አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008
አንቀፅ 12. ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ማለት

https://t.me/lawsocieties
1/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) እና (3) ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ናቸው የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡-
ሀ) ሠራተኛው ካለፈው፣ አሁን ካለው ወይም ወደፊት ከሚመጣው ቅጥር ጋር በተያያዘ የተቀበለው ደመወዝ፣ ምንዳ፣ አበል፣ ጉርሻ፣ ኮሚሽን፣
የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማበረታቻ ስጦታ ወይም
ሌላ የአገልግሎት ዋጋ ክፍያ፤ለ) ያለፈን፣ የአሁኑን ወይም የወደፊትን ቅጥር አስመልክቶ ሠራተኛው የሚቀበለው የዓይነት ጥቅማ ጥቅም ዋጋ፤
ሐ) ተቀጣሪው ከሥራ ሲቀነስ፣ ሥራውን ሲለቅ ወይም
ሥራውን እንዲለቅ ለማግባባት የሚከፈል ገንዘብን ጨምሮ የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት
በፈቃደኝነት፣ በስምምነት ወይም በዳኝነት ውሳኔ መሠረት የተቀበለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን፤

2/ በመቀጠር የሚገኝ ገቢ ከግብር ነፃ የተደረገን ገቢ አይጨምርም፡፡

3/ ማንኛውም ቀጣሪ ተቀጣሪው መክፈል የሚኖርበትን ግብር
ከተቀጣሪው ገቢ ላይ ሳይቀንስ ራሱ ለተቀጣሪው በሙሉ
ወይም በከፊል የከፈለለት እንደሆነ፣ በቀጣሪው የተከፈለው
የግብር መጠን ተቀጣሪው ከመቀጠር ከሚያገኘው ግብር
በሚከፈልበት የገንዘብ መጠን ላይ ተደምሮ ግብሩ ይሰላል፡፡

4/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከደመወዝ ሌላ በዓይነት የሚሰጡ ጥቅማጥቅሞች ዋጋ የሚወሰንበትንና ግብር የሚከፈልበትን ሁኔታ አስመልክቶ ደንብ ያወጣል፡፡
በሌላ በኩል፣
በአዋጁ አንቀፅ 65 ከገቢ ግብር ነፃ የሆነ ገቢ የዘረዘረ ሲሆን፣
እነሱም:_
1/ ለዚህ አዋጅ አፈፃፀም ሲባል የሚከተሉት ገቢዎች ከገቢ
ግብር ነፃ ናቸው፡-

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ሀ) ሚኒስትሩ በዚህ ፊደል ተራ በቁጥር (2) ፣(3) ፣(4)
እና (6) በተመለከቱት ላይ በሚያወጣው መመሪያ
የሚያደርገው ገደብ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለተቀጣሪው የሚከፈሉ የሚከተሉት ገቢዎች ከገቢ ግብር ነፃ ናቸው፡-

(1) ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፤

(2) በሥራ ውል መሠረት ለሠራተኛው የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፤

(3) በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈል አበል

(4) ሠራተኛው ከመደበኛ ሥራው ውጪ ሥራውን ለማከናወን ሲንቀሳቀስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ እና የውሎ አበል፤

(5) የመጓጓዣ ወጪው በቅጥር ውሉ መሠረት የተከፈለ ከሆነ ከሥራ ቦታው ውጪ ተመልምሎ
ለተቀጠረ ሠራተኛ ወደ ሥራው ሲመጣ ወይም ሥራውን አጠናቆ ሲመለስ የሚከፈለው የመጓጓዣ
ወጪ፣ እንዲሁም የውጭ ሀገር ሠራተኞች ከሀገራቸው ሲመጡና ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ
የሚከፈል የመጓጓዣ ወጪ፤

(6) የማዕድን ማውጣት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርና የንግድ ሥራ የሚሠራ ቀጣሪ
ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብና መጠጥ፤

