ከባንኮች የራሳችን ያልሆነን ገንዘብ ማውጣት፣ ማስተላለፍ ወይም ከሌላ ሰው መቀበል ያስጠይቃል?
#የወንጀልን_ተጠያቂነትን_ በተመለከተ
በሳይበር ምህዳር መስፋፋት ምክንያት አዳዲስ ወንጀሎችና አዳዲስ የወንጀል አፈፃፀም ስልቶች በመፈጠራቸው እንዲሁም በሃገሪቱ የኮምፒውተር ወንጀልን የሚገዙ መሰረታዊም ሆነ የሥነ-ሥርዓት ሕጎች በበቂ ሁኔታ ባለመኖራቸው ምክንያት የኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጅ ወጥቶ ሥራ ላይ ውሏል።
ይህ አዋጅ ታዲያ በኮምፒውተር አማካይነት የሚፈፀሙ የማታለል ወንጀል፣ ማለትም በተጭበረበረ መንገድ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት የኮምፒውተር ዳታን በመለወጥ፣ በማጥፋት ወይም ሌላ ማንኛውንም ጉዳት በማድረስ ሌላ ሰው ላይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ያደረሰ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና ከብር 10,000 እስከ ብር 50,000 በሚደርስ መቀጮ ወይም ወንጀሉ ከባድ በሆነ ጊዜ እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከብር 10,000 እስከ ብር 100,000 በሚደርስ መቀጮ እንደሚቀጣ ይደነግጋል።
ገንዘቡን ራሱ በተለያየ የኤሌክትሮኒክስ መንገዶች የፈፀመው ሰው በላይኛው ድንጋጌ ሊጠየቅ ይችላል። ገንዘቡ የተላለፈለት ወይም የተቀበለ ሰውስ?
የኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ የወንጀል ፍሬ ወይም ውጤት የሆኑ ንብረቶችን መያዝ፣ መደበቅ ወይም ማስቀመጥ ኃላፊነት እንደሚያስከትል በግልፅ ይደነግጋል። ይህ የመሸሸግ ወንጀል በሁለት መንገዶች ሊፈፀም ይችላል። የመጀመሪያው ወንጀለኞቹን ለመርዳት ወይም በቀጥታ ከወንጀል ድርቲቱ ጥቅም ለማግኘት ታስቦ ሲፈፀም ሲሆን ሁለተኛው ገንዘቡ የወንጀል ፍሬ መሆኑን ማወቅ ሲገባቸው በቸልተኝነት ወይም በሌላ ማናቸውም ምክንያት ገንዘቡን ተቀብሎ ይዞ መገኘት ነው።
ገንዘቡ የሚላክበት ምክንያት መኖሩን እና አግባብነቱን እንዳጣራ ሕጉ ይጠብቅብናል። የራሱን ገንዘብ የሚልክበት ምክንያት የሌለው ሰው ገንዘብ ሲያስተላልፍልን መጠየቅ እንዲኖርብን ያደርጋል። በተለይ የአንድ ባንክ ሥርዓት መበላሸቱን የሚገልፅ ዜና በማህበራዊ ሚዲያ እና ሌሎች የዜና ምንጮች በስፋት ተወርቶ ሲገኝ ገንዘቡ ተሰርቆ ሊሆን እንደሚችል ለመገመት የሚያስቸሉን አመላካች ነገሮች በመሆናቸው ከወንጀል ተጠያቂነት አናመልጥም። ገንዘቡ ከትክክለኛ ባለቤቱ በወንጀል ድርጊት አማካኝነት የተወሰደ መሆኑ ሲረጋገጥ እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ እስራት ሊያስቀጣ ይችላል።
ድርጊቱ በኮምፒውተር ሥርዓት አማካኝነት የተፈፀመ እንደመሆኑ መጠን በኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጁ ሊታይ ቢችልም፣ ከላይ ከተጠቀሱት ሁኔታዎች በተጨማሪ የአዋጁ ድንጋጌ ላይ ያለውን ቴክኒካል ቃላት አያሟላም የሚባልበት ሁኔታ ቢኖር ድርጊቱ መደበኛውን የስርቆት ወንጀልን ሊያቋቁም ይችላል።
