማስጠበቅ በጀት ከመንግስት እና ከሌሎች ህጋዊ ምንጮች ማግኘት እንደሚችል ወጪዎቹንም የመንግስት ፋይናንስ መርሆች መሰረት በኮሚሽኑ በሚፀድቅ ውስጠ ደንብ መሰረት የመፈፀም ሙሉ ነፃነት
እንዳለው ተመልክቷል፡፡

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክርን ተግባራዊ ለመድረግ እና አላማዎቹን ስኬታማ ለማድረግ የመንግስት አካላት፣ የተለያዩ ማህበራዊ እና የግል አደረጃጀቶች፣ ህዝቡ፣ ግለሰቦች፣ አለምአቀፍ ተቋማት ትልቅ ሀላፊነትና ድርሻ አላቸው፡፡ ህጉም ኮሚሽኑ ለሚያቀርባቸው ህጋዊ ጥያቄዎች መተባበር ግዴታ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ ከዚህ አንፃር ሂደቱ ካለው ፋይዳ አንፃር ሁሉም የበኩሉን ድጋፍ፣ ትብብር፣ ተሳትፎ እንዲያደርግ ይጠበቃል፡፡

በንቃተ ሕግ፣ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
በሴቶች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ሁለተኛዉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተከፈተ
ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2014 ዓ.ም
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በሴቶች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ሁለተኛዉን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዛሬ መክፈቱን አስታወቀ፡፡
መስሪያ ቤቱ ከዚህ በፊት አገልግሎት ይሰጥበት የነበረውን እና መገናኛ ደራርቱ ቱሉ ህንጻ ላይ የሚገኘውን ቅርንጫፍ ሶስት በመባል የሚታወቀውን ጽ/ቤት በሴት ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
አቶ ሙሉቀን አማረ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሴቶች በተመደቡበት የስራ ኃላፊነት እና ቦታ በታማኝነት እና በጥንቃቄ የሚሰሩ በመሆናቸው ያላቸውን የማገልገል አቅም እና ችሎታ አጠናክረው እንዲቀጥሉበት ለማድረግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተከፍቷል ብለዋል፡፡
የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አሰፋሽ ወ/ገብርኤል በበኩላቸው “ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መከፈት ከ68 በመቶ በላይ ለሆኑት ሴት ሰራተኞቻችን እውቅና መስጠት በመሆኑ የእንኳን ደስ አላችሁ” በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስፋፋ የመጣውን የሀሰተኛ ሰነድ መበራከት እና የሙስና አመለካከት ለመዋጋት የሁሉም ሰራተኛ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን ይህንን በተመለከተ በዋና ዳይሬክተሩ አጠር ያለ ማብራሪያ/አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሴቶች ብቻ አገልግሎት እንዲሰጥ የተደረገው በአገራችን ለአርባ ስድስተኛ ጊዜ “እኔም የእህቴ ጠባቂ ነኝ!” በሚል መሪቃል የሚከበረውን አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ነው፡፡
ከአንድ አመት በፊት የመጀመሪያ የሆነው በሴቶች ብቻ አገልግሎት እንዲሰጥ የተደረገው እና ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው ቅርንጫፍ ስምንት ጽ/ቤት በአገልግሎት አሰጣጥ ጥሩ አፈጻጸም እንዳለው ተገልጿል፡፡
Legality of Levying Income Tax on Illegal Amounts Received by a Taxpayer ---- Personal Reflection

By:- Natae Ebba Kitila

The central focus this piece wants to press on is the legality of the collection of income tax on illegally driven amounts. In doing so, the writer will try to unpack some important elements from the Income-tax proclamation No 979/2016.

Enjoy reading!

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2024-legality-of-levying-income-tax-on-illegal-amounts-received-by-a-taxpayer-personal-reflection
ቅን-ልቦና በሰበር ችሎት ክፍል አንድ
አብርሃም ዮሐንስ
ውክልና
ሰ_መ_ቁ. 14974 ቅጽ 1
ተወካዩ የራሱን ጥቅም የሚመለከት ጉዳይ ሲያጋጥመው ሁኔታውን ለወካዩ ሳያሳውቅና ወካዩ ሳይስማማ ስራውን እንዳይፈጽም ይከላከላል፡፡ ስለወኪልነት የተደነገጉትን የፍ/ብሔር ድንጋጌዎች ስንመለከትም ተወካዩ ከወካዩ ጋር በሚኖረው ግንኙነት ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እንደሚገባ እና የውክልና ስልጣኑን የሚያስቀሩ ምክንያቶች እንዳለበት (የፍ/ብ/ህ/ቁ 2208)፣ ተወካዩ ስራውን የሚፈጽመው በተለይ ለወካዩ ጥቅም ሊሰጥ የሚችል መንገድ ብቻ መሆን እንዳለበት (ፍ/ብ/ህ/ቁ 2209(1))፣ እንዲሁም ተወካዩ በራሱ ስም ከወካዩ ጋር የሚያደርገው ውል ወካዩ ካላጸደቀው በቀር ሊፈርስ እንደሚችል (የፍ/ህ/ቁ 2188) መደንገጋቸው ተወካዩ ለወካዩ ፍጹም ታማኝ መሆን እንዳለበት እና ለወካዩ ጥቅም ብቻ መስራት እንዳለበት፣ የጥቅም ግጭት ባለበት ጊዜ ሁሉ ሁኔታውን ለወካዩ የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበት የሚያስገነዝቡ ናቸው፡፡ በመሆኑም Aንድ ተወካይ የጥቅም ግጭት ባለበት ጊዜ ለወካዩ ሳያሳውቅ የሚየከናውነውን ስራ ወካዩ ሊቃወመው የሚችል መሆኑን እና በዚህ ሁኔታ የተከናወነው ስራም ወካዩ ካላፀደቀው በቀር ወካዩ ራሱ እንደፈጸመው ሊቆጠር እንደማይገባ ከውክልና ግንኙነት Aጠቃላይ ዓላማ እና ከፍ/ብ/ህጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡
ሰ_መ_ቁ. 26399 ቅጽ 5
ሿሚው በግልጽም ይሁን በዝምታ እንደራሴው ሥልጣኑ ቀሪ ከሆነ በኋላ የሠራውን ሥራ ያልተቀበለው መሆኑ ከተረጋገጠ የዚሁ ያለመቀበል ውጤት በቁጥር 2193 ተደንግጓል፡፡ የዚህን ድንጋጌ ይዘት ስንመለከት aôሚው ይህንኑ የእንደራሴውን ሥራ ካልተቀበለው ምን ጊዜም ይኸው ውል ፈራሽ ነው የሚል Aይደለም፡፡ ይልቁንም ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1808
እስከ 1818 ድረስ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ተከትሎ የውሉ መፍረስ ወይም መሰረዝ ሊወሰን የሚችል መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ይህም እነዚህኑ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች በመከተል ውሉ ሊፈርስ የማይችልበት አጋጣሚ ያለ መሆኑን የሚያሳይና ነገር ግን ውሉ የሚፈርስ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ውሉ በመፍረሱ ምክንያት በቅን ልቦና ከእንደራሴው ጋር በተዋዋሉት 3ኛ ወገኖች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ካሣ የሚጠየቅበት መንገድ የሚያመቻች ድንጋጌ ነው፡፡
ሰ_መ_ቁ. 77983 ቅጽ 15
ተወካዩ ከወካዩ ጋር የሚያሰተሳስረው ግንኙነት ውስጥ ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እንደሚገባ በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2208(1) ስር ተደንግጓል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ተወካዩ የተወካይነት ሥራውን የሚፈጽመው በተለይ የወካዩን ጥቅም ሊሰጥ በሚችልበት መንገድ ብቻ መሆን እንዳለበት በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2209 (1) ድንጋጌ ያሳያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተወካዩ በውክልና ሥራው ላይ በሚገኝባቸው ጊዜዎች ሁሉ በውክልና በተሰጠው አደራ አንድ መልካም የቤተሰብ አባት ቤተሰቡን ለመጠበቅ እንደሚያደርገው ሁሉ በትጋትና በጥንቃቄ መጠበቅ ያለበት መሆኑን በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2211(1) ስር በግልጽ ተደንግጓል፡፡
አስፈላጊ ወጪ
ሰ_መ_ቁ. 81081 ቅጽ 14
የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2168 ድንጋጌ ይዘት ሲታይም አንድ ሰው ለተወሰነ ጊዜ በእጁ ያቆየውን እቃ እንዲመለስ የተገደደ እንደሆነ ለሕግ ወይም ለውል ተቃራኒ የሚሆን ድንጋጌ ከሌለ በቀር የተባለውን እቃ ከመለዋወጥ የተነሳ ያሉት መብቶችና ግዴታዎች ከድንጋጌው ቀጥለው ባሉት ደንቦች መሰረት የሚወሰን መሆኑን የሚያስገነዝብ ሲሆን በዚሁ ድንጋጌ ስር ከሰፈሩት ደንቦች መካከል አንዱ የሆነው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2169 ስር የተቀመጠው ደግሞ የያዘውን እቃ እንዲመልስ የተገደደ ሰው በእቃው ላይ ያደረገው ወጪ ሊመለስለት የሚገባው ወጪው የግድ አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ ስለመሆኑና ወጪው አስፈላጊ ሳይሆን ከቀረ ወይም ወጪው እቃውን እንዲመለስ በተገደደው ሰው ወይም ተገዳጁ ኃላፊ በሚሆንበት ሰው ጥፋት ምክንያት ከሆነ ወጪው ሊመለስ የማይችል መሆኑን ያሳያል፡፡
ሕጉ በአንቀጽ 2171(1) ስርም ለእቃው የተደረገው ወጪ የእቃውን ዋጋ ግምት ከፍ አድርጎት እንደሆነም እቃውን ለመመለስ የተገደደው ሰው ስለዚሁ ጉዳይ ያወጣው ገንዘብ ሊመልስለት እንደሚገባ የደነገገ ሲሆን ይህ ወጪ በክፉ ልቦና ስለመደረጉ የተረጋገጠ ወይም ርትዕም የሚያስገድድ ከሆነ ደግሞ ዳኞች ወጪውን ለመቀነስ ወይም ጭራሹን ለማስቀረት የሚችሉበት አግባብ መኖሩንን የተጠቃሹ ድንጋጌ ቀጣይ የሆነው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2172((1) ይዘት ያሳያል፡፡
ይህ ድንጋጌ አንድን ወጪ በክፉ ልቦና የተደረገ ነው ለማለት የሚቻልበት አግባብም ወጪው በተደረገበት ጊዜ ወጪውን የሚጠይቅ ሰው እቃውን ለመመለስ ግዴታ ያለበት መሆኑን ያውቅ እንደነበረ ወይም ማወቅ ይገባው የነበረና ርትዕም ሲያስገድድ መሆኑን በመለኪያነት አስቀምጧል፡፡
ስለሆነም እነዚህ ድንጋጌዎች ሲታዩ አንድ ሰው የሌላ ሰው ንብረት ይዞ ሲጠቀም ከቆየና ንብረቱን በሚጠቀምበት ጊዜ ንብረቱን ከጥፋት ወይም ከብልሽት ለማዳን ሲል ተገቢውን ወጪ ቢያወጣ ይኼው ወጪ በሕጋዊ ባለሃብቱ እንዲተካለት መጠየቅ የሚችልበት አግባብ የሚኖረው ወጪው የግድ አስፈላጊ ከሆነና በቅን ልቦና የተደረገ መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የሚያስገነዝቡ ሲሆን በክፉ ልቦና የተደረገ ስለመሆኑ የተረጋገጠውን ወጪ ግን እቃውን እንዲመለስ የተደረገ ሰው ሊቀነስበት ወይም ጭራሹንም ዳኞች ሊያስቀሩት የሚችሉ ስለመሆኑ ሕግ ስልጣን የሰጣቸው መሆኑን ድንጋጌዎች ያስረዳሉ፡፡
ሽያጭ
ሰ_መ_ቁ. 88084 ቅጽ 15
በህግ ጥበቃ የሚደረግለት መብት ሣይኖር በስሙ የተመዘገበ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት የምስክር ወረቅተ ከያዘ ሰው ንብረቱን በመንደር ውል የገዛ ገዢ ተገቢውን ማጣራት በማድረግና፣ በጥንቃቄ፣ የገዛና የቅን ልቦና ያለው ነው ለማለት አይቻልም።
ሰ_መ_ቁ. 100931 ቅጽ 17 የልዩነት ሀሳብ
ከሽያጭ ውል ጋር በተያያዘ ሕጉ ጥበቃ የሚያደርገው የቅን ልቦና ገዥ ነኝ ለሚል ሰው ብቻ ሳይሆን የአእምሮ ጉድለት ያለባቸው ግለሰቦችም ሕጋዊ መብታቸው እንዳይጣስ የወራሾችም መብትና ጥቅም ጭምር ለማስከበር እንደሆነ በፍ/ሕ/ቁ. 339 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ተመልክቷል፡፡
ቅን-ልቦና በሰበር ችሎት ክፍል ሁለት
#አለ_ህግ
ከውል ውጭ ሀላፊነት
ሰ_መ_ቁ. 82154 ቅጽ 15
አንድ የመንግስት መስሪያ ቤተ ለሰራተኛው ተግባር ኃላፊነት ሊህረው የሚችለው በሰራተኛው የተፈፀመው ጥፋት የሥራ ጥፋት ሆኖ ሲገኝ ሲሆን አንድ ጥፋት የስራ ጥፋት ነው ተብሎ የሚወሰደውም ጥፋት አድራጊው በዚህ ጥፋት ላይ የወደቀው በቅን ልቡና በስልጣኑና ለስራው ክፍል መልካም ያደረገ መስሎት የፈፀመው መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑና ከዚሀ ውጪ በሆነ በማናቸውም ሌላ ጉዳይ ግን ጥፋቱ እንደግል ጥፋት ሁኖ እንማሚቆጠር የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2126 እና 2127(1) እና (2) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያስረዳሉ፡፡ ጥፋቱ በቅን ልቦና ያልተፈፀመ መሆኑም በተቃራኒ ማስረጃ ሊረጋገጥ እንደሚችልና ተቃራኒ ማስረጃ ካልቀረበ ግን የራተኛው አሰራር በቅን ልቦና እንደተሰራ በሕጉ ግምት እንደሚወሰድበት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር
2127/3/ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ያሳያል፡፡

ሰ_መ_ቁ. 132017 ቅጽ
በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰበት መኪና በወቅቱ ተጠግኖ ወደ ስራ ቢመለስ በአደጋው ምክንያት የተቋረጠን የገቢ መጠን ለመቀነስ ወይም ለማቅለል በቅን ልቦናና በማስተዋል የተደረገ እንቅስቃሴ ከሌለ በደረሰ ጉዳት መጠን በሙሉ ካሳ ሊጠየቅ ስላለመቻሉ፡

የስነ-ስርዓት ህግ
የሰ/መ/ቁ.81616 ቅጽ 14
በሕጉ አግባብ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ተከራክሮ ያጣውን ወይም የተከለከለውን መብት ከሕግ ስነ-ሥርዓትና ቅን -ልቦና ውጭ በሆነ አኳኃን ፍርዱን በሚያስፈጽመው ፍ/ቤት ለመጐናፀፍ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተገቢነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም፡፡
ሰ_መ_ቁ. 91103 ቅስ 15
አንድ ተከራካሪ ወገን በሌላኛው ተከራካሪ ወገን ቅን ልቦና ውጪ በሆነ ተግባር ለክርክር ተዳርጎ መገኘቱ ከተረጋገጠ የወጪና ኪሳራ ጥያቄ ውድቅ ማድረግ የስነ ስርዓት ሕጉ ሊያሳካ ከአሰበው ዓላማ ውጪ በመሆኑ የሕግ መሰረት የሌለው ነው፡፡
የውጪና ኪሳራ ጥያቄን አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ በመጠኑ ላይ በሕጉ ስልጣን የተሰጠው መሆኑና ረቺ ሁልጊዜ ወጪና ኪሳራ እንዲተካለት መደረግ የሌለበት መሆኑ ግንዛቤ የሚወሰድበት ቢሆንም ከቅን ልቦና ውጪ ለክርክር የተጋበዘውን ወገን በተመለከተ ግን የክርክሩ ረቺ መሆኑ እስከታወቀ ድረስ ቅን ልቦና ከሌለው ወገን በክርክሩ ምክንያት ያወጣውን ወጪ እንዲተካለት ማድረግ ክርክሮች ያላግባብ እንዳይፈጠሩ የማድረግ ውጤት ያለው በመሆኑ ተግባራዊ ሊደረግ የሚገባው ነው፡፡
ሰ_መ_ቁ. 93987 ቅጽ 16
የዚህ ድንጋጌ ይዘቱና መንፈሱ ሲታይ ክርክሩ መኖሩን ከጅምሩ እያወቀ ውጤቱን በመጠበቅ ከፍርዱ በኋላ የፍርድ መቃወሚያ የሚያቀርበውን ወገን አቤቱታውን በመቀበል ለማስተናገድ አስፈላጊ ያለመሆኑን ሁሉ ያስገነዝባል፡፡ይህም የክርክር አቀራረብ በቅን ልቦና የተመሰረተ ሁኖ በአነስተኛ ወጪ፣ጉልበትና አጭር ጊዜ ፍትሐዊነት ያለውን ውሳኔ ለመስጠት የሚቻልበት አግባብ እንዲኖር እና ሕግ አውጪ ከፈለገበት አላማ ጋር መጣጣም ያለበት መሆኑም የሚታመን ነው፡፡
እንግዲህ አቤቱታውን የሚያቀርበው ወገን የቅን ልቦና ተከራካሪ ሁኖ መሰረታዊ መብቱን ማስከበር የሚችልበት የስነ ስርዓት ሕግ አግባብ እንዲኖር ሕግ አውጪ የፈለገ ሲሆን ይህንኑ መመዘኛ የሚያሟላ አቤቱታ አቅራቢ የሚቃወመው ፍርድ ዋጋ ያለው፣ያልተፈፀመ መሆን እንደአለበትም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 ድንጋጌ ይዘት ያስረዳል፡፡በሌላ አገላለፅ የፍርድ መቃወሚያ የሚቀርብበት ፍርድ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ያልተሻረና አፈጻጸሙም ያልተጠናቀቀ ሊሆን እንደሚገባ ሕጉ
ያሳያል፡፡
ሰ_መ_ቁ. 101079 ቅጽ 17
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሠረት የተዘረጋው ሥርዓት አስቀድሞ በተሰጠው ውሣኔ መብቱ የሚነካበት ወገን ባለበት ውሣኔ እንዳልተሰጠበት ተቆጥሮ እንደገና ክርክር የሚጀምርበት ሥርዓት ነው፡፡ መሰረታዊ አላማም ቅን ልቦና ያላቸው ወገኖች በመሰረታዊ ሕግ የተጠበቀላቸው መብት ባለመከራከር ዋጋ እንዳያጣ ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡
ስጦታ
ሰ_መ_ቁ. 90959 ቅጽ 16
ስጦታው ከቅን ልቦና ውጪ የተደረገ ነው እስከተባለ ድረስ በስጦታ አድራጊው ድርሻ ጭምር ፈራሽ የማይሆንበት ሕጋዊ ምክንያት ያለመኖሩን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2438(1) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ተገንዝበናል፡፡
ቼክ ቅጽ 7
የንግድ ሕግ ቁጥር 841 ድንጋጌ መሠረት የቼኩ አውጪ በአምጪው ላይ መቃወሚያ ሊያደርግ የሚችለው ቼኩን ያገኘው ቅን ልቦና በጐደለው ሁኔታ ወይም ቼኩን ሲያገኝ ከባድ ጥፋት ያደረገ መሆኑ ሲረጋገጥ እንደሆነ ነው፡፡
የውል መሰረዝ
24221፤ 24974 ቅጽ 7
የውል ይሰረዝልኝ Aቤቱታም ለፍርድ ቤት በቀረበ ጊዜ ዳኞች ውሉ እንዲሰረዝ ከመወሰናቸው በፊት የተዋዋዮችን
ጥቅምና በቅን ልቦና የሚያስፈልገውን መሠረት ማጤን እንዳለባቸው እንደዚሁም ዓይነተኛ የውል መጣስ ተግባር /fundamእntal brእach of contract/ ካልተፈጸመ ውሉ ይሰረዝ ሊሉ እንደማይችሉ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1785 ላይ ተመልክቷል።
አብርሃም ዮሐንስ
Capital Increament and Dividend.pdf
1 MB
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Mikias Melak)
"Golden Rule"⭕️‼️
Treat others only in a ways that you are willing to be treated in the same exact situation.👍
To Apply it,You would imagine yourself in the exact place of the other person on the same receiving end of the action.

if you act in a given way toward another, and yet are unwilling to be treated that way in same circumstances, then, you violate the rule.

finally, ♻️📚📙📘📗📕📒📔
To apply the above Golden Rule adequately, we need knowledge and imagination.💊
🔍we need to know what effect our actions have on the lives of others.📝✏️
and we need to be able to imagine ourselves.🔗
Vividly and adequately, in the others person place on the receiving end of action.🔚🔴
with knowledge, imagination and Golden Rule, we can progress far in our moral thinking....♏️
My last note of Ethics
to you....♊️2011E.C
well noted‼️‼️‼️‼️‼️‼️
https://t.me/LawyerEthiopia
ጠበቃ እና የህግ አማካሪ
Lawyer and Legal Adviser
We offer you Reliable services with a very high sense of responsibility.
Contact us;
EthiopianLawFamily@gmail.com
ማስታወቂያ
**
በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብር መማር ለምትፈልጉ የትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ;
......
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የግል አመልካቾችን ተቀብሎ በቅዳሜና እሁድ መርሀግብር በተለያዩ የቅድመ ምረቃ ኘሮግራሞች በዲላ፤ ሀዋሳ፤ ይ/ጨፌ እና ሻሸመኔ ማዕከላት አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
**)

በማህበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ
በህግ ት/ቤት
1 LL.B Degree in law (Hawassa and Dilla)
*****
አመልካቾች ማሟላት የሚገባቸው
1. ከታወቀ ኮሌጅ በዲኘሎማ የተመረቃችሁበትን የትምህርት ማስረጃችሁን (ዲኘሎማና ትራንስክሪፕት) ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ በግንባር በመቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
2. ከሁለት አመት ወዲህ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈትነው በዘመኑ ለከፍተኛ ትምህርት የሚያስገባ ውጤት ይዘው መቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
3. COC የሚያስፈልጋቸው የት/ት መስኮች የ COC የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
4. የመመዝገቢያ 50 ብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡
 የመመዝገቢያ ቦታ፡-
 ለዲላ ማዕከል አመልካቾች ኦዳያአ ግቢ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳ/ጽ/ቤት በየትኛውም የሥራ ቀናት፤ ለሀዋሳ ማዕከል አመልካቾች ሀዋሳ ታቦር ት/ት ቤት ቅዳሜና እሁድ ማስተባበሪያ ቢሮ፤ለይ/ጨፌ ማዕከል አመልካቾችን ይ/ጨፌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና ለሻሸመኔ ማዕከል አመልካቾችን ሻሸመኔ መሰናዶ ት/ቤት ቅዳሜና እሁድ ማስተባበሪያ ቢሮ፡፡
የመመዝገቢያ ጊዜ፡- ከመጋቢት 15/2014ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 16/2014 ዓ.ም
#Addis Ababa City Council#

▪️1 - IT Support Officer III
▪️2 - Documentation Officer
▪️3 - Website Administrator II

▪️4 - 🔴legal drafting specialty
▪️5 - 🔴legal drafting specialty

▪️Find More Details Here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3JICIcx

▪️Deadline - April 05 , 2022

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ልዩልዩ #አለ_ችሎት #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
ውድ የአለ_ህግ ቤተሰቦች መልካም እሁድ (መልካም ዕለተ ሰንበት)
Dear ALE Families, have a Good Sunday (Happy Sabbath)
#አለ_ህግ #lawsocieties #Ale_lawsocieties @lawsocieties