አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Happening right now...
LHR has organized a one and half days specialized capacity building training on the enforcement of socio-economic rights for practising lawyers at Azzeman Hotel, Addis Ababa.

Day-2
The participants continue to discuss in detail the protection of economic, social and cultural rights in the Ethiopian legal system. The protection of economic social cultural rights jurisprudence in Ethiopia and share their experiences on the topic. They also discuss the steps lawyers have to take to protect these groups of rights.


ሼር #Share @lawsocieties
🟩@lawsocieties
🟨@lawsocieties
🟥@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
🟢🟡🔴 ማስታወቂያ
የጥብቅና ፈቃድ ለማውጣት ለምትፈልጉ በሙሉ❗️❗️

የፌዴራል የጀመሪያ ደረዳ ፍ ቤት የጥብቅና ፈቃድ በፈተና ለማግኘ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮያዊ መመዝገብ የሚችል መሆኑን እንገልፃለን።

1. እውቅና ካለው _ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምርት ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ እና በህግ መያ ቢያንስ ሶስት (3) ዓመት ወይም በሕግ ዲኘሎማ የተመረቀና በሕግ ሙያ አምስት (5) ዓመት የሥራ ልምድ ያለው፣

2 ከኢትዮጵያ ውጪ ካለ ከፍተኛ የትምህርት ቋም በሕግ የመመሪያ ዲግሪ ያለውና በኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ ሙያ ለአምስት (5) ዓመት የሰራ፣

3. hሚሰራበት ተቋም የመልካም ስነ-ምግባር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ 4. በመጨረሻ ጊዜ ይሰራበት ክነበረበት ተቋም ተቋሙን ከለቀቀበት ጊዜ በፊት ባሉት 2 አመታት ዉስጥ በከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት ያልተቀጣ፣
5. የመመዝገቢያ 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/
6. የታደሰ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ

7. የትምህርትና "ሥራ ልምድ : ማስረጃ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ፣
8. ከግል መ/ቤት የሚቀርብ የሥራ ለምድ ግብር የከፈለበት ስለመሆኑ፣
9. በአማርኛ ያልተፃፉ ማንኛውም የሚቀርቡ ማረጃዎች በአማርኛ ተተርጉመው አንድ ላይ ማቅረብ፣
10.አዲሱ የትምህርት ፖሊስ በህግ ዲሎማ የተመረቀ ከሆነ የብቃት ማረጋገጫ ምዘና COC ተፈትኖ ያላፈበትን ውጤት ማቅረብ አለበት

ማሳሰቢያ፦

❖ የመመዝገቢያ ቀን መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ ም እስh መጋቢት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት፣
❖ የመመዝገቢያ ቦታ- ባንቢስ/ኡራኤል ቤተክርቲያን አካባቢ ፍትህ ሚኒስቴር ሕንፃ ጠበቆች አተዳደር ቢሮ 2ኛ ፎቅ
❖ የፈተና ኮድ የሚሰጥብት ቀን ከመጋቢት 15 እስከ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ጠበቆች አስተዳደር ቢሮ 2ኛ ፎት፣

* ፈተና የሚስጥበተ ቀንና ቦታ-መጋቢት 17 ቀን 2014 ዓ ም ከጥዋቱ 3.00 ሰአት ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን, ህንፃ አዳራሽ ውስጥ ይሆናል።

የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር

ሼር #Share @lawsocieties
🟩@lawsocieties
🟨@lawsocieties
🟥@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ጥበቃ በአዲሱ የንግድ ሕግ

በንግድ ማኅበራት አስተዳደር ውስጥ ከሚጠቀሱት ጉዳዮች አንዱ የአነስተኛ ባለአክሲዮኖች መብት ጥበቃ ነዉ፡፡ ሕግ በተለይም የንግድ ሕግ የባለአክሲዮኖችን መብትና ግዴታ ማስፈፀሚያ መሳሪያ እንደሆነ ሁሉ የአነስተኛ ባለአክሲዮኖች መብትንም የሚጠብቅ መሆን አለበት፡፡ ሀገራት ለአነስተኛ ባለአክሲዮኖች መብት ማስጠበቂያ ደንቦችን በንግድ ሕጎቻቸዉ ያካትታሉ፡፡ በሀገራችን አዲሱ የንግድ ሕግ ከተካተቱ አዳዲስ ጉዳዮች አንዱ የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ጥበቃ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ የአነስተኛ ባለአክሲዮኖች ምንነት እና በንግድ ማህበራት እንቅስቃሴ ውስጥ ለእነዚህ ባለአክሲዮች የሚጠበቁ መብቶች ተዳሰዋል፡፡

1. የአነስተኛ ባለአክስዮኖች ምንነት
በንግድ ማኅበራት አስተዳደር ዉስጥ አነስተኛ ባለአክሲዮኖች የሚለዉ ሐረግ አንድ ወጥ የሆነ ትርጉም የለዉም፡፡ አንድ ባለአክሲዮን ብቻዉን አነስተኛ ባለአክሲዮን ሊሆን ይችላል፡፡ ብቻዉን የንግድ ማኅበር ከግማሽ በላይ አክሲዮኖች የያዘ አንድ ባለ አክሲዮን ደግሞ ከፍተኛ (አብላጫ) ባለአክሰዮን ይሆናል፡፡ በተቃራኒዉ ደግሞ ከግማሽ በታች ያላቸዉ ብዙኃን ባለአክሲዮኖች በድምፅ ከተበለጡ አነስተኛ ባለአክሲዮኖች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የሀገራችን የንግድ ህግ ሲታይ በተለያዩ ክፍሎች ዉስጥ አነስተኛ ባለ አክሲዮኖች የሚለዉን ሀሳብ እንደ አዉዱ በተለያየ መንገድ ይፈታዋል፡፡ በአብዛኛዎቹ ክፍሎች ዉስጥ ከጠቅላላ ካፒታል አሥር በመቶ (10%) ያላቸዉን እንደ አነስተኛ ባለአክሲዮኖች ሲወስድ በአንዳንድ ክፍሎች ቢያንስ ሃያ በመቶ (20%) ያላቸዉን እንደ አነስተኛ ባለአክሲዮን በመዉሰድ ለመብት ማስጠበቂያ ድንጋጌዎች መፈጸም እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀምጣል፡፡ በሌሎች ድንጋጌዎች የአክስዮን መጠን ሳይጠይቅ ማንኛዉም ባለአክስዮን እንደ አነስተኛ ባለአክሲዮን የሚበቅባቸዉ ሁኔታዎች አሉ፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ አነስተኛ ባለአክሲዮን ማለት በማኅበሩ ያላቸዉ የአክሲዮን ድርሻ ከግምሽ በታች የሆነ ወይም ዝቅተኛ የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው ባለአክሲዮኖች ማለት ነዉ፡፡

