አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የኢትዮጵያ የኩባንያ ሕግ (3ኛው የተሻሻለ እትም) በቅርብ ቀን ታትሞ ይወጣል፡፡ ስለ 2ኛው እትም የተለያዩ ገንቢ ሀሳቦችን በመስጠት ላበረታታችሁኝ ሁሉ ምስጋናዬን እያቀርብኩ ስለ 3ኛው እትም ጥቂት መረጃ ልስጣችሁ፡፡

የገጽ ብዛት፡478
የመጽሐፉ መጠን፡ B5 (width 17.6 cm Height 25 cm)
ISBN 978-99944-3-573-1
አከፋፋይ፡ አንከቡት መጻሕፍት

ይህ 3ኛ እትም ከአዲሱ የንግድ ሕግ አንጻር ከእንደገና የተከለሰ ሲሆን አምስት አዳዲስ ምዕራፎችም ተካተውበታል፡፡ እነዚህም፡-

ስለ ባለ አንድ አባል ኩባንያ
ስለ ካፒታል/አክሲዮን ገበያ አሰራር
ስለ ተቧደኑ ኩባንያዎች
ስለ ኩባንያዎች ማህበራዊ ኃላፊነት
በኩባንያዎች ውስጥ ስለሚደረጉ መሠረታዊ ለውጦች (ለምሳሌ የካፒታል ለውጥ፣ ውህደት፣ የማህበር ዓይነት መለወጥ፣…)

ስለ መጽሐፉ ከመግቢያው ላይ ተቀንጮቦ የተወሰደ ጥቂት ማብራሪያ ይሄውላችሁ፡-

ይህ መጽሐፍ የሚያጠነጥነው ኩባንያ እንዴት እንደሚቋቋም፣ እንዴት እንደሚተዳደርና እንደሚፈርስ ነው፡፡ መጽሐፉ ከአዲሱ የንግድ ሕግ፣ ከተለያዩ አዋጆች፣ የፍርድ ውሳኔዎችና የሌሎች አገራት ተሞክሮዎች በመነሳት የኢትዮጵያን የኩባንያ ሕግ ይተነትናል፡፡ የኩባንያ ሕግ ዋና ትኩረት ሰዎች ኃላፊነት የተወሰነበትን አደረጃጀት (ኩባንያን) ተጠቅመው በጋራ የንግድ ስራን ሲሰሩ የሚፈጠሩ ችግሮችን መፍታት ነው፡፡ እነዚህ ችግሮች በዋናነት ሦስት ናቸው፡፡ አንደኛው የኩባንያው አስተዳዳሪዎች ባለአክሲዮኖችን እንዳይበድሉ መከላከል ነው፤ ሁለተኛው አብላጫ ድርሻ ያላቸው አነስተኛ ድርሻ ያላቸውን እንዳይበድ መከላከል ነው፡፡ ሦስተኛው ጉዳይ ሰዎች የኩባንያ አደረጃጀትን በመጠቀም በሦስተኛ ወገኖች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ መከላከል ነው፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱት አብዛኛዎቹ ርዕሰ-ጉዳዮች (ከክፍል ሁለት እስከ ክፍል አራት ያሉት) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እነዚህን ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ሕግ እንዴት እንደሚመልስ የሚተነትኑ ናቸው፡፡
መጽሀፉ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ተከፋፍሎ የቀረበ ነዉ፡፡ ክፍል አንድ ስለ ንግድ ማህበራት በጠቅላላው የሚዳሰስበት ሲሆን በውስጡ ሁለት ምዕራፎችን ይዟል፡፡ እነዚህም ስለ ኩባንያዎች የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ የሚናገረው ምዕራፍ አንድ፣ እና ስለ ንግድ ማህበራት ዓይነቶች እና ባህሪዎቻቸው የተተነተነበት ምዕራፍ ሁለት ናቸው፡፡ በምዕራፍ አንድ የሚነሱት ሀሳቦች በጥቅሉ ሁሉንም ነጋዴዎች የሚመለከቱ በመሆናቸው ለግል ንግድም (sole proprietorship) ተፈጻሚ የሆኑ ሕጎች የተዳሰሱበት ነው፡፡ ለዚህኛው ምዕራፍ ምንጭ የሆኑ ሕጎች የአዲሱ ንግድ ሕግ አንደኛ መጽሐፍ እና የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ፣ አዋጁን ለማስፈጻም የወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ናቸው፡፡ ምዕራፍ ሁለት ሁሉንም ዓይነት የንግድ ማህበራት የሚመለከቱ የንግድ ሕጉ ሁለተኛው መጽሐፍ ጠቅላላ ድንጋጌዎች የተዳሰሱበት ክፍል ነው፡፡ የመጽሐፉ ርዕስ እንደሚያመለክተው ትኩረቱ ኩባንያዎች ላይ ስለሆነ የሽርክና ማህበራት በዚህ ምዕራፍ ብቻ ነው የተዳሰሱት፡፡ ቢሆንም እያንዳንዱ የሽርክና ማህበር ዓይነት ራሱን በቻለ ንዑስ ርዕስ ስር ቀርቧል፡፡
ክፍል ሁለት ስለ አክሲዮን ማህበር የቀረበበት ክፍል ሲሆን በውስጡ ብዙ ምዕራፎችን ይዟል፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ስምንት ምዕራፎች አሉ፡፡ እነዚህም ከምዕራፍ ሦስት እሰከ አስር ያሉት ሲሆኑ ስለአክሲዮን ማህበር አመሰራረት፣ ስለ አክሲዮን ማህበር ካፒታልና አጠባበቁ እንዲሁም ስለ አክሲዮን፣ ስለ ኩባንያዎች መልካም አስተዳደር፣ ስለ ዳይሬክተሮች ቦርድ፣ ስለ ኩባንያ ኦዲተር፣ ስለ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ስለ አነስተኛ ባለአክሲዮኖች ጥበቃ፣ ስለ ኩባንያዎች መግለጫ እና ስለ ካፒታል/አክሲዮን ገበያ የሚዳስሱ ክፍሎች ናቸው፡፡የመጨረሻው ስለ ካፒታል ገበያ የሚዳሰስበት ክፍል አዲሱ የካፒታል ገበያ አዋጅ ወደ ስራ ሲገባ በአብዛኛው ተፈጻሚነቱ የአክሲዮን ማህበራት ላይ ስለሚሆን በዚህ ረገድ ከአክሲዮን ማህበራት ሕግ ጋር ያለውን ዝምድና እና ተፈጻሚነት ለማብራራት ታስቦ የገባ ምዕራፍ ነው፡፡
ክፍል ሦስት በኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት እየተሰራባቸው ስላሉት ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ማህበራት የተዳሰሰበት ክፍል ነው፡፡ ክፍሉ ከምዕራፍ አስራ አንድ እሰከ ምዕራፍ አስራ አራት ያሉትን አራት ምዕራፎች ይይዛል፡፡ ምዕራፍ አስራ አንድ ስለ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አመሠራረት ይዳስሳል፡፡ ምዕራፍ አስራ ሁለት ስለ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታል እና አክሲዮን ይቀርብበታል፡፡ እንዲሁም ምዕራፍ አስራ ሦስት ስለ ኃላፊነቱ ተወሰነ የግል ማህበር አካላት፣ ስልጣንና ኃላፊነት የተዳሰሰባቸው ክፍሎች ናቸው፡፡ በዚህ ክፍል የመጨረሻው ምዕራፍ ስለ ባለአንድ አባል ኃለፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የሚዳሰስበት ነው፡፡ ይህ በአዲሱ የንግድ ሕግ ከተከዋወቁት የኩባንያ ዓይነቶች አንደኛው ነው፡፡ ባለአንድ አባል ኩባንያ የኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ልውጥ (variant) ስለሆነ በዚህ ክፍል ውስጥ ይቀርባል፡፡
ክፍል አራት ሌሎች ልዩ ልዩ ርዕሰ-ጉዳዮች የሚደሰሱበት ክፍል ነው፡፡ ይህም ከምዕራፍ አስራ አምስት እስከ ምዕራፍ አስራ ስምንት ያሉትን አራት ርዕሶች የሚሸፍን ሲሆን በሌሎች ክፍሎች ውስጥ ሊቀርቡ የማይችሉ ነገር ግን በጣም አስፈላጊ ርዕሶች የተዳሰሱበት ክፍል ነው፡፡ ምዕራፍ አስራ አምስት ስለ መሠረታዊ ለውጦች የቀረበበት ሲሆን ኩባንያዎች ከምስረታ ጀምሮ እስከ መፍረስ ድረስ በሚኖራቸው ዕድሜ የሚያልፉባቸው መሠረታዊ ለውጦች የሚቀርብበት ነው፡፡ የመሠረታዊ ለውጥ ዓይነቶች፣ አደራረጋቸው እና በለውጥ የማይስማሙ አባላት መብት በዚህ ምዕራፍ ይቀርባል፡፡ ምዕራፍ አስራ ስድስት ስለ ኩባንያዎች መቧደን ሲሆን የቡድን ዓይነቶች፣ የእናት ኩባንያዎች እና የተቀጥላዎች ግንኙነት፣ የተቀጥላ ኩባንያ አነስተኛ ባለአክሲዮኖችና የባለገንዘቦች መብቶችን የተመለከቱና ተያያዥ ሀሳቦች ይቀርቡበታል፡፡ ይህ በአዲሱ የንግድ ሕግ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ርዕስ ነው፡፡
ምዕራፍ አስራ ሰባት ስለ ኩባንያዎች ማህበራዊ ኃላፊነት ነው፡፡ ይህም ኩባንያዎች በማህበረሰብ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተቋማት እንደመሆናቸው ያለባቸውን ማህበራዊ ኃላፊነት ትክክለኛ አረዳድና አተገባበር የሚቃኝ ምዕራፍ ነው፡፡ የመጨረሻው ምዕራፍ አስራ ስምንት ስለ ኩባንያዎች መፍረስና ሂሳብ መጣራት የሚቀርብበት ይሆናል፡፡ ይህ ምዕራፍ የአክሲዮን ማህበርን እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን የመፍረስ፣ የሂሳብ ማጣራት እና የመዝጋት ሂደት እና ሕጋዊ ውጤት የሚተነትን ክፍል ነው፡፡
#Share #Ale_Law
#አለ_ህግ #Ale_Law
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
#አለ_ህግ ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ክሶች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች 🔴ሁሉም ሕጎች በአንድ🔴 All in one, for All.
አለ_ህግ፣ መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው። contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.com

https://t.me/lawsocieties
#Share
#አለ_ህግ
#አለ_ስራ
Lawyers for Human Rights (LHR) is pleased to announce the signing of a Memorandum of Understanding (MoU) with Abbay Media. Both parties have agreed to strengthened and collaborate on their own respective roles in bringing social change that is favourable to Human rights and the protection of Human Rights in general.

The joint effort will reinforce the contribution of civil societies and media engagement in the human rights space; resulting in much better cooperation and interaction for better protection and promotion of human rights values.

#Ethiopia #HumanRight #HumanRightLawyers #LawyersforHumanRights #LHR #media #abbay
አቢሲኒያ ባንክ በሚከተሉት የስራ መደቦች ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
👩 position:-
1 - Legal Officer
2 - District IFB Business Manager
3 - Cameraman & Video Editor
📚 ትምህርት ዓይነት እና ደረጃ፡-
LLB Degree in Law,MA/BA Degree in Accounting, Management, Marketing, Banking and Finance, Economics or other business related fields,Diploma in Cinematography, Photography, or other related fields.
🇪🇹 የስራ ቦታ : አዲስ አበባ , ሀዋሳ
🧭የምዝገባ ጊዜ /Deadline/: እስከ መጋቢት 15 /2014 ዓ.ም
🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ !
https://jobs.amazonethiopia.com/job/bank-of-abyssinia-11/

Position 1 – Legal Officer

Education – LLB Degree in Law.
Experience-Minimum of 6 years banking
Experience, of which 3 years in the area of Law.
Place of Work – Addis Ababa
Deadline – march 24/22
proclamation-no-881-2015-corruption-crimes-proclamation.pdf
4.7 MB
ATTORNEY
Nyala Insurance Share Company (NISCO)

Addis Ababa

Full–time

LLB Degree Minimum of 1 year experience as attorney, preferably in financial industry, Age: Not more than 35 Place of Work: Addis Ababa Deadline Date March 27, 2022
HOW TO APPLY
Interested applicants who fulfill the above requirements are invited to submit their application with non-returnable copy of CV and credentials to the under mentioned postal address or in person at our HO (Protection House) 3rd floor Room No. 307 located around 22 Mazoria Mickey Leland Road.

• N.B. Only short listed applicants will be contacted and invited for interview. • NYALA INSURANCE S.C. (NISCO) • PROTECTION HOUSE P O. Box 12753 Addis Ababa

#አለ_ህግ #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_ስራ
#አለ_ልዩልዩ
#አለ_ችሎት
#አለ_ዜና
#አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና
#አለ_መረጃ
#አለ_ትምህርት
#አለ_ሁሉም
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
መመሪያ ቁጥር 14-2010 ዓ.ም.docx
74.8 KB
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትሕ ቢሮ የተሻሻለው የዐቃብያነ-ሕግ የደረጃ እድገት መመሪያ መመሪያቁጥር 14-2010 ዓ.ም
የኢትዮጵያና የውጭ ሀገር ገንዘቦች መያዝ ላይ ያለው ገደብ እና የወንጀል ተጠያቂነት🔴
ገንዘብ እንደ ሀብት መለኪያ ሆኖ ከማገልገሉ ባለፈ የመገበያያ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ለዚህ እዲረዳ ሀገራት የየራሳቸው የሆነ ሕጋዊ ገንዘብ አላቸው፡፡ ይህን የራሳቸውንም ሆነ የሌላ ሀገር ገንዘብ ስለአያያዝና አጠቃቀሙ ምንዛሬን ጨምሮ የሚያስተዳድሩበት ሥርዓት ይዘረጋሉ፡፡ በዚህ አጭር ፅሑፍ የኢትዮጵያና የውጭ ሀገር ገንዘቦችን አያያዝ በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣው መመሪያን ማዕከል አድርገን ያሉት ገደቦች ምን እንደሚመስሉ ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

1. የገንዝብና የውጭ ሀገር ገንዘብ ምንነት

ቀደም ባሉት ጊዜያት ግብይቶች ሁሉ ቁስን በመለዋወጥ ወይም ዕቃን በዕቃ በቀጥታ መለዋወጥን (Barter System) መሰረት ያደረጉ ነበሩ፡፡ በዚህ ስርዓት ውስጥ ግብይት እጅግ ከባድ ስለሆነ ቀስ በቀስ ሌላ የግብይት ስርዓቱን የሚያቀላጥፍ በማስፈለጉ ምክንያት በራሳቸው ዋጋ ያላቸው ቁሶች ጉልህ ሚናቸውን መጫወት ጀመሩ፡፡ ለአብነት ወርቅ፣ ብር እና የመሳሰሉት ቁሶች በተፈጥሯቸው ከገንዘብነት ባለፈ ለሌላ ጉዳይ አገልግሎት ላይ መዋል የሚችሉ ናቸው፡፡ በሂደት ግን ይህም አሰራር ተቀይሮ ለብቻው በራሱ ገንዘብ ሆኖ ከማገልገል ውጭ ዋጋው ኢምንት የሆነ፤ መንግስታት አትመው ወይም አሳትመው ስርጭቱን እንዲሁም ተመኑን የሚያስቀምጡለት ስርዓት የተፈጠረ ሲሆን እነዚህም አሁን የምንገለገልባቸው የወረቀት ገንዘብና ሳንቲሞች ናቸው፡፡

