አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Legal Counsel

Cola Holding

Addis Ababa

Apply on LinkedIn

Full–time

We’re looking for a Legal Counsel to join our team in Ethiopia. Cola Group consists of many diversified and rapidly growing companies headquartered in a historical building at 5 Parliament Square, Castletown, Isle of Man. It has a competence center in Dubai, a software development team in Kyiv and operational centers across Africa: Nairobi, Addis Ababa, and Lusaka. We already have a team of over 80 employees and we are expecting to grow to 250 by the end of 2021 and plan to triple this number by the end of 2022. As a Legal Counsel you’ll be responsible for providing general business legal advice (including compliance related matters) to the local management, as well as on a group level. We’re on the lookout for forward-thinking innovators with a passion for sustainability. If you match this description, get in touch! What You’ll Do · Provide advice on the legal and regulatory risk involved in offering betting services and platform software solutions to the gaming industry · Prepare, review and negotiate contracts · Manage claims handling and litigation where relevant · Identifying legal issues, providing analysis of legal risks and assisting in the creation and implementation of solutions · Manage company law matters · Advise on tax application · Participate in the working groups to develop the betting regulation in Ethiopia Your Qualifications · LLB Degree · Admission as an Attorney at Law (preferably) · Minimum 4 years experience in private sector (betting sector is preferred). · Fluent in English · Excellent communication and people's skills · Appetite for responsibility and challenges; with a drive to own and deliver solid results If you meet the above requirements for this Legal Counsel job in Ethiopia, we would like to hear from you! Please send your CV through today! If you do not receive any feedback within 7 days of your application, please be advised that you were not successful in making the shortlist
Apply on LinkedIn
በሀገር እና በመንግስት ደህንነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች
--------------------------------------------

ሀገር እና መንግስት
በዓለም ዓቀፍ ህግ መሠረት ሀገር ማለት አራት ሁኔታዎችን ያካተተ ሲሆን ሀዝብ፤ መንግስት፤ ግዛት ያለዉ እንዲሁም ልዓላዊነቱ የተከበረ በሌሎች ሀገራት ሙሉ እዉቅና ያገኘ ማለት ነዉ ፡፡ መንግስት ሀገር ለሚለዉ ትርጉም አንዱ አካል ሲሆን ህዝቦች በዲሞከሪያሲያዊ ምርጫ የወከሉት ህዘብን የሚመራና የሚያስተዳድር ተቋም ነዉ፡፡ በ1987 ዓ.ም በወጣዉ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀጽ 1 የኢትዮጵያ መንግስት ስያሜ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ፤ ዲሞክሪያሲያዊ፤ ሪፐብሊክ መንግስት ተብሎ ይጠራል፡፡ አንቀጽ 2 የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን የፌዴራል አባሎች ወሰንን የሚያጠቃልል ሆኖ በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት የተወሰነ ነዉ፡፡ በዚህ ህገ መንግስት አንቀጽ 47 (1) መሠረት የፌዴራል አባሎች ወሰን የተባሉት የክልሎችን የአስተዳደር ወሰን ማለት ሲሆን በቀጣይ በህገ መንግሰቱ የሚካተተዉን የሲዳማን ክልል ጨምሮ አስር ናቸዉ፡፡ ክልሎች እኩል መብትና ሥልጣን አላቸዉ፡፡ የመንግስትና ክልልሎች የስልጣን አወቃቀር በሶስት አካላት የተከፈለ ነዉ፡፡ እነርሱም ህግ አዉጪ፤ የህግ አስፈጻሚ እና የዳኝነት አካል ናቸዉ፡፡
ህግ አዉጪ ሲባል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ የህግ አስፈጻሚ ማለት የሚኒስተሮች ም/ቤትና ሌሎች ተቋማት እና የዳኝነት አካል ፍርድ ቤት ሲሆኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከየክልሎቹ የተዉጣጣ ተወካይ ሆኖ ህግ የመተርጎም ሥልጣን ያለዉ ማለት ነዉ፡፡ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 50 እና 53 መሠረት የፌዴራሉ መንግስት የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አሉት፡፡ ከፍተኛዉ ሥልጣን ለህግ አዉጪ አካል የተሰጠ ነዉ፡፡ ተጠሪነቱም ለህዝብ ነዉ፡፡ የምክር ቤቱ አባላት ለህዝቡ ፡ ለህገ መንግስቱ እና ለህሊናቸዉ ተገዢ ይሆናሉ፡፡ ህዝብ አመኔታ በአጣበት ጊዜ አባላቱን በህግ መሠረት የማስወገድ መብት አለዉ፡፡ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት በህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሁለት ሶስተኛ ድምጽ ሲጸድቅ ፕሬዚዳንት ይሆናል፡፡ ፕሬዚዳንቱ የሀገሪቱ ርእሰ ብሄር ነዉ ፤ የስራ ዘመኑ 6 ዓመት ሲሆን ከሁለት የስራ ዘመን በላይ አይመረጥም፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብላጫ ድምጽ ካለዉ ፖሊቲካ ድርጅት በህዝብ የተመረጡ፤ የሀገሪቱ ርእሰ መስተዳድር ወይም መሪ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ እንዲሁም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዝ ናቸዉ፡፡ የስራ ዘመኑ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስራ ዘመን ነዉ፡፡ በጠቅላለዉ የኢትጵያ መንግስት ፓርላመንተሪያዊ ስርዓት የሚከተል ሆኖ የፌዴራላዊ አወቃቀር ያለዉ ስርዓተ መንግስት ነዉ፡፡

የሀገር ሉዓላዊነት
ሉዓላዊነት ሀገር የሚለዉን ጽንሰ ሃሳብ ለማዋቀር የምንጠቀምበት የሀገር የነጻነት መገለጫ አንዱ ፍሬ ጉዳይ ነዉ፡፡ ህዝብ፤መንግስትና የግዛት ወሰን ተከበሮ የሚቆየዉ ሉዓላዊነቷ በተከበረና በታፈረች ሀገረ ነዉ፡፡ ሉዓላዊት ሀገር የረሷ የሆነ ህዝብ፤ አስተዳደር ፤ መልካዓምድር፤ ታሪክ፤ በሕል፤ ህግና ሥርዓት እንዱሁም ሌሎች በርካታ መገለጫዎች አላት፡፡ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ከብዙ ሺ ዘመናት ጀምሮ ተከብሮ የቆየ ነዉ፡፡ ማንኛዉም ኢትዮጵያዉ የሀገር ሉዓላዊነትን የማክበር፤ የማስከበርና የማስጠበቅ የህግ ኃላፊነት አለበት፡፡ በኢፍድሪ ህገ መንግሰት አንቀጽ (1) የኢትዮጵያ ህዝቦች የሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤቶች ናቸዉ፡፡ (2) ይህ ህገ መንግስት የሉዓላዊ ሥልጣን መገለጫቸዉ ነዉ፡፡ (3) ሉዓላዊነታቸዉ የሚገለጸዉ በመረጧቸዉ ተወካዮቻቸዉ እና በቀጥታ በሚያደርጉት ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ ነዉ፡፡ በዚህ ህገ መንግስት እና ዜጎች በመረጧቸዉ ተወካዮቻቸዉ በኩል የሚወጡ ህጎችን የሚጻረር ማንኛዉም ዜጋ፤ የመንግስት አካላት፤ የፖሊቲካ ድርጅት፤ ማህበራት፤ የዉስጥ ወይም የዉጪ ወራሪ የኢትዮጵያን ህዝቦች የሉዓላዊ ሥልጣን መዳፈር ነዉ፡፡ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 86 (1-6) መሠረት የኢትዮጵያ የዉጭ ግንኙነት የተመሠረተዉ የህዝቦቿን ጥቅምና የሀገሪቱን ሊዓላዊነት በሚያስከብር መልኩ መሆን እንዳለበት፤ በሌሎች ሀገራት ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት፤ የጋራ ጥቅምና የእኩልነት መርህ ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት ፤ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብር መሆኑን በሚያረጋግጥ ሁኔታ፤ ከጎረቤት ሀገራት እና ከሌሎች አፍሪካ ሀገሮች ጋር በየጊዜዉ እያደገ የሚሄድ የኢኮኖሚ ህብረት እና የህዝቦች ወንድማማችነት የሚያጎለብት፤ በሀገሮች መካከል የሚነሱ ግጭቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱ ጥረት ማድረግ ዋናዉ የብሔራዊ ፖሊሲ መርሆችና ተግባራት መሆናቸዉን በግልጽ አስቀምጧል፡፡

