አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
። የወራሽነት ደረጃና የውርስ ህግ።።።።።

በፍትሀብሔር ሕግ ቁጥር 842-856

1. የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች

የሟች ልጆች በመጀመሪያ ደረጃ የሟች ወራሾች ናቸው ፡፡ ከውርሱም እያንዳንዱ ትክክል ድርሻ ይቀበላሉ፡፡ ፡፡ የሟች ልጆች ወይም ከልጆቹ አንዱ ሞተው እንደ ሆነና ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ትተው እንደ ሆነ በነሱ ምትክ ሆነው ይወርሳሉ ፡፡

2. ሁለተኛ ደረጃ ወራሾች

ሟች ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ያልተወ እንደ ሆነ አባትና እናቱ ወራሾች ይሆናሉ፡፡ አፈጻጸሙም ፡ የሟች አባትና እናት የውርሱን ንብረት እኩል በእኩል ይካፈላሉ፡፡ ከአባት ከእናት አስቀድሞ የሞተ ቢኖር የነሱን ፈንታ ልጆቻቸው ወይም ሌሎች ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆቻቸው እነሱን ተተክተው ይወርሳሉ፡፡ከነዚህ መስመሮች በአንዱ መስመር ያለው ወራሽ ቢታጣ ውርሱ በሙሉ በሌላው መስመር ላለው ወራሽ ይሰጣል፡፡

3. ሶስተኛ ደረጃ ወራሾች

ሟቹ ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ወይም አባት ወይም እናት ወይም የነርሱ ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆች የሌለው እንደ ሆነ አያቶች ወራሾች ይሆናሉ፡፡ የውርሱ እኩሌታው በአባት መስመር ላሉ አያቶች ወይም ወደታች ለሚቆጠሩ ተወላጆቻቸው ይሆናል የቀረው የውርሱ እኩሌታ በእናት መስመር ላሉ አያቶች ወይም ወደታች ለሚቆጠሩ ተወላጆቻቸው ይሆናል፡፡ በአባት ወይም በእናት የትውልድ መስመር የዘር ተከታታይ ሳይኖረው የሞተ አያት ድርሻውን ለዚሁ መስመር ወራሾች ይተላለፋል፡፡ አንድ የትውልድ መስመር የዘር ተከታታይ ሳይኖራቸው የሞቱ አያቶች ማናቸውም የውርስ ሃብት ሁሉ ለሌላው ወገን የዝምድና መስመር ወራሾች ይተላለፋል::

4. አራተኛ ደረጃ ወራሾች

የሦስተኛ ደረጃ ዘመድ ወራሾች የሌሉ እንደሆነ የሟቹ ቅድመ አያቶች ወራሾቹ ይሆናሉ፡፡ የውርሱ እኩሌታ የአባት መስመር ለሆኑ ቅድመ አያቶች ወይም ለተወላጆቻቸው ይሰጣል ፡ ቀሪው እኩሌታ ደግሞ የእናት መስመር ለሆኑ ቅድመ አያች ወይም ለተወላጆቻቸው ይሰጣል ፡፡

5. አምስተኛ ደረጃ ወራሽ

ዘመዶች የሌሉ እንደሆነ የሟቹ ሃብት ወራሽነት ለመንግስት ይተላለፋል፡፡

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
https://t.me/lawsocieties
#Alehig #አለ_ህግ #lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Live stream started
Live stream finished (2 hours)
ስለ ፍርድ አፈጻጸም.pdf
415.3 KB
ስለ ፍርድ አፈጻጸም

በዚህ አጭር ጽሑፍ የተብራሩ ሥነ-ሥርዓታዊ ጉዳዮች፡-

👉 ፍርድ እንዲፈጸም ስለሚቀርብ ማመልከቻ

👉 የፍርድ ባለዕዳውን ስለመመርመር

👉 ለፍርድ አፈጻጸም ንብረትን ስለማስከበር

👉 በተከበረ ወይም በተያዘ ንብረት ላይ ሦስተኛ ወገኖች የሚያቀርቡት መቃወሚያ

👉 ለፍርድ አፈጻጸም ንብረትን የመሸጥ ሥነ-ሥርዓት
https://t.me/lawsocieties
።።።።። Before You Judge...።።።።።

People called him madman but I was surprised when he moved close to me and said, “can I ask you a very important question?”
I nodded in acceptance and then he asked, “am I a madman?”
The obvious answer, from a sane person will be, "no", and that was what I said.
“Thank you!”, he replied.
Then he said, “just because I don’t see things the way other people do, does that make me a madman?”
"No", I answered again.

He bent down, wrote “W” and asked me what he wrote.
At this point, I was already feeling ashamed, getting involved in a lengthy conversation with him.
In a hurry to leave, I said “w", but I was amazed when he replied to my answer, “You only saw 'W', because of the angle at which you are looking at it. If you turn upside down, you'll see “M”. If you look from the right side, it is “3”, and looking at it from the left side, it is “E”.

The fact that I don’t see things at the perspective that everyone is seeing it doesn’t make me a madman, he said. Then he left.

I pondered for so long about this and its application to life.
Because we act and relate to people based on the perspective at which we are looking at their situation. Have you taken your time to look at other possible perspectives?

I then decided that, before I get angry with, or act against, or judge anyone that has done something unfavourable to me, I will view it in at least three possible perspectives;

1. My own perspective,
2. His own perspective and
3. Others perspective'.


So, before you judge people, before you rage your anger on them, take a little time to view their angle or perspective, and, if you still cannot see a reasonable reason, then you may act REASONABLY!"
via hope Africa
https://t.me/lawsocieties
Vacancy title:
Legal consultant for Transaction Advisor


 Type: FULL TIME , Industry: Law, Public Safety, Corrections and Security , Category: Legal ]

Jobs at:
Clinton Health Access Initiative

Deadline of this Job:
03 November 2022  

Duty Station:
Within Ethiopia , Addis Ababa , Horn of Africa

Summary
Date Posted: Tuesday, October 25, 2022 , Base Salary: Not Disclosed.

Skills and Attributes
• Advanced knowledge of Ethiopian public, investment, business and commercial law, prior experience in conducting legal due diligence for Public Private Partnership projects;
• Direct work experience on ‘Transaction Advisory’ role for PPP projects and familiarity with private sector engagement in PPP projects;
• Having experience of drafting or reviewing PPP agreements.
• Strong professional link with global legal consultants experienced in PPP transactions;
• Detailed-oriented ability to work at a fast pace and meet deadlines;
• Strong writing skills with ability to synthesise and articulate information;
• Demonstrated ability to set priorities and work both independently and collaboratively;
• Ability to function and communicate professionally and effectively;
• Language: The consultant must have an excellent knowledge of English, including ability to set out a coherent argument in presentations and interactions. Capacity to communicate fluently with different stakeholders (civil society, government authorities, local communities, project staff)
• Practical experience in complaint management, strategic planned of procurement for public organizations.
• Extensive experience in Ethiopian data set and the Ethiopian context; Experience in formulating development strategies and policies.
• Computer skills; full command of Microsoft applications (Microsoft word, excel and power-point) and common internet applications will be required.

Work Hours: 8

Experience in Months: 84

Level of Education: Associate Degree
Job application procedure

How to Apply

CHAI-EthiopiaHR@clintonhealthaccess.org and/ Or www.ethiojobs.net 


https://t.me/lawsocieties
You tube ቸናላችንን Subscribe ስታደርጉ እከሌ በማለት ስማችሁን ጠቅሶ Subscribe አድርጓል ብሎ በኢሜል መልዕክት ስለሚያደርሰን እስከ አሁን ድጋፋችሁን በተግባር ሰብስክራብ በማድረግ ከጎናችን የቆማችሁ እናመሰግናለን።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCXYKAPt4crrhEx62KvcPzBw
You tube ቸናላችንን Subscribe
ስላደረጋችሁ እናመሰግናለን።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCXYKAPt4crrhEx62KvcPzBw
#የገቢ_ግብር
የገቢ ግብር  ከሚባሉት መካከል :- ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ላይ የሚጣል ግብር ፣ ከንግድ ከሚገኝ ትርፍ ላይ የሚጣል ግብር ፣ ከቤት ኪራይ ከሚገኝ ገቢ ላይ የሚጣል ግብር ፣ የፈጠራ መብትን በማከራየት በሚገኝ ገቢ ላይ የሚጣል ግብር ፣ ከእድል ሙከራ በሚገኝ ገቢ ላይ የሚጣል ግብር  ፣  ከአክሲዮን ትርፍ ድርሻ በሚገኝ ገቢ ላይ የሚጣል ግብር፣ የተወሰኑ የካፒታል ንብረቶችን በማስተላለፍ ከሚገኝ ገቢ ላይ የሚጣል ግብር ይጠቀሳሉ ::

ለምሳሌ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ላይ የሚጣልን ግብር ብንመለከት ::

በየወሩ ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ምጣኔ  የሚገኝ ገቢ በብር.         
      
      
      
0-600. 👉👉👉👉👉👉 👉👉0%
601-1,650.  👉👉👉👉👉 10%
1,651-3,200. 👉👉👉👉👉  15%
3,201-5,250.  👉👉👉👉 20%
5,251-7,800.  👉👉👉👉👉 25%
7,801-10,900. 👉👉👉👉 30%
ከ10,900 በላይ.  👉👉👉👉 35%


https://t.me/lawsocieties
ACSO-User-Manual-AMH-1.pdf
1.2 MB
የበጎ አድራጎት ማህበራትን መመስረት ለምትፈልጉ የህግ ማእቀፉን የሚገልጽ መመሪያ

የዋና ዳይሬክተሩ መልእክት
ማስተባበያ

ምዕራፍ 1 : መግቢያ
አዲስ የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊነት
በአዲሱ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 1113/2010 የተደረጉ አንኳር ለውጦች

ምዕራፍ 2 : የተፈፃሚነት ወሠን

ምዕራፍ 3 : የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ
የኤጀንሲው አላማዎች
የኤጀንሲው ስልጣንና ሃላፊነት
የኤጀንሲው አደረጃጀት
ቦርዱ
ዳይሬክተሩና ምክትል ዋና ዳይሬክተር

ምዕራፍ 4 : ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምስረታ እና ምዝገ ባ መርሆዎች
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚቋቋሙበት መርሆዎች
የምዝገባ ሂደት

ምዕራፍ 5 : የበጎ አድራጎት ድርጅትና ማህበራት አይነቶች
የውጭ እና ሀገር በቀል ድርጅቶች
የውጭ ድርጅቶች
የሀገር በቀል ድርጅቶች

ምዕራፍ 6 : በአዲሱ አዋጅ የተካተቱ የሰራ ጉዳዮች
የስራ ነፃነት
ሀብት፣ የማፈላለግ፣ የመቀበል እና የመጠቀም መብት ውስጣዊ የፋይናንስ ቁጥጥር ስርዓት
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አመራር
ሪፖርት እና ቁጥጥር የሪፖርት አይነቶች እና የሚቀርብበት ጊዜ ሪፖርት እርምጃዎች
መዋሃድ፣ መከፈል እና መለወጥ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ማስጠንቀቂያ እገዳ መፍረስ እና ከመዝገብ መሠረዝ የመሰማት መብት የመፍረስ ውጤቶች ራስን የማስተዳደር ማዕቀፍ
ማውጫ
@lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#የሥራማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሥሩ ለሚገኙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ጀማሪ ባለሙያዎችን /Intern/ በኮንትራት ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

በዚሁም መሠረት

- በህግ፣ በኮምፒውተር ሳይንስ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በኮምፒውተር ኢንጅነሪንግ፣ በሶሺዎሎጂ፣ ሶሻል ወርክ፣ በህዝብ አስተዳደር፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በሰው ኃብት አስተዳደር፣ በቢዝነስ ሊደርሺፕ፣ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በግዢ እና ንብረት አስተዳደር፣ በጋዜጠኝነት እና ስነጽሁፍ፣ በግራፊክስ ዲዛይን፣ በፖለቲካል ሳይንስ እና አለምአቀፍ ግንኙነት እንዲሁም ተያያዥ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው/ያላት

- አማካይ የመመረቂያ ውጤታቸው 3.5 እና ከዛ በላይ የሆነ፤

- ጥሩ የሆነ የአማርኛ እና የእንግሊዘኛ ቋንቋን ክህሎት (መናገር፣ መጻፍ እና ማንበብ) ያለው/ያላት፤

- የማይክሮሶፍት ኦፊስ (MS Word, Excel, Outlook, and PowerPoint) እውቀት እና በአግባቡ የመጠቀም ችሎታ ያላት/ ያለው፤

- የተቋሙን ደንብና መመሪያ የሚያከብር/ የምታከብር፤

- የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፤

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ቦርዱ ገልጿል።

ለመመዝገብ  https://forms.office.com/r/HvBrmNfKaX

* ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ

* ከአማርኛ በተጨማሪ ሌሎች የሀገር ውስጥ ቋንቋዎችን መናገር፣ መጻፍ እና ማንበብ የሚችሉ አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡
#tikvahethmagazine
የቅድመ ግብር ክፍያ ስርዓት (1).pdf
2.9 MB
ስለ ቅድመ ግብር ክፍያ ስርዓት (WITHHOLDING) ለአዲስ ግብር ከፋዮች የተዘጋጀ ማብራሪያ

#ethiopia #Tax 🇪🇹
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Entrust🔷ETC)
#አለ_ህግ የእናንተን ድጋፍ የሚፈልግበት ጊዜ አሁን ነው።
የአለ ህግን ዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራብ (Subscribe) በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩን። 🙏👁‍🗨👁‍🗨👁‍🗨👁‍🗨👁‍🗨

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCXYKAPt4crrhEx62KvcPzBw

#Ale_Hig #አለ_ህግ @Lawsocieties

Subscribe our youtube.
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCXYKAPt4crrhEx62KvcPzBw
ℹ️ #በጥፋት_ከሥራ_የሚያሰናብቱ_በቂ_ምክንያቶች ⤵️

1/ የሥራ ሰዓት አለማክበር

የሥራ ሰዓት አለማክበር ሲባል በሥራ መግቢያ ሰዓት ማርፈድ፤ ከሥራ መውጪያ ሰዓት ቀደም ብሎ መውጣትና በሥራ ሰዓት የሥራ ቦታን ጥሎ መሄድን ያጠቃልላል፡፡ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 አንቀጽ 27(1) ሀ መሠረት 👉በሥራ ውሉ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች ውጭ ሠራተኛው የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በስድስት ወር ውስጥ በጠቅላላው ለስምንት ጊዜ የስራ ሰዓት ያላከበረ ከሆነ የሥራ ውልን ለማቋረጥ አሠሪው መብት ይኖረዋል ::

2/ ከሥራ መቅረት

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 ከተመለከቱ እረፍቶች እና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ውጭ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው #በስድስት ወር ውስጥ ለአምስት ቀናት ከስራ
መቅረት፤ የሥራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ እንሚያቋርጥ በአዋጁ አንቀጽ 27(1) ለ ተመልክቷል፡፡

3/ ማታለል ወይም ማጭበርበር

የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት በዋነኛነት በመተማመን ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ ሠራተኛው ታማኝ ሆኖ የመገኘት ግዴታውን ወደ ጎን በመተው በአሠሪው ላይ የሚፈጽማቸው የማታለልና የማጭበርበር ድርጊቶች የሥራ ውሉን ለማቋረጥ በቂ ተደርገው የመወሰዳቸው አግባብነት የሚያከራክር አይሆንም፡፡ ይሁን እንጂ ማታለል ወይም ማጭበርበር በመፈጸሙ ብቻ የስንብት እርምጃ መውሰድ ተገቢ አይደለም፡፡ ህጉ ማታለል ወይም ማጭበርበር ሲኖር የሥራ ውል የሚቋረጥባቸውን ሁኔታዎች በግልጽ ያስቀመጠ እንደመሆኑ በቅድሚያ ሁኔታዎቹ ተሟልተው ሊገኙ ይገባል፡፡

በአዋጁ አንቀጽ 27(1) ሐ እንደተመለከተው በሥራው ላይ የማታለል ወይም የማጭበርበር ተግባር መፈጸም የሥራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ አንደኛው በቂ ምክንያት ነው፡፡

4/ በአሠሪው ንብረት ወይም ገንዘብ አላአግባብ መጠቀም

ሠራተኛው ለሥራው የተሰጡትን መሣሪዎችና ዕቃዎች ሁሉ በጥንቃቄ የመጠበቅ የህግ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ ስለሆነም ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ ሥራውን እንዲያከናውን የሚረዱት ሌሎች ከአሠሪው የተረከባቸውን ንብረቶች በራሱ ወይም በሌላ ሰው ጉዳት እንዳይደርስባቸው ብሎም ለብክነትና ለብልሽት እንዳይዳረጉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እና ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ለሚሰራው ሥራ ዓላማ ካልሆነ በስተቀር የግሉን ወይም የሌላ 3ኛ ወገን ብልጽግና በመሻት ሊጠቀምባቸው አይገባም፡፡ ግዴታው የታማኝነቱ ቁልፍ መገለጫ ነው፡፡ የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት በመተማመን ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ በማናቸውም የአሠሪውን ጥቅም በሚመለከቱ ጉዳዮች ሠራተኛው ሁልጊዜ ታማኝ ሆኖ መገኘት አለበት፡፡

በመሆኑም በአዋጁ አንቀጽ 27(1) ሐ መሠረት በአሠሪው ንብረት ወይም ገንዘብ አላአግባብ መጠቀም የሥራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በቂ ምክንያት ነው፡፡

5/ ጠብ አጫሪነት ወይም አምባጓሮ

በሥራ ቦታ ላይ የሚከሰት ጠብ እና አምባጓሮ ሰላማዊ የሥራ አካባቢን የሚያውክና ስርዓት አልበኝነትን የሚያነግስ በመሆኑ በአጭሩ ካልተቀጨ የአሠሪውን ምርታማነት በእጅጉ ይጎዳል፡፡ አንድ ሠራተኛ ተመድቦ የሚሰራበት ሥራ ከሌላ ሠራተኛ ሥራ ጋር በእጅጉ የተሳሰረ ነው፡፡ ጠብና አምባጓሮ ሲፈጠር ሥራ በቅንጅትና በመግባባት አይሰራም፡፡ ከአሠሪው ድርጅት ምርትና አገልግሎት የሚፈልጉ ደንበኞችም ያርቃል፡፡ የአንቀጽ 27(1) ረ አይነተኛ አላማ በሥራ ቦታ ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ነው፡፡ በመሆኑም በአዋጁ አንቀጽ 27(1) ረ መሠረት በስራ ቦታ ጠብ አጫሪ መሆን ወይም አምባጓሮ መፍጠር የሥራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በቂ ምክንያት ነው፡፡

6/ በአሠሪው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ አንቀጽ 27(1) ሸ አነጋገር ሠራተኛው ከሥራ የሚሰናበተው ሆነ ብሎ ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዳት ሲያደርስና ጉዳቱም የደረሰው በአሠሪው ንብረት ወይም ከድርጅቱ ሥራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባለው ማናቸውም ንብረት ላይ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር አራት የጥፋቱ ማቋቋሚያዎች አንድ ላይ ተሟልተው መገኘት እንዳለባቸው እንረዳለን፡፡ ይኸውም፤

#አንደኛ ጉዳት ደረሰበት የተባለው ነገር “ንብረት” መሆን አለበት፡፡ በሌላ አነጋገር ህጉ ለንብረት የሰጠውን ፍቺ ማሟላት ይኖርበታል፡፡

#ሁለተኛ ንብረቱ የአሠሪው ወይም ከድርጅቱ ሥራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያለው ንብረት ሊሆን ይገባል፡፡

#ሶስተኛ አሠሪው በንብረቱ ወይም ከድርጅቱ ሥራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባለው ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ብሎም በጉዳቱና በድርጊቱ መካከል የምክንያትና ውጤት ግንኙነት ስለመኖሩ ማስረዳት ይኖርበታል፡፡ የምክንያትና ውጤት ግንኙነት ሲባል ሠራተኛው ማድረግ የሌለበትን በማድረጉ ወይም ማድረግ ያለበትን ባለማድረጉ ምክንያት ጉዳት መከሰቱን ለማመልከት ነው፡፡

#አራተኛ ሠራተኛው ጉዳቱን ያደረሰው ሆነ ብሎ ወይም በከባድ ቸልተኝነት ስለመሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

በመሆኑም በአዋጁ አንቀጽ 27(1) ሸ መሠረት በአሠሪው ንብረት ወይም ከድርጅቱ
ሥራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባለው ማናቸውም ንብረት ላይ ሆነ ብሎ ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ የሥራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በቂ ምክንያት ነው፡፡

7/ የወንጀል ጥፋተኝነትና እስራት

የወንጀል ጥፋተኝነት የሥራ ውልን ለማቋረጥ በራሱ በቂ ምክንያት ባይሆንም በውጤቱ ሠራተኛውን ለያዘው ሥራ ብቁ የማያደርገው ከሆነ [አንቀጽ 27(1) ሰ] ወይም የእስራቱ ጊዜ ከሰላሳ ቀን ከበለጠ [አንቀጽ 27(1) በ] ህጋዊ የስራ ውል ማቋረጫ ምክንያት ይሆናል፡፡ በአንቀጽ 27(1) ሰ ከጥፋተኝነት ባለፈ የእስራት ፍርድ እንዲኖር የግድ አይልም፡፡ ሠራተኛው ቅጣቱ ቢገደብለትም ብሎም በገንዘብ መቀጮ ብቻ ቢቀጣም ጥፋተኛ የተባለበት ወንጀል ብቃቱን የሚያሳጣው ከሆነ ከአሠሪው ጋር ያለው ግንኙነት ይቋረጣል፡፡

8/ የሥራ ውጤት መቀነስ (መለገም)

ሠራተኛው መውጫና መግቢያ ሰዓት አክብሮ በሥራ ቦታ መገኘቱ ብቻውን የመስራት ግዴታውን እየተወጣ ነው አያስብልም፡፡ ግዴታውን ሲወጣ መላ ጉልበቱን፤ ችሎታውንና ዕውቀቱን በመጠቀም የተመደበበትን ሥራ ጥንካሬና ትጋት በተሞላበት መልኩ በማከናወን ውጤት ማምጣት አለበት፡፡ በዳተኝነት፤ ልግመኝነትና ንዝህላልነት ሥራን መበደል ካለማስጠንቀቂያ የሚያሰናብት ጥፋት ነው፡፡ የሥራ ችሎታ መቀነስ በአንቀጽ 28(1) ሀ በማስጠንቀቂያ የሥራ ውልን የሚያቋርጥ በቂ ምክንያት ሲሆን ይህም ተፈጥሯዊ በሆነ ምክንያት ሊከሰት ስለሚችል በአንቀጽ 27(1) ሠ ጥፋት ከሆነው የሥራ ውጤት መቀነስ እንዲለይ ተደርጓል፡፡ አንቀጽ 27(1) ሠ ተፈጻሚ የሚሆነው ሠራተኛው የመስራት ችሎታውና ብቃቱ እያለው ሆነ ብሎ ወይም በቸልተኝነት ከሚጠበቅበት በታች በመስራት ሥራ ሲበድል ማለትም ሲያለግም ነው፡፡

የሕግ አማካሪና ጠበቃ ሳሙኤል ግርማ
https://t.me/YehigGuday
እሁድ ማታ 3 ስዓት ቀጥታ ስርጭት 👈👈👈

እሁድ 👇👇👇👇👇👇
3 ስዓት ላይ በዚህ ቴሌግራም ይጠብቁ

ሼር በማደረግ ሰዎቸን ይጋብዙ👆👆👆

Live 🔘 Live on Telegram 👈👈

#አለ_ህግ #Ale_Hig

Topic_"Fair trial under the criminal procedure from the constitution perspective.
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Topic of the discussion
.
☑️👁‍🗨 "

🔘 Live on Telegram                       

Speaker: ☑️ Kassahun Yibeltal
(Dr. Cand)


Starting Time: 9:00PM -
[Sunday evening]

Join us: https://t.me/lawsocieties

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን        
  👉 https://t.me/lawsocieties
Federal Auditor General ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Postion:5 Positions
1:Senior Lawyer,
2:Procurement Officer and
3: Executive Secretary

📚የትምህርት ዓይነት እና ደረጃ:
LLB degree in Law and College diploma or degree.

🇪🇹 የስራ ቦታ: Addis Ababa

🧭የምዝገባ ጊዜ ፡እስከ ህዳር
1/2015 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ

https://jobs.amazonethiopia.com/job/federal-auditor-general/

🔰https://t.me/lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
እሁድ ማታ 3 ስዓት ቀጥታ ስርጭት 👈👈👈

እሁድ 👇👇👇👇👇👇
3 ስዓት ላይ በዚህ ቴሌግራም ይጠብቁ

ሼር በማደረግ ሰዎቸን ይጋብዙ👆👆👆

Live 🔘 Live on Telegram 👈👈

#አለ_ህግ #Ale_Hig

Topic_"Fair trial under the criminal procedure from the constitution perspective.
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Topic of the discussion
.
☑️👁‍🗨 "

🔘 Live on Telegram                       

Speaker: ☑️ Kassahun Yibeltal
(Dr. Cand)


Starting Time: 9:00PM -
[Sunday evening]

Join us: https://t.me/lawsocieties

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን        
  👉 https://t.me/lawsocieties
ስለ Exit Exam ከሚመለከተው አካል መረጃ አግኝተናል።

በቀነ ቀጠሮ በዚሁ ቻናል በቀጥታ ስርጭት ገብተው ማብራሪያ ይሰጣሉ 👈
የሚመቻቸውን ቀን እንዳሳወቁን እናሳውቃለን🙏
የዛሬ ውይይታችን 3 ስዓት ይጀምራል 👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿 _"Fair trial under the criminal procedure from the constitution perspective. ሼር በማድረግ ተደራሽ አድርጉት 👉🏿👉🏿 https://t.me/lawsocieties