የውጭ ሀገር ገንዘብ ምንነትን አስመልክቶ በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 በአንቀፅ 2(5) ሥር እንደሚከተለው ተተርጉሟል፡- “የውጭ ሀገር ገንዘብ ማለት ከኢትዮጵያ ገንዘብ በስተቀር ከኢትዮጵያ ውጭ በማናቸውም ሀገር ሕጋዊ ገንዘብ የሆነና በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረግ ክፍያ ተቀባይነት እንዳለው ብሔራዊ ባንክ ያሳወቀው ማናቸውም ገንዘብ ነው” ይላል፡፡ በዚህ ትርጉም መሰረት አንድ የውጭ አገር ገንዘብ በኢትዮጵያ ተቀባይነት እንዲያገኝ ሁለት መሰረታዊ ነገሮች ሟሟላት እንደሚጠበቅበት ይገልፃል፡፡ 1ኛ በሌላ ሃገር ህጋዊ የሆነ ገንዘብ መሆን አለበት፣ 2ኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ ለክፍያ ያሳወቀው መሆን አለበት የሚሉ መስፈርቶች ተቀምጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተቀባይነት እንዳላቸው ያሳወቃቸው ማለትም በቋሚነት በሕግ ተለይተው የታወቁ የውጭ ሀገር ገንዘቦች ባይኖሩም በየጊዜው ዋጋ እየተመነ የሚያወጣቸውና የተለመዱ የውጭ ሀገር ገንዘቦች አሉ፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ ከብሔራዊ ባንክ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው የሚከተሉት ገንዘቦች በወቅቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ለክፍያ እውቅና የተሰጣቸው ገንዘቦች ናቸው፡፡ እነዚህም የጃፓን የን፣ የኖርዌይ ክሮን፣ የስዊድን ክሮነር፣ የቻይና ይዋን፣ የዴንማርክ ክሮነር፣ የሳውዲ ሪያል፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ድርሀም፣ የአውስትራሊያ ዶላር፣ የካናዳ ዶላር፣ የአሜሪካ ዶላር፣ የሲውዘርላንድ ፍራንክ፣ የእንግሊዝ ፓውንድ እና የአውሮፓ ዩሮ ናቸው፡፡ ከነዚህ የገንዘብ ዓይነቶች ውጪ የሌላ ሀገር ገንዘብ ይዞ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ ተጠያቂነት የለበትም ማለት ነው፡፡

2. የውጭ ሀገር ገንዘብ የመያዝ ገደብ

ገደብና ክልከላው የተቀመጠው በመመሪያ ቀጥር FXD/49/2017 ሲሆን በውጭ ሀገር ገንዘቦች ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ብርም ላይ ጭምር ነው፡፡ በዚህ መመሪያ መሰረት ክልክላና ገደቡ በሁለት ተከፍሎ ተቀምጧል፡፡ ይኸውም ዜግነትን መሰረት ሳያደርግ የኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነና የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ በሚል የተከፈለ ነው፡፡ በዜግነት እና በነዋሪነት መካከል ያለው ልዩነት ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሚፈልግ ቢሆንም ባጭሩ ለመግለፅ ዜግነት በትውልድ ወይም በሕግ የሚገኝና በአንድ ሀገር እራሱን የቻለ ዜጋ ያልሆነ ሰው የማያገኘው መበትና ግዴታን የሚያሰጥ ግለሰብን ከሀገር ጋር የሚያስተሳስር (የሚያዛምድ) ሥርዓት ሲሆን ነዋሪነት ማለት ደግሞ ዜግነት ያለውም የሌለውም ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በአዋጅ ቁጥር 354/95 አንቀፅ 13-15 እና በደንብ ቁጥር 144/95 አንቀፅ 26-31 ባሉት ድንጋጌዎች መሰረት ነዋሪ ማለት ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ፈቃድ አግኝቶ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ሰው ማለት ነው፡፡

ክልከላውን በተመለከተ በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው በውጪ ሀገር በነበረው ጉዞ ምክንያት መጠኑ ከ1,000 (አንድ ሺ) የአሜሪካን ዶላር በላይ ወይም ለዚሁ ተመጣጣኝ የሆነ የውጭ ሀገር ገንዘብ በእጁ የያዘ ሰው ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ቅፅ አማካኝነት በአቅራቢያ ለሚገኝ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ማሳወቅ ወይም ዲክሌር ማድረግ እንዳለበት እና በ30 ቀናት ውስጥ ባንክ በመሄድ ወደ ኢትዮጵያ ብር መመንዘር እንዳለበት በመመሪያው አንቀፅ 4.1(a) እና 4.2 ሥር ተደንግጓል፡፡ መጠኑ ከ1,000 (አንድ ሺ) የአሜሪካን ዶላር ያነሰ ወይም ለዚሁ ተመጣጣኝ የሆነ የውጭ ሀገር ገንዘብ ይዞ ወደ ሀገር የገባ ሰው ምንም እንኳን በሕጉ የማሳወቅ ግዴታ ባይጣልበትም በ30 ቀናት ውስጥ ወደ ሕጋዊ ባንኮች ሄዶ ወደ ኢትዮጵያ ብር የመመንዘር ግዴታ አለበት፡፡

ከውጪ ሀገር የገባም ባይሆን በሆነ አጋጣሚ ማንኛውንም ያክል መጠን ያለው የውጪ ሀገር ገንዘብ ያለው ሰው ገንዘቡ በእጁ ከገባበት ወይም ለጉምሩክ ኮሚሽን ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ብር መመንዘር እንዳለበት በመመሪያው አንቀፅ 3 እና 4.2 (a) ላይ ተደንግጓል፡፡ የውጭ ሀገር ገንዘብ ያለው ሰው በባንክ ወደ ኢትዮጵያ ብር መመንዘር አለበት ብቻም ሳይሆን ከቀነ ገደቡ በላይ መያዝ እንደማይችል ወይም ክልክል እንደሆነ በመመሪያው ላይ ተደንግጓል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ ያልሆነ ሰውም ቢሆን ወደ ሀገር በሚገባበት ጊዜ ከ3,000 የአመሪካን ዶላር በላይ ወይም ለዚሁ ተመጣጣኝ የሆነ የሌላ ሀገር ገንዘብ የያዘ እንደሆነ በአየር ማረፊያዎች ወይም በሌሎች የመግቢያ በሮች ላይ ለሚገኝ የጉምሩክ ኮሚሽን ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው ቅፅ ላይ ሞልቶ የማሳወቅ ወይም Diclare የማድረግ ግዴታ እንዳለበት በመመሪያው አንቀፅ 4.1 (b) ሥር ተደንግጓል፡፡

በመመሪያው አንቀፅ 4.2 (c) መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ዲክሌር ያደረገውን የውጭ ሀገር ገንዘብ ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ባንክ ሄዶ ወደ ኢትዮጵያ ብር የመመንዘር ግዴታ አለበት፡፡ ቢሆንም እስከ የቪዛው (ቪዛ ማለት በኢትዮጵያ ነዋሪ ላልሆነ ሰው ለተወሰነ ጊዜ የሚሰጥ የመኖሪያ ፈቃድ ነው) ማለቂያ ጊዜ ድረስ ማቆየት እንደሚችል በአንቀፅ 4.2 (c) ተደንግጓል፡፡

3. የኢትዮጵያ ብር ላይ የተጣለ ገደብ

ከላይ በተጠቀሰው መመሪያ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው ከውጪ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ እና ከኢትዮጵያ ውጪ የሚሄድ ሰው ላይ እንጂ ማንኛውም ሰው ላይ የተጣለ ገደብ እንዳሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ወይም ከኢትዮጵያ የሚወጣ ማንኛውም ሰው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተወሰነው ወይም ከተፈቀደው መጠን በላይ የኢትዮጵያን ገንዘብ ይዞ ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት ወይም ለመውጣት እንደማይችል በአዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀፅ 18(6) ሥር ተደንግጓል፡፡ የተፈቀደው የገንዘብ መጠንን አስመልክቶ የመመሪያ ቁጥር FXD/49/2017 አንቀፅ 2.1 መሰረት ከውጪ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ሰውም ሆነ ከኢትዮጵያ ወደ ውጪ ሀገር የሚሄድ ሰው 1,000 (አንድ ሺ) በላይ ብር መያዝ እንደማይችል ተደንግጓል