አሳሳቢው ወንጀል እና የአዲስ አበባ የራይድ ሹፌሮች
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በራይድ ታክሲ የትራንስፓርት አገልግሎት በሚሰጡ ሹፌሮች ላይ የሚፈፀም ግድያንና የከባድ ውንብድና ወንጀልን በተመለከተ የተጣሩ የምርመራ መዛግብትን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ
በራይድና በሌሎች የትራንስፓርት አገልግሎት ድርጅቶች አማካኝነት የሚሰጡ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ለከተማው ማህበረሰብ ቀልጣፋ የሆነ ትራንስፖርት በመስጠት የከተማውን ማህበረሰብ ችግር በመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል፡፡
አገልግሎቱ በትራንስፓርት ዘርፉ ከሚሰጠው ጥቅም ባሻገር ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት በዚህ ዘርፍ ተሰማርተው ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን በሚደግፉ አሽከርካሪዎች ላይ በተለያየ ጊዜ አሰቃቂ #ወንጀሎች ተፈጽመዋል፡፡
ወንጀሎቹ ከተፈፀሙበት ጊዜ ጀምሮ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ከተሰጠው ስልጣንና ተግባር አኳያ፤ በተቋሙ የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ በርካታ የወንጀል ምርመራዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በቅርቡም ከነሀሴ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከዐቃቤ ህግና ከመርማሪ ፖሊሶች የተውጣጣ የጋራ ቡድን በማዋቀር 9 የምርመራ መዝገቦችን በማደራጀት ጥልቅ የሆነ ምርመራ ሲደረግ ቆይቷል፡፡
በምርመራ ግኝቱ ማረጋገጥ እንደተቻለውም በራይድ የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ሹፌሮች ላይ የወንጀል ተግባሩን የሚፈፅሙት የውንብድና ቡድኑ አባላት አብዛኛውን ጊዜ ወንጀሉን ከመፈፀማቸው በፊት የትራንስፖርት አገልግሎት ፈላጊ በመምሰል፣ መልካም ግንኙነት በመፍጠር ተበዳይ በሆኑት ሹፌሮች ላይ እምነት እንዲያድርባቸው ካደረጉ በኋላ አብዛኛውን ጊዜ ከአዲስ አበባ ወደ ዝዋይ መስመር በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ ከተሞች የትራንስፓርት አገልግሎት እንዲሰጣቸው ያደርጋሉ፤ በኋላም አገልግሎቱን ወደ ሚያገኙበት አካባቢ ሹፌሮቹን በመውሰድ እና በአንዳንድ ሁኔታዎችም አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ ራቅ ወዳሉና ሰዎች ወደማይበዙባቸው ቦታዎች በምሽት በመውሰድ ሹፌሮቹን ለሽንት አቁምልን በማለት ካስቆሙ በኋላ ወንጀሉን የሚፈጽሙ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡
የምርመራ ግኝቱ እንደሚያመላክተው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡትን አሽከርካሪዎች በጋራ በመሆን በስለት በመውጋት፣ በገመድ አንገታቸውን በማነቅና በሽጉጥ ተኩሰው #በመግደል #አስክሬናቸውን በመጣል ተሽከርካሪዎቹንና ሌሎች ንብረቶችን እንደሚወስዱ ተረጋግጧል፡፡
በቡድን የተደራጁ የወንበዴ ቡድኖች በሹፌሮቹ ላይ ጥቃት በመሰንዘር የሚያሽከረክሩትን ተሽከርካሪና ሌሎች ንብረቶች ከወሰዱ በኋላ የወሰዱትን ተሽከርካሪ በዝቅተኛ ዋጋ ያለምንም ህጋዊ ሰነድ በመግዛት አይነታቸውን በመቀየር፣ ታርጋ በመለጠፍ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሌላ የተደራጀ ቡድን መኖሩም በምርመራ ተረጋግጧል፡፡ የምርመራ ቡድኑ በዚህ የውንብድና ቡድን ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹን ወንጀል ፈፃሚዎንና በውንብድና ተግባር የተወሰዱ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
ምርመራቸው በተጠናቀቁና ክስ በተመሰረተባቸው መዝገቦች ላይ እንደታየው ቡድኑ ሶስት የሚሆኑ ሰዎችን በመግደል ሟቾች ሲያሽከረክሩት የነበሩትን ተሽከርካሪና ሌሎች ንብረቶችን የወሰዱ ሲሆን በዚህም ሂደት ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ህይወት ጠፍቷል፡፡ በተመሳሳይም በሌሎች ምርመራቸው በሂደት ላይ ባሉ መዝገቦችም ንብረት ከመዘረፉ ባለፈ የሰው ህይወት መጥፋቱ ተረጋግጧል፡፡
የምርመራ ቡድኑ ባደረገው እልህ አስጨራሽና ጠንካራ ምርመራ በዚህ የወንበዴ ቡድን ውስጥ ሆነው ወንጀሉን በተደራጀ ሁኔታ ሲፈፅሙ የነበሩ ሰዎችን በመያዝ ከተደራጀው 9 የምርመራ መዝገቦች ውስጥ 6 መዝገቦችን በማጠናቀቅ በ12 ተከሳሾች ላይ እስከ ሞት ፍርድ ድረስ በሚያስቀጣ በከባድ የውንብድና ወንጀልና በህገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል ክስ የተመሰረተ ሲሆን በቀጣይም ምርመራቸው እየተከናወኑ በሚገኙ መዝገቦች ላይ ጥልቅ ምርመራ በማድረግ አጥፊዎችን በህግ የማስጠየቅ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በራይድና በሌሎች ድርጅቶች አማካኝነት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሹፌሮች በቡድን በመሆን አገልግሎት በሚጠይቁ ሰዎች ላይ #ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡
አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜም ስለደንበኛው ሙሉ መረጃ መጠየቅና መያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ ውጭ ወይም አዲስ አበባ ውስጥም ሆኖ ጭር ወዳለ ቦታ አገልግሎት በሚጠይቁ ሰዎች ላይ አጠራጣሪ ሁኔታ ካዩባቸው ለጥንቃቄ የሚረዱ ተግባራትን በመፈፀም፣ በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላቶች መረጃዎችን በመስጠት፤ በተደጋጋሚ እንደሚታየውም አገልግሎት በመስጠት ሂደት የተለየ ግንኙነት የሚፈጥሩ ደንበኞች ላይ ትውውቅ አለን በሚል መዘናጋት መፈጠር የሌለበት መሆኑን እና መሰል ክስተቶችም ሲያጋጥሙ ማህበረሰቡ አገልግሎቱን ለሚሰጡ ሹፌሮች ድጋፍ እንዲያደርግና ለፀጥታ አካላት መረጃ በመስጠት የዘውትር ትብብር እንዲያደርግ ስንል እንጠይቃለን፡፡
የፕሬስ መግለጫ
ከፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ
https://t.me/lawsocieties
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Please #Share በማድረግ ሂይወትን እንታደግ 🙏
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👉

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

የሽያጭ #ውል በኢትዮጵያ #ሕግ👈👈👈
የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ላይ ሲኖሩ የተለያዩ ህጋዊ ውጤት ያላቸውን ድርጊቶች ያከናውናሉ፡፡
ከነዚህም አንዱ ውል ሲሆን የሽያጭ የውል ደግሞ የውል አንዱ ዘርፍ ነው፡፡ የሽያጭ ውል በሻጭና በገዢ መካከል የሚፈፀም ስምምነት ሲሆን ሻጭና ገዢ የሚኖራቸውን መብትና ግዴታ የሚያካትት ነው፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ የሽያጭ ውል ምንነት፣ የሽያጭ ውል አመሰራረት እንዲሁም የሻጭና የገዢን ግዴታዎች እንመለከታለን፡፡
የሽያጭ ውል ምንነት
የሽያጭ ውል የጠቅላላው የውል ግዴታ አንድ አካል እንደመሆኑ የሽያጭ ውል ምንነትን ከማየታችን በፊት ስለ ውል ምንነት ማየቱ ተገቢ ነው፡፡ ውል ማለት ንብረታቸውን የሚመለከቱ ግዴታዎችን ለማቋቋም ወይም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ባላቸው ተወዳዳሪ ግንኙነት በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መሀል የሚደረግ ስምምነት እንደሆነ በፍትሐብሔር ህግ በቁጥር 1675 ትርጉም ሰጥቶታል፡፡ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ የኢትዮጵያ የውል ሕግ መሰረተ ሀሳቦች በሚለው መፅሀፋቸው ውስጥ “ውል አንድን ግዴታ ወይም ከዚሁ ግዴታ ጋር የተያያዙ ሌሎች በርከት ያሉ ግዴታዎችን የሚያቋቁም ተግባርን የሚያመለክት አነጋገር ነው” በማለት ተርጉመውታል፡፡ “በዚህ ግዴታ ባለገንዘብ የሆነው ወገን አንድ ነገር እንዲፈጸምለት የመጠየቅ መብት የሚኖረው ሲሆን ባለዕዳው ደግሞ አንድን ነገር የመፈጸም ግዴታ ይጠበቅበታል” በማለት አብራርተው ገልፀውታል፡፡
ወደ ሽያጭ ውል ስንመጣ "ሽያጭ" ማለት ሻጭ የሆነው አንዱ ወገን ገዢ ለሆነው ሌላው ወገን ዋጋው በገንዘብ የተወሰነ አንድ ነገር ገዢው ሊከፍለው ግዴታ በገባበት መሰረት ሊያስረክብና ባለሀብትነቱን ሊያስተላለፍ የሚገደድበት ውል እንደሆነ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2266 ላይ ተመልክቷል፡፡
የፀና ውል እንዲኖር መሟላት ያለባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች
በገዢና በሻጭ መካከል የሚደረገው ውል በሕግ ተቀባይነት እንዲኖረው ከዚህ የሚከተሉትን መሰረታዊ ጉዳዮች ማሟላት ይኖርበታል፡፡ እነዚህም የተዋዋይ ወገኖች የመዋዋል ችሎታ፣ የተዋዋይ ወገኖች ፈቃድ እንከን በሌለበት አኳኋን የተገለጸ መሆኑ፣ ተዋዋዮች የሚዋዋሉበት ጉዳይ ወይም ፍሬ ነገር ፀንቶ ባለ ሕግ ያልተከለከለ፣ ለመልካም ሥነ-ምግባር ተቃራኒ ነው ተብሎ በማኅበረሰቡ ውስጥ ያልተወሰደ፣ አፈፃፀሙ በተዋዋዮች አቅም ተግባራዊ ሊሆን የሚችልና በእርግጠኛነትም የተገለፀ እንዲሁም ሕጉ ውሉ የሚደረግበትን ፎርም በደነገገ ጊዜ የውሉ አቀራረጽ በተጠየቀው ፎርም የተዘጋጀ መሆኑ ናቸው፡፡ ከእነዚህ መስፈርቶች የአንዱ አለመሟላት በሻጭና በገዢ መካከል የተደረገውን ውል ውጤት አልባ ሊያደርገው የሚችል ስለሆነ ሻጭና ገዢ በጥንቃቄ ሊያስቡበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
የሽያጭ ውል አመሰራረት
እንደማንኛውም የውል ዓይነቶች የሽያጭ ውልም ተዋዋይ ወገኖች (ገዢና ሻጭ) በዕቃው ምንነትና ዋጋ ላይ ተነጋግረው ስምምነት ላይ ሲደርሱ የሽያጭ ውሉ ይመሰረታል፡፡ ይህም ማለት ገዢና ሻጭ በውሉ ፍሬ ነገሮች ላይ ስምምነታቸውን ሲገልፁ ውሉ እንደተፈፀመ ይቆጠራል ማለት ነው፡፡ አቀራረብና አቀባበል (Offer and Acceptance) የሚባሉት የውል ህግ መሰረታዊ አነጋገሮች ከተሟሉም ሽያጩ መፈፀሙን ያሳያል፡፡ ይህን አገላለፅ ወደ ሽያጭ ውል ስናመጣው አቀራረብ (Offer) የሚባለው ሻጭ ንብረቱን ለመሸጥ (የዋጋና ሌሎች ዝርዝሮችን አካቶ) ወደ ገበያ ሲያወጣ ማለት ሲሆን አቀባበል (Acceptance) የሚባለው ደግሞ ገዢ ንብረቱን ለመግዛት ፍላጎት ማሳየቱ እና ለመግዛት መወሰኑን የሚያሳይ ነው፡፡ እዚህ ላይ አቀራረብ የሚያደርገው የንብረቱ ሻጭ ብቻ ሳይሆን ገዢውም ዕቃውን ለመግዛት ፍላጎት ያለው መሆኑን ገልፆ ለባለንብረቱ ጥያቄ ቢያቀርብለት አቀራረብ (Offer) አደረገ ማለት ሲሆን ሻጩም ይኼን ተቀብሎ ለመሸጥ ሲስማማ አቀባበል (Acceptance) አደረገ ማለት እንችላለን፡፡
የፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 1681 መሰረት አንድ የሆነ ዓይነት ውል ውስጥ ለመግባት የሚፈልግ ሰው (ለምሳሌ፡- ለመግዛት ወይም ለመሸጥ) ለቀረበለት የውል ጥያቄ ፈቃዱን በቃል፣ በጽሑፍ ወይም በተለመዱ ጠቅላላ ምልክቶች ወይም ለውሉ መነሻ ከሆነው ምክንያት የተነሣ ግዴታ ለመግባት መፍቀዱን በማያጠራጥር አሠራር ለማስታወቅ የሚቻል ሲሆን ጥያቄ አቅራቢው ለውሉ አቀባበል የተለየ አሠራር ለመወሰን ይችላል፡፡
የሻጭ ግዴታዎች
ሻጭ የሚከተሉት ሶስት መሠረታዊ ግዴታዎች አሉበት፡-
ዕቃ የማስረከብ ግዴታ
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2273(1)፣ 2274 እና በተከታዮቹ መሰረት ሻጭ በውሉና በተጨማሪው ውስጥ የተመለከተውን ነገር ለገዢው በውሉ ልክ መስጠት ወይም ማስረከብ አለበት፡፡
የእቃውን ባለሀብትነትን የማስተላለፍ ግዴታ
የሽያጭ ውል ዋና ዓላማ የሚሸጠውን ዕቃ ባለሀብትነት ከሻጭ ወደ ገዥ ለማዛወር በመሆኑ በፍትሐብሔር ህጉ አንቀፅ 2273(2) እና 2281 መሰረት ሻጭ የሸጠውን እቃ ባለሀብትነትን ለገዢ የማስተላለፍ ግዴታ አለበት፡፡
ዋስትና የመስጠት ግዴታ
የሻጩን መድህንነት አስመልክቶ ሻጭ ባለሀብትነቱን ለገዢው ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆኑትን ተግባሮች ለመፈፀም ግዴታ እንዳለበት በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2281 እና 2282 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህም ሻጩ የሸጠውን ነገር በሙሉ ወይም በከፊል ይለቀቅልኝ የሚል ጠያቂ ቢመጣ ሻጩ መመለስ አለበት፡፡ ሆኖም ገዢው በገዛው ነገር ላይ ይለቀቅልኝ ባይ መኖሩን በውሉ ጊዜ አውቆ እንደሆነ ግን ሻጩ መጪውን ለመመለስ ቃሉን ሰጥቶ ካልተገኘ በቀር መድህንነት እንደማይኖርበት በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2283(1) ተደንጓል፡፡ ከዚህ የምንረዳው ገዢ ዕቃው የኔ ነው ባይ ሊነሳበት እንደሚችል ተረድቶ የሚመጣውን እቀበላለሁ ወይም እኔው እራሴ የኔ ነው ባዩን ሞግቼ እመልሳለሁ ብሎ ወዶና ፈቅዶ ከገባበት ሻጩ የኔ ነው ባዩን የመመለስ ግዴታ እንደማኖርበት ነው፡፡ ነገር ግን ገዢው ይለቀቅልኝ ባይ ወይም የኔ ነው ባይ ሊነሳበት እንደሚችል እያወቀ ወዶ ቢገባበትም ሻጭ ይለቀቅልኝ ባይ መኖሩን አውቀህ ብትገባም ይለቀቅልኝ ባዩን ለመመለስ እኔው ራሴ መድህን ነኝ የሚል የውል ግዴታ ገብቶ ከሆነ ግን ሻጭ በመድህንነት ከመጠየቅ አይድንም፡፡ በተጨማሪም ገዢው ይለቀቅልኝ ባይ መኖሩን የሽያጩ ውል በሚደረግበት ጊዜ ቢያውቅም ይለቀቅልኝ ባይነቱ ሊፈጠር የቻለው ሻጩ በሰጠው የዋስትና መያዣ ምክንያት ከሆነ ሻጩ ይለቀቅልኝ ባይ መኖሩን አውቀህ ስለገዛህ መድህንነት የለብኝም ሊል እንደማይችል በህጉ ቁጥር 2283(2) ተደንግጎ ይገኛል፡፡
የገዢ ግዴታዎች
ገዢም በበኩሉ የራሱ የሆኑ ግዴታዎች አሉበት፡፡ በዋናነት የገዥ ግዴታዎች ተብለው የሚታወቁት የዕቃውን ዋጋ የመክፈል፣ የገዛውን ነገር የመረከብ እና በውሉ የገባቸው ሌሎች ግዴታዎች እንደሆኑ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2303 እና ተከታዮቹ ሰፍሮ እናገኘዋለን፡፡
የዕቃውን ዋጋ የመክፈል ግዴታ ሲባል የገዥው ገንዘብ የመክፈል አቅም ያለው መሆንና የሚከፈለውን የገንዘብ መጠን ማዘጋጀቱን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን እንደየውሉ ዝርዝርና የአካባቢው ባህል በተለመደው መልኩ መክፍል ግዴታንም ያካትታል፡፡ ክፍያ የሚፈፀምበት ቦታና ጊዜም ወሳኝ በመሆኑ ክፍያው በውላቸው ላይ የተገለፀ ከሆነ በዛው ቦታ መፈፀም የሚገባው ይሆናል፡፡ በውላቸው ላይ ከፍያ የሚፈፀመው ሻጭ ዕቃውን ለገዥው በሚያስረክብበት ወቅት ነው የሚል ሀሳብ ካለበት ደግሞ ክፍያው የሚፈፀምት ቦታ ዕቃው የሚረከብበት ቦታ ይሆናል ማለት ነው፡፡

በውላቸው ውሰጥ እነዚህ ዝርዝሮች ከሌሉበት ግን ክፍያው የሚፈፀምበት ቦታ በሻጩ አድረሻ እንደሆነ በፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 2309 ተደንግጓል፡፡ ሽያጩ የዱቤ በሆነ ጊዜ ደግሞ ዋጋው መከፈል ያለበት በውሉ ተገልፆ ከሆነ በውሉ መሰረት ካልተገለፀ ግን ገዢው የገዛውን ነገር ከተረከበ በኋላ ሻጩ እንደጠየቀ ወዲያውኑ መሆን እንዳለበት በህጉ አንቀፅ 2311 ተደንግጓል፡፡
#ማጠቃለያ
በአጠቃላይ የሽያጭ ውል መሰረታዊ ሀሳቦች ከላይ የተገለፁት ሲሆኑ የሸያጭ ውል በእለት ተእለት ኑሯችን የምንተገብረው ህጋዊ ውጤት የሚያስከትል ድርጊት እንደመሆኑ በህጉ ዙሪያ ያለንን እውቀት በማዳበር እና ህጉ ተከትሎ በመንቀሳቀስ እራሳችንን ከአላስፈላጊ እንግልት መታደግ ይጠበቅብናል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
#ማጠቃለያ
በአጠቃላይ የሽያጭ ውል መሰረታዊ ሀሳቦች ከላይ የተገለፁት ሲሆኑ የሸያጭ ውል በእለት ተእለት ኑሯችን የምንተገብረው ህጋዊ ውጤት የሚያስከትል ድርጊት እንደመሆኑ በህጉ ዙሪያ ያለንን እውቀት በማዳበር እና ህጉ ተከትሎ በመንቀሳቀስ እራሳችንን ከአላስፈላጊ እንግልት መታደግ ይጠበቅብናል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
የውጭ ምንዛሬ
ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ተድርጓል።
ከዚህ ቀደም ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፎ በነበረው የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ማድረግ በማስፈለጉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዕቃዎች ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክና ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡
ማሻሻያ የተደረገባቸው ከውጭ የሚገቡ እቃዎች የሚከተሉት ናቸው ፦
1. በታሪፍ ቁጥር 9401. 9000 እና 9403. 9000 የሚመደቡ እቃዎች ክፍሎች ማምረቻ ግብአቶች፣
2. ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን በውጭ ምንዛሬ የመሸጥ ፍቃድ ያላቸው ሬስቶራንቶችና ሱፐር ማርኬቶች የራሳቸውን የውጭ ምንዛሬ ተጠቅመው የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፣
3. ባለ ኮከብ ሆቴሎች የራሳቸውን የውጭ ምንዛሬ ተጠቅመው የሚያስመጧቸው ዕቃዎችና
4. የቀረጥ ነጻ ሱቆች የሚያስመጧቸው ዕቃዎች
የውጭ ምንዛሬ ክልከላው የማይመለከታቸው መሆኑ ተገልጽዋል፡፡
ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ የ38 እቃዎች ዝርዝር በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወሳል (ለማስታወሻ ከላይ ተያይዘዋል) ።
ምንጭ፦ ገንዘብ ሚኒስቴር

ሰ-መ-ቁ 221716.pdf
824 KB
አሰሪና ሰራተኛ ህግ- ክፍያ ለዘገየበት የሚከፈል ቅጣት- አከራካሪ ክፍያ ሰ-መ-ቁ 221716
አብርሃም ዮሐንስ
የስራ ውል ከመቋረጡ በፊት ማስጠንቀቂያ በተለያየ መንገድ መስጠቱን የሚከራከር አሰሪ ፍርድ ቤት የማስጠንቀቂያ አሰጣጥ ስርዓቱ በህጉ አግባብ ባለመሆኑ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እንዲከፍል ሲወሰንበት ይህንኑ ክፍያ በማዘገየት በሚል ቅጣት ሊከፍል አይገባም።
ሰራተኛው የጠየቀው ክፍያ አከራካሪ ከሆነ አሰሪው ያመነውን ያህል በህጉ በተገለጸው ጊዜ ገድብ ውስጥ መክፈል እንዳለበት የአዋጁ በአንቀጽ 37 ያመለከታል። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው የክፍያው ዓይነትና መጠን እንደጉዳዩ ባህርይ የሚለያይ በመሆኑ አከራካሪ የሆነውን እና አከራካሪ ያልሆነውን በመለየት አሰሪው በህግ የተጣለበትን ግዴታ መፈጸም ይጠበቅበታል።
አብርሀም ዮሀንስ

Forwarded from Yehualashet Tamiru
It is to be recalled that the Ministry of Finance has banned 38 items from entering the country by restricting banks from opening L/C. Now, the Ministry of Finance amended this restriction on the following items:
• Inputs for production of items categorized under tariff classification No. 9401. 9000 (seats and others) and 9403. 9000 ( furniture and others)
• Those supermarkets and restaurants which have the license to receive payment in hard currency and import items by their own foreign currency
• Those ranked hotels imported items using their own hard currency
• Items imported by duty free shops
Source: Yehualashet Tamiru Tegegn

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁ 1234-2013 አንቀጽ 28
#ያስቀርባል /አያስቀርብም የሚወሰነው በአጣሪ ችሎት ሳይሆን ዋናውን ጉዳይ በሚያዩት አምስት ዳኞች የተሰየሙበት ችሎት ነው።
#ሶስት ዳኞች የተሰየሙበት ችሎት ስልጣኑ በሁለት ነገሮች ላይ ብቻ ነው
1- በአመልካቹ አቤቱታ ላይ የተጠቀሰው የህግ ስህተት በአዋጁ አንቀጽ ፪ ንዐስ አንቀጽ (፬) የሚወድቅ ስለመሆን ማጣራት። ለምሳሌ የምዘና ማስረጃን ጠቅሶ የሰበር አቤቱታ ካቀረበ አጣሪ ችሎቱ ውድቅ ያደርገዋል።
2- የሰበር አቤትታ የቀረበበት ውሳኔ በአዋጁ አንቀጽ ፲ አግባብ “የመጨረሻ ውሳኔ” መሆኑን ማጣራት
ሲጠቃለል በአዋጅ ቁጥር 1234 መሰረት ያስቀርባል/አያስቀርብም ስልጣኑ አምስት ዳኞች የሚገኙበት ዋናው ችሎት ነው።

መሠረታዊ የሕግ ስህተት እና የአጣሪ አጣሪ
(በአልማው ወሌ)
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 28 (3) ምን አስቦ ነው?
ሁለት ጊዜ የማጣራት ስራ እንዲሰራ?፣
ድሮውም ሆነ አሁን ያለው የሰበር አጣሪ ችሎትና የባለ 5/7 ዳኞች ሰበር ችሎት በተጨባጭ የሰሩት ወይም አሁን እየሰሩ ያሉት እንዴት ነው?፣
የሰበር አቤቱታ ወደ 5 ዳኞች ሰበር ችሎት በሰበር አጣሪ ችሎት ከተመራለት በኋላ የሰበር ተጠሪን ሳይጠራ ባለ 5 ዳኞች ሰበር ችሎት ጉዳዩ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ተብሎ ሊዘጋ ይችላልን?፣
አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩት ጭብጥ የሚለው በሰበር አጣሪ ነው ወይስ በባለአምስቱ ዳኞች ሰበር ሰሚ ችሎት?፣
ባለ ሶስት ደኞች ሰበር አጣሪ ችሎቱ ለተጠሪ መጥሪያ መላክ አይችልም ማለት ነው?፣
በዚህ ረገድ አሁን እየተሰራ ያለው አጣሪ ችሎቱ ጭብጥ መስርቶ ጉዳዩን ለባለአምስቱ ዳኞች እንዲቀርብ እና ተጠሪም በጭብጡ መሰረት መልስ በጽሁፍ እንዲሰጥበት ተገልጾ መጥሪያ ወጪ ማድረግ አይደለንም?...ከሆነስ ከሕግ ውጪ ነው የሚሰራው ማለት ነው?
በአጠቃላይ የተጠቃሹ ንዑስ ድንጋጌ አቀራረጽ የሰበር አቤቱታ በሚታይበት ስርዓት ውስጥ የማጣራቱ ሂደት ሁለት ጊዜ (በባለ ሶስት እና በባለ አምስት ዳኞች ሰበር ችሎት) ሊታይ እንደሚገባ፣ ጭብጥ መስርቶ ተጠሪን መጥራት የሚችለው ባለአምስቱ ዳኞች ሰበር ሰሚ ችሎት መሆኑን በሚያስገነዝብ መልኩ የተደነገገ ሁኖ የሚታይ ሲሆን በተጨባጭ እየተሰራ ያለው ግን እንደ ንዑስ ድንጋጌው አገላለጽና አነጋገር አይደለም፡፡
ስለሆነም ድንጋጌው ሕጉን በማርቀቅ ሂደት በተከሰተ ግድፈት (Poor Drafting) የተቀመጠ ነው? ወይስ ሆነ ተብሎ የማጣራቱን ሂደት ጥብቅ ለማድረግ የመጣ አዲስ አካሄድ ነው?፣ ባለ 5 ዳኞች ሰበር ሰሚ ችሎት ባለ 3 ዳኞች የሰበር አጣሪ ችሎት ዳኞች በአዋጁ አንቀጽ 2 (4) እና 10 መሰረት ጉዳዩ በሰበር ችሎቱ ሊታይ የሚገባው ነው ብለው ከወሰኑ በኋላ ይኼው ውሳኔያቸው በባለ 5 ዳኞች ታይቶ ውድቅ የሚሆን/ሌላ ጭብጥ ተመስርቶ ተጠሪ የሚጠራ ከሆነ የባለ 3 ዳኞች አጣሪ ችሎት አስፈላጊነትስ የቱ ላይ ነው?...... ብዙ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ይመስለኛል፡፡
ለማንኛውም የአዋጁ ድንጋጌ ይዘት የሚከተለውን ይመስላል፡፡
1234/2013
አንቀጽ 28 (1)፡-
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሰበር ችሎት የሚቀርቡ ጉዳዮችን ክርክር አመራር ሥነ ሥርዓትን በተመለከተ የሚያወጣው ደንብ እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲ መሠረት አቤቱታ በሰበር የሚሰማው አስቀድሞ ሶስት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የተሰየሙበት ችሎት ውሳኔው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ ንኡስ አንቀጽ (፬) እና አንቀጽ ፲ ላይ በተመለከቱት መሠረት በሰበር ችሎት መታየት አለበት ብሎ ሲወሰን ነው፡፡ ብሎ ይደነግጋል፡፡
ንዑስ ቁጥር ሶስት ደግሞ፡-
በአማርኛው ቅጅ፡-
-የሰበር ችሎቱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሰረት የተመራለትን ጉዳይ መርምሮ አቤቱታ በቀረበበት ጉዳይ ላይ ያስቀርባል ብሎ ከተረዳ ጭብጥ በመያዝ በተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት በአመልካች ከቀረበው የሰበር ማመልከቻ እና መጥሪያ ጋር ይልካል፡፡ ይላል፡፡
በእንግሊዝኛው ቅጅ ደግሞ፡-
-When the Cassation Division to which the application is referred concludes upon examination of the application that the case has a merit, it shall frame issue and send the same with the Cassation application and summon to the respondent to reply in writing. ብሎ ያስቀምጣል፡፡
ሌላው የሠበር አጣሪ የሰበር አቤቱታውን በቃል ሲሰማ የሕግ ባለሙያ ያልሆነ አቤት ባይን እስኪ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አስረዳ ብሎ የሚጠይቅበት አሰራር የሕግ መሠረቱ ምንድን ነው?፣ ከሰበር ዓላማ ጋርስ ይሄዳል?
አጣሪ ችሎቱ አቤቱታውን ከሠማ በኋላ ውጤቱን በሬ/ጽ/ቤት ተከታታሉት !የሚለው አሰራር ምንጩ ሕግ ነውን? ፣ ለአቤቱታ አቅራቢ ጥሩ ያልሆነ የምርመራ ውጤቱ ወዲያውኑ ቢነገረው ሊደነግጥ/ሊጮህ ይችላል ብሎ አስቦ ይሆን? በግልጽ ችሎት የመሰማት መብትስ ውጤቱን መስማትንም አያካትትምን?
ለነገሩ አያስቀርብም የሚል ውጤት ወዲያው ሲነገራቸው መድኃኒት የጠጡና የወደቁ፣ ግቢውን በጩኸት የቀወጡ ....ተዝለፍልፈው የወደቁ ...ባለጉዳዮች ያጋጥሙ እንደነበር አስታውሳለሁ:: የሆነ ሁኖ ሕግ ገዥ መሆን የለበትም ወይ?
ባለ አምስት ዳኞች ችሎትስ የፍርድ አጻጻፍና አገላለጽ ሥርዓቱ በልማድ/ከመደበኛው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ) የመጣ ነው ወይስ ችሎቱ በአሰራር ያዳበረው?.....የልዩነት ሐሳብ አጻጻፍና አገላላጽስ ተገቢነት አለው?....ወዘተ
የዳኞች አመዳደብስ?.......
NB:_
የኢትዮጵያ የሠበር እና የአስገዳጅ ሕግ ትርጉም ስርዓት በሚለው መጸሐፌ(coming soon)
የእኔን አቋም በዝርዝር አስቀምጬአለሁ!

.......👇👇👇👇👇👇👇
በፍትህ ስርዓቱ ስላጋጠመው አደጋ የመፍትሄ አቅጣጫ እና
ለዳኞች እና አቃቤ ህጎች ፍልሰት ምክንያቶቹ እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫዎች‼️
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
እሁድ 2:30 ቀጥታ ስርጭት
🔘 Live on Telegram 👈👈
#በአለ_ህግ ቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን።
ሼር በማድረግ ላልሰማ ያሰሙ ወደ ወይይቱ ይጋብዙ👆👆👆
የእለቱ እንግዳችን
👇👇👇👇👇👇👇👇
"አቶ ወንድወሰን ዮሐንስ
በሀዋሳ ዪንቨርሲቲ የህግ መምህር
የህግ አማካሪና ጠበቃ
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ዳኛ እና በህግ ሙያ ከ15 አመት በላይ ልምድ ያላቸው.......🙏
ከባለፈው ሳምንት የቀጠለ.......
ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
👉 https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig
Watch "Ale_Hig🔴አለ_ህግ" on YouTube
https://youtube.com/channel/UCXYKAPt4crrhEx62KvcPzBw
በፍትህ ስርዓቱ ስላጋጠመው አደጋ የመፍትሄ አቅጣጫ እና
ለዳኞች እና አቃቤ ህጎች ፍልሰት ምክንያቶቹ እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫዎች‼️
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
እሁድ 2:30 ቀጥታ ስርጭት
🔘 Live on Telegram 👈👈
#በአለ_ህግ ቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን።
ሼር በማድረግ ላልሰማ ያሰሙ ወደ ወይይቱ ይጋብዙ👆👆👆
የእለቱ እንግዳችን
👇👇👇👇👇👇👇👇
"አቶ ወንድወሰን ዮሐንስ
በሀዋሳ ዪንቨርሲቲ የህግ መምህር
የህግ አማካሪና ጠበቃ
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ዳኛ እና በህግ ሙያ ከ15 አመት በላይ ልምድ ያላቸው.......🙏
ከባለፈው ሳምንት የቀጠለ.......
ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
👉 https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig
Watch "Ale_Hig🔴አለ_ህግ" on YouTube
https://youtube.com/channel/UCXYKAPt4crrhEx62KvcPzBw
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
201235.pdf
833.1 KB
በሁከት ይወገድልኝ ክርክር የማይስተናገዱ ጉዳዮች
Abrham Y
ውል እንዲፈርስ ሰ/መ/ቁ 201235
ሁከት እንዲወገድ በቀረበ ክስ ላይ ለይዞታው መነሻ የሆነ ሽያጭ ወይም ሌላ ውል እንዲፈርስ የተጠየቀ ዳኝነት በሌለበት ሁኔታ ውሉ ፈርሶ ተዋዋይ ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ ፍርድ ሊሰጥ አይገባም።
የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሊቀርብ የሚችለው በይዞታው በእውን በሚያዘው ሰው ሰላማዊ የይዞታ አጠቃቀም ላይ ችግር ወይም መሰናክል ሲፈጠር ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1140 እና 1149 ድንጋጌዎች ይዘት መረዳት ይቻላል። በዚህ መልኩ ለቀረበው ክስ የሚሰጠው ዳኝነትም የተነሳው ህውከት እንዲወገድ እንዲሁም ስለደረሰ ጉዳት ኪሳራ እንዲከፈል ሊሆን ይችላል። በተለይ ተከሳሽ አድራጎቱን የሚፈቅድ መብት እንዳለው በፍጥነትና በማይታበል ዓይነት ካላስረዳ በቀር ሁከቱ እንዲወገድ እንደሚታዘዝ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1149(3) ሥር ተመልክቷል። በአንፃሩም ሁከቱን ፈጠረ ከተባለው ሰው ጋር የተደረገ በውል ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ካለ ግንኙነቱ የሚገዛበት የውልና የህግ አግባብ ተለይቶ ራሱን ችሎ ዳኝነት ሊሰጥበት ይገባል።
ፍ/ብ/ህ/ቁ 1149(3)፤ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 182(2)

አዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አዲስ የስራ ማስታወቂያ በ0 አመት እና በልምድ በተለያዩ የስራ መደቦች
35 Positions
Deadline: Nov 25, 2022
35 Positions
Deadline: Nov 25, 2022
ስለ ህግ ጉዳይ መረጃ እና ማብራሪያዎች ከፈለጉ
ይህንን የዩቱብ ቻናል ሰብስክራብ አድርጉ እንዲደረግ ለሌሎች አጋሩ።
please, Subscribe‼️🙏
https://www.youtube.com/@Lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆
"Ale_Hig🔴አለ_ህግ" on YouTube
👇👇👇👇👇👇

📌New Vacancy Abyssinia bank S.c .
Position 3: Administrative Assistant
Position 4: Foreclosure Officer
Position 5: Surveillance Officer
Position 6: Senior Attorney
📌For More Detail
https://lucyjob.com/job/abyssinia-bank-s-c-6-positions/

LucyJob
Abyssinia Bank S.C | 6 positions - LucyJob
Abyssinia Bank S.C wants to hire qualified applicants to the following positions
#ተከሳሽ_በሌለበት_የወንጀል_ክስን_ማየት፣
በመርህ ደረጃ ክስ መሠማት ያለበት ተከሳሽ ባለበት ነው፡፡ በወንጀል ተጠርጥሮ የተከሰሰ ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱ ደርሶትና ተረድቶት የመሰማት ሕገ መንግሥታዊ መብት እንዳለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንሥግሥት አንቀጽ 2ዐ ደንግጓል፡፡ ይህ ማለት ግን የወንጀል ክስ ሁሉ ተከሳሽ ፍርድ ቤት ካልቀረበ ታይቶ አይወሰንም ማለት አይደለም፡፡
በሕግ ተለይተው በተመለከቱ ወንጀሎች ላይ ተከሳሽ በሌለበትም ክሱን መርምሮ መወሰን ይቻላል፡፡ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ አራተኛ መድሐፍ አንቀጽ 2 ልዩ ሥነ ሥርዓት በሚለው በምዕራፍ አንድ ቁጥር 160/2/ ሥር ነገሩ ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን ተከሳሽ ካልቀረበ ወይም ለመቅረቱ በቂ ምክንያት የሚሰጥለት እንደራሴ ካልቀረበ እንዲያዝ ትዕዛዝ ፍ/ቤት እንደሚሰጥ ይደነግጋል፡፡ በዚህ ትዕዛዝ መሠረት መፈፀም ካልተቻለ ተከሳሹ በሌለበት ነገሩን ለመስማት ፍ/ቤቱ እንደሚያስብበት የዚሁ ቁ. 160/3/ ያስቀምጣል፡፡ ከዚህ መርህ ሁለት ነጥቦችን እናያለን፡፡ ተከሳሽ ሲቀር የመጀመሪያው የፍ/ቤቱ ተግባር እንዲያዝ ማዘዝ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሌለበት ጉዳዩን ለማየት ማሰብ ናቸው፡፡
አንድን የወንጀል ክስ ተከሳሽ በሌለበት መስማትና መወሰን የሚቻለው በቁ. 161/2/ መሠረት ከ12 ዓመት በማያንስ ጽኑ እሥራት የሚያሳስር ወንጀል የሠራ ወይም በቀድሞ ወ/መ/ሕግ ቁ. 354-365 በአዲሱ የወንጀል ሕግ ቁ. 343 እስከ 354 ድረስ ያሉ ወንጀሎች ፈጽሞ ጽኑ እሥራት ወይም ከ5ዐዐዐ ብር በላይ በሚያስቀጣ ወንጀል የተከሰሰ ሲሆን እና እንዲሁም በውጭ ሀገር ጥገኛ ሆኖ ጥገኛ ያደረገው ሀገር አሳልፎ ያልሰጠው እንደሆነ ነው ቁ. (161/3/) ተከሳሹ በቁ. 160/2/ ካልቀረበ ወይም ለመቅረቱ በቂ ምክንያት ካልተሰጠና ወንጀሉ በቁ. 161/2/ እና /3/ የተመለከተው ከሆነ ክሱ በሌለበት እንዲሰማ ይታዘዛል፡፡ በቁ. 162 መሠረት ፍ/ቤት በጋዜጣ ማስታወቂያ ተከሳሽ እንዲጠራ የሚያዘው ነገሩ እንዲሰማ ቀጠሮ በተሰጠበት ቀን ባይቀርብ በሌለበት ጉዳይ እንዲታይ በታዘዘው መሠረት ቀጥሎ እንደሚታይ ለማስታወቅ ነው፡፡ ከጋዜጣ በተሻለ በሌላ መንገድ መጥሪያው ለተከሳሽ ሊደርስ ይችላል ከተባለም አማራጩ ለፍ/ቤት የተተወ ነው፡፡
በተግባር የሚታየው አሠራር የተለየ ሊመስል ይችላል በቁ. 161 የተመለከቱት ሁኔታዎች በተሟሉበትም ቢሆን ፍ/ቤት የተከሳሽን ጉዳይ በሌለበት ለማየት የሚወሰነው በጋዜጣ ማስታወቂያ ጥሪ ካደረገ በኋላ ነው ምናልባትም ይህ አሠራር የተከሳሹን መብት በተሻለ መንገድ ይጠብቅለታል ከሚል የመነጨ ይመስላል፡፡ ነገር ግን ፍ/ቤቱ ተከሳሹ የቀረው ያለበቂ ምክንያት መሆኑን ካረጋገጠ በጋዜጣ ጥሪ የሚያደርግበት አግባብ የለም፡፡
በዚህ ሁኔታ በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ የተፈረደበት ሰው ፍርዱ ውድቅ እንዲደረግለት ፍርዱን ባወቀ በ3ዐ ቀን ውስጥ ለፈረደው ፍ/ቤት ማመልከት ይችላል (ቁ. 164,197,198) ማመልከቻውም ተቀባይነት የሚያገኘው ተከሳሹ ፍ/ቤት ያልቀረበው መጥሪያው ስላልደረሰው ወይም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የቀረ መሆኑን ማስረዳት ከቻለ ብቻ ነው፡፡ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ምንድነው የሚለውን የመወሰን ኃላፊነት የፍርድ ቤቱ ነው፡፡ ማመልከቻው ተቀባይነት አግኝቶ ፍ/ቤቱ በሌለበት የሰጠውን ውሣኔ ውድቅ ካደረገው ጉዳዩ/ ክሱ እንደገና በሌላ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት እንዲታይ ይታዘዛል ቁ. 202፡፡
በሌለበት የተፈረደበት ፍርድ እንዲነሳለት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ የተደረገበት ተከሳሽ ይግባኝ ማለት የሚችለው በቅጣቱ ላይ ብቻ ነው፡፡