አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ማስታወቂያ
የዜጎች መብት እና የመንግስት ግዴታ በፌደራል አሰተዳደር ሥነ-ሥርዓት ሕግ
👆👇👆👇👆👇👆👇👆👇
በፍትሕ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ የዜጎች ፍትህ የማግኘት መብት መሰረታዊ የሆነ መብት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በመንግስት የአሰራር ፍትሀዊነት እና ግልፅነት ጭምር የሚገለፅ ነው፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 12 የመንግስት አሰራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን እንዳለበት እና ማንኛውም ኃላፊና የሕዘብ ተመራጭ ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ እንደሚሆን ደንግጓል፡፡ በዚህ መነሻነትም የፌደራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 የወጣ ሲሆን አዋጁ ለዜጎች የተለያዩ መብቶችን የሚሰጥ እና በመንግስት ላይ ደግሞ ግዴታዎችን የሚጥል ነው፡፡ ይህ አዋጅ የወጣበት ምክንያት ይህን ሕገ መንግሰታዊ መርሆ መሰረት በማድረግ የአስተዳደር ተቋማት በሰዎች መብቶችና ጥቅሞች ላይ የሚያስከትሉትን ጣልቃ ገብነት በሕግ የሚመራና ለሕግ የሚገዛ መሆኑን ለማራጋገጥ፣ የእነዚህ ተቋማት የውሳኔ አሰጣጥና መመሪያ አወጣጥ መርሆችንና ሥነ-ሥርዓት እንዲሁም በአስተዳደራዊ ውሳኔዎችና መመሪያዎች ቅር የተሰኘ ሰው የውሳኔዎቹንና የመመሪያዎቹን ሕጋዊነት በፍርድ ቤት የሚያስመረምርበት ሥርዓት በመደንገግ አስተዳደራዊ ፍትሕን ማስፈን በማስፈለጉ ነው፡፡ በአዋጁ መሰረት ዜጎች የተለያዩ መብቶች ያሏቸው ሲሆን አገልግሎት የማግኘት መብት፣ የመሳተፍ መብት፣ ቅሬታ የማቅረብ መብት፣ በፍርድ ቤት ክለሳ የመጠየቅ መብት የሚሉት እና ሌሎች መብቶች አሏቸው፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ በአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ለዜጎች የተሰጡ መብቶችን እና የመንግስት ግዴታዎችን የምንመለከት ይሆናል፡፡
የዜጎች መብት በአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ሕግ
የአስተዳደር ተቋማት ወሳኔ ሲሰጡም ሆነ መመሪያ ሲያወጡ በሰዎች መብቶች እና ጥቅሞች ላይ የሚያስከትሉት ተጽዕኖ በሕግ የሚመራ እና ለሕግ የሚገዛ መሆን እንዳለበት ከላይ በመግቢያው ያየን ሲሆን ጉዳዩ የፍርድ ቤት ክለሳንም ይጨምራል፡፡ በመሆኑም ዜጎች የሚከተሉት መብቶች አሏቸው፡-
1. መመሪያን በተመለከተ፡-

• መመሪያ እንዲወጣ የመጠየቅ መብት
ማንኛውም ሰው መብቱን ወይም ጥቅሙን በሚመለከት የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ያላወጣ ቢሆንም የአስተዳደር ውሳኔ እንዲሰጠው የመጠየቅ መብት ያለው ስለመሆኑ በፌደራል የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ አንቀጽ 4(3) ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ እንዲሁም አንድ የአስተዳደር ተቋም ሊያወጠው የሚገባውን መመሪያ በተገቢው ጊዜ ሳያወጣ ቢቀር መመሪያውን እንዲያወጣ ማንኛውም ሰው በጽሁፍ መጠየቅ ይችላል (አንቀጽ 6)፡፡

• አስተያየት የመስጠት መብት
አንድ የአስተዳደር ተቋም በአዋጁ አንቀጽ 8 መሰረት በሚያቀርበው ረቂቅ መመሪያ ላይ ዜጎች አስተያየት የመስጠት መብት አላቸው፡፡

• የመሳተፍ መብት
የአስተዳደር ተቋሙ በመመሪያው ረቂቅ ላይ የጽሁፍ አስተያየት ከበቃ በኋላ መመረያው ከመጽደቁ በፊት በሚያዘጋጀው የውይይት መድረክ ዜጎች የመሳተፍ መብት አላቸው (አንቀጽ 10(1))፡፡

• መመረያውን የማግኘት መብት
በአዋጁ አንቀጽ 17(3) መሰረት ማንኛውም የመመሪያውን ቅጂ ማግኘት የሚፈልግ ሰው መመሪያውን ባለበት ሁኔታ የመመልከት ወይም ወጪውን ሸፍኖ ከአስተዳደር ተቋሙ የማግኘት መብት አለው፡፡

2. የአስተዳደር ውሳኔን በተመለከተ

• አቤቱታ የማቅረብ መብት
የአስተዳደር ውሳኔ እንዲሰጥ የሚቀርብ ጥያቄን ዜጎች በራስ ወይም በተወካይ አማካኝነት የማቅረብ መብት ያለቸው መሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 20 ተደንግጓል፡፡

• የመደመጥና የመሰማት መብት
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠው ሰው የአስተዳደር ወሳኔ ከመስጠቱ በፊት የሚመለከተውን ሰው ፍሬ ነገር እና ማስረጃ በሚገባ ማዳመጥ እና መመርመር እንዲሁም እንደነገሩ ሁኔታ የሦስተኛ ወገን ተቃዋሚን እና የሕዝብን አስተያየት ማድመጥ አለበት (አንቀጽ 28)፡፡ ማንኛውም አስተዳደራዊ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ጉዳዩ በሚገባ መሰማት አለበት (አንቀጽ 36) ፡፡

• የእኩልነት መብት
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 25 ላይ ማንኛውም ሰው በሕግ ፊት እኩል መሆኑ ተደንግጓል፡፡ እንዲሁም በፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ አንቀጽ 32 የአስተዳድ ውሳኔ የሚሰጠው ሰው ሁሉንም ተገልጋዮች በዘር፣ በብሔር፣ በቀለም፣ በፆታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በማኅበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት መጠን፣ በትውልድ ሁኔታ ወይም በሌላ ምክንያት ልዩነት ሳያደርግ መወሰን እንዳለበት ደንግጓል፡፡

• የአስተዳር ውሳኔውን የማግኘት መብት
በአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጁ አንቀጽ 39 ላይ በተደደነገገው መሰረት ማንኛውም የአስተዳደር ውሳኔ ከነምክንያቱ ለተገልጋዩ በጽሁፍ መሰጠት አለበት፡፡
• ቅሬታ የማቅረብ መብት
ማንኛውም ሰው በተላለፈበት የአስተዳደር ውሳኔ ላይ ለአስተዳደር ተቋሙ ቅሬታ የማቅረብ መብት አለው (አንቀጽ 43)፡፡ የአስተዳደር ተቋሙ የሰጠውን ውሳኔ በአዋጁ አንቀጽ 47 መሠረት ወዲያውኑ ለቅሬታ አቅራቢው በጽሁፍ መስጠት አለበት፡፡
• የውሳኔ እገዳ ጥያቄ የማቅረብ መብት
ዜጎች ለአስተዳደር ተቋሙ ማንኛውንም ሕጋዊ አቤቱታ የማቅረብ መብት አላቸው፡፡ የአስተዳደራዊ ውሳኔ ወዲያውኑ መፈፀም በመብቱ ወይም በጥቅሙ ላይ የማይመለስ ጉዳት የሚያደረስበት ሰው ውሳኔው እንዲታገድለት ውሳኔውን ለሰጠው ተቋም አቤቱታ ማቅረብ ይችላል (አንቀጽ 41)፡፡

3. በፍርድ ቤት የሚደረግ የአስተዳደር መመረያዎች እና ውሳኔዎች ክለሳ

• የክለሳ አቤቱታ የማቅረብ መብት

• ማንኛውም ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ ቤት እንዲከለስ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፡፡ እንዲሁም ማንኛውም በአስተዳደር ውሳኔ ጥቅሙ የተነካበት ሰው ውሳኔው በፍርድ ቤት አንዲከለስ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል (አንቀጽ 48)፡፡
• የአስተዳደር መመሪያ ወይም ውሳኔ እንዲከለስ አቤቱታ የሚቀርበው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔም የመጨረሻ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የአስተዳደር መመሪያን በተመለከተ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለቀርብበት ይችላል (አንቀጽ49)፡፡
• የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ ቤት የሚከለሰው በሶስት ምክንያቶች ሲሆን ይህም
1. በአዋጁ የተመለከቱትን የሥነ ሥርዓት ድንጋጌዎች ሳይከተል የወጣ መሆኑ ሲረጋገጥ፣
2. ከተቋሙ የሥልጣን ገደብ ውጪ የወጣ ሲሆን
3. ከመመሪያ በላይ ከሆኑ ሌሎች ሕጎች የሚቃረን ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡
በሌላ በኩል የአስተዳደር ውሳኔ የሚከለሰው በአዋጁ የተደነገጉትን መርሆዎች የጣሰ ሲሆን ነው (አንቀጽ 50 (1 እና2) ፡፡
ቅሬታው መመሪያው ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ90 ቀናት ጊዜ ውስጥ መቅረብ የሚገባው ሲሆን የአስተዳደር ውሳኔን የተመለከተ ከሆነ ውሳኔ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር የ30 ቀናት ጊዜ ውስጥ መቅረብ እንዳለበት ተመላክቷል፡፡ ነገር ግን የክለሳ ምክንያት የሆነው ከአስተዳደር ተቋሙ የሥልጣን ገደብ ውጪ የወጣ መመሪያ ሲሆን ወይም የወጣው መመሪያ በእርከን ከመመረያ በላይ ከሆኑ ሌሎች ሕጎች የሚቃረን ሲሆን የአስተዳደር መመሪያው በፍርድ ቤት እንዲከለስ የሚቀርብ አቤቱታ በማናቸውም ጊዜ ሊቀርብ ይችላል (አንቀጽ 53) ፡፡
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from MAcK
Let see my work
የአምስት ዓመቷን ታዳጊ ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው ወጣት #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ

በመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ የአምስት ዓመቷን ታዳጊ ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰውን የ17 ዓመት ወጣት #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ የወረዳው ፍርድ ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን የወምበራ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የ10ኛ ክፍል ተማሪና የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ግለሰብ በአስገድዶ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ዕለተ ዓርብ ታህሳስ 26/2016 ዓ/ም በደብረ―ዘይት ከተማ 02 ቀበሌ ሲሆን በተለምዶ ሳንቂ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 10 ሰዓት ገዳማ የአምስት ዓመቷን ህፃን አስገድዶ የመድፈር ድርጊት ከፈፀመ በኃላ በመኖሪያ ቤቱ መያዙ ተገልጿል።

የወምበራ ወረዳ ፍርድ ቤት ከወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት የተላከለትን በቂ የሰውና የህክምና እንዲሁም የዐቃቢ ህግ ማስረጃዎችን በማረጋገጥ የምርመራ ስራ ሲያከናውን ቆይቶ ተከሳሹን ጥፋተኛ በማለት ውሳኔ አስተላልፎበታል።

በዚህም መሠረት የወረዳው ፍርድ ቤት መጋቢት 09/2016 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ወጣት #የ6ወር እስራት እንደተበየነበት የወምበራ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት የፍርድ ቤቱን የወንጀል ችሎት ዋቢ በማድረግ #በደብዳቤ በላከው መረጃ መጥቀሱ ተገልጿል።

መረጃው የመተከል ዞን የወምበራ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው የ17 ዓመት ወጣት 6 ወር ተፈረደበት ይለናል የወምበራ ኮሚኒኬሽን።

የ5 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው የ17 ዓመቱ ወጣት #በ6ወር እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል።

የ10ኛ ክፍል ተማሪና የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ግለሰብ በአስገድዶ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በደብረ―ዘይት ከተማ 02 ቀበሌ በተለምዶ " ሳንቂ በር " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

በዕለቱ የ5 ዓመቷ ህፃን ላይ አስገድዶ የመድፈር ድርጊት ከፈፀመ በኃላ በመኖሪያ ቤቱ ነው የተያዘው።

ጉዳዩን የተከታተለው የወምበራ ወረዳ ፍርድ ቤት  መጋቢት 9 በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ወጣት የ6 ወር እስራት ፈርዶበታል።

ይህን መረጃ በ @tikvahethMagazine ላይ የተመለከቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት " ቀልድ ነው ? ምን አይነት ፍርድ ነው ? ወንጀሉን ፍፁም የማይመጥን አሳዛኝ ፍርድ ነው " ብለውታል።

@tikvahethiopia

ፍትሕ የት ነሽ
አለሕግAleHig ️
የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው የ17 ዓመት ወጣት 6 ወር ተፈረደበት ይለናል የወምበራ ኮሚኒኬሽን። የ5 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው የ17 ዓመቱ ወጣት #በ6ወር እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል። የ10ኛ ክፍል ተማሪና የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ግለሰብ በአስገድዶ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በደብረ―ዘይት ከተማ…
ሕግ አላማው በዋናነት መቅጣት ሳይሆን ማስተማር እና በሌሎች እንዳይደገም መቀጣጫ ማድረግ ቢሆንም👈👈

ይህ ውሳኔ ግን አያስተምርም ፣ ወንጀሉ ድጋሜ እንዳይፈፀም ሊከለክልም አይችልም

የሴቶችን መብት ጥሰት ወንጀል ያቃለለ መስሎ ይሰማኛል። 🔊🔊🔊
በ 5 ዓመት ህፃን ላይ ለደረሰ የመደፈር ወንጀል #6 (ስድስት) ወር ቅጣት

#አለሕግ #Alehig
Any comment ....
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM