አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የብድር ውል ‼️
(የፍትሐብሔር ሕግ ከቁጥር 2471-2489)
የብድር ውል ምንነት፡- የተለያዩ ፅሑፎች እንደሚያስረዱት ብድርን በተመለከተ ሁሉንም ሊያግባባ የሚችል አንድ ወጥ የሆነ ትርጉም አናገኝለትም፡፡ የፍትሐብሔር ሕጋችን የሚከተለውን ትርጉም ሰጥቶታል፡- “የሚያልቅ ነገር ብድር ማለት ከተዋዋዮቹ አንዱ ወገን አበዳሪው ሌላውን ተበዳሪ ሰው የተበደረውን ነገር በዓይነቱ ለመመለስ ተገዳጅ በማደረግ ገንዘብ ወይም በማገልገል የሚያልቅ ሌላ ነገር ለተበዳሪው ለመስጠትና ሀብትነቱን ለማስተላለፍ የሚገደድበት ውል ነው” ይላል፡፡ ከዚህ ትርጓሜ መረዳት እንደሚቻለው ብድርን በሚመለከት ሕጉ በሚያልቅ ነገር ላይ ብቻ እንጂ ከዛ ባለፈ ማለትም በማያልቅ ነገር ወይም ቋሚ የሆነ ንብረትን የማያካትት መሆኑን ነው፡፡ የድንጋጌውን አጠቃላይ ይዘት ስናይ አመላለሱ በዓይነት ወይም በአገልግሎት ሊሆን እንደሚችል እና ውሉ አስገዳጅ መሆኑንም ያሳያል፡፡
የዉል አመሠራረት፡- የብድር ውል የውል አንድ አካል እንደመሆኑ መጠን አመሰራረቱም ሆነ አፈፃፀሙ በጠቅላላው የውል ሕግ መርሆች የሚገዛ በመሆኑ የብድር ውልን ዝርዝር ድንጋጌዎች ከማየታችን በፊት ስለውል አመሰራረት ባጭሩ አይተን ብናልፍ የተሻለ ግንዘቤን ይፈጥራል፡፡ ዉል ስምምነት ቢሆንም ከሌሎች ስምምነቶች የሚለየዉ በአፈፃፀሙ ከበስተጀርባዉ የሕግ ድጋፍ ያለዉ ስምምነት መሆኑ ላይ ነዉ፡፡

አንድ ውል የሚፀና ውል ነው ለማለት የሚከተሉትን መርሆች ማሟላት አለበት፡- 1ኛ ዉል የሚፈፀመዉ ለመዋዋል ችሎታ ባላቸዉ ሰዎች መካከል ብቻ መሆኑ (እድሜዉ ለአቅመ አዳም/ሄዋን ያልደረሰ ወይም አይምሮዉ ህመም ያለበት ሰዉ ወይም በፍርድ ቤት የተከለከለ ሰዉ ችሎታ እንደሌለዉ ይቆጠራል፡፡) 2ኛ ዉል የሚደረገው በተወያያቹ ነፃ ፍቃድ ብቻ የሚደረግ መሆኑ፡፡ 3ኛ ተወያይ ወገኖች የሚዋዋሉበት ጉዳይ በእርግጠኝነት የሚቻል እና ህጋዊና ሞራላዊ ጉዳይ ላይ መሆን የሚገባው መሆኑ፡፡ 4ኛ የዉል አቀራረጹ ወይም አፃፃፉ (ፎርም) በህግ ተለይተዉ የተቀመጡ ወይም ተዋዋይ ወገኖች ተለይቶ እንዲቀመጥ ከተስማሙበት የዉል ጉዳይ በቀር የተለየ የዉል ፎርም አያስፈልግም፡፡

የአበዳሪና ተበዳሪ ግዴታዎች፡- አበዳሪና ተበዳሪ የራሳቸው የሆኑ ሊያከብሯቸው የሚገቡ ግዴታዎች አሉባቸው፡፡ በቅድሚያ የአበዳሪው ግዴታዎችን ስናይ ሕጉ የአበዳሪውን ግዴታዎች በተመለከተ የሽያጭ ውልን በሚደነግገው ክፍል ላይ የሻጩ ግዴታዎች ተብለው የተገለፁት ደንቦች በአበዳሪ ላይ ተግባራዊ ይሆናሉ ይላል፡፡ በፍትሐብሔር ሕጉ የሻጭ ግዴታዎች ናቸው የተባሉት ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1ኛ ዕቃ የማስረከብ ግዴታ፡- የሽያጭ ውል ከተከናወነ በኋላ ሻጭ የግብይት ምክንያት የሆንውን ዕቃ/ንብረት ለገዥ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡ 2ኛ ስመ-ሀብት የማስተላለፍ ግዴታ፡- ከላይ ለማንሳት እንደተሞከረው የሽያጭ ውል ልዩ መገልጫ ከሆኑት ጉዳዮች ውስጥ ሻጩ የሽጭ ምክንያት የሆነውን ንብረት ስመ-ሀብትን የማስተላለፍ ግዴታ ያለበት መሆኑ ነው፡፡ የባለቤትነት መብት መተላለፍን በተመለከተ የብድር ውል ከሽያጭ ውል ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር የብድር ውሉ በትርጉም ክፍሉ ላይ እንደሰፈረው አላቂ ዕቃን ብቻ የሚመለከት በመሆኑ ዕቃውን ለተበዳሪው በሚያስረክብበት ወቅት የባለቤትነት መብትም አብሮ መተላለፍ መቻሉ ነው፡፡ 3ኛ ዋስትና የመስጠት ግዴታ፡- ሌላኛው የሻጭ ግዴታ ከተሸጠው ዕቃ ጋር በተገናኘ ለሚፈጠሩ ችግሮች ለገዥው ዋስትና የመስጠት ግዴታ ነው፡፡

የተበዳሪውን ግዴታዎች በተመለከተ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ዕዳውን መልሶ ከመክፈል ጋር የሚገናኝ ነው፡፡ ተበዳሪ የብድር ውል ውስጥ ሲገባ የተበደረውን ነገር በዓይነቱ ለመመለስ ወይም በገንዘብ የሚመለስ ሲሆን እነዚህን በወቅቱ የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡ የብድሩ አመላለስ በማገልገል የሚያልቅ ሲሆን ደግሞ ለአበዳሪው ተገቢውን)
የብድር ማስረጃ፡- ማስረጃ ማለት አንድ በፍርድ ቤት ምርመራ ላይ ያለ በጭብጥ የተያዘ አከራካሪ ጉዳይ እውነት መሆንና አለመሆኑን በሚያሳምን ሁኔታ ማረጋገጥ እንዲያስችል በግብአት የሚቀርብ ፍሬ ነገር ስለመሆኑ ብ/ጀነራል ታጠቅ ታደሰ “የማስረጃ ሕግ መሰረተ ሀሳቦች” በሚለው መፅሐፋቸው ገልፀውታል፡፡ ማስረጃ ማለት ይህ ከሆነ በሁለት ሰዎች መካከል የብድር ውል ተደርጓል ወይስ አልተደረገም የሚለውን ጥያቄ በምን ማረጋገጥ እንችላለን? የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ ቀጥለን እናያለን፡፡ የፍ/ሕጋችን በአን. 2472 ስር የብድር ማስረጃ በሚል ርእስ የሚከተለውን ደንግጓል፡-
(1) በብድር የተሰጠው ገንዘብ ከብር 500 በላይ ሲሆን የብድሩን ውል በፅሑፍ ወይም በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም መሐላ ካልሆነ በስተቀር ለማስረዳት አይቻልም፡፡
(2) ለብድር ውል ማናቸውም ሌላ ዓይነት ማስረጃ ለማቅረብ አይቻልም ፡፡ (3) እንዲሁም ከብር 500 የበለጠ ገንዘብ የመክፈል ነገር በዚህ ዓይነት ይፈፀማል፡፡ በዚህም መሰረት የብድሩ መጠን ብር 500 እና ከዛ በታች ከሆነ በማንኛውም ዓይነት ማስረጃ ለምሳሌ በቦታው የነበረ የሰው ምስክር በመስማት ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑን እና መጠኑ ከዛ በላይ ከሆነ ግን ከሦስቱ የማስጃ ዓይነቶች መካከል በአንዱ ካልሆነ በስተቀር በሌላ በምንም መንገድ ማረጋገጥ የመማይቻል መሆኑን ነው መረዳት የሚቻለው፡፡ እነዚህን ሦስት የማስረጃ ዓይነቶች ቀጥለን እንመልከት፡፡
የመጀመሪያውና የበለጠ አስተማማኝ የሆነው ማስረጃ የፅሑፍ ማስረጃ ነው፡፡ ይህም ማለት ገና ከጅምሩ የብድር ውሉ ሲደረግ በፅሑፍ የተደረገ ሲሆን ያንን ፅሑፍ ለፍርድ ቤት በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል፡፡ በሌላ አነጋገር ከብር 500 በላይ የሆነ የብድር ውል በፅሑፍ እንዲሆን ሕጉ አስገዳጅ የሚመስል ድንጋጌ ያስቀመጠ በመሆኑ ከላይ ካነሳነው የውል አመሰራረት መርሆች መካከል የተለየ ፎርም የሚፈልግ መሆኑን ማየት ይቻላል፡፡ ሁለተኛው የማረጋገጫ መንገድ በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ነው፡፡ ይህም ማለት ተበዳሪው በፍርድ ቤት ቀርቦ በከሳሹ የቀረበበትን ክስ ማለትም ከከሳሹ ገንዘብ የተበደረ መሆኑን፣ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ በማያሻማ መንገድ ካመነ በቀላሉ የብድሩ መኖር የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡ ሦስተኛውና የመጨረሻው የማረጋገጫ መንገድ በመሐላ የማረጋገጥ ሂደት ነው፡፡ መሐላ ማለት በክርክር ወቅት አንድ ተከራካሪ ወገን በሚያቀርበው ማስረጃ ወይም በሚናገረው ፍሬ ነገር እውነትነትን ለማረጋገጥ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ቅፅ ላይ የሚሰጡት ማረጋገጫ ነው፡፡

የብድር መመለሻ ጊዜ፡- ብድር ውል እንደመሆኑ መጠን ለተዋዋይ ወገኖች ሰፊ ነፃነት መሰጠት አለበት፡፡ በመሆኑም ሕጉ ስለብድር መመለሻ ጊዜ በተዋዋይ ወገኖች የተወሰነ ጊዜ በሚኖርበት ወቅት ይህንኑ ዕውቅና በመስጠት ክፍያው በዛ ጊዜ መሆን እንደሚገባው ሕጉ አፅንኦት ሰጥቶበታል፡፡ ከዚህም ባለፈ ብድሩ ወለድ የሌለበት ከሆነ የተበደረውን ገንዘብ ለመመለስ ማሰቡን ለአበዳሪው ከአንድ ወር በፊት አስታውቆ የመመለሻ ጊዜው ከመድረሱ በፊት ሊመልስለት እንደሚችልም ሕጉ ይደነግጋል፡፡ የብድሩ መመለሻ ጊዜ በተዋዋይ ወገኖች ያልተወሰ በሚሆን ጊዜ ሕጉ ብድሩ በምን ያክል ጊዜ ውስጥ ሊከፈል እንደሚገባው ደንግጓል፡፡ ይኼውም አበዳሪው መልስልኝ ሲል ከጠየቀበት ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መመለስ እንዳለበት ተደንግጓል፡፡.........
.......................ተበዳሪውም በአበዳሪው ሳይጠየቅ መክፈል ቢፈልግ ለመክፈል ያለውን ሀሳብ ከአንድ ወር በፊት ካስታወቀ በኋላ ዕዳውን መመለስ እንደሚችል እንዲሁ ተደንግጓል፡፡

በብድር ላይ ሊኖር ስለሚችል ወለድ፡- በብድር ውል ላይ ሊኖር ስለሚችል ወለድም ለተዋዋይ ወገኖች ነፃ ፈቃድ የተተወ ጉዳይ ነው፡፡ ብድሩ ወለድ የሚከፈልበት ስለመሆኑ በውሉ በግልፅ ካልተገለፀ ግን ተበዳሪው በምንም መልኩ ወለድ እንዳይከፍል ሕጉ ጥበቃ ያደርግለታል፡፡ ሕጉ በብድር ውሉ ላይ ወለድ ይኑር አይኑር የሚለውን ጉዳይ በተዋዋይ ወገኖች እንዲወሰን ነፃነት የሰጠ ቢሆንም በወለድ መጠኑ ልክ ላይና ስለሚከፈልበት ጊዜ ወይም ወለዱ ስለሚሰላበት ጊዜ ግን ገደብ አስቀምጧል፡፡ በዚህም መሰረት ተዋዋይ ወገኖች የወለዱን መጠን በዓመት ከ12 በመቶ በላይ ማድረግ እንደማይችሉ ገደብ ጥሏል፡፡ እንዲሁም የወለዱ መጠን በውሉ ላይ ካልተገለፀ እና ወለድ የሚከፈልበት ብድር መሆኑ ብቻ ተገልፆ ከሆነ ወይም ወለዱ ከ12 በመቶ በላይ ይሆናል የሚል የውል ቃል ካለ መከፈል የሚችለው የወለድ መጠን በዓመት 9 በመቶ ብቻ እንደሚሆንና የሚሰላውም ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ ብድሩ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር በየዓመቱ መጨረሻ ላይ መሆን ይገባዋል ይላል ሕጉ ፡፡

የብድር አከፋፈል (የሚከፈለው ነገር)፡- በብድር አመላለስ ወቅት ሌላው ግለፅ መሆን ያለበት ጉዳይ ብድሩ በየትኛው ሀገር የገንዘብ ዓይነት ነው? ከብድሩ በኋላ የምንዛሬ ዋጋ መለዋወጥ ቢያጋጥምስ ምን ይሆናል? የሚለው ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የፍትሐብሔር ሕጉ ግልፅ ድንጋጌዎች አሉት፡፡ በዚህም መሰረት የብድር ውሉ የተደረገው በኢትዮጵያ ብር ከሆነ ብድሩ በሚመለስበት ወቅት ባለው ሕጋዊ የኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ ወይም ለዚህ የገንዘብ መጠን የሚተካ የውጭ ምንዛሬ በማቅረብ ከዕዳው ነፃ እንደሚሆን ተደንግጓል፡፡ የሚከፈለውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ የብድር ውሉ በሚከናወንበት ጊዜ በትክክል የተበደረውን ያክል እንጂ ሌላ ነገር እንደማያካትትና በመሀል ሊያጋጥም የሚችለውን ወይም ያገጠመውን የገንዘቡ ዋጋ መለዋወጥ ግምት ውስጥ መግባት እንደሌለበትም ሕጉ አያይዞ ይገልፃል፡፡ ብድሩ በውጭ አገር ገንዘብ ተደርጎ ከነበረ ደግሞ ብድሩ በሚከፈልበት ጊዜ በዛ አገር ሕጋዊ መገበያያ በሆነው የገንዘብ ኖት መከፈል ያለበት ሲሆን መጠኑም የተበደረውን ያክል ብቻ መሆን እንዳለበት ሕጉ አመልክቷል፡፡ የብድር ውሉ የተደረገው ከገንዘብ ውጪ ባሉ የሀብት ዓይነቶች በሚሆንበት ጊዜ ለምሳሌ፡- ለምግብ የሚሆኑ ነገሮች፣ ሸቀጦች ወይም መአድናት ሲሆኑ ተበዳሪው በተበደረው ልክ ብዛቱንና ዓይነቱን በመክፈል ከዕዳው ነፃ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ከብድሩ በኋላ በሚኖር የዋጋ መለዋወጥ የብድድር አመላለሱን መጠንና ዓይነት ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ የለም፡፡
federal attorney general
share share
#share #Share
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤት የሚከተለውን ይመስላል

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል።

በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል።

ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
በኮንስትራክሽን ውል ስለ ግንባታ ስራ ርክክብ/Acceptance/
======**=======
#በኮንስትራክሽን ውል ሁለት አይነት የግንባታ ስራ ርክክብ ያለ ሲሆን ይሄውም ግዚያዊ ርክክብ(provisional acceptance) እና የመጨረሻ ርክክብ(final acceptance) የሚያካትት ነው፡፡
#በዚህ ጽሁፍ በዋናነት በኮንስትራክሽን ውል ህግ እውቅና የተሰጣቸውን የርክክብ አይነቶች ምንነትና ተያያዥ ውጤታቸውን አስመልክቶ የህግ ድንጋጌዎችን እና አሁን ላይ በመንግስት ተቋማት እየተሰራበት ያለውን የፒፒኤ 2011 ጀኔራል ኮንዲሽን ድንጋጌዎችን ባካተተ ሁኔታ ለማብራራት ተሞክሯል፡፡
**
#ግዚያዊ ርክክብ/Provisional Acceptance/
#ግዜአዊ ርክክብ በተለይ በኮንስትራክሽን ውል የተመለከቱ የግንባታ ስራዎች ተከናውነው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ማለትም አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በስራው ላይ የሚደረግ የምርመራ ማረጋገጫ ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3274(1) ይደነግጋል፡፡ ይሄውም አሰሪው በትክክል የተገነባውን ግንባታ በእጁ አግብቶ መያዙን ጭምር ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ ጊዜአዊ ርክክብ በዋናነት የተሰራውን የግንባታ ስራ አሰሪው መብቱን ጠብቆ በመጀመሪያ የሚረከብበት ሂደት ነው ማለት ነው፡፡በስራው ላይ ምርመራ መደረጉንም የሚያረጋግጥ ነው፡፡
#ፒፒኤ 2011 ክሎስ 84.1 ላይ የስራ ምርመራ/verification and test/ በመሀንዲሱ ተቋራጭ ባለበት ሊደረግ እንደሚገባ በመርህ ደረጃ ተቀምጧል፡፡ሆኖም ግን ተቋራጩ ምርመራው ከሚካሄድበት እለት ከ30 ቀን በፊት በተገቢ ሁኔታ እንዲያውቀው ተደርጐ በምርመራው እለት ያልተገኘ እንደሆነ የስራ ምርመራው ተቋራጩ በሌለበት ሊካሄድ እንደሚችል ይፈቅዳል፡፡
#እንግዲህ መሀንዲሱ ስራውን ከመረመረ በኋላ ያላመነበትን የስራ ክፍል ፈርሶ እንደገና እንዲሰራ ወይም እንዲጠገን ተደርጐ የጥራት ደረጃውን ባሟላ ሁኔታ እንዲከናወን ለማዘዝ እንደሚችል ፒፒኤ ክሎስ 85 ይፈቅድለታል፡፡
#በዚህም መሰረት ግንባታው የስራ ምርመራውን ካለፈ አሰሪው ግንባታውን የሚረከበው ይሆናል ማለት ነው፡፡ስለዚሁም የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት ለተቋራጩ የሚሰጠው ይሆናል፡፡በመሰረቱ ተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንዲሰጠው መጠየቅ ያለበት ስራው ሊጠናቀቅ ይችላል ብሎ ከሚያስብበት ከ15 ቀን በፊት መሆን ይኖርበታል፡፡ከዚያም መሀንዲሱ ጥያቄው በደረሰው በ30 ቀን ውስጥ የስራ ምርመራውን አጠናቆ ሰርተፍኬቱን መስጠት ወይም ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡መሀንዲሱ ሰርተፍኬቱን ሳይሰጥ ወይም ጥያቄውን ውድቅ ሳያደርግ 30 ቀኑ ያለፈ እንደሆነ ለተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንደተሰጠው ግምት እንደሚወሰድ ፒፒኤ ክሎስ 87 ያስቀምጣል፡፡
#ሌላው ተቋራጩ በስራው ላይ ያደረገው መሻሻል/መለወጥ ቢኖር እንኳ በዝምታ ግዜአዊ ርክክብ ከተደረገ መሻሻሉ ተቀባይነት እንዳገኘ የህግ ግምት እንደሚያስወስድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(2) ይደነግጋል፡፡እዚህ ላይ ተቋራጩ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት የመስራት ግዴታ ያለበት መሆኑ ይታዎቅ፡፡ ስለዚህ የህግ ግምቱ እሳቤ ተቋራጩ ከዲዛይኑ በመውጣት አሻሽሎ የሰራው ስራ ኖሮ በግዜአዊ ርክክብ ወቅት በዝምታ አሰሪው ካለፈው እንደተቀበለው ይቆጠራል ነው፡፡
#እንዲሁም ግዜአዊ ርክክብ መደረጉ የመድህንነት ጊዜው(warranty period) መጀመሩን እንደሚያመለክት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(3) ይደነግጋል፡፡
**
#የመድህንነት ጊዜ(warranty period/Defects Liability period)
#የመድህንነት ጊዜ(warranty period) የሚባለው ከጊዜአዊ ርክክብ እስከ መጨረሻ ርክክብ ያለው ጊዜ ሲሆን አሰሪው ግንባታው በተቋራጩ በደህና ሁኔታ ስለመሰራቱ ለመመርመርና ለማረጋገጥ የሚያስችለው ጊዜ ነው፡፡የጊዜው ርዝማኔም በውላቸው ላይ የሚወሰን ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3277 ይደነግጋል፡፡ ሆኖም በውሉ ላይ የመድህንነት ጊዜው ርዝማኔ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ከጊዜአዊ ርክክብ ቀን ጀምሮ 365 ቀን ስለመሆኑ የፒፒኤ ክሎስ 88.7 ያስቀምጣል፡፡
#ተቋራጩ በዚሁ በመድህንነት ጊዜ በተለይ የተበላሹ ስራዎችን እንዲያድሳቸው በአሰሪው በታዘዘ ጊዜ የማስተካከል ግዴታ እንዳለበት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3278 ይደነግጋል፡፡ ለዚህም ለጥገና ወጭ ሲባል ከተቋራጩ ክፍያ ላይ ሪቴንሽን ገንዘብ(retention money or bond) 5% እየተቀነሰ በአሰሪው ይያዛል፡፡
#በመድህንነት ጊዜ ውስጥ የተለዩ ብልሽት ያለባቸው ስራዎችን እንዲያስተካክል ተቋራጩ ተጠይቆ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያላስተካከለ እንደሆነ አሰሪው የማስተካከያ ስራውን በተቋራጩ ወጭ በራሱ ወይም ሌላ ቀጥሮ ሊያሰራው ወይም ውሉን ሊያቋርጥ ስለመቻሉ ፒፒኤ ክሎስ 88.3 ለአሰሪው መብት ይሰጠዋል፡፡
**
#ከፊል ርክክብ/Partial Acceptance/
-በፒፒኤ ክሎስ 86 ላይ የግንባታ ስራው በከፊል እርክክብ የሚደረግበትንም አማራጭ ያስቀምጣል፡፡ይህ ማለት የተወሰነውን የስራ ክፍል(part of the work) ከአጠቃላይ ውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ በውል ላይ ከተቀመጠ ተቋራጩ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከአጠቃላይ የውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ ይገደዳል ማለት ነው፡፡በዚህም በአንድ ውል ውስጥ በተለያየ ጊዜ ጊዜአዊ ርክክብ ሊደረግ የሚችልበትን ሁኔታ ይፈጥራል ማለት ነው፡፡
**
#የመረሻ ርክክብ/Final Acceptance/
#የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/ በተለይ የመድህንነት ጊዜ ካለቀ በኋላ እና ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደህና ሁኔታ የፈጸመ መሆኑን አሰሪው ሲያረጋግጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በእጁ የሚያደርግበት(definitively appropriate) ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279 ይደነግጋል፡፡
#የመጨረሻ ርክክብ አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት በአስገዳጅ ሁኔታ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279(2) ላይ ተደንግጓል፡፡ሆኖም ጊዜአዊ ርክክብ/ Provisional Acceptance/ በሚመለከት ግን በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት የሚያስገድድ ግልጽ ህግ የለም፡፡ስለዚህ ስራው ተጠናቆ አሰሪው ግንባታውን በእጁ ካስገባ ጊዜአዊ ርክክብ መደረጉን የሚያስገነዝብ ይሆናል ማለት ነው፡፡በእርግጥ በጽሁፍ መደረጉ ይመከራል፡፡
#በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3282 ላይ እንደተቀመጠው ከመጨረሻ ርክክብ በኋላ ተቋራጩ እስከ 10 አመት ድረስ ስለስራው አሰራር ጉድለት ተቋራጩ ሀላፊነት አለበት፣መድህን ሆኖ ይቀጥላል፡፡በመጨረሻ ርክክብ ወቅት የሚታዩ ለነበሩ ጉድለቶች(apparent defect) ግን ተቋራጩ ሀላፊነት የለበትም፡፡ሀላፊነቱ የሚመለከተው ግንባታው በውሉ የተመለከተውን የታለመለትን ጥቅም እንዳይሰጥ የሚያደርጉ ወይም አጠቃቀሙን በጣም ውድ የሚያደርጉና አክሳሪ የሚያደርጉ ጉድለቶችን ነው፡፡
#henoktayelawoffice
አለ_ህግ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ክሶች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች 🔴ሁሉም ሕጎች በአንድ🔴 All in one, for All.
አለ_ህግ፣ መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው። contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.com
https://t.me/lawsocieties
የአስተዳደር ህግ እና ህገ መንግስታዊ መርሆዎች.....

የአስተዳደር ህግ እና የህገ መንግስት ትስስር እና ተዛምዶ

የህግ የበላይነት

የስልጣን ክፍፍል

የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት አፈፃፀም

መሰረታዊ የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች

ተጠያቂነት ግልፅነት እና የህዝብ ተሳትፎ

የአስተዳደር ህግ እና ህገ መንግስታዊ መርሆዎች

የአስተዳደር ህግ እና የህገ መንግስት ትስስር እና ተዛምዶ

የአስተዳደር ህግ ጽንስቱ ሆነ ውልደቱ ከህገ መንግስት እንደመሆኑ ከዚህ የህግ ክፍል ጋር ብዙ ባህርያትን ይጋራል፡፡ ሁለቱም የመንግስትና የግለሰብ ግንኙነትን በሚመራው ‘የህዝብ አስተዳደር ህግ’ ተብሎ በሚጠራው የህግ ክፍል ውስጥ ይመደባሉ፡፡ አብዛኛዎቹ የአስተዳደር ህግ ጥያቄዎች በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የህገ መንግስታዊነት ጥያቄዎችን ያስነሳሉ፡፡ የአስተዳደር ህግን በጥልቀት ለመረዳት ከተፈለገ ሂደቱ መጀመር ያለበት ህገ መንግስትን በማጥናት ነው፡፡ በምሁራኑ አንደበት ይኸው እውነታ እንዲህ ይገለፃል፡፡

የአስተዳደር ህግ ከህገ መንግስታዊ መሰረቱ ተለይቶ በደንብ ሊታወቅ ሆነ ሊጠና አይችልም፡፡

የአስተዳደር ህግ በህገ መንግስት ማስፈጸሚያ መሳሪያነቱ የዝምድናቸውን ገጽታ በሚገባ ለማወቅ ይረዳናል፡፡ በዚህ የተግባሪነት ሚናው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት ላይ የተቀመጡትን የህገ መንግስታዊነትና የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች እንዲሁም የግለሰቦች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በተጨባጭ እንዲረጋገጡ በማድረግ ህገ መንግስቱን በማስፈጸም ረገድ እንደ አንድ መሳሪያ ያገለግላል፡፡

እ.ኤ.አ በ1959 ዓ.ም. የጀርመን የፌደራል አስተዳደር ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት እንደተናገሩት የአስተዳደር ህግ ‘ተጨባጭ ህገ መንግስት’ ማለትም በተግባር የሚታይ ህገ መንግስት ነው፡፡a የአንድ አገር ህገ መንግስት በዋነኛነት የዜጐችን ሰብአዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፖለቲካዊ መብቶችና ነጻነቶች ይደነግጋል፡፡ የዜጐች መብት በሌላ ግለሰብ፣ ማህበር ወይም የንግድ ድርጅት ሊጣስ ይችላል፡፡ ትልቁ አደጋ ያለው ግን ከመንግስት በተለይም ከስራ አስፈፃሚው አካል በኩል ነው፡፡ መብቶች በሚገባ እንዲጠበቁ የመንግስት አስተዳደር ልኩ ተለይቶ በታወቀ የስልጣን ገደብ ውስጥ ሊከናወን ይገባል፡፡ ሆኖም ስልጣን ሁልጊዜ በህጉ መሰረት ግልጋሎት ላይ ይውላል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ የግድ በአግባቡ ሊገራና ልጓም ሊበጅለት ይገባል፡፡

የአስተዳደር ህግ የስልጣን መቆጣጠሪያ መሳሪያ ነው፡፡ በዚህ ተግባሩ ውጤታማ የስልጣን ቁጥጥር የዜጐች ህገ መንግስታዊ መብትና ነፃነት እንዳይጣስ ዋስትና ይሰጣል፡፡ መንግስቱን በተግባር እንዲተረጐም የሚደርገውም በዚህ መንገድ ነው፤ ስልጣንን በመቆጣጠር የዜጐችን መብት በተጨባጭ ማቀዳጀት፡፡

ይህ ሚናውን በሌሎች ህገ መንግስታዊ መርሆዎች አንጻርም ጎልቶ ይታያል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት በዋነኛነት ከሚደነግጋቸው የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች መካከል ግልፅነት፣ ተጠያቂነትና የህዝብ ተሳትፎ ይገኙበታል፡፡b ግልጽነት እውን የሚሆነው የመንግስት ባለስልጣናትና የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ለዜጐች መረጃ የመስጠት ግዴታቸው ከነዝርዝር አፈፃፀሙ ጭምር በህግ ተደንግጐ ሲገኝ ነው፡፡ ተጠያቂነት፤ ጠያቂውና ተጠያቂው ተለይቶ የተጠያቂነት ስልቱ በዝርዝር ህግ ካልተቀመጠ በተግባር አይረጋገጥም፡፡ የህዝብ ተሳትፎ እንዲሁ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች በሚሰጡት ውሳኔ በተለይም ደንብና መመሪያ ሲያወጡ በጉዳዩ ጥቅም ካላቸው ወገኖች ሀሳብና አስተያየት እንዲቀበሉ የሚያስገድድ የህግ ድንጋጌ ከሌለ የህዝብ ተሳትፎ በተጨባጭ አይታይም፡፡

ግልፅነትን፣ ተጠያቂነትንና የህዝብ ተሳትፎን በተግባር ለማረጋገጥ የሚወጡ ህጐች በአስተዳደር ህግ የሚካተቱ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ህጉ እነዚህ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች በተግባር እንዲረጋገጡ በማድረግ ህገ መንግስቱን ያስፈጽማል፡፡

በህገ መንግስትና በአስተዳደር ህግ መካከል ያለው የጠበቀ ግንኙነት ልዩነታቸው የላላ መሆኑን ያሳያል፡፡ ሊጠቀስ የሚችል ቀጭን ልዩነት ቢኖር የወሰን እና የህጎች የተፈጻሚነት ደረጃ (Hierarchy of Laws) ልዩነት ነው፡፡

ከወሰን አንፃር ህገ መንግስት አጠቃላዩን የመንግስት አወቃቀርና የሶስቱን የመንግስት አካላት ብሎም በፌደራልና በክልል መንግስታት ያለውን የስልጣን ክፍፍል ስለሚወስን በይዘቱ በጣም ሰፊ ነው፡፡ በአንፃሩ የአስተዳደር ህግ የአንደኛውን የመንግስት አካል ማለትም የስራ አስፈፃሚውን ስልጣን፣ ግዴታና ተግባር ብሎም የውሳኔዎቹን ህጋዊነት የሚመለከት ህግ ነው፡፡ በህግ አውጭው የሚወጣ ህግ እና ፍ/ቤቶች የሚሰጡት ውሳኔ ህገ መንግስታዊነት ከጥናት አድማሱ በላይ ነው፡፡ ስለሆነም ከወሰናቸው አንጻር ህገ መንግስት መስፋቱ የአስተዳደር ህግ መጥበቡ እንደ አንድ የልዩነት ነጥብ ተደርጐ ሊወሰድ ይችላል፡፡

ሁለተኛው ልዩነት የህጎች መሰላል (Hierarchy of Laws) ሲሆን በህጐች መካከል ያለውን የደረጃ ዝምድና ይመለከታል፡፡ ህገ መንግስት የአንድ አገር የበላይ ህግ እንደመሆኑ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና የአሰራር ልምዶች ዋጋ የላቸውም፡፡ የአስተዳደር ህግ በደረጃው ከህገ መንግስት ዝቅ ብሎ የሚገኝ እንደመሆኑ መቼም ቢሆን ከህገ መንግስቱ ጋር መጣጣም አለበት፡፡ ግጭት በተነሳ ጊዜ የበላይ የሆነው ህገ መንግስት ሁልጊዜ ተፈፃሚነት አለው፡፡
አብርሃም ዮሐንስ የህግ አማካሪና ጠበቃ
ይቀጥላል.........
#አለ_ህግ
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
ይርጋ መነሻ ጊዜ
ይርጋ መቆጠር የሚጀምርበት ጊዜ

የይርጋ ቀን መቆጠር የሚጀምረው ግዴታውን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነው ወይም ውሉ የሚሰጠው መብት ከተሰራበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ የሥራ ውል የተቋረጠበትና የስንብት ደብዳቤ የተሰጠበት ቀን ከተለያየ ይርጋ መቆጠር የሚጀምረው ደብዳቤው ለሠራተኛው ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ. 94931 ቅጽ 16፣ ፍ/ብ/ህ/ቁ. 1846

በፍትሐ ብሔር ስነ-ስርዓት ህጉ የሚገኙት የጊዜ ገደቦች አቆጣጠር የሚመራው በፍትሐ ብሔር ህግ ባሉት የጊዜ አቆጣጠር ደንቦች ነው፡፡ ጉዳዩ በሌለበት ታይቶ ውሳኔ የተሰጠበት ወገን ውሳኔው እንዲነሳለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 78/1/ መሰረት በአንድ ወር ውስጥ የሚያቀርበው ጥያቄ የአንድ ወር ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ውሳኔ መሰጠቱን ከተረዳበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ ሆኖም የመጀመሪያው ቀን ለይርጋው ጊዜ መቆጠር መነሻ አይሆንም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 76601 ቅጽ 13፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 78/1/

በወራሾች መካከል ውርስ እንዲጣራ አቤቱታ መቅረብ ያለበት በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሲሆን ይህም ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው አንደኛው ወራሽ የውርሱን ንብረት በእጁ ካደረገበት እንጂ ስመ ሀብቱን በስሙ ካዞረበት ጊዜ ጀምሮ አይደለም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 52407 ቅጽ 11፣ ፍ/ህ/ቁ. 1000/1/

ከውርስ ሃብት ጋር በተያያዘ ወራሽ የሆነና አካለ መጠን ያልደረሰ ሰው ላይ የይርጋ ጊዜ ሊቆጠር የሚገባው አካለ መጠን ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ. 57114 ቅጽ 11

ይዞታን አስመልክቶ ከሚነሳ የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ ጋር በተያያዘ ተፈፃሚ የሚሆነው የይርጋ ጊዜ መቆጠር ያለበት አቤቱታ አቅራቢው የይዞታ መብቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ካገኘበት ቀን ጀምሮ እንጂ አቤቱታ የቀረበበት ድርጊት መፈፀም ከጀመረበት ዕለት አይደለም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 60392 ቅጽ 11፣ ፍ/ብ/ህ/ቁ. 1140፣ 1149፣ 1146/1/፣ 1144/2/
Channel photo updated
የህግ የበላይነት

ብዙ ምሁራን በየፊናቸው በምርምርና ጥናት ባገኙት እውቀት ተመርኩዘው የህግ የበላይነት መርህ ምንነት፤ ይዘትና ፋይዳውን አስመልክቶ አያሌ ንድፈ ሀሳባዊ ትንታኔዎችን አቅርበዋል፡፡ በአገራችን ደግሞ አባቶችና እናቶች በልባቸው ከተጻፈው እውነትና ከልምድ ከቀዱት ቱባ እውቀት በመነሳት የህግ የበላይነትን ጽንስ ሀሳብ በአንድ አባባል እንዲህ ይገልጹታል፡፡

“በፍርድ ከሄደች በቅሎዬ ያለፍርድ የሄደች ዶሮዬ!”

የዚህ ተረትና ምሳሌ አንኳር መልዕክት ለጥቂት ሰዎች ብቻ የተገለጠ ሳይሆን በመላው ማህበረሰብ ዘልቆ የገባ ሀቅ ነው፡፡ እናም ይህን የህግ የበላይነት ፅንሰ ሓሳብን ጠንቅቆ ያወቀው ማህበረሰብ ህግ ሲጣስ፤ ፍትህ ሲጓደል፤ መብት ሲታፈን፤ ስርዓት አልበኝነት ሲነግስ፤ ማን አለብኝነትና በዘፈቀደኝነት ሲንሰራፋ፤ የግሉ የሆነችው ዶሮ ከህግ እና ከፍርድ ውጭ ሲቀማ ድምፁን አጉልቶ ይጮሀል፤ በህግ አምላክ! ይላል፡፡ የጮኸው የዶሮዋ ዋጋ አንገብግቦት አይደለም፡፡ የተወሰደችበት መንገድ እንጂ፡፡ በፍርድ ከሆነ፤ በህጉ መሰረት ከሆነ እንኳንስ ለዶሮ ለበቅሎም ቄብ አይሰጠውም፡፡

በህዝብ አስተዳደር፤ ፖለቲካ ሳይንስ፤ ህግ እና በሌሎችም የጥናት መስኮች የሚገኙ ምሁራን ስለ የህግ የበላይነት ምንነትና ይዘት ያላቸው ግንዛቤና አስተሳሰብ የተራራቀ ከመሆኑ የተነሳ ጽንሰ ሀሳቡ አሁንም ድረስ ቁርጥ ያለ ትርጓሜ አልተገኘለትም፡፡ አንድ የመስኩ ምሁር ይህንን ሀሳብ በማጠናከር እንዳብራራው፤

‘[T]he rule of law’, like ‘democracy’, has no single meaning: it is not a legal rule, but a moral principle, which means different things to different people according to their particular moral positions.a

በዚህ የተነሳ በተለያዩ አገራት የፖለቲካና የህገ መንግስት ስርዓት ውስጥ ይዘቱና አፈጻጸሙ የተለያየ አንዳንዴ የማይጣጣም መልክ በመያዙ መሰረታዊ እሳቤው ወጥነት ርቆታል፡፡

ለምሳሌ በእንግሊዝ አንደኛውና የህግ የበላይነት መገለጫ በመንግስትና በግለሰብ መካከል የሚነሱ ክርክሮች በመደበኛ ፍ/ቤቶች ብቻ መዳኘታቸው ነው፡፡ ያ ማለት በእንግሊዛዊ አይን ፈረንሳይ ውስጥ የህግ የበላይነት የለም እንደ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በፈረንሳይ በግለሰብና በመንግስት መካከል የሚነሱ ክርክሮች ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ የሚዳኙት ከመደበኛ ፍ/ቤት ትይዩ ራሱን ችሎ በተቋቋመ የአስተዳደር ፍ/ቤት ስርዓት አማካይነት ነው፡፡ በእንግሊዝ ሌላኛው የህግ የበላይነት ትርጉም የግለሰቦች መብትና ነፃነት መደበኛ ፍ/ቤቶች በቀረቡላቸው ተጨባጭ ጉዳዮች የሚሰጡት ውሳኔ ውጤት ነው የሚል ይዘት አለው፡፡ ይህ አስተሳሰብ በእንግሊዝ እውነት ቢሆንም የኛን አገር ጨምሮ የተጻፈ ህገ መንግስት ባላቸው እንደ አሜሪካ ባሉ አገራት የዜጐች መብቶችና ነፃነቶች በህገ መንግስቱ ላይ በጽሑፍ ይዘረዘራል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በሊብራል ዲሞክራሲ ስርዓት ውስጥ የህግ የበላይነት ማለት በህጉ መሰረት ከመግዛትና ከማስተዳደር ባለፈ የህጉ ይዘት (ለምሳሌ ፍትሐዊነቱ፤ የዜጐችን መብት ማክበሩ፣ ህጉ የወጣው ህዝብ ወዶና ፈቅዶ በመረጣቸው ተወካዮች መሆኑ ወዘተ…) ብሎም የገለልተኛና ነፃ ፍ/ቤቶች፤ የዲሞክራዊ ተቋማት፤ ነፃ ፕሬስ ወዘተ… መኖር ሁሉም በህግ የበላይነት ጽንስ ሀሳብ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ የሊብራል ዲሞክራሲ ጠበል አልተጠመቁም በሚባልላቸው መንግስታት (ለምሳሌ በቻይና) ጽንሰ ሀሳቡ ስልጣን ያለው አካል በሚያወጣቸው ህጐች መሰረት መግዛትና ማስተዳደር ላይ ብቻ የተገደበ ነው፡፡

የህግ የበላይነት መርህ የአስተዳደር ህግ (በተለይ በእንግሊዝ) የተተከለበት መሰረት ነው፡፡ በዚህ መርህ መሰረት ስራ አስፈፃሚው፣ የአስተዳደር መ/ቤቶች እና የአስተዳደር ጉባዔዎች የሚሰጡት ውሳኔ በህጉ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡ በመንግስት አስተዳደር ውስጥ ህጋዊነት የሚሰፍነው ስልጣን የተሰጠው ማናቸውም የመንግስት አካል የሚወስዳቸው እርምጃዎች፣ የሚፈጽማቸው ድርቶች፣ የሚሰጣቸው ውሳኔዎች እና የሚያወጣቸው ደንብና መመሪያዎች በህግ ጥላ ስር መሆናቸው ሲረጋገጥ ነው፡፡

የመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡት ውሳኔ በህግ ከተቀመጠው የስልጣን ክልል በላይ ከሆነ ውሳኔው የህግ የበላይነት መርህን እንደሚጥስ ጥርጥር የለውም፡፡ ህጋዊነት መከበሩን ማረጋገጥ ማለት አስተዳደራዊ ድርጊት፣ ውሳኔ፣ እርምጃ፣ ደንብና መመሪያ በህግ በተቀመጠው የስልጣን ገደብ ውስጥ መሆኑን አሊያም አለመሆኑን ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የመደበኛ የፍርድ ቤቶች ተግባር ነው፡፡ ይህንን ተግባር በሚያሳንስ መልኩ በፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ላይ በህግ አውጭው የሚደረግ ገደብ በውጤቱ የህግ የበላይነት መርህን ይሸረሽራል፡፡ ገደቡ በህግ የበላይነት መርህ ላይ ከሚፈጥረው አደጋ በተጨማሪ የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት ያጣብባል፡፡ በተለይም ይህ መብት ህገ-መንግስታዊ እውቅና የተሰጠው ከሆነ የፍርድ ቤቶችን ስልጣን መገደብ ዞሮ ዞሮ የዜጎችን ህገ-መንገስታዊ መብት መገደብ ነው፡፡

የህግ የበላይነት መርህ የአስተዳደር ህግ መሰረት ብቻ ሳይሆን ገደብ ጭምር እንደሆነ ማውሳት ያስፈልጋል፡፡ የውሳኔን ህጋዊነት ማረጋገጥ በይዘቱ ላይ መቆጠብን ያስከትላል፡፡ ፍ/ቤቶች የህግ የበላይነት በማስከበር ሚናቸው የአስተዳደራዊ ውሳኔዎች ይዘት እንዳያጣሩ ወይም በፖሊሲ ጥያቄዎች ጣልቃ እንዳይገቡ ይገድባቸዋል፡፡
አብርሃም ዮሐንስ የህግ አማካሪና ጠበቃ
ይቀጥላል.....................
#አለ_ህግ
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
የህፃናት መብት

ሕፃናት እንደ ማንኛውም ተፈጥሮአዊ ሰው መብት ያላቸው ሲሆን በሥነ-አዕምሮአዊ፣ ሥነ-ልቦናዊ፣ ማኅበራዊ ግንኙነት እንዲሁም አካላዊ ሁኔታ ምክንያት ተጨማሪ ጥበቃ እንደሚያስፈልጋቸው በዓለም አቀፍና ብሔራዊ ህግ ማዕቀፎች ተደንግጓል፡፡ በዚህ የንቃተ ህግ ፅሁፍ በአጠቃላይ መሰረትዊ የህፃናት መብቶች እና ህፃናትን በተመለከተ የተደነገጉ መርሆችን ለመዳሰስ ተሞክሯ፡፡

1. የህፃን ትርጉም

ለሕፃንነት የሕግ ትርጓሜ መስጠትን አስፈላጊ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል ዋነኛው የመብትና ግዴታ ወሰን (scope of rights and duties) ለማወቅ ስለሚያስችል ነው፡፡ እንዲሁም ሕፃናት ለአደጋ ተጋላጭ ከመሆናቸው አኳያ ልዩ ጥበቃ (special protection due to vulnerability) ስለሚያስፈልጋቸው ህፃናትን በመለየት ይህን ጥበቃ ለማድረግ ነው፡፡
ህፃን ማን ነው ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ አገራት ሕጎች የተለያየ ትርጓሜ ሰጥተዋል፡፡ ምንም እንኳ አንድ ወጥ የሆነ የሕፃን ትርጓሜ ባይኖርም ሕፃን የሚለው ቃል ብዙ አገራት ዕድሜን ግምት ውስጥ ያስገባ ትርጉም ይጠቀማሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር በአንዳንድ አገሮች ሕፃን ለሚለው ትርጓሜ ለመስጠት ማኅበራዊ አረዳድን (social construction of age) ግምት ውስጥ የሚያስገቡ ሲሆን ለምሳሌ በጉርምስና ወቅት የሚታዩ አካላዊ ለውጦች እና የድምፅ መጎርነን ከግምት ውስጥ ያስገባሉ፡፡

በዓለም አቀፍ የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀፅ 1 የተመለከተው ዕድሜን መሠረት ያደረገ ትርጉም ሲሆን “ሕፃን ማለት ማንኛውም ዕድሜው ከአሥራ ስምንት ዓመት በታች የሆነ የተፈጥሮ ሰው” እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ሆኖም በምን ጉዳይና ምን ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ ዝቅ ማድረግ ወይም 18 ዓመት ሳይሞላ ለአካለ መጠን መድረስ እንደሚቻል ባያስቀምጥም አገራት በሚያወጡት ሕግ መሠረት ከአሥራ ስምንት ዓመት በታች መውረድ የሚቻልበት አጋጣሚም እንዳለ በኮንቬንሽኑ ተገልጧል፡፡ በዚሁ መሰረት ለምሳሌ በኢትዮጵያ ለጋብቻ ሊባል ማለትም ከባድ ምክንያት ሲያጋጥም ተጋቢዎቹ ወይም ከተጋቢዎቹ የአንዳቸው ወላጆች ወይም አሳዳሪ በሚያቀርቡት ጥያቄ መሰረት ፍትህ ሚኒስትሩ ከመደበኛ የጋብቻ እድሜ (18 ዓመት) ከሁለት አመት ያልበለጠ ጊዜ በመቀነስ እንዲጋቡ ሊፈቅድ ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሕፃኑ ከሞግዚት አስተዳደር ነፃ እንደወጣ (emancipated) ይቆጠራል፡፡ ይህ የዕድሜ ጣራ መድረሻ (አሥራ ስምንት ዓመት) ከየት እንደሚጀምር በግለፅ የተደነገገ ነገር ባይኖርም በኮንቬንሽኑ መግቢያ ላይ እንደተገለፀው ከመወለድ በፊትም ማለትም በጽንስ ወቅትም ጥበቃ እንዳለ ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የአፍሪካ የሕፃናት መብቶች እና ደህንነት ቻርተር አንቀፅ 2 ሕፃን ለሚለው ትርጓሜ ሲሰጥ “ሕፃን ማለት ማንኛውም ዕድሜው ከአሥራ ስምንት ዓመት በታች የሆነ የተፈጥሮ ሰው ነው” በማለት ደንግጓል፡፡

በኢትዮጵያ ለሕፃን ያለውን ትርጉም ስንመለከት ሀገሪቱ ፌደራላዊ ስርዓት የምትከተል በመሆኑ እና የ1987 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራስያዊ ሪፐብሉክ ሕገ መንግሥት የፌደራል እና የክልል መንግሥታት የየራሳቸውን የቤተሰብ ሕግ እንዲያወጡ ስለሚፈቅድ የተለያየ የሕፃን ትርጓሜ ሊኖር የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ በፌደራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 215 መሠረት አካለ መጠን ያልደረሰ ሰው ማለት ጾታ ሳይለይ ዕድሜው አሥራ ስምንት ዓመት ያልሞላው ልጅ ነው፡፡

2. የህፃናት መብት መርሆዎች

ዓለም አቀፍ እና አገር አቀፍ ሕጎች የሕፃናት መብቶችን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል በማሰብ የተለያዩ መርሆዎችን አውጥተዋል፡፡ እነዚህ መርሆዎች የሕፃናት መብቶች ለማስከበር እና ማስተግበር ከፍተኛ አስተዋፅዖ አላቸው፡፡ ከእነዚህ መርሆዎች ዋነኛው የሆነው ለሕፃናት ጥቅምና ደህንነት ቅድሚያ መስጠት (Best interest of the child) የሚለው መርህ ነው፡፡ በዚህ ረገድ እ.ኤ.አ በ1959 የወጣው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሕፃናት መብቶች መግለጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕፃናት ጥቅም እና ደህንነት ቅድሚያ መስጠት የሚለውን መርህ አካቶ የወጣ ዓለም አቀፍ ሰነድ ነው፡፡ በመሆኑም ሕፃናት ነክ ውሳኔዎች ሲወሰኑ (ለምሳሌ ወላጆቻቸው የሚለያዩ ከሆነ ከማን ጋር መኖር እንዳለባቸው ሲወሰን) ውሳኔ ሰጭ አካላት ለሕፃናት ጥቅምና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት የሕግ ግዴታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተያያዘ ሁኔታ የኮንቬንሽኑ አራት ዋና ዋና መርሆዎች በሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን ውስጥ የተዘረዘሩትን ሌሎች መብቶች ለማስፈፀም እና ለመተርጎም የሚያገለግሉ ናቸው ፡፡

እነርሱም፣
• የእኩልነት መብት (The Non-discrimination clause) የኮንቬንሽኑ አንቀፅ 2
• ለህፃናት ጥቅምና ደህንነት ቅድሚያ መስጠት (The Best Interest of the Child) የኮንቬንሽኑ አንቀፅ 3)
• የመሳተፍ መብት (The Right to participation) ኮንቬንሽኑ አንቀፅ 12፣
• በሕይወት የመኖር እና የመልካም አስተዳደግ መብት (The Right to life, survival and development) የኮንቬንሽኑ አንቀፅ 6፣ ናቸው፡፡

3. መሰረታዊ የህፃናት መብቶች በኢትዮጵያ

የሀገራችን ህገ መንግስት ለህፃንነት ትርጉም ያልሰጠ ወይም የእድሜ ገደብ ያላስቀመጠ ቢሆንም የህፃናትን መብት ዝርዝር በአንቀፅ 36 ስር ደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት ማንኛውም ህፃን የሚከተሉት መብቶች አሉት፡-

1. በህይወት የመኖር መብት፣
2. ስምና ዜግነት የማግኘት መብት፣
3. ወላጆቹን ወይም በህግ የማሳደግ መብት ያላቸውን ሰዎች የማወቅና የእነሱንም እንክብካቤ የማግኘት መብት፣
4. ጉልበት ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፣ በትምህርት፣ በጤናውና በደህንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ስራዎች እንዲሰራ ያለመገደድ ወይም ከመስራት የመጠበቅ፣
5. በትምህርት ቤቶች ወይም በሕፃናት ማሳደጊያ ተቋሞች ውስጥ በአካሉ ከሚፈፀም ወይም ከጭካኔና ኢ-ሰብዓዊ ከሆነ ቅጣት ነፃ የመሆን መብት ናቸው፡፡

በተጨማሪም በህገ መንግስቱ እንደተደነገገው ህፃናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰዱበት ጊዜ በመንግስታዊ ወይም በግል በጎ አድራጎት ተቋሞች፣ በፍርድ ቤቶች፣ በአስተዳደር ባለስልጣኖች ወይም በህግ አውጪ አካላት የህፃናት ደህንነት በቀደምትነት መታሰብ አለበት፡፡ ወጣት አጥፊዎች በማረሚያ ወይም በመቋቋሚያ ተቋሞች የሚገኙ በመንግስት እርዳታ የሚያድጉ ወጣቶች በመንግስት ወይም በግል እጓለ ማውታን ተቋሞች (የህፃናት ማሳደጊያዎች) ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ከአዋቂዎች ተለይተው መያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ከጋብቻ ውጪ የተወለዱ ሕፃናት በጋብቻ ከተወላዱ ሕፃናት ጋር እኩል መብት አላቸው፡፡ እንዲሀም መንግስት ለእጓለ ማውታን ልዩ ጥበቃ እንደሚያደርግላቸው እና በጉዲፈቻ የሚያድጉበት ሥርዓት የሚያመቻቹና የሚያስፋፉ፣ ደህንነታቸውንና ትምህርታቸውን የሚያራምዱ ተቋሞች እንዲመሰረቱ እንደሚያበረታታ ይደነግጋል፡፡
በአጠቃላይ ህፃናት የሚከተሉት አለም አቀፍ መሰረታዊ መብች ሊጠበቁላቸው ይገባል፡፡
• የእኩልነት መብት:- በጾታ፣ በዘር፣ በጎሳ፣ በቋንቋ፣ በኢኮኖሚ አቋም፣ በብሔር ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት ወይም አድሎአዊ በሆነ በማንኛውም ሁኔታ ላይ በመመርኮዝ ልዩነቶች ሊደረጉ አይገባም፡፡
• መብላት እና መጠለያ የማግኘት መብት:- ሁሉም ልጆች ለትክክለኛው እድገታቸው አስፈላጊ የሆነውን ምግብ የማግኘት እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በሚኖሩበት ቤት የማግኘትና የመደሰት መብት አላቸው ፡፡
• የትምህርት መብቶች:- ሁሉም ልጆች ችሎታቸውን ለማዳበር እና የራሳቸውን የወደፊት ዕድል ለመፍጠር ትምህርት የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ምክንያቱም ለትክክለኛው ሥነ-ልቦናዊ፣ ስሜታዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገታቸው አስፈላጊ ነው፡፡
• የጤንነት መብት:- ልጆች ጤንነታቸውን ለመንከባከብ እና ለማቆየት እንዲሁም በሽታን ለመከላከል አስፈላጊ የሕክምና ክትትል እና እንክብካቤ ማግኘት አለባቸው፡፡ ወደ ጤናማ አዋቂዎች እንዲያድጉ ጥሩ ፈውስ የማግኘት መብት አላቸው፡፡
• በሕይወት የመኖር መብት፡- ሕፃናት ህይወታቸውን አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ነገሮች የመጠበቅ እና የመትረፍ (right of protection and survival) መብት አላቸው፡፡ እንዲሁም በቂ የኑሮ ደረጃ (adequate standard of living) የማግኘት መብት አላቸው፡፡

በአጠቃላይ ህፃናት በተለይ በእድሜያቸው ምክንያት ለተለያዩ አደጋዎች የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ስለሆነ መንግስት በሂደት (progressively) የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በፈቀደ መጠን የህፃናትን ደህንነት ለማስጠበቅ የህፃናትን መብት ለማክበር፣ ለመጠበቅ እና ለማሟላት ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
በንቃተ ሕግ፣ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት
#አለ_ህግ
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
The application has finished.
they have taken what they want.
Stop applying. Save your time.
#አለ_ህግ
#አለ_ስራ
#አለ_ህግ
#አለ_ችሎት
#አለ_ስራ
#አለ_ዜና
#አለ_ትምህረት
#አለ_ልዩ ልዩ
......................
የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ክሶች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች 🔴ሁሉም ሕጎች በአንድ🔴 All in one, for All.

አለ_ህግ፣ መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው።
contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.com

@lawsocieties

#አለ_ህግ

#Share #Share #Share #Share
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade 42.docx
43.2 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade.pdf
272.5 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade 42.docx
43.2 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade 4.pptx
118 KB