2. አነስተኛ ድርሻ ላላቸው ባለአክሲዮኖች የሚደረግ የሕግ ጥበቃ እና የጥበቃው መነሻ
እንደ ሀገራችን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ሰዎች ለኢንቨስትመንት የሚሆን ተቀማጭ ገንዘብ ስለማይኖራቸው ዜጎች ያላቸውን ውስን ሀብት አስተባብሮ ወደ ሥራ ማስገባት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህ እንዲሳካ ደግሞ ዜጎች የቆጠቡትን ትንሽ ገንዘብ በንግድ ማኅበር ውስጥ ካስገቡ በኋላ ለምዝበራ እንዳይዳረጉ የሚከላከል ስርዓት መኖር አለበት።

የቀድሞዉ የንግድ ሕጋችን በማኅበራት ውስጥ አነስተኛ ድርሻ ይዘው የሚገቡትን ባለሀብቶች ከዘረፋ፣ ካልተገባ ጫና ወይም በደል ለመታደግ ያለሙ ድንጋጌዎች በበቂ ሁኔታ አላካተተም። አዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 364 ይህን ሁኔታ ለመለወጥ እና አነስተኛ ድርሻ ያላቸውን የኩባንያ አባላት ከምዝበራ እና ኢፍትሃዊ አሰራር ለመጠበቅ የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን አካቷል። በዚህ ረገድ ሕጉ ያደረጋቸው ለውጦች በሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው። እነዚህም፡-
1. ግልጽነትን ማስፈን፡- አንድ ኩባንያ ከኩባንያው ጋር ዝምድና ካላቸው ሌሎች ድርጅቶች ጋር ስለሚያደርጋቸው ውሎች አነስተኛ ድርሻ ያላቸው ባለአክሲዮኖች የተሟላ መረጃ እንዲያገኙ እና የጥቅም ግጭትን ለማስወገድ የሚረዱ በርካታ ድንጋጌዎች በህጉ ውስጥ የተካተቱ ሲሆን አንቀጽ 323፣ 324፣ 325፣ 406፣ 392፣ 393፣ 396፣ 503 እና 504ን መጥቀስ ይቻላል።

2. ተጠያቂነትን ማስፈን፡- የንግድ ማኅበር ሥራ አመራር በተለይ የዳይሬክተሮችን ኃላፊነት በማያሻማ መልክ የሚያስቀምጡ እና ተጠያቂነትን የሚያሰፍኑ አሰራሮችን ለመዘርጋት ያለሙ በርካታ ድንጋጌዎች በአዲሱ የንግድ ህግ ውስጥ ተካተዋል። በዚህ ረገድ አዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 308፣ 326፣ 327፣ 329፣ 339፣ 366(1)(2)፣ 367(2) 400 እና 406 ተጠቃሽ ናቸው።


3. በሥራ አመራር ውስጥ የማኅበርተኞችን ተሳትፎ ማጎልበት፡- አዲሱ የንግድ ሕግ ማኅበርተኞች በንግድ ድርጅታቸው አመራር ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚደነግጉ በርካታ ድንጋጌዎችን ተካተዋል፡፡ በዚህ ረገድ አዲሱ ሕግ አንቀጽ 312(3)፣ 316፣ 354፣ 362፣ 405፣ 406፣ 453፣ 520 እና 529ን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። እያንዳንዱ የአክሲዮን ማኅበር ድረ-ገጽ እንዲኖረው እና በድረ-ገጹም ላይ የማኅበርተኞችን ንቁ ተሳትፎ ለማረጋገጥ የሚረዱ መረጃዎች እንዲሰጥ የሚደነግጉት አንቀጽ 492-494 ይህን ያሳያሉ።

3. የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ማስጠበቂያ መንገዶች
የንግድ ሕጉ ያስቀመጣቸዉ የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ማስጠበቂያ ድንጋጌዎች በሁለት ዓይነት ሊታዩ የሚችሉ ሲሆኑ አነዚህም ጉዳትን ተከላካይ /Preventive/ እና የማስተካከያ /restorative/ ናቸዉ፡፡ ጉዳት ተከላካይ ድንጋጌዎች አነስተኛ ባለአክስዮኖች ላይ የመጨቆን ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ ውሳኔዎችን ከመወሰናቸዉ በፊት አነስተኛ ባለአክስዮኖች እንዲሰማሙ በመደንገግ ዉሳኔዉን ከመፈፀም እንዲያግዱት ያስችላቸዋል፡፡ በሌላ በኩል የማስተካካያ ድንጋጌዎች ጉዳት ከደረሰ በኋላ የማስተካከያ መንገዶችን ይደነግጋሉ፡፡ ለምሰሌ በፍርድ ቤት ከሶ ካሳ የማስከፈል መብት ከእነዚህ የሚመደብ ነዉ፡፡ ከጉዳት በኋላ በፍርድ ቤትም ይሆን በአስተዳደራዊ መንገድ ማስተካከል ከባድ ስለሚሆን ችግሮችን አስቀድሞ መከላከል ከማስተካከል የተሻለ ይሆናል፡፡

ማንኛዉም የድምፅ የበላይነትን በመጠቀም ከፍተኛ ባለአክስዮኖች አነስተኛ ባለአክስዮኖችን አግልለዉ የማኅበሩን ሀብት ለግላቸዉ የሚጠቀሙበት አሰራር በአነስተኞች ላይ በደል ማድረስ ነዉ፡፡ አነሰተኛ ባለአክስዮኖች በኩባንያዉ ጉዳዮች ላይ እንዳይሳተፉ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የሚያገል አሰራር የባለአክስዮኖችን መብት የሚጥስ ነዉ፡፡ ለአነሰተኛ ባለአክስዮኖች የመብት ጥሰቶች ህጎች የተለያዩ ዓይነት መፍትሔዎች የሚሰጡ ሲሆኑ አንዳንዶቹ በቀጥታ የመክሰስ (የማስተካከያ እርምጃ የመዉሰድ) መብት ሲሰጡ ሌሎች ደግሞ በተዘዋዋሪ ይከለክላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሕግ በአብዛኛዉ ለእንደነዚህ ያሉ የመብት ጥሰቶች የሚሰጠዉ ከአሁን በፊት ያለዉ ተዘዋዋሪ ነበር፡፡ በአዲሱ የንግድ ሕግ ግን በቀጥታ የመክሰስ (የማስተካከያ እርምጃ የመዉሰድ) መብትን ሰጥቶ እናገኘዋለን፡፡ በአብዛኛዉ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቶ በጉባዔዉ የመብት ጥሰት ያስከተሉ ዉሰኔዎችን ዉድቅ ማስደረግ ወይም በዳይሬክተሮች ቦርድ አማካኝነት ጉዳት በማኅበሩ ላይ ደርሶም ከሆነ እንዲከሰሱ በጠቅላላ ጉባዔዉ አሰወስኖ መክሰስ ነዉ፡፡

4. የጉባዔ አካሄድ እና የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት
በጠቅላላ ጉባዔ አካሄድ ድንጋጌዎች ዉስጥ የአነስተኛ ባለአክስዮኖችን መብት የሚያስጠብቁት አሰራሮች በብዙ ሕጎች ሰፍረዉ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ዋና ዋናዎቹ በደብዳቤ በድምፅ የመስጠት መብት፣ ጉባዔ በሚደረግበት ጊዜ አክስዮንን በማኅበሩ የማስቀመጥ ግዴታ አለመኖር፣ የድምር ድምፅ /Commulative Voting/ አሰራር እና አንድ አክስዮን አንድ ድምፅ የሚለዉ አሰራር በንግድ ህጋችን በቁጥር 383 (2) ስር ተመልክቷል፡፡ ይህ ንዑስ ቁጥር እያንዳንዱ አክስዮን አንድ ድምፅን ይሰጣል ይላል፡፡ የዚህ ድንጋጌ ዓላማ የተወሰኑ አክስዮኖች እጥፍ ድምፅ የሚያስገኙ፣ የሌሎች ደግሞ አንድ፣ የከፊሎቹ ግማሽ ወዘተ… በሚል ዓይነት ልዩነት እንዳይፈጠር ለመከላከል ነዉ፡፡ ስለዚህ በአንዳንድ አባላት የተለየ ድምፅ
የሚያስገኝ ልዩ አክስዮን ሊኖራቸዉ አይችልም፡፡ በቦርድ አባላት ምርጫ ወቅት የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ማስጠበቂያ አሰራር የድምር ድምፅ አሰራር ነዉ፡፡ ይህ ግን በሕጋችን በግልፅ የተቀመጠ ደንብ አይደለም፡፡ ነባሩ ንግድ ሕግ ቀጥር 352 ስለተመጣጣኝ ዉክልና የሚናገር ሲሆን በግልፅ የድምር ድምፅ አሰራር ግን አይደነግግም፡፡

ሌላዉ ከጠቅላላ ጉባዔዉ ዉሳኔ ጋር በተዘዋዋሪ የሚያያዘዉ እና የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ላይ ተፅዕኖ ሊፈጥር የሚችል ጉዳይ አዳዲስ አክስዮኖች ሲወጡ እያንዳንዱ አባል ባለዉ ድርሻ መጠን የመግዛት መብት ነዉ፡፡ ይህ በቁጥር 345 (4) እና በቁጥር 470(1) ላይ የተቀመጠ መርህ ነዉ፡፡ የዚህ መርህ ዓላማ በማኅበሩ ዉስጥ ያለዉን የይዞታ ስብጥር ማስጠበቅ ሲሆን ጠቃሚነቱ በማኅበሩ ዉስጥ ያለዉ የኃይል ሚዛን እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡

5. አነስተኛ ባለአክስዮኖች ከኦዲትና ቁጥጥር አንፃር ያላቸዉ መብቶች
ከኦዲት ሥራ ጋር የተያያዘ የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብቶች በአዲሱ የንግድ ሕግ ዉስጥ ተካተዋል፡፡ እነዚህም በቁጥር 343(2) እና በቁጥር 355 ላይ የተቀመጡት ድንጋጌዎች ናቸዉ፡፡ "ከማኅበሩ ዋና ገንዘብ ዉስጥ ቢያንስ 20% ያለዉ ባለአክስዮን (ባለአክስዮኖች) ራሳቸዉ የመረጡትን የውጭ ኦዲተር መሾም ይችላሉ" በማለት የአነስተኛ ባለአክስዮኖች የራሳቸዉን ኦዲተር የመሾም መብት እንዳላቸዉ ይናገራል፡፡ ይህን መብት አነስተኛ ባለአክስዮኖች ከተጠቀሙበት በማኅበሩ ዉስጥ ቢያንስ ሁለት ኦዲተሮች (በጠቅላላ ጉባዔዉ የሚሾምና በአነስተኛ ባለአክስዮኖች የሚሾም) ይኖራሉ ማለት ነዉ፡፡ ይህ ኦዲተሮች ለዳይሬክተሮች ወይም ለአብላጫ ባለአክስዮኖች በመወገን ሊፈጠሩ የሚችሉትን አደጋ ይቀርፋል ተብሎ ይታመናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቁጥር 355 ላይ ነፃ ኦዲተር እንዲሾም ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወይም አግባብ ያለዉ ሌላ የመንግስት መስሪያ ቤት ማመልከቻ ስለማቅረብ ይናገራል፡፡ የማኅበሩ ሥራ አመራር አነስተኛ የአክስዮን ድርሻ ያላቸዉን ማኅበርተኞች ወይም ማኅበሩን በሚጎዳ አኳኋን መከናወንና አለመከናወኑን መርምረዉ ሪፖርት የሚያቀርቡ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ኤክስፐርቶች መሾም አለበት፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት ከማኅበሩ ካፒታል አስር በመቶ (10%) ያለዉ (ያላቸዉ) ባለአክስዮኖች ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴሩ አቤቱታ ማቅረብና ማኅበሩ ኦዲት እንዲረግ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ከኦዲት ስራ ጋር የተያያዙ የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ቀላል አይደሉም፡፡ በማኅበሩ አስተዳዳሪዎች ወይም በከፍተኛ ባለ አክስዮኖች የሚደርስባቸውን የመብት ጥሰት ለመግታት እና መብታቸውን ለማስከበር አጅግ ጠቃሚ ናቸዉ፡፡

6. አክስዮን ሸጦ የመውጣት የአነስተኛ ባለአክሲዮኖች መብት
በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 292 መሰረት የማህበሩን ዋና ገንዘብ ዘጠና በመቶ የሚወክለ አክስዮኖች በአንድ ጊዜ በማህበርተኛ የተያዙ እንደሆነ አነስተኛ ባለአክስዮኖች ማህበርተኛው አክስዮኖቻቸውን እንዲገዛቸው የመጠየቅ መብት አላቸው። ጥያቄ አቅራቢው ባአአክስዮን አክስዮኖቹ ስለሚገዙበት ሁኔታ በተለይም የአክስዮኖቹን ዋጋ የንግድ ሕግ ስለወሰነበት መንገድ መረጃ ከጥያቄው ጋር ማቅረብ አለበት። ጥያቄ የቀረበለት ማህበርተኛ የቀረበለትን ዋጋ ያልተቀበለ እንደሆነ ማህበሩ በተመዘገበበት ቦታ ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት የአክስዮኖቹን ዋጋ የሚወስን ባለሞያ መሾም አለበት። አክስኖቹን ለመሸጥ ጥያቄ ያቀረበው ባለአክሲዮን የአክሲዮኖቹን ዋጋ ለመወሰን የወጣውን ወጪ መሸፈን አለበት። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አክስዮን እንዲገዛ ጥያቄ የቀረበለት ማህበርተኛ የሰጠው ዋጋ ተማኙ ባለሞያ ከወሰነው ያነሰ እንደሆነ ወጪውን በከፊል ወይም በሙሉ እንዲሸፍን ፍርድ ቤቱ ሊያዘው ይችላል፡፡

በአጠቃላይ የአነስተኛ ባለአክሲዮኖች መብት መጠበቅ የማኅበሩን ህልውና መጠበቅ ነዉ፡፡ ይህም የማኅበሩን መልካም አስተዳደር የተሳካና የንግድ አላማውን ዉጤታማ ያደርገዋል፡፡ በዚህ የተነሳ አነስተኛ ባለአክስዮኖች ከሌሎች ከፍተኛ ድርሻ ካላቸው ባለአክስዮኖች፣ ከዳይሬክተሮች ቦርድ፣ ከጠቅላላ ጉባዔዉ እና በአዲተሮች አማካኝነት ከሚሰነዘሩ ያልተገቡ ጫናዎችና የመብት ጥሰቶች መጠበቂያ መንገዶች በአዲሱ የንግድ ሕግ ተደንግገዉ ይገኛሉ፡፡
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች
____

የጤና ሚኒስቴር ከከተኛ ትምህርት ተቋማት በህክምና፣ ነርሲንግ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ፣ ጤና መኮንን፣ ሚድዋይፈሪ፣ ፋርማሲአንስቴዥያ፣ ዴንታል ሜድስን እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ #ለተመረቁ ባለሙያዎች በሚያዝያ 2014 ዓ.ም የብቃት #ምዘና #ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የፈተናው ምዝገባ ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም የሚካሄድ ስለሆነ ተመዛኞች hple.moh.gov.et ላይ በመግባት አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃ በማያያዝ online እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

1) ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቃችሁ ተመዛኞች ከምዝገባ በፊት የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ህጋዊነትና ትክክለኛነት በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን (የቀድሞው የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጄንሲ-HERQA) በኩል ማረጋገጥ (Authenticate ማስደረግ) እና ስማችሁ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወደ ተቋማችን እንዲተላለፍ ማድረግ ይጠበቅባችኋል፡፡

2) ከዚህ ቀደም የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን Authenticate ያስደረጋችሁ እና ስማችሁ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወደ ተቋማችን የተላለፈላችሁ ተመዛኞች ድጋሚ Authenticate ማስደረግ አይጠበቅባችሁም፡፡

3) ምዝገባው ለሁሉም ተመዛኞች (የመንግስትም ሆነ የግል ተቋም ተመራቂዎች) online የሚካሄድ ሲሆን online ያልተመዘገበ ተመዛኝ ለፈተና መቀመጥ የማይችል መሆኑን እናሳስባለን፡፡

4) የonline ምዝገባችሁን አጠናቃችሁ Submit ካላችሁ ከ 72 ሰዓት (3 ቀናት) በኋላ ወደ ሲስተሙ በመመለስ ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) መዝግባችሁ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
#Share ለሁሉም ጤና.
የመክሰር ሕግ በኢትዮጵያ

በአሁኑ ጊዜ በኪሳራ ምክንያት የንግድ ድርጅትን መዝጋትና ንብረቱን ሸጦ ለገንዘብ ጠያቂዎች ማከፋፈል የመጨረሻ እንጂ የመጀመርያ አማራጭ አይደለም። ይህ ሀሳብ በሀገራችን አዲሱ ንግድ ህግ አንድ የንግድ ድርጅት ኪሳራ ሲገጥመው ከተቻለ ድርጅቱን ለማትረፍ፣ ካልተቻለም የተገኘውን ያክል ንብረት ከብክነት በመታደግ ለገንዘብ ጠያቂዎች በፍትሐዊ መንገድ ለማከፋፈል ስለሚቻልበት ሁኔታ የሚደነግጉ የኪሳራ እና የመጠባበቂያ ስምምነትን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ስር ተካቶ ይገኛል፡፡ ይህ ጽሁፍ ስለ መክስር ሥነ ሥርዓት እና አፈፃፀሙን የሚዳስስ ነው፡፡

የመክሰር ትርጉምና ታሪካዊ አመጣጥ

የመክሰር ህግ ታሪካዊ አመጣጥን ዕድገቱ ከሰው ልጆች የግብይት ስርዓት ማደግ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንደሆነና ከጥንት ሮማውያን ጀምሮ ቀስ በቀስ የሀቀኛ ተበዳሪ መክሰርንና ለሌላ ቅጣት ከመዳረግ ይልቅ ዕዳው በንብረቱ ላይ እንዲፈፀም የማድረግ እና የገንዘብ ጠያቂዎችን የንብረት መብት ለማስጠበቅ ታስቦ የመጣ የሕግ ማዕቀፍ መሆኑ ይገለፃል፡፡ የመክሰር ህግ የራሱ የሆነ ጤናማ የኢኮኖሚ ግንኙነት የመፍጠርና ግንኙነቱ ሲደፈርስም ስርዓት ባለው መንገድ አንዱ የሌላውን ሀብት በመውሰድ እንዳይበለፅግና ሁሉም በሀብት ላይ ያለውን የተጠቃሚነት መብቱን እንዲሰራበት ለማስቻል የሚወጣ ሕግ ነው፡፡

የመክሰር ትርጉምን በሚመለከት የተለያዩ ፃህፍት እየተረጎሙት የመጡ ሲሆን ለግንዛቤ ይረዳን ዘንድ እነዚህ ቀጥሎ ያለዉን ትርጓሜ ለማስፈር ተሞክሯል፡፡ የሀገራችን የ1952 ቱ የንግድ ሕግ ቁጥር 969 ስለመክሰር የሚያስፈልግ ሁኔታ በሚል ስር “ማንኛውም ከንግድ የተያያዘውን ዕዳውን መክፈል ያቋረጠና መክሰሩ በፍርድ የተወሰነ ሁሉ የከሰረ ሆኖ የሚቆጠር ነው” በማለት ይደነግጋል፡፡ ከዚህ ትርጓሜ መገንዘብ እንደሚቻለው መክሰር ዕዳን ለመክፈል ካለመቻልና ይሄውም በፍርድ ቤት ከሰሯል የሚል ውሳኔ ሲሰጥበት አንድ ሰው ከስሯል ሊባል እንደሚችል ነው፡፡ በሌላ አባባል አንድ ሰው ዕዳውን መክፈል አለመቻሉ ብቻ እንደከሰረ እንደማያስቆጥረውና ከስሯል ብሎ የመወሰን ስልጣን ለመደበኛ ፍርድ ቤት የተሰጠ መሆኑን ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ብዙ አገሮች መክሰር “Bankruptcy” ከንግድ ጋር ብቻ ተያይዞ መታየት የለበትም ከሚል አመለካከት በመነሳት መክሰር በማንኛውም ዕዳውን ለመክፈል ባልቻለ ግለሰብም ተፈፃሚነት እንዲኖረው የሚያስችል ህግ በማውጣት ላይ ናቸው፡፡

የመክሰር ህግ ተፈፃሚነት

የተለያዩ አገሮች የተለያዩ የመክሰር ህግ (Bankruptcy Law) ያላቸው ሲሆን እንደ አካሄድም የተለያየ አሰራርን የሚከተሉ ናቸው፡፡ በአንዳንድ ሀገራት የመክሰር ህግ ተፈፃሚነት እስከ ግለሰብ የሚዘልቅ ነው፡፡ በሌሎች ሀገራት የህግ ማዕቀፍ የተወሰኑ ልዩነቶችን ብቻ በመፍጠር የመክሰር ህግን በግለሰቦች፣ ነጋዴዎችም ሆኑ ነጋዴ ባልሆኑ ላይ ተፈፃሚነት ያለው ነው፡፡ የሀገራችን ህግ ሲታይ አዲሱ የንግድ ህግ ስንመጣ በዚህ ህግ አንደኛ መፅሐፍ በቁጥር 5 መሰረት ነጋዴ በሆኑ ሰዎችና በዚህ ህግ አንደኛ መፅሐፍ በቁጥር 234 መሰረት የእሽሙር ማህበር ከሆኑት በቀር በንግድ ማህበሮች ሁሉ ላይ ተፈፃሚዎች ይሆናሉ፡፡ ይህ ማለት ግለሰቦች ሆነው በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 5 ላይ የተዘረዘሩ ተግባራትን የሚያከናውኑ ከሆነ ከእሽሙር ማህበር በስተቀር ሌሎች የንግድ ማኅበራት በመክሰር ህግ የሚዳኙ መሆናቸውን የሚደነግግ ነው፡፡

የመክሰር ሥነ-ሥርዓት ስለ መክፈት

በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 705 መሰረት የመክሰር ሥነ ሥርዓት የሚከፈተዉ ክፍያዎችን ያቋረጠ ባለዕዳ አቤቱታ ሲያቀርብ ነዉ፡፡ ባለዕዳዉ በዚህ መጽሐፍ ርዕስ ሦስት መሰረት መልሶ የማደራጀት ሥነ-ሥርዓት ለመክፈት አስቀድሞ አቤቱታ ያቀረበ ካልሆነ በስተቀር ክፍያዎችን ያቋረጠዉ ባለዕዳ በጣም ቢዘገይ በ45 ቀናት ዉስጥ የመክሰር ሥነ-ሥርዓት ለመክፈት ለፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብ አለበት፡፡ ይህ ግዴታ በኅብረት የሽርክና ማኅበር ዉስጥ በእያንዳንዱ ማኅበርተኛ ላይ እንዲሁም ሁለት ዓይነት ኃላፊነት ባለበት የሽርክና ማኅበር ዉስጥ ኃላፊነታቸዉ ባልተወሰነ ማኅበርተኞች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ጊዜው ያልሞላዉ እና የኢኮኖሚ ወይም የፋይናንስ ችግር በተጨባጭ ያጋጠመዉ ወይም ያጋጥመዋል ተብሎ የሚጠበቅ ባለዕዳ ሲያመለክት ብቻ ነዉ፡፡ ባለዕዳዉ የቅርብ ጊዜ የሒሳብ መግለጫዎችን፣ የገንዘብ ችግሮችን ሁኔታ እና የሚፈቱበትን መንገድ የሚያስረዳ ጽሁፍ እንዲሁም የገንዘብ ፍሰት ቅድመ ትንበያ ኪሳራን ለሚመለከተዉ ፍርድ ቤት የሚያቀርብ ሲሆን ፍርድ ቤቱ አስፈላጊ ናቸዉ ብሎ የሚያምናቸዉን ሌሎች ማናቸዉም ሰነዶች እና መረጃዎች ባለዕዳዉ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሊሰጥ ወይም እንደባንኮች እና የታክስ ባለሥልጣን አካላት ያሉ 3ኛ ወገኖችን እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡ አስገዳጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ሕጎች እንደተጠበቁ ሆነዉ ዕዳን መልሶ የማዋቀር የባለዕዳዉን ንብረቶች እና እዳዎች ወይም ሌላ ማንኛዉንም የባለዕዳዉን የካፒታል መዋቅር ክፍል አወቃቀር፣ ሁኔታዎች ወይም መዋቅር መቀየርን ወይም የንግድ ሥራዉን ንብረቶች ወይም ክፍሎች ወይም አጠቃላይ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴዉን በመንቀሳቀስ ላይ እንዳለ የንግድ ሥራ መሸጥን እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ ማናቸዉንም የሥራ ሂደት ለዉጦችን ማድረግን ወይም ከእነዚህ ዉስጥ የተወሰኑትን ወስዶ ማቀናጀትን ሊያካትት ይችላል፡፡

የመክሰር ሥነ-ሥርዓት በማን ይከፈታል

• ከባለዕዳዉ ጋር በአንድነትና በተናጠል ኃላፊ የሆኑ ሰዎች፣
• በባለዕዳዉ ላይ ጊዜዉ የደረሰ እና መከፈል ያለበት የክፍያ ጥያቄ ያላቸዉ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ገንዘብ ጠያቂዎች፣
• ከመክሰር ሥነ-ሥርዓት ዉጭ ባለዕዳዉን ንብረት እንዲያጣራ የተሾመ ንብረት አጣሪ፣
• ባለዕዳዉ የንግድ ሥራ ማቋረጡ ባለዕዳዉን ከሚመለከት የወንጀል ሥነ ሥርዓት ግልጽ በሚሆንበት ጊዜ ማንኛዉም ዐቃቤ ሕግ፣አቤቱታ በሚያቀርቡበት ጊዜም እንዲሁ ሊከፈት ይችላል፡፡
• በተጨማሪም በባለዕዳዉ ላይ በመካሄድ ላይ ባለ ሥነ-ሥርዓት የተነሳ ባለዕዳዉ ክፍያዎችን ያቋረጠ መሆኑ ግልጽ በሚሆንበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ በራሱ ተነሳሽነትም የመክሰር ሥነሥርዓት ሊያስጀምር ይችላል፡፡ ባለዕዳዉ ክፍያዎችን ያቋረጠ መሆኑን ያረጋገጠዉ ፍርድ ቤት ጉዳዩን በዚህ መጽሐፍ መሰረት የመክሰር ፍርድ ለመስጠት ሥልጣን ወዳለዉ ፍርድ ቤት ይልካል፡፡

ስለ መክሰር የሚሰጥ ፍርድ

ለመጀመሪያ ጊዜ ጉዳዩ በሚሰማበት ጊዜ ወይም አግባብ በሚሆንበት ጊዜ የኪሳራ መርማሪዉ ሪፖርት ሲደርሰዉ ፍርድ ቤቱ፡-
 ባለዕዳዉ የከሰረ መሆኑን ያዉጃል፣
 ተቆጣጣሪ ዳኛዉን ይሾማል፣
 የመክሰር ሥነ-ሥርዓትን ለማከናወን የከሰረዉን ሰዉ ንብረት ጠባቂ ይሾማል፣
 ክፍያዎች የተቋረጡበት ቀን መልሶ በማደራጀት ሥነ ሥርዓት ዉስጥ ያልተወሰነ ከሆነ ክፍያዎች የተቋረጡበትን ቀን ይወስናል፡፡

የመክሰርን ሥራ የሚያስፈጽሙ ሰዎችና አባላት

 ፍርድ ቤት- የመክሰር ሥነ-ሥርዓትን በመክፈት ረገድ ፍርድ ቤት ሥልጣን እንዳለዉ ከአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 604 እና አንቀጽ 715 መሰረት መረዳት ይቻላል፡፡
 ተቆጣጣሪ ዳኛ- ስለተቆጣጣሪ ዳኛዉ ሹመት እና ሥልጣን አዲሱ የንግድ ሕግ 716 እና 717 ን መመልከት ይቻላል፡፡
 የከሰረ ሰዉ ንብረት ጠባቂ- በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 718 መሰረት ፍርድ ቤቱ የመክሰር ሥነ ሥርዓት እንዲከፈት በሚሰጠዉ ፍርድ ዉስጥ አንድ የከሰረ ሰዉ ንብረት ጠባቂ ይሾማል፡፡ በሥነ-ሥርዓቱ ወቅት በማናቸዉም ጊዜ የከሰረዉ ሰዉ ንብረት ጠባቂ በማንኛዉም ገንዘብ ጠያቂ፣ በገንዘብ ጠያቂዎች ኮሚቴ ወይም በዐቃቤ ሕግ በሌላ እንዲተካ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ፍርድ ቤቱም በራሱ ሥልጣን የከሰረዉ ሰዉ ንብረት ጠባቂዉን በሌላ ሊተካ ይችላል፡፡ የከሰረሰዉ ንብረት ጠባቂ ሥልጣን እና ግዴታዎችም በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 720 ላይ ተመልክቷል፡፡
 የገንዘብ ጠያቂዎች ኮሚቴ- ተቆጣጣሪ ዳኛዉ የመክሰር ሥነ ሥርዓት በተከፈተ በ10 ቀናት ዉስጥ ከፍተኛ መጠን ያላቸዉ የክፍያ ጠያቂዎች ካላቸዉ የገንዘብ ጠያቂዎች መካከል 5 አባላትን የያዘ የገንዘብ ጠያቂዎች ኮሚቴ እንደሚያቋቁም በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 722 ላይ ሰፍሯል፡፡ የኮሚቴዎች መብትና ግዴታም በዚሁ ሕግ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
 ዐቃቤ ሕግ- በመክሰር ሥነ ሥርዓት ዉስጥ ዐቃቤ ሕግ ሥልጣን ያለዉ ሲሆን ይህን ሥነ ሥርዓት ከማስፈጸም ጋር ግንኙነት ያላቸዉ ማናቸዉንም የባለቤትነት ማረጋገጫዎች መዛግብትና ሰነዶች ተቆጣጣሪ ዳኛዉ እንዲቀርበለት የማዘዝ መብት በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 724 መሰረት አለዉ፡፡ እንዲሁም የዐቃቤ ሕግ መብቶች በዚሁ ሕግ አንቀጽ 740 ሥር ሰፍሮ ይገኛል፡፡

የመክሰር ሥነ ሥርዓት የሚዘጋባቸዉ ምክንያቶች

በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 696 መሰረት የመክሰር ሥነ ሥርዓትን መልሶ መክፈት (እንደገና እንዲጀመር ለፍርድ ቤቱ ማመልከት) መቻሉ እንደተጠበቀ ሆኖ የመክሰር ሥነ ሥርዓት በሚከተሉት ምክንያቶች ሊዘጋ ይችላል፡-
 ከንብረት ማጣራት የተገኘዉን ገንዘብ ጨርሶ በማከፋፈል፣
 የሚበቃ ንብረት ባለመኖሩ እና
 ከንብረቱ የሚፈለግ ዕዳ ባለመኖሩ ሲሆኑ 2ኛ እና 3ኛ ምክንያቶች ዝርዝራቸዉ በዚሁ ሕግ ከአንቀጽ 795 እሰከ 797 ድረስ ተደንግገዉ ይገኛሉ፡፡

የከሰረን ሰው ነፃ ስለመደረግ (Discharge)

ነባሩ የንግድ ሕግ የሚከስሩ ነጋዴዎች ከዕዳ ነፃ የሚወጡበት የሕግ ድንጋጌ አላካተተም። በዚህም ምክንያት ብዙ ነጋዴዎች የኪሳራን ሥነ-ሥርዓት ፈቅደው እንዳያመለክቱ ሊያደርግ ችሏል። ዘመናዊ የሆኑ የኪሳራ ሕጎች ንፁህ ነጋዴዎች በተወሰነ መልኩ የኪሳራ ሥነ-ሥርዓቱ ከተዘጋ በኋላ ነፃ የሚሆኑበትን ሁኔታ ይደነግጋሉ። አዲሱ የንግድ ህጋችን ነጋዴዎች የኪሳራ ሥነ-ሥርዓቱ በሕጉ መሰረት ካበቃ በኋላ ከዕዳ ነፃ የሚሆኑባቸውን የሕግ ድንጋጌዎች በመፅሐፍ ሦስት በርዕስ 5 አንቀጽ 799 ሥር አስቀምጧል። በዚህም መሰረት አንድ የኪሳራ ውሳኔ የተላላፈበት ነጋዴ የኪሳራው ብይን ከተሰጠበት ቀን አንስቶ ከሶስት ዓመት በኋላ ከዕዳ ነፃ ለመሆን ለፍ/ቤት ማመልከት እንደሚችል በአዲሱ የንግድ ሕግ ተካቷል።

ይህ መብት በዘፈቀደ ለሁሉም የሚሰጥ አይደለም። ንጹህ የሆኑ የተፈጥሮ ሰው ነጋዴዎችን ብቻ የሚመለከት ነው። እንደዚህም ሆኖ ከኪሳራ ጋር ተያያዠነት ያላቸውን ወንጀሎች ፈፅሞ የተፈረደበት፤ ንብረት ስለመደበቁ ወይም ማሸሹ ማስረጃ የቀረበበት፤ በኪሳራ ሥነ-ሥርዓት ሂደት ያልተባበረ ወይም ግዴታውን ያልተወጣ ነጋዴ ወይም ተደጋጋሚ የኪሳራ ውሳኔ በአምስት ዓመት ውስጥ ያስተናገደ ነጋዴ ይህን መብት አያገኝም። ከዕዳ ነፃ አይደረግም። በተጨማሪም የተወሰኑ ዕዳዎች ሌሎች ሕጎች በልዩ ሁኔታ ካልፈቀዱ በስተቀር ነፃ እንደማይደረጉ በአዲሱ የንግድ ሕግ ተካቷል።

ቀላል የኪሳራ ሥነ-ሥርዓት

ቀላል የኪሳራ ሥነ-ሥርዓት ዓላማ ሥነ-ሥርዓቱን ቀላል፤ ጊዜና ወጪ ቆጣቢ በማድረግ ለኪሳራ የተዳረጉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በሥነ-ሥርዓቱ ከንግድ ሥርዓቱ የሚወጡበትን ሥርዓት መዘርጋት ነው። ቀላል የኪሳራ ሥነ-ሥርዓት ሊከፍቱ የሚችሉት አነስተኛና መካከላኛ ኢንተርፕራይዞች ሲሆኑ እነሱም የሚከተሉትን መመዘኛዎች የሚያማሉ ከሆነ ነው፡- 1) ባለፉት 12 ወራት የሒሳብ ሚዛናቸው የሀብት መጠን ከ20 ሚሊዮን ብር ያነሰ ከሆነ፤ 2) የሠራተኛ ቁጥራቸው ከ10 ያነሰ ከሆነ፤ ወይም 3) ባለፉት 12 ወራት ዓመታዊ ሽያጫቸው ከ5 ሚሊዮን ብር ያነሰ ከሆነ ነው።

ይህን ሥነ-ሥርዓት ቀላል የሚያሰኙት ዋና ዋና ባህርያት የሚከተሉት ናቸው፡- 1) የሚቀርቡት ሰነዶችና አባሪዎች ዝርዝር አጭር መሆናቸው፤ 2) በፍ/ቤቱ ተቆጣጣሪነትና በንብረት ጠባቂው ኃላፊነት ብቻ (ተቆጣጣሪ ዳኛና የገንዘብ ጠያቂዎች ኮሚቴ ሳያስፈልግ) ሥነ-ሥርዓቱን ማከናወን መቻሉ፤ 3) የንብረት ማጣራትና መሸጥ ተግባራት የተንዛዛውን መደበኛ ሥነ-ሥርዓቶች የግድ አለመከተላቸው፤ 4) ንብረት ጠባቂው የባለዕዳውን ንብረት አጣርቶ፤ ሸጦ በአንድ ዓመት ውስጥ የማከፋፈል ግዴታ የተጣለበት መሆኑና ሥነ-ሥርዓቱም በአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ የታጠረ መሆኑ፤ እና 5) በዚህ ሥነ-ሥርዓት ሥር አልፈው ፋይላቸው የተዘጋላቸው የተፈጥሮ ሰዎች ከዕዳ ነፃ ወዲያውኑ ሊታወጅላቸው መቻሉ፤ናቸው። ፍ/ቤቱም ቀላል የኪሳራ ሥነ-ሥርዓት ከተከፈተ ባንድ ዓመት ውስጥ መጠናቀቁን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

በንቃተ ሕግ፣ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት
Sebeawinet Vol. 4.pdf
870.5 KB
Its finally here vol. 4 of Sebeawinet magazine.
ሰብአዊነት_ስብስብ_ለሰብአዊ_መብቶች_በኢትዮጵያ_መጽሄት፟_ዕትም_1.pdf
2.4 MB
ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ ሰብአዊነት የተሰኘውን የመጀመሪያውን በሰብአዊ መብቶች ላይ ያተኮረ መፅሄት ሲያቀርብላችሁ በደስታ ነው፡፡( Association for Human Rights in Ethiopia is happy to announce the launch of its first Magazine ሰብአዊነት dedicated to advocating, informing and educating about Human Rights, Human Rights laws and and current human rights situations in Ethiopia. ) IF YOU ARE INTERESTED YOUR ARTICLE BEING FEATURED IN OUR NEXT "ሰብአዊነት" MAGAZINE, PLEASE CONTACT US VIA FACEBOOK at (Association for Human Rights in Ethiopia Page)
ሰብአዊነት እትም 2 ቁጥር 2.docx
402.5 KB
It is finally Here; Find Sebawinet Magazine Volume 2
Forwarded from አለሕግAleHig ️
የማስረዳት ግዴታ
=================
=====================
• ዓቃቤ ህግ ጉዳዩን የማስረዳት ግዴታና ኃላፊነቱን ተወጥቷል ወይስ አልተወጣም? የሚለው ነጥብ እልባት የሚሰጠው ባቀረበው የወንጀል ክስ ውስጥ የተገለፁትን ፍሬ ጉዳዮች ትክክለኛነት የወንጀል ክሱን ለማስረዳት ባቀረባቸው የተለያዩ ማስረጃዎች የሚያረጋግጡና በወንጀል ክሱ ውስጥ የተገለፀው ፍሬ ጉዳይና ክሱን ለማስረዳት የቀረቡት ማስረጃዎች እርስ በርሳቸው የሚደጋገፉና ተያያዥነት ያላቸው ሆነው ሲገኙ ነው፡፡
የወንጀል ክስ ያቀረበ ከሳሽ ጉዳዩን የማስረዳት ግዴታና ኃላፊነቱን ተወጥቷል ወይም አልተወጣም? የሚለውን ጭብጥ ለመወሰን የመጀመሪያው የማነፃፀሪያና የመመዘኛ መስፈርት ራሱ ከሳሽ ያቀረበው የወንጀል ክስ ማመልከቻ ነው፡፡ አንድ ድርጊት የተፈፀመ መሆኑን በመግለጽ ክስ ያቀረበ ወገን በክሱ የገለፀውን ፍሬ ጉዲይ የማስረዳት ግዴታና ኃላፊነት አለበት የሚለው የማስረጃ ሕግ መርህ ይህንኑ የሚያጠናክር ነው፡፡ ዓቃቤ ህግ ጉዳዩን የማስረዳት ግዴታና ኃላፊነቱን ተወጥቷል ወይስ አልተወጣም? የሚለው ነጥብ እልባት የሚሰጠው ባቀረበው የወንጀል ክስ ውስጥ የተገለፁትን ፍሬ ጉዳዮች ትክክለኛነት የወንጀል ክሱን ለማስረዳት ባቀረባቸው የተለያዩ ማስረጃዎች የሚያረጋግጡና በወንጀል ክሱ ውስጥ የተገለፀው ፍሬ ጉዳይና ክሱን ለማስረዳት የቀረቡት ማስረጃዎች እርስ በርሳቸው የሚደጋገፉና ተያያዥነት ያላቸው ሆነው ሲገኙ ነው፡፡ በአጠቃላይ ከሳሽ ክሱን ለማስረዳት ያቀረባቸው ማስረጃዎች ለጉዳዩ ያላቸው አግባብነት (Relevancy of evidence) እና የከሳሽ ማስረጃ የአስረጅነት ዋጋ ያላቸውና ታዓማኒነት ያላቸው መሆኑ የሚመረመረው ከሳሽ በወንጀል ክስ ማመልከቻው የገለፃቸውን ፍሬ ጉዳዮች መሰረት በማድረግ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 51706 ቅጽ 10
L.C.L
ኢትዮ-ሕግ💎Ethio-Law
#henoktaye
https://t.me/LawyerEthiopia
https://t.me/LawyerEthiopia