(7) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
መንግሥት በውጭ አገር ለሚመድባቸው ሠራተኞች የሚከፈል አበል፤
ለ) የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግሥት
መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም
የፌደራልና የክልል መንግሥታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፤
ሐ) ለሠራተኛው ጥቅም ተብሎ ከተቀጣሪው የወር ደመውዝ 05% (አሥራ አምስት በመቶ) ባልበለጠ መጠን በየወሩ በቀጣሪው የሚዋጣ የጡረታ መዋጮ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ፤
መ) በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እና በግል
ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ
የጡረታ ገቢ፤
ሠ) የኢትዮጵያ የፌደራል፣ የክልል ወይም የአካባቢ መንግሥታት ወይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
ከመደበኛ ሥራዎቻቸው ጋር በተያያዘ የሚያገኙት
ገቢ፤
ረ) በዓለም ዐቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፤
ሰ) በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
መንግሥት በተደረገ ስምምነት (ከዚህ በኋላ
"ከግብር ነፃ ማድረግ የሚያስችል አንቀጽ" ተብሎ
የሚጠቀስ) መሠረት ማናቸውም ገቢ ከግብር ነፃ
የሚሆነው የሚከተሉት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ነው፡-
(1) ስምምነቱ የተደረገው ለመንግሥት የገንዘብ፣
የቴክኒክ፣ ሰብአዊ ወይም አስተዳደራዊ እርዳታ ለማቅረብ የሆነ እንደሆነ፤
(2) ከግብር ነፃ ማድረግ የሚያስችለውን አንቀጽ
በሚመለከት ሚኒስትሩ መስማማቱን በጽሁፍ
ሲገልጽ፤
ሸ) በማንኛውም መስክ ለላቀ የሥራ ክንውን ወይም
በታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ 1)፴5 መሠረት የሚሰጥ ሽልማት፤
ቀ) በተቀባዩ ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው
ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፤
በ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶9 የተደነገገው እንደተጠበቀ
ሆኖ፣ ስጦታውየመቀጠር፣የኪራይ ወይም የንግድ ሥራ ገቢ ካልሆነ በስተቀር በስጦታ ወይም
በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፤
ተ) በትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትን በነፃ ለመከታተል የሚፈፀም ክፍያ፤
ቸ) ለቀለብ ወይም ለህፃናት ድጋፍ የሚሰጡ ክፍያዎች፤
ኀ) ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ጋር የማይገናኝ የንግድ ሥራ ገቢን ሳይጨምር ለትርፍ
ያልተቋቋመ ድርጅት የሚያገኘው ገቢ፤
ነ) ገንዘብ በሚቆጠርበት ጊዜ ለሚደርሰው ጉድለት
ማካካሻ በሚሆን መጠን ብቻ ቀጣሪው ለተቀጣሪው
የሚከፍለው እና ለዚሁ ዓላማ መዋሉ የተረጋገጠ
የጥሬ ገንዘብ ማካካሻ ክፍያ፤
ኘ) በኢትዮጵያ ፀንቶ በሚሰራበት ሕግ መሠረት በተለይ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገ ገቢ፤
አ) ለመኖሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፤
ከ) በነዳጅ ሥራ ላይ የተሰማራ ሥራ ተቋራጭ ለንዑስ
ሥራ ተቋራጮች የሚፈፅመው ክፍያ፡፡
2/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ለኢኮኖሚ፣
ለአስተዳደራዊ ወይም ለማህበራዊ ምክንያቶች አንድን ገቢ ከገቢ ግብር ነፃ ሊያደርግ ይችላል፡፡
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
via #tax and business law blog
https://t.me/lawsocieties
።።።።።።። 👇።።።።።።።።።።።
👉 @lawsocieties @AleHig👈
።።።።።።።።።።። 👆።።።።።።።።።።።
የቅድመ ግብር ክፍያ ስርዓት (1).pdf
2.9 MB
ስለ ቅድመ ግብር ክፍያ ስርዓት (WITHHOLDING) ለአዲስ ግብር ከፋዮች የተዘጋጀ ማብራሪያ

#ethiopia #Tax 🇪🇹