የትዊተር አጠቃቀም እና ያለው ተፅኖ !
የህወሃቶቹ ተሟጋች Alex De Wall ትናንት ምሽት ባወጣው ጽሁፉ " ማህበራዊ ሚዲያውን ኢትዮጵያውያኖቹ ( እርሱ የአቢይ ደጋፊ ሲል ይጠራናል) አጨናንቀውታል። ለእያንዳንዱ ጽሁፍ በብዙ ቁጥር እየመጡ ምላሽ ይሰጣሉ የተለየ ሀሳብም ለመስማት ፈጽሞ ፈቃደኞች አይደሉም። " ሲል አማሯል።
የዛሬ ስምንት ወር ትዊተር የህወሃት ምንደኞች መፈንጫ ነበር። ዛሬ ብዙ ቢቀረንም ትዊተር ላይ ኢትዮጵያውያን እንደ ተርብ ነው የሚናደፉት። የሀሰት ጆንያ ተሸክሞ የመጣን ፈረንጅ በራሱ ቋንቋ በበቂ አመክንዮና ማስረጃ የሚሞግቱ ኢትዮጵያውያን እጅግ ብዙ ናቸው። ኢትዮጵያውየን የአሜሪካና አውሮፓ ፖለቲከኞች ስለ ሀገራችን የሚጽፉትን በመሰለኝና ደሳለኝ ሳይሆን በጥንቃቄ አስበውበት እንዲሆንም አስገድደዋል።
ጥሩ እርምጃ እየታየ ቢሆንም ገና ብዙ ይቀረናል።
፩. ትዊተር መረጃን በማባዛትና ማስራጨት ላይ ብዙ አንሰራም። ለምሳሌ ትናንት አልጀዚራ ህወሃት ዘርፎ ትግራይ ላይ ስላገታቸው የእርዳታ መኪኖች ያወጣውን ዜና ሼር ያደረገው ሰው ሃምሳ አይሞላም። የህወሃት ሰዎች አቢይን የሚተች ጽሁፍ ማንም ያውጣ በሺዎች ነው የሚያጋሩት ፣ ከዚያ መማር ግድ ይላል።
፪. ደጋግመን እንዳልነው ትዊተርም ይሁን ፌስ ቡክ ላይ የግድ ጸሀፊ መሆን አይጠበቅብንም። ነገር ግን ለኢትዮጵያ ድምጽ የሆኑትን የሚከተሉትን ሰዎች follow, retweet & like እናድርግ ። ጽሁፎቻቸውና መረጃዎቻቸው ለበለጠ አንባቢና አድማጭ እንዲደርስ እናድርግ።
፫. የመንግስት ባለስልጣናትና ተቋማትን ( ለምሳሌ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ) ጽሁፎችና መግለጫዎችን ላይክ ፣ ሪትዊት እናድርግ። ጉዳዩ አቢይን አልያም ደመቀ መኮንን የመውደድ አልያም የመጥላት አይደለም። #የሀገር #ጥቅምን #የማስጠበቅ እንጂ።
በዚህ በሰለጠነው አለም Twitter አካውንት ከሌለህ ፌስ ቡክ (Facebook) ላይ ምንም አታመጣም።