በባንኩ የኮምፒውተር ሥርዓት ላይ ምንም ዓይነት ጥቃት ያላደረሰ ሰው፣ ነገር ግን 2ሺ ብር ሊያወጣ ጠይቆ ኤቲኤም ማሽኑ 5ሺ ብር ቢሰጠው ግለሰቡ ልዩነቱን እና የርሱ ያልሆነውን 3ሺህ ብር የመመለስ ግዴታ አለበት። ያንን ባያደርግ አግኝቶ በመደበቅ ወንጀል ሊጠየቅ ይችላል። ይህ ወንጀል አንድ ሰው ከህጋዊ መንገድ ውጪ ንብረት አግኝቶ በዚሁ ንብረት ያለአግባብ ለመበልጸግ በማሰብ ንብረቱን ለመደበቅ የሚፈጽመው የወንጀል ተግባር ነው፡፡ ማንም ሰው የማይገባውን ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የሌላ ሰው ንብረት የሆነውን በስህተት ወይም ባልታሰበ ድንገተኛ አጋጣሚ ነገር፣ ከባለንብረቱ ፈቃድ ውጭ በሆኑ ማናቸውም ሁኔታ ከባለቤቱ እጅ ወጥቶ በእጁ የሚገኝን ንብረት ወይም እቃ ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ካደረገ በወንጀል ያስጠይቀዋል፡፡ ይህንን የፈፀመ ሰው በመቀጮ ወይም በቀላል እስራት ያስቀጣል ሲል የወንጀል ህጉ ደንግጓል፡፡
ያለአግባብ መበልፀግ ህግ የውል፣ የንብረት እና ከውል ውጭ ያለ ሃላፊነት ህግ ክፍል በተጨማሪ የፍታብሔር ግንኙነትን የሚገዛ የህግ ክፍል ነው፡፡ ያለአግባብ መበልፀግ ህግ በመሰረታዊነት የሚመነጨው ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት መበልፀግ የለበትም ከሚለው መርህ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛው ሰው በሌላ ሰው ጉዳት ወይም ኪሳራ ምክንያት ያለአግባብ የበለፀገ እንደሆነ ጉዳት ወይም ኪሳራ ለደረሰበት ሰው ካሳ የመክፈል ግዴታ እንደሚኖርበት ይህ የህግ ክፍል ያስገድዳል፡፡
ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው የስራ ድካም ወይም የሌላ ሰው ሀብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ እና ባለሀብቱ ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ጥቅም ባገኘበት ልክ ለባለሀብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ካሳ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት ሕጉ ያስቀምጣል፡፡ ያለአግባብ መበልፀግ በመሰረታዊነት ሶስት ሁኔታዎችን ያካተተ ሲሆን አንድን ሰው በዚህ የህግ ክፍል በመክሰስ ካሳ ለማስከፈል እነዚህ ሶስት ሁኔታዎች በድምር መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1ኛ. ተከሳሽ በገንዘብ ሊለካ የሚችል ጥቅም ያገኘ መሆኑ፤
2ኛ ይህ ጥቅም የተገኘው በከሳሽ ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት መሆኑ እንዲሁም
3ኛ. የተገኘበት መንገድ አለአግባብ ወይም ምንም አይነት ህጋዊ መንገድ የማይቀርብበት መሆኑ ናቸው፡፡
Via #EthioLegalshield
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
አወ ያስጠይቃል!!!
የወንጀል እና የፍትሐብሔር ተጠያቂነት ሊኖር ይችላል።

#የፍትሐብሔር_ተጠያቂነትን_ በተመለከተ

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ! 0920666595
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

👍20❤3🔥3👎1👏1😁1