አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የወራሽነት ምስክር ወረቀት (certificate of heir)

የወራሽነት ምስክር ወረቀት(certificate of heir) ምንድነው?

# የወራሽነት ምስክር ወረቀት በአጭሩ ለመግለጽ ህጋዊ የውርስ ስርዓት ለሟላ የሟች ወራሽ ለሆነው ሰው የሟቹ ወራሽ መሆኑንና ከውርሱ የሚገባውን ድርሻ በተመለከተ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ተረጋግጦ የሚሰጥ የጽሁፍ ማረጋገጫ ነው ለማለት ይቻላል።

ወራሽ የሆነው ሰው ከውርሱ የሚያግኘውን ድርሻ የሚያመለክት የወራሽነት ምስክር ወረቀት እንዲሰጡት ዳኞችን ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህግ 996(1) ይደነግጋል።ከፍርድ ቤት የወራሽነት ምስክር ወረቀት መያዝ በወራሹ ሲጠየቅ የሚሰጥ እንጂ ህጉ ሟችን ለመውረስ የግድ ከፍርድ ቤት የወራሽነት ማስረጃ ማውጣት እንዳለበት የሚያስገድድ አይደለም።
በዚህ ጉዳይ የፌ.ጠ.ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 22 መ/ቁ 130284 ለይ በሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም የውርስ ሰርተፊኬት አንድ ሰው የራሱን ወራሽነት ለማስረዳት የሚወስደው ማስረጃ እንጂ ሌሎች ወራሾች አለመኖራቸውን የሚያሳይ ሰነድ ስላለመሆኑ፣ እና በግራ ቀኙ የሟች ወራሾች መሆናቸው በማረጋገጥ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ከማስረጃነት በዘለለ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ በሚያዘው መሰረት ከሌሎች ሰዎች ክርክር ተደርጎበት ውሳኔ ያገኘና በፍርድ ያለቀ መቃወሚያ የማይቀርብበት ተደርጎ ሊወሰድ የማይገባ ስለመሆኑ ትርጉም ተሰጥቶበታል።በተመሣሣይ መልኩ በፌ.ጠ.ፍ.ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ14 መ/ቁ 73247 አንድ ወራሽ የወራሽነት መብት በሌለው ንብረት ላይ ከህግ ውጪ የወራሽነት ሠርተፍኬት መያዙ በተረጋገጠ ጊዜ ይኸው ማስረጃ እንዲሰረዝ አቤቱታ ሊቀርብ እንደሚችል አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።
#በመሠረቱ የመወረስ መብት የሚገኘው በህግ ወይም በኑዛዜ ሲሆን ፍ/ቤት አስቀድሞ ለአመልካቹ ያለውን የውርስ መብቱ አረጋግጦ የሚሰጥ እንጂ ለአመልካቹ የውርስ መብትን የሚስጥ አይደለም።በፌ.ጠ.ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 20 መ/ቁ 113529 ለይ በተሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ለአንድ ውርስ ወራሽ የሆነ አንድ ሰው ውርስ ከተከፈተ ቡሃላ የሞተ እንደሆነ የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባያወጣም ለውርሱ አይገባም እስካልተባለ ድረስ የወራሸነት መብቶች ለእርሱ ወራሾች የሚተላለፍ ስለመሆኑ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል። የወራሽነት ሰርትፍኬት አስገዳጅ የሆነ ህጋዊ ውጤት ይኖረዋል።
# የወራሽነት ምስክር ወረቀት የያዘው ወራሽ የምስክር ወረቀቱ እስካልተሰረዘ ድረስ ህጋዊ የውርስ መብት እንዳለውና ከውርሱ ድርሻ የሚገባ እንደሆነ ተደረጎ ይቆጠራል።አሁን በተግባር ባለው ሁኔታ የወራሽነት ምስክር ወረቀት አንደ ሰው ከያዘ ቡሃላ ወራሹ በሰርተፍኬቱ መሠረት ህጋዊ ውጤት ያላቸውን(valid juridical acts) ተግባራት መፈጸም ይጀምራል ማለትም ስመ ንብረት የማዞር ከባንክ ገንዘብ የማውጣትና ሌሎች መብቶች ማከናወን ይችላል ማለት ነው።የውርስ ሰርተፍኬት ውርሱ ከመጣራቱ በፊት ነው ወይስ የውርስ መጣራቱ ሂደት ከተጠናቀቀ ቡሃላ ነው ሊሰጥ የሚገባው የሚለው ጥያቄ አከራካሪ ሲሆን ይታያል የውርስ ማጣራት ሂደት ከመጠናቀቁ በፊት የሚሰጠው ምስክር ወረቀት ህጋዊ ወራሾች ከመለየታቸው በፊት እና ከማነኛውም እዳ ነጻ የሆነ የውርስ ንብረት ተጣርቶ ባልተለየበት ሁኔታ የሚሰጥ በመሆኑ አግባብነቱ አጠያያቂ ይሆናል በዚሁ ጉዳይ ለይ የፌ.ጠ.ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ18 መ/ቁ110022 በሰጠው ውሳኔ ፍ/ቤቶች የወራሽነት ማስረጃ ወይም የምስክር ወረቀት ብቻ አንዲሰጡ ማመልከቻ ሲቀርብላቸው ውርስ እንዲጣራ የሚሰጡት ትእዛዝ የማይገባና አላስፈላጊ ስለመሆኑ ትርጉም ሰጥቶት እናግኛለን።

Source
*የፍትሐብሔር ህግ
*የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ
*Blacks law dictionary
*የውርስ ህግ material

BY PAUL.K JUDGE AT WOREDA COURT

https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties