አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የተጠቃለሉ ህጎችን መጠቀም ለምትፈልጉ ሁሉ
የተቋማችንን ድረ ገጽ www.eag.gov.et ላይ በመግባት ከሚመጡ አማራጮች ውስጥ ሕጎች የሚለውን በመክፈት ከሚመጡ ሶስት አማራጮች ውስጥ ደግሞ የተጠቃለሉ ሕጎች የሚለውን በመምረጥ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን ወይም በጎግል መፈለጊያ ሳጥን ውስጥ http://laws.eag.gov.et/Layout/ventivell/AEAG.aspx በማስገባት በቀጥታ ወደ ተጠቃለሉ ህጎች መሄድ ትችላላችሁ ፡፡
የንቃተ-ሕግ ጥያቄ : ዳኛ ነዎት ፍርድ ይስጡበት (እዉነተኛ የፍርድ ቤት ክርክር መነሻ ያደረገ ጥያቄ)

የ16 ዓመት ታዳጊ ወጣት ወ/ሪት "በ" የአቶ "ቀ" የቤት ሰራተኛ ነበረች። አንድ ዕለት አሳቻ ሰዓት ጠብቆ አቶ "ቀ" ወ/ሪት "በ" አስገድዶ የደፈራት በመሆኑ ወ/ሪት "በ" ላልተፈለገ እርግዝና ተዳረገች።

ይሁን እንጂ የተፈጸመባትን የአስገድዶ መደፈር በደል ሰዉ ያለገኛል በሚል ፍራቻ ለማንም ሳታወራ እያለ ወ/ሪት "በ" የመዉለጃ ጊዜዋ ደረሰባት። የወ/ሪት "በ"ን እርግዝና ካወቀች በኋላ የአቶ "ቀ" ባለቤት በባለቤቷ ምክርና ግፊት ወ/ሪት "በ"ን ከቤቷ አባረረቻት።

ወ/ሪት "በ" የተወለደችበት አከባቢ ማህበረሰብ ባህል መሠረት ከጋብቻ ዉጪ ያረገዘች እና የአባቱ ማንነት የማይታወቅ ህጻን የወለደች ሴት ትወገዛለች ፤ ትረገማለች። ከማህበረሰቡና ቤተሰቦቿ ዉግዘት እና መራገም የተነሳ ትቀሰፋለች ፤ ትሞታለች የሚል እምነት አለ። ወ/ሪት "በ" በዚህ ባህል ዉስጥ ነዉ ያደገችዉ።

ታዲያ ወ/ሪት "በ" ከአቶ "ቀ" ቤት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ተባርራ ከወጣች በኋላ መሄጃ አጥታ "አ" የሚባል ሐይማኖት ተቋም አጥር ጥግ ተኝታ እያለች ሚጥ ይይዛትና ወንድ ልጅ ወለደች። ይሁን እንጂ የወለደችዉን ልጅ የማሳደግ አቅምም የላትም ፤ ይዛዉ ወደ ወላጆቿ ብትወስደዉ የሚደርስባት ማህበራዊ መገገልና ስነልቦናዊ ጉዳት እንዲሁም በመቅሰፍት ሕይወቷን አጣለሁ የሚል ፍርሀት ዉስጥ ወደቀች። በዚህ ምክንያት የወለደችዉን ልጅ በጨርቅ ጠቅልላ በሐይማኖት ተቋሙ አጥር ጥግ አስቀምጣ እያለቀሰች እየሮጠች እያለ በአከባቢው የነበሩ ሰዎች ይዘዋት ለፖሊስ አሳልፈዉ ሰጧት። ፖሊስ በምርመራ ጊዜ "አንቺ ሕጻኑ ይሙት ብዬ ጥየዋለሁ" ካልሽ አናስርሽም ብሎ በመናገሩ በፖሊሱ ሀሳብ ተስማምታ ቃሏን ሰጠች።

ዓቃቤ ህግ የፖሊስ ምርመራ መዝገብ መሠረት አድርጎ ወ/ሪት "በ"ን በሰዉ ላይ የመግደል ሙከራ ወንጀል ፈጽማለች በማለት ክስ አቀረበ። ለፖሊስ የሰጠችዉን ቃል በማስረጃነት አያይዞ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

እርስዎ ዳኛ ቢሆኑ:-"

👉 ወ/ሪት "በ" በመንግስት ወጪ ተከላካይ ጠበቃ እንዲመደብላት ይወስናሉን? ለምን?

👉ወ/ሪት "በ"ን በሰዉ መግደል ሙከራ ወንጀል ጥፋተኛ በማለት የቅጣት ዉሳኔ ይወስኑባታልን? ለምን?

እርስዎ ተከላካይ ጠበቃ ቢሆኑ:-

👉 የወ/ሪት "በ"ን መብት ለማስከበር ምን ምን ዓይነት ማስረጃዎችን መነሻ በማድረግ ጉዳዩን በሚመለከተዉ ፍርድ ቤት ፊት ቀርበዉ ይከራከራሉ?
ችሎቱ ሞልቷል ። የባልና ሚስት ክርክር ። ባልና ሚስቱ ሰነድ አልባ ቤት ላይ እየተከራከሩ ነው።

ዳኛው ጠየቁ = ቤቱ ሕጋዊ ነው?
ሚስት = መለሰች አዎ በ88 ፣97 እና 2003 የአየር ካርታ ላይ ፀድቆ ይታያል።
ዳኛ = ቤቱን በጋራ ነው ያፈራችሁት?
ሚስት = ኧረ በፍፁም። እኔ ነኝ ጠላ ጠምቄ እንጀራ ጋግሬ የሰራሁት።
ዳኛ = ባለቤትዎትስ?
ሚስት = እርሱማ ምን ስራ አለው? ሰፈር ቁጭ ብሎ ሲያወራ ነው የሚውለው። ቁጭ ከማለቱ የተነሳ እርሱም ከቤቱ እኩል በ 88 ፣ 97 እና 2003 አየር ካርታዎች ላይ ይታያል።
ዳኛ = ባል ምን ትላለህ?
ባል = ሶስቱም አየር ካርታዎች ላይ ከመታየት በላይ ህጋዊ ባለቤት የሚያደርግ ምን ማስረጃ አለ ክቡር ፍርድ ቤት?
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
ኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር EWLA

የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በፌደራል ደረጃ በ1987 ዓ.ም በሴት የህግ ባለሙያዎች የተቋቋመ ፤ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተመዘገበ ሃገር በቀል የሲቪክ ማህበር ሲሆን ላለፉት ከ25 ዓመታት በላይ የሴቶችን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ሕጋዊ መብቶች እንዲታወቁ በማድረግ ሴቶች በሕገ-መንግስቱ እና በሌሎች ሕጎች በተመላከቱ መብቶቻቸዉ እንዲጠቀሙ የሚያግዙ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ፡፡

የማህበሩ ግብ ሴቶች በሁለንተናዊ ዘርፍ እኩል ተጠቃሚና ተሳታፊ እንዲሆኑ አስተዋፅኦ ማድረግ ሲሆን በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን መከላከልና ለሴቶች ከጥቃት የፀዳ አከባቢን መፍጠር አላማዉ አድርጎ በሶስት ፕሮግራሞቹ ማለትም የህግ ምርምር እና ጥናት፣ የህዝብ ማስተማርና አቅም ግንባታ እንዲሁም ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት በመስጠት ይሰራል፡፡  👍👍👍👇👇👇👇👇👇👇
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ልዩልዩ #አለ_ችሎት #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Legal Trainee
Commercial Bank of Ethiopia
Addis Ababa

Full–time

Required Education, Qualification and Experience:................................................LLB Degree in Law with zero year of work experience Salary : ...................................................... As per the Bank’s salary scale Term of Employment: ............................. Permanent Place of Work: .......................................... All Districts Year of Graduation:...................................Only 2020/21 Graduates CGPA:......................................................... 3.0 and above Application Date:.......................................March 21, 2022 – March 31, 2022 Age: ............................................................ 35 and Below Note: Interested and qualified applicants should apply through CBE career website https://vacancy.cbe.com.et, and required to attach Degree document, curriculum vitae, work experience, 8th grade certificate document and other necessary credentials within ten consecutive working days from the date of this announcement. However, the bank has full right to cancel or take any other alternative in this regard.
• Only shortlisted applicants will be communicated for exam and interview.
• All documents should be scanned in pdf or docx formats only and the size of the documents should be less than 2MB. You can use the following link to learn how to apply on CBE’s Career Website

Report this listing

Commercial Bank of Ethiopia
#በነፃ የስልክ ጥሪ ማዕከል #7711 በመደወል በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ይጠቁሙ ፤ ድምፅዎት እንዲሰማ ያድርጉ
#Let your voices be heard and report incidences of violence against women in the election by calling toll free#7711
#Yeroo filaannoo dhiibbaa dubartoota irra gahuu karaa lakkooffsaa bilbilaa tolaa #7711 irratti bilbiluudhan odeeffaannoo nuu biraan gahaa sagaleen isaani akka dhaga’aamuu ga’ee keessaan ba’aa
#Dooroh uddur sayyot yakkeh Yan bood currik yan telephone nebroh fateena, #7711 ah haak ascossa aba. Isinni xongolo kah tantaabbime innah aba