በሀገር እና በመንግስት ደህንነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ምንድን ናቸዉ ?
በ1996 ዓ.ም በወጣዉ የወንጀል ህግ አንቀጽ 238 እስከ 246 ያሉት ድንጋጌዎች በሀገር እና በመንግስት ደህንነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መሆናቸዉን በግልጽ ደንግጓል፡፡ በዚህ ህግ አንቀጽ 238 (1) እና (2) መሠረት ማንም ሰዉ በኃይል፤ በዛቻ፤ በአድማ ወይም በማናቸዉም ህገ ወጥ መንገድ የፌዴራሉን ወይም የክልል መንግስትን ያፈረሰ፤የለወጠ ወይም ያገደ ከሆነ፤የተቋቋመዉን ሥርዓት ያፈረሰ ወይም የለወጠ ከ3 ዓመት እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡ ወንጀሉ ሲፈጸም በህዝብ ኑሮ እና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ቀዉስ ፈጥሮ ከሆነ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ወይም የሞት ቅጣት ያስከትላል፡፡ አንቀጽ 240 (1) ማንም ሰዉ በህገ መንግስት በተቋቋሙት አካላት ወይም በለሥልጣናት ላይ ህዝብ፤ ወታደሮች፤ሽፍቶች የትጥቅ አመጽ እንዲያነሱ ያደረጃ ወይም የመራ ከሆነ ወይም ዜጎችና ነዋሪዎችን የጦር መሳያዎችን በማስታጠቅ አንዱ በሌላዉ ወገን እንዲነሳሳ ያደረገ ከ10 ዓመት እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡

ንኡስ ቁጥር (2) ወንጀሉ ሲፈጸም በህዝብ ኑሮ እና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ቀዉስ ፈጥሮ ከሆነ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ወይም የሞት ቅጣት ያስከትላል፡፡ ንኡስ ቁጥር (3) በጦር መሣሪያ በሚደረግ የአመጽ እንቅስቃሴ ወይም የማነሳሳት ተግባር ዉስጥ በራሱ ፍቃድ የተሳተፈ ሰዉ ከ7 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡ የወንጀሉ ፈጻሚ በማስረጃ የተረጋገጠበት ከሆነ ከዚህ ወንጀል በተጨማሪ በግድያ፤ በአካል ጉዳት፤ ንብረት ላይ በደረስ ዉድመት ወይም በሌሎች ወንጀሎች በተደራቢነት ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ የሀገሪቱን የፖሊቲካ ግዛት አንድነት በመንካት በሃይል ወይም በእጅ አዙር የሀገሪቱ አንድነት እንዲፈርስ ወይም የፌዴሬሽን እንዲከፋፈል ወይም ህዝብ እንዲገነጠል የሚያደርግ የወንጀል ተግባር የፈጸመ ከ10 ዓመት እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት የሚቀጣ ሲሆን ነገሩ ከባድ ሲሆን የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ወይም የሞት ቅጣትን ያስከትላል፡፡

በተጨማሪ የሀገሪቱን የ የልዑአላዊነቱ ግዛት በመዳፈር የኣለም ዐቀፍ መርሆች፤ ህጎችን እና ስምምነቶች በመጣስ ለህዝብ ደህንነት አስጊ የሆነ ተግባር ለመፈጸም ወደ ሀገሪቱ ግዛት የገባ ማንኛዉም ሰዉ ወይም ሀገር እስከ አስር አመት ጽኑ አስራት ይቀጣል፡፡ በሌላ በኩል የሀገሪቱን መንግስት መድፈር ወንጀል መሆኑም ተደንግጓል ፡፡ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 244(1) መሠረት ማንኛዉም ሰዉ በንግግር ፤ በተግባር ወይም በማናቸዉም ህገወጥ ተግባር የሀገሪቱን መንግስት በአደባባይ ያወረደ፤ የሰደበ፤ ስምኑን ያጠፋ ወይም በሀሰት የወነጀል ከሆነ ከሶስት ወር በላይ በሆነ
እስራት እና በገንዘብ ይቀጣል፡፡ በአንቀጽ 246 (1 እና 2) ስር ሀገሪቱ ሉዓላዊ ነጻነቷን እንድታጣ፡ ሀገሪቱን አደጋ ላይ ለመጣል የዉጭ መንገስት ጣልቃ እንዲገባ ለመገፋፋት ወይም የዉጭ መንግስታት በሀገሪቱ ላይ በጠላትነት እንዲወጋት፤ እንዲወራት፤ እንድትያዝ እና እንድትከበብ ያደረገ ማንም ሰዉ ከ5 ዓመት እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡ ነገሩ ከባድ በሆነ ጊዜ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ወይም በሞት ፍርድ ይቀጣል፡፡

የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 2/2 የጥላቻ ንግግር” ማለት በአንድ ሰው ወይም በተወሰነ ቡድን ማንነት ላይ ያነጣጠረ፣ ብሔርን፡ ብሔረሰብንና ህዝብን፣ ሃይማኖትን፤ ዘርን፣ ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ ሆን ተብሎ ጥላቻን፣ መድሎን ወይም ጥቃትን የሚያነሳሳ ንግግር ነው፡፡ በአንቀጽ (1) እና (2 ) የጥላቻ ንግግር ያደረገ ሰዉ እስከ ሁለት ዓመት ወይም ከ100 ሺ ብር በማይበልጥ እስራት ይቀጣል፡፡ ንግግሩ ጉዳት አድርሶ ከሆነ ከ5 ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ይቀጣል ፡ ፡ በአዋጁ አንቀጽ 11 ሰው ሲባል በተፈጥሮ ወይም በህግ ሰዉነት የተሰጠዉ አካል ሲሆን በዚህ አነጋገር መንግስት በህግ ሰዉነት የተሰጠዉ አካል ማለት ነዉ፡፡ መንግስት ላይ የሚፈጸሙ ማናቸዉም የጥላቻ ንግግሮች በዚህ አዋጅ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

በዓለም ዓቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት የሚታዩ ወንጀሎች
ማንኛዉም ሀገር ሉዓላዊነቱ የተከበረ ነዉ፡፡ ሀገራት በዓለም አቀፍ የትብብር መስኮች ስምምነት እስካልፈጸሙ ድረስ ማንኛዉም ሀገር የሌላዉን ሉዓላዊ ሀገር ጣልቃ ገብቶ የመዳፈር መብት የለዉም፡፡ በዓለም ዓቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ህግ በአንቀጽ 5 መሰረት ይህ ፍርድ ቤት የዘር ማጥፋት፡ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል፡ የጦር ወንጀል እንዱሁም የጠበኝነት ወንጀሎች ማየት ሥልጣን አለዉ፡፡ ሱዳን የኢትዮጵያን የልዑአላዊ ግዛት በመዳፈር ከአራቱ ዓለም ዓቀፍ ወንጀሎች አንዱ የሆነዉን የጠበኝነት ወንጀል {the crime of aggression} በመፈጸም መሬት የወረረች መሆኑን ከሀገር ዉስጥም ሆነ ከዉጭ ሀገር የመረጃ ምንጮች ለመረዳት ተችሏል፡፡ የሱዳንን የጠባጫሪነት ተግባር ሽፋን በመጠቀም ሀገሪቱን ግዛት ለመድፈር ሙከራ ያለ ስለመሆኑም አመላካች መረጃዎች እንዳሉ መረዳት ይቻላል፡፡ እንዲህ አይነቱ የወንጀል ተግባር በኢትዮጵያ ወንጀል ህግ ከባድ ቅጣት የሚስከትል መሆኑን ከላይ በዝርዝር ተቀምጧል፡፡ በዓለም ዓቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ህግ አንቀጽ 77 መሠረት የጠበኝነት ወንጀል {the crime of aggression} የፈጸመ ማንኛዉም አካል እንደነገሩ ሁኔታ ከ30 ዓመት ያልበለጠ እስራት ይቀጣል፡፡ ከእስራቱ በተጨማሪም በገንዘብ የሚቀጣ ሲሆን በወንጀሉ የተገኘዉም ሀብትና የወንጀሉ ፍሬ የሚወረስ መሆኑን ይደነግጋል ፡፡ በአጠቃላይ በሀገር እና በመንግስት ደህንነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሀገር ሊያፈርሱ የሚችሉና የዜጎችን የመኖር ህልዉና አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ከባድ ወንጀሎች በመሆናቸዉ ሁሉም ዜጋ ወንጀል ከመስራት እራሱን ሊቀጥብ ይገባል፡፡ ሀገሩን ከአጥፊዎች የመጠበቅና የመከላከል ከፍተኛ የህግ ሃላፊነት አለበት፡፡ ወንጀል ሳይፈጸምም ሆነ ከተፈጸመ በኋላ አጥፊዎችን ለህግ በማቅረብ ለፍትህ እርዳታ በመስጠት የህግና የዜግነት ግዴታዉን በመወጣት የሀገር ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል፡፡
የትዊተር አጠቃቀም እና ያለው ተፅኖ !

የህወሃቶቹ ተሟጋች Alex De Wall ትናንት ምሽት ባወጣው ጽሁፉ " ማህበራዊ ሚዲያውን ኢትዮጵያውያኖቹ ( እርሱ የአቢይ ደጋፊ ሲል ይጠራናል) አጨናንቀውታል። ለእያንዳንዱ ጽሁፍ በብዙ ቁጥር እየመጡ ምላሽ ይሰጣሉ የተለየ ሀሳብም ለመስማት ፈጽሞ ፈቃደኞች አይደሉም። " ሲል አማሯል።

የዛሬ ስምንት ወር ትዊተር የህወሃት ምንደኞች መፈንጫ ነበር። ዛሬ ብዙ ቢቀረንም ትዊተር ላይ ኢትዮጵያውያን እንደ ተርብ ነው የሚናደፉት። የሀሰት ጆንያ ተሸክሞ የመጣን ፈረንጅ በራሱ ቋንቋ በበቂ አመክንዮና ማስረጃ የሚሞግቱ ኢትዮጵያውያን እጅግ ብዙ ናቸው። ኢትዮጵያውየን የአሜሪካና አውሮፓ ፖለቲከኞች ስለ ሀገራችን የሚጽፉትን በመሰለኝና ደሳለኝ ሳይሆን በጥንቃቄ አስበውበት እንዲሆንም አስገድደዋል።

ጥሩ እርምጃ እየታየ ቢሆንም ገና ብዙ ይቀረናል።

፩. ትዊተር መረጃን በማባዛትና ማስራጨት ላይ ብዙ አንሰራም። ለምሳሌ ትናንት አልጀዚራ ህወሃት ዘርፎ ትግራይ ላይ ስላገታቸው የእርዳታ መኪኖች ያወጣውን ዜና ሼር ያደረገው ሰው ሃምሳ አይሞላም። የህወሃት ሰዎች አቢይን የሚተች ጽሁፍ ማንም ያውጣ በሺዎች ነው የሚያጋሩት ፣ ከዚያ መማር ግድ ይላል።

፪. ደጋግመን እንዳልነው ትዊተርም ይሁን ፌስ ቡክ ላይ የግድ ጸሀፊ መሆን አይጠበቅብንም። ነገር ግን ለኢትዮጵያ ድምጽ የሆኑትን የሚከተሉትን ሰዎች follow, retweet & like እናድርግ ። ጽሁፎቻቸውና መረጃዎቻቸው ለበለጠ አንባቢና አድማጭ እንዲደርስ እናድርግ።

፫. የመንግስት ባለስልጣናትና ተቋማትን ( ለምሳሌ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ) ጽሁፎችና መግለጫዎችን ላይክ ፣ ሪትዊት እናድርግ። ጉዳዩ አቢይን አልያም ደመቀ መኮንን የመውደድ አልያም የመጥላት አይደለም። #የሀገር #ጥቅምን #የማስጠበቅ እንጂ።
በዚህ በሰለጠነው አለም Twitter አካውንት ከሌለህ ፌስ ቡክ (Facebook) ላይ ምንም አታመጣም።
#Share us your twitter account here and we will follow you‼️
#Twitter
Write on group @ALE_lawsocieties
We DO NOT STOP FIGHTING UNTIL JUSTICE IS SERVED!
URGENT!


About Unjust USA Sanction!
አዳዲስ ቲዊቶች! 🔥🔥🔥🔥🔥🔥

💪🇪🇹💪🇪🇹💪🇪🇹💪🇪🇹💪
ሪቲዊት: ቲዊት : ላይክ እና ፎሎው ያድርጉ
#UnityforEthiopia daily WITH depicting PICTURES
ከገላጭ ስዕሎች ጋር

የኢትዮጵያ የቲውተር ወታደሮች ዛሬም ይፋለማሉ!

RETWEET, LIKE and FOLLOW ያድርጉ❗️

LINK and TWEETS 👇👇👇

https://twitter.com/mikiasmelak?t=CAo0cNgZ9joxaT7ry3xjRw&s=09
Uploads this Twitter application
base.apk
18.6 MB
Twitter for Android/IOS)
App ትዊተርን ይጠቀሙ‼️
via #UnityForEthiopia
ወደ ትዊተር ግቡ!

Follow members and they will Follow you 👇
Is @lawsocities channel helpful?
Anonymous Poll
89%
Yes
4%
No
5%
Some how
0%
Don't know
1%
Who cases
We need to discuss on some issues regularly.
Anonymous Poll
29%
Voice chat
7%
Video chat
26%
Groups chat
50%
Both voice and group chat
dear members Please choose your convenient days not more than 3 days for our Voice chat group's discussion?
Anonymous Poll
25%
Monday
21%
Tuesday
22%
Wednesday
26%
Thursday
37%
Friday
46%
Saturday
56%
Sunday
ገባ ገባ በሉ online ያላችሁ።
ለማንኛውም የስነ ልቦና እና ስነ አዕምሮ ችግሮች Healing Minds የተለየ አማራጭ ይዞ ቀርቧል

⓵ Digital Based Therapy (በ Video Call)

⓶ Home Based Therapy (በአካል በቤቶት አልያም እርሶ በመረጡት ስፍራ ሆነዉ ህክምና ማግኘት ይችላሉ።

ህክምና ለማግኘት ከዚህ በታች ያለዉን link በመጫን ይመዝገቡ

👉 https://bit.ly/3tqIDM9

🔈 ለበለጠ መረጃ @PsychINFO ቻናልን አልያም @HealingMindsSMHC ግሩፕን ይጎብኙ!

👉 በ ቅንነት Share በማድረግ ለወዳጅ ዘመዶት ያጋሩ!
3ቱ አስገዳጅ ህጎች!

1. ሦስት ነገሮችን ጠብቅ!
★ ሀገር
★ እናት
★ ዓይን

2. ለሦስት ነገሮች ተዘጋጅ!
★ ለኃላፊነት
★ ለእውቀት
★ ለትዳር

3. ሦስት ነገሮችን አክብር!
★ ቃልኪዳን
★ ጓደኛ
★ ትዳር

4. ሦስት ነገሮችን ተቆጣጠር!
★ ምላስህን
★ ቁጣህን
★ ስሜትህን

5. ሦስት ነገሮችን አድንቅ!
★ ውበት
★ ሕይወት
★ ተፈጥሮን

6. ሦስት ነገር ጥላ!
★ሀሜት
★ ቅናት
★ ተንኮል

7. ሦስት ነገሮች ያስፈልጉሃል!
★ እምነት
★ ተስፋ
★ ፍቅር

8. ሦስት ነገሮችን ለዚህ ፔጅ አበርክት!
★ ላይክ
★ ኮመንት
★ ሼር

በኢትዮጵያ ቱደይ
የከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ስልጣን ከአዲሱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ አንፃር

በ፡ አብዱሰላም ሳዲቅ ሙክታር

የከተማ ፍርድ ቤቶች የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 በስራ ላይ ሲውል ስልጣንና ሀላፊነታቸውን በማሻሻል ብቅ ብሏል፡፡ ይህ ጽሑፍ እነዚህ የከተማ ፍርድ ቤቶች ምን አይነት አዲስ ስልጣን ተጨመረላቸው?፣ በፍትሐብሔር እና በወንጀል ጉዳዮች ሥልጣናቸው እስከምን ድረስ ነው? እና በተጨመረላቸው ስልጣን ምክንያት የስራ ጫና ሊኖር ስለሚችል ምን አይነት ዝግጅት ማድረግና በህዝብና በተገልጋዩ ማህበረሰብ አመኔታ ያላቸው ፍርድ ቤቶች ለመሆን ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል የሚሉትን በአጭሩ ያስዳስሰናል፡፡

መልካም ንባብ!
https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2006-the-jurisdiction-of-city-courts-under-the-new-federal-courts-proclamation/amp
የወራሽነት ምስክር ወረቀት (certificate of heir)

የወራሽነት ምስክር ወረቀት(certificate of heir) ምንድነው?

# የወራሽነት ምስክር ወረቀት በአጭሩ ለመግለጽ ህጋዊ የውርስ ስርዓት ለሟላ የሟች ወራሽ ለሆነው ሰው የሟቹ ወራሽ መሆኑንና ከውርሱ የሚገባውን ድርሻ በተመለከተ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ተረጋግጦ የሚሰጥ የጽሁፍ ማረጋገጫ ነው ለማለት ይቻላል።

ወራሽ የሆነው ሰው ከውርሱ የሚያግኘውን ድርሻ የሚያመለክት የወራሽነት ምስክር ወረቀት እንዲሰጡት ዳኞችን ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህግ 996(1) ይደነግጋል።ከፍርድ ቤት የወራሽነት ምስክር ወረቀት መያዝ በወራሹ ሲጠየቅ የሚሰጥ እንጂ ህጉ ሟችን ለመውረስ የግድ ከፍርድ ቤት የወራሽነት ማስረጃ ማውጣት እንዳለበት የሚያስገድድ አይደለም።
በዚህ ጉዳይ የፌ.ጠ.ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 22 መ/ቁ 130284 ለይ በሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም የውርስ ሰርተፊኬት አንድ ሰው የራሱን ወራሽነት ለማስረዳት የሚወስደው ማስረጃ እንጂ ሌሎች ወራሾች አለመኖራቸውን የሚያሳይ ሰነድ ስላለመሆኑ፣ እና በግራ ቀኙ የሟች ወራሾች መሆናቸው በማረጋገጥ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ከማስረጃነት በዘለለ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ በሚያዘው መሰረት ከሌሎች ሰዎች ክርክር ተደርጎበት ውሳኔ ያገኘና በፍርድ ያለቀ መቃወሚያ የማይቀርብበት ተደርጎ ሊወሰድ የማይገባ ስለመሆኑ ትርጉም ተሰጥቶበታል።በተመሣሣይ መልኩ በፌ.ጠ.ፍ.ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ14 መ/ቁ 73247 አንድ ወራሽ የወራሽነት መብት በሌለው ንብረት ላይ ከህግ ውጪ የወራሽነት ሠርተፍኬት መያዙ በተረጋገጠ ጊዜ ይኸው ማስረጃ እንዲሰረዝ አቤቱታ ሊቀርብ እንደሚችል አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።
#በመሠረቱ የመወረስ መብት የሚገኘው በህግ ወይም በኑዛዜ ሲሆን ፍ/ቤት አስቀድሞ ለአመልካቹ ያለውን የውርስ መብቱ አረጋግጦ የሚሰጥ እንጂ ለአመልካቹ የውርስ መብትን የሚስጥ አይደለም።በፌ.ጠ.ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 20 መ/ቁ 113529 ለይ በተሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ለአንድ ውርስ ወራሽ የሆነ አንድ ሰው ውርስ ከተከፈተ ቡሃላ የሞተ እንደሆነ የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባያወጣም ለውርሱ አይገባም እስካልተባለ ድረስ የወራሸነት መብቶች ለእርሱ ወራሾች የሚተላለፍ ስለመሆኑ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል። የወራሽነት ሰርትፍኬት አስገዳጅ የሆነ ህጋዊ ውጤት ይኖረዋል።
# የወራሽነት ምስክር ወረቀት የያዘው ወራሽ የምስክር ወረቀቱ እስካልተሰረዘ ድረስ ህጋዊ የውርስ መብት እንዳለውና ከውርሱ ድርሻ የሚገባ እንደሆነ ተደረጎ ይቆጠራል።አሁን በተግባር ባለው ሁኔታ የወራሽነት ምስክር ወረቀት አንደ ሰው ከያዘ ቡሃላ ወራሹ በሰርተፍኬቱ መሠረት ህጋዊ ውጤት ያላቸውን(valid juridical acts) ተግባራት መፈጸም ይጀምራል ማለትም ስመ ንብረት የማዞር ከባንክ ገንዘብ የማውጣትና ሌሎች መብቶች ማከናወን ይችላል ማለት ነው።የውርስ ሰርተፍኬት ውርሱ ከመጣራቱ በፊት ነው ወይስ የውርስ መጣራቱ ሂደት ከተጠናቀቀ ቡሃላ ነው ሊሰጥ የሚገባው የሚለው ጥያቄ አከራካሪ ሲሆን ይታያል የውርስ ማጣራት ሂደት ከመጠናቀቁ በፊት የሚሰጠው ምስክር ወረቀት ህጋዊ ወራሾች ከመለየታቸው በፊት እና ከማነኛውም እዳ ነጻ የሆነ የውርስ ንብረት ተጣርቶ ባልተለየበት ሁኔታ የሚሰጥ በመሆኑ አግባብነቱ አጠያያቂ ይሆናል በዚሁ ጉዳይ ለይ የፌ.ጠ.ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ18 መ/ቁ110022 በሰጠው ውሳኔ ፍ/ቤቶች የወራሽነት ማስረጃ ወይም የምስክር ወረቀት ብቻ አንዲሰጡ ማመልከቻ ሲቀርብላቸው ውርስ እንዲጣራ የሚሰጡት ትእዛዝ የማይገባና አላስፈላጊ ስለመሆኑ ትርጉም ሰጥቶት እናግኛለን።

Source
*የፍትሐብሔር ህግ
*የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ
*Blacks law dictionary
*የውርስ ህግ material

BY PAUL.K JUDGE AT WOREDA COURT

https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties