አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የጋብቻ መፈፀም የሚያስከትለው ውጤት
#ጋብቻ አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት በሁለት ሰዎች (ባልና ሚስት) መካከል የሚፈጠም ህብረት እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ የሀገራችን ቤተሰብ ህግ ለጋብቻ ትርጉም ያልሰጠ ሲሆን ጋብቻ ለማቋቋም ሊሟሉ የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን እና ጋብቻ የሚፈፀመው በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡

በህግ ፊት የፀና ጋብቻ ለመፈጸም የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው፡፡ በዚህ መሰረት የሁለቱ ሰዎች ፈቃድ መኖር፣ በህጉ የተቀመጠው ዝቅተኛ እድሜ መሟላት፣ የዝድና አለመኖር፣ በጋብቻ ላይ ጋብቻ አለመኖር መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

ጋብቻ በተለያዩ ሶስት መንገዶች ሊፈጸም ይችላል፡፡
እነዚህም በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈፀም፣ የሀይማኖት ጋብቻ እና የባህል ጋብቻ ናቸው፡፡ በእነዚህ መንገዶች የተፈፀመ ጋብቻ ተመሳሳይ ውጤት ያለው ሲሆን በእነዚህ መንገዶች አስፈላጊውን ሁኔታ በማሟላት የተፈጸመ ጋብቻ የሚያስከትለው ውጤቶች እንደሚከተለው ተብራርተዋል፡፡

1. ጋብቻ በተጋቢዎች ግላዊ ግንኙነት ላይ የሚያስከትለው ውጤት

i. አብሮ መኖር
ባልና ሚስት ጋብቻ ከፈፀሙ በኋላ አብረው እንዲኖሩ በህግ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ የመኖሪያ ቦታቸውንም አብረው የሚወስኑ ይሆናል፡፡ ሆኖም ባልና ሚስቱ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ተለያይተው ለመኖር መስማማት አይከለከሉም፡፡ ይህ ስምምነት መቀየሩ አግባብ ካልሆነ በስተቀርም ተጋቢዎች ወይም ከሁለት አንዳቸው አስበው ሊቀይሩትም ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ የባልና ሚስቱ የሥራ ቦታ ሊለያይ የሚችልበት አጋጣሚ ሲፈጠር ሁለቱም በያሉበት ሆነው ሥራቸውን ለመሥራት ሊስማሙ የሚችሉ ሲሆን አመቺ ሆኖ ካላገኙትም ሀሳባቸውን መቀየር ይችላሉ፡፡

ይህ ብቻ ሳይሆን ተጋቢዎች ጋብቻ ተሳስረው ሲኖሩ ለጤናቸው አደገኛ ካልሆነ በስተቀር ከጋብቻ የሚጠበቀውን መደበኛ የሩካቤ ሥጋ መፈፀምም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን የሚቃረን ስምምነት ውጤት አይኖረውም፡፡ በተጨማሪም በማንኛውም ሁኔታ አንዳቸው ለሌላኛው ታማኝ የመሆን ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ አንዳቸው ሳይታመኑ የአመንዝራነት ድርጊት ቢፈፅሙ በተበደለው ተጋቢ አቤቱታ አቅራቢነት በእስራት ወይም በመቀጮ ሊያስቀጣ የሚችል የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል ነው፡፡

ii. መከባበር፣ መተጋገዝና መደጋገፍ

ባልና ሚስት በትዳር በሚኖሩበት ጊዜ አንዳቸው ሌላኛውን የማገዝና የመደገፍ እንዲሁም ተከባብሮ የመኖር ሀላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ይህንን ሀላፊነት በስምምነት ፈፅሞ ሊያስቀሩት እንደማይችሉ በህግ ተደንግጓል፡፡

iii. ቤተሰብን በጋራ መምራት

ጋብቻ በሁለቱ ተጋቢዎች ተወስኖ የማይቀርና ልጆችን የሚፈጥርና የቤተሰብ መሰረት የሚሆን ተቋም ነው፡፡ በዚህም የልጆች አስተዳደግ፣ ትምህርት፣ ጤና ወዘተ የመሳሰሉ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች በተጋቢዎች እንዲሟሉ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ አንፃር ባልና ሚስት እኩል መብት እንዳላቸው በቤተሰብ ህግ ደንግጓል፡፡ በዚህም በማናቸውም ረገድ የቤተሰቡን ደህንነትና ጥቅም ለማስጠበቅ፣ ልጆቻቸው በመልካም ሥነ ምግባር እንዲታነፁ፣ ተገቢ ትምህርት እንዲቀርሙና ሀላፊነት የሚሰማቸው ዜጎች ሆነው እንዲያድጉ ለማድረግ ባልና ሚስቱ መተባበር ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ጋብቻ በንብረት ረገድ የሚያስከትለው ውጤት

ጋብቻ በተጋቢዎች ግላዊ ግንኙነት ላይ ውጤት እንዳለው ሁሉ በንብረት ረገድም የራሱ የሆነ ውጤት የሚያስከትል ነው፡፡ ንብረትን በተመለከተ ጋብቻ የግል እና የጋራ ንብረት ውጤት የሚስከትል ነው፡፡

i. የግል ንብረት ምንነትና አስተዳደር

የግል ንብረት የምንለው ሁለቱ ተጋቢዎች ከጋብቻው በፊት በየግል የነበሯቸው ንብረቶች ወይም ከጋብቻው በኋላ በውርስ ወይም በየግላቸው በስጦታ ያገኟቸው ንብረቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ንብረቶች በጋብቻውም ዘመን የግላቸው ሆነው ይቀጥላሉ፡፡ እነዚህን ንብረቶች ሸጦ የሚገዛው ንብረት የራሱ የሚሆን ሲሆን ይህ የሚሆነው ግን በፍርድ ቤት የግሌ ይባልልኝ ብሎ ሲጠይቅና ሲፀድቅለት ነው፡፡

የግል ንብረት አስተዳደርን በተመለከተ የግል ንብረቱ ባለቤት የሆነው ተጋቢ ሊያዝበት የሚችል ሲሆን ሌላኛው ተጋቢ እንዲያስተዳድረው በጋብቻ ውል ሊስማሙ የሚችሉ ከመሆኑም በላይ ውክልና በመስጠት ሌላኛው ተጋቢ እንዲያስተዳደር ሊያደርግ ይችላል፡፡

ii. የጋራ ንብረት ምንነትና አስተዳደር

የጋራ ንብረትን በተመለከተ የጋራ ንብረት የሚባለው ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ በግብይት የሚያገኟቸው ንብረቶች፣ ባልና ሚስት በግል ጥረታቸው የሚገኝ ገቢ፣ ከግል እና ከጋራ ንብረታቸው የሚገኟቸው ገቢዎች ሁሉ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በስጦታ ወይም በኑዛዜ በጋራ የተሰጧቸው ንብረቶች የጋራ ንብረቶች ናቸው፡፡ እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን ካላስረዳ በስተቀር በአንደኛው ተጋቢ ስም የተመዘገበ ሀብትም ቢሆን እንኳን የተጋቢዎች የጋራ ሀብት እንደሆነ የህግ ግምት የሚወሰድበት መሆኑ ነው፡፡

በንብረት አስተዳደር ረገድ የጋራ ንብረታቸውን አንደኛው ተጋቢ እንዲያስተዳድረው ካልተስማሙ፣ ችሎታ የለውም በሚል ካልተወሰነ፣ ንብረት የማስተዳደር መብቱ ካልተገፈፈ፣ ወይም በማናቸውም ምክንያት ንብረታቸውን ማስተዳደር የማይችል ሆኖ ካልተገኘ በስተቀር የጋራ ንብረታቸውን በጋራ ያስተዳድራሉ፡፡ ሆኖም በተጠቀሱት ምክንያቶች አንደኛው ተጋቢ ብቻውን ንብረቱን የሚያስተዳድር ከሆነ ለሌላኛው ተጋቢ መረጃ የመስጠት ሃላፊነት አለበት፡፡

በገቢ ረገድ ሁለቱም ተጋቢዎች ገቢያቸውን በየራሳቸው መቀበል የሚችሉ እንዲሁም በግል ወይም በጋራ የባንክ ሂሰብ ከፍተው ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡ ይህ ማለት ግን አንደኛው ተጋቢ ሌላኛው ተጋቢ እንዲቀበልለት ስልጣን ለመስጠት የሚከለክለው ነገር የለም፡፡ በየግል የሚያገኙትንም ገቢ ሌላኛው ተገቢ ሲጠይቅ ማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡

ከንብረት በተጨማሪ በጋብቻ ውስጥ እዳ ሊኖር እንደሚችል የሚጠበቅ ነው፡፡ ልክ እንደንብረት ሁሉ እዳም የግል ወይም የጋራ ተብሎ የሚከፈል ነው፡፡ እዳው ለባልና ሚስት እና ለልጆቻቸው የዕለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማሟላት ወይም ባል ወይም ሚስት ቀለብ የመስጠት ግዴታቸውን ለመወጣት የተገቡ እዳዎች እንዲሁም ከባልና ሚስት በአንደኛው ወይም በዕዳ ጠያቂው አመልካችነት ለትዳር ጥቅም ስለመሆኑ ፍርድ ቤት የተቀበለው እዳ በጋራ የሚከፍሉት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የሚኖረው እዳ የግል ይሆናል ማለት ነው፡፡ አከፋፈሉ ሲታይ የጋራ እዳ ከባልና ሚስቱ የጋራ ሀብት የሚከፈል ሲሆን ዕዳውን ለመሸፈን በቂ በማይሆን ጊዜ ከባል ወይም ከሚስት የግል ሀብት የሚከፈል ይሆናል፡፡

በአንፃሩ የግል ዕዳ ከባለዕዳው ተጋቢ የግል ሀብት የሚከፈል ሲሆን ዕዳው ለመሸፈን በቂ በማይሆንበት ጊዜ ከጋራ ሀብት የሚከፈል ይሆናል፡፡ እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ከጋራ ሀብት ሲባል በድርሻው ልክ እንጂ የሌላኛውን ተጋቢ ጥቅም በሚነካ መልኩ ሊሆን እንደማይችል ነው፡፡
የንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
#አለ_ህግ #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share #lawsocieties
..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
የሂሳቡ ባለቤት ቼክ ፈርሞ ባልሰጠበት ሁኔታ የባለቤቱን ፊርማ አስመስለው በመፈረም ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ወጭና ገቢ በማድረግ ከባድ የሙስና ወንጀል በፈፀሙ ተከሳሾች ላይ ክስ ተመሰረተ።

የሂሳቡ ባለቤት ቼክ ፈርሞ ባልሰጠበት ሁኔታ የባለቤቱን ፊርማ አስመስለው በመፈረም ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ወጭና ገቢ በማድረግ መንግስታዊ ሰነዶችን በሀሰት አስመስሎ በማዘጋጀትና በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል በፈፀሙ ተከሳሾች ላይ ክስ ተመስርቷል ።

ክሱን የመሰረተው በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ዐቃቤ ህግ ነው ።

የዐቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው 1ኛ ተከሳሽ ሹክረዲን ሙሃመድ 2ኛ ሳሙዔል ዳምጤ እና 3ኛ መሳይ ታደሰ ጥር 21/2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዋሽ 7 ቅርንጫፍ ደንበኛ በሆኑት መዲና ሔንኬብ የውሃ ስራዎች ድርጅት ከተንቀሳቃሽ ሂሳብ ቁጥራቸው ላይ የሂሳቡ ባለቤት ቼክ ፈርመው ባልሰጡበት ሁኔታ የሂሳብ ባለቤቱን ፊርማ አስመስለው በመፈረም እረስ በርሳቸውና በሌሎች ግለሰቦች 12‚235,000 ( አስራ ሁለት ሚሊየን ሁለት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ብር ) ወጭና ገቢ ያደረጉ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ሀሰተኛ ቼኮችን በማቅረብ የወሰዱትን ገንዘብ ለመደበቅና ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ በማሰብ የሞባይል ባንኪንግን ተጠቅመው በተለያዩ ግለሰቦች ወደተከፈተ አካውንት ያስተላለፉ በመሆኑ ተከሳሾች በፈፀሙት መንግስታዊ ሰነዶችን በሀሰት አስመስሎ ማዘጋጀትና በሀሰት ሰነድ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል አንዲሁም በወንጀል ድርጊት የተገኘን ሀብት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ተከሰዋል ።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ወንጀል ቸሎት በህግ ጥላ ስር ላለው 1ኛ ተከሳሽ የክስ ቻርጁ አንዲደርሰው ተደርጎ የክስ መቃወሚያ ካለው እንዲያቀርብ እንዲሁም ያልተያዙትን 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደግሞ ፖሊስ አፈላልጎ እንዲያቀርብ ታዞ ይህንኑ ለመጠባበቅ ለሚያዝያ 10/2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።
የፍትሐ ብሄር ፍትህ አስተዳደር ዘርፉን ለማሻሻል ያስችላል የተባለ የፍትሐ ብሄር ፍትህ አስተዳደር ፖሊሲ የመቅረጽ ስራ ተጀመረ

ግለሰባዊ ግንኙነቶችን እና መብቶችና ግዴታዎችን (private relationships, rights and obligations) የሚደነግገውንና የሚገዛውን እንዲሁም የንብረት፣ የውል፣ የቤተሰብ፣ የውርስ፣ ከውል ዉጭ ኃላፊነትን እና የመሳሰሉትን ህግጋት አካትቶ የሚይዘውን የፍትሐ ብሄር ፍትህ አስተዳደር ዘርፍ ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ለማስቻልና በተቀናጀ መልኩ የለውጥ ስራ እንዲሰራ የሚያግዝ የፍትሐ ብሄር ፍትህ አስተዳደር ፖሊሲ ለማርቀቅ የሚያስችል ጥናት የማከናወን ስራ ተጀምሯል፡፡

ጥናቱ ለረዥም አመታት በስራ ላይ የቆዩትን የዘርፉን ህግጋት፣ አተገባበራቸውን እና ወቅቱ የሚጠይቀውን ሀገራዊ፣ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ለውጥ የሚዳስስ ሲሆን ፖሊሲውን ለማርቀቅ የሚረዱ ምክረ ሀሳቦችን አጎልብቶ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡

በጥናቱ ውጤት መነሻነት የሚረቀቀው ፖሊሲም የፍትሐ ብሄር ክርክር ስርዓቱን፣ የአማራጭ የግጭት መፍቻ አተገባበርን፣ ነጻ የህግ ድጋፍን፣ የፍትሐ ብሄር ህግጋት መሻሻልን፣ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ ማዘመንን እና የመሳሰሉትን ወሳኝ እና አስቻይ ነጥቦችን እንደሚያካትት ተገልጿል፡፡ የፖሊሲው መዘጋጀት ከዚህ ቀድሞ ወጥ እና የተጠና አሰራር ስርዓት ባልነበረበት ሁኔታ ያገጥም የነበረውን ችግር ከመፍታትም በዘለለ ዘርፉ ተገቢውን ትኩረት አግኝቶ በመርህ የሚመራ እንዲሆን የሚያደርግ ሲሆን የህዝቦች ተጠቃሚነትንም የሚያሰፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን የመንግስት ተቋማትን የፍትሐ ብሄር ክርክር ተጋላጭነት መንስዔዎችን ቀድሞ ለማወቅ እና ለመከላከል የሚረዳ የአሰራር ስርዓት በጥናት ላይ በመመስረት የመዘርጋት ስራም ተጀምሯል፡፡ ይህ የአሰራር ስርዓት የመንግስት ተቋማት በተለያዩ ጊዜያት ሲያጋጥሟቸው በነበሩ የፍትሐ ብሄር ክርክር ጉዳዮች ምክንያት ሲባክን የነበረን ከፍተኛ ሀብት የሚያድን ከመሆኑም በላይ ተቋማቱ በህግ በተቋቋሙለት አላማ ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል ተብሏል፡፡

ሁለቱም ጥናቶች በፍትህ ሚኒስቴር እና በዩ ኤስ ኤይድ ፍትህ ፕሮጀክት ትብብር የሚከናወኑ ሲሆን በጥናቶቹ ሂደት ውስጥ በዘርፉ የላቀ እውቀት እና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች የሚሳተፉ መሆኑ ታውቋል፡፡ በስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ በተቋሙ የፍትሔብሄር ፍትህ አስተዳደር ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ሄኖክ ተስፋዬ፣ በዩ ኤስ ኤይድ ፍትህ ፕሮጀክት የስራ ሃላፊዎች እና ጥናቱን የሚመሩት ባለሙያዎች ጥናቶቹን በተመለከተ ሀሳባቸውን አካፍለዋል፡፡

በስተመጨረሻም የፍትህ ሚኒስቴር የመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው በመድረኩ ተገኝተው የስራ አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡ በዚሁም የጥናቶቹ ዝግጅት በይፋ ተጀምሯል፡፡
በወንጀል_ጉዳዮች_የዓቃቤ_ህግ_የህግ_ትርጉም_ማብራሪያ.pdf
1.1 MB
በወንጀል ጉዳዮች የአተረጓጎም ልዩነት ያለባቸውን ድንጋጌዎች ላይ ወጥነት ያለው ትርጉም ለማምጣት እንዲቻል የተዘጋጀ የሕግ ማብራሪያ

🟥 @lawsocieties
#1-
ደሀ ደንብ
ዳኝነት ሳይከፈል፣ በነፃ መዝገብ ማስከፈት

ክስ ለማቅረብ የፈለገ ወገን ከፍርዱ ለሚያገኘው የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል የገንዘብ አቅም የሌለው ከሆነ ክሱን ያለዳኝነት ገንዘብ በደሀ ደንብ መሠረት የማቅረብ መብት እንዳለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 215 ተደንግጓል፡፡ ክሱን የሚያቀርበው ወገን ድሀ በመሆኑ ምክንያት የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍል ክሱን አቅርቦ እንዲያሰማ ሊፈቅድለት ይገባል? የሚለው ጉዳይ ሊለይ የሚችልበት ዝርዝር አፈፃፀም ደንቡም ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 እና ተከታዩ ድንጋጌዎች ተመልክቷል፡፡ እነዚህ ደንቦች ተፈፃሚነታቸው ክስ ለማቅረብ በፈለገ የተፈጥሮ ሰውም ሆነ በሕግ ሰውነት ያላቸው ወገኖችም ጭምር ነው፡፡
በዚህም መሠረት ድሀ ነኝ፤ መብቴን ለማስከበር ያለኝ ፍላጐቴ በዳኝነት ገንዘብ እንቅፋት ምክንያት ሊሰናከል አይገባም፡፡ ስለሆነም በድሀ ደንብ መሠረት ክሱን በነፃ እንዳሰማ ይፈቀድልኝ የሚል ማናቸውም ከሳሽ ድሀ መሆኑን ሊያመለክት የሚችል የሚገኝበትን የገንዘብ አቋም ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ ይህም ከሳሹ የሚገኝበት የገንዘብ አቋም ከተረጋገጠ በኋላ ለክሱ ሊከፈል የሚገባው የዳኝነት ገንዘብ መጠን ከሳሹ ከሚገኝበት የገንዘብ አቋም አኳያ ተገናዝቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 መሠረት ድሀ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ሊለይ ይገባል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 79555 ቅጽ 14፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467
አንድ ሰው በፍርድ ሊያልቅ የሚገባው ጉዳይን ፍርድ ቤት ይዞ ሲቀርብ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ መክፈል ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 215፣ ከ467 እስከ 479 ድረስ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ያሳያሉ፡፡ የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የማይችል ሰው ክስ ለማቅረብ የሚችልበት አግባብ ስለመኖሩም ተጠቃሽ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡ አንድ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመክፈል የማይችል ሰው በደሃ ደንብ ክስ ለማቅረብ የሚችል ሲሆን ለመክፈል አቅም እያለው ክስ ያቀረበ መሆኑ ከተረጋገጠ ግን መዝገቡ እንደሚዘጋ፣ የተዘጋ መዝገብ ደግሞ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ /ገንዘቡን/ ለመክፈል ዝግጁ እስከሆነ ድረስ የሚንቀሳቀስለት መሆኑን የሥነ ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች መንፈስና ይዘት ያስገነዝባሉ።
ሰ/መ/ቁ. 52942 ቅጽ 12፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467-479 ....ይቀጥላል --- source ፦Amharic Legal Glossary Abrham Yohanes
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
እንኳን ለትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም ፋሲካ!

#ፋሲካ #fasika #Ethiopia
አዋሽ ባንክ በሰባት የስራ መደቦች በዜሮ ዓመት ( አዲስ ተመራቂዎችን) እና የስራ ልምድ ያላቸውን ሰራተኞች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

📚ትምህርት ዓይነት እና ደረጃ:- Degree in Banking & Finance, Accounting, Management, 🔴Law, Economics, Marketing Management, Business Administration, Public Administration, and Development Management, International Trade & Investment Management, Cooperative Business Management & Auditing, IT, Computer Science, Software Engineering, Electrical Engineering (Communication & Computer Engineering streams only) or similar qualification

🇪🇹 የስራ ቦታ ፡- Addis Ababa

🧭የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ ሚያዚያ 23/2014 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://jobs.amazonethiopia.com/job/awash-bank-job-vacancy-6/
------------------------------------------------
የብድር ውል
የብድር ውል (በኢትየጵያ የፍትሐብሔር ሕግ ከቁጥር 2471-2489) ከዚህ እንደሚከተለው ብድር የሚለውን ቃል ፍቺ ይሰጣል፡፡
“የሚያልቅ ነገር ብድር ማለት ከተዋዋዮቹ አንዱ ወገን አበዳሪው ሌላውን ተበዳሪ ሰው የተበደረውን ነገር በዓይነቱ ለመመለስ ተገዳጅ በማደረግ ገንዘብ ወይም በማገልገል የሚያልቅ ሌላ ነገር ለተበዳሪው ለመስጠትና ሀብትነቱን ለማስተላለፍ የሚገደድበት ውል ነው” ይላል፡፡
በተቋማችን የብድር ውል ለመዋዋል ሁለቱም ወገኖች ሊያሟላቸው የሚገባቸውን ዝርዝር ቅድመ ሁኔታዎች ከዚህ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
. በተቋሙ የDARIS ስርዓት የተዘጋጀ ሰነድና የአገልግሎት ቁጥር፤
. ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጫ ሰነድ፤
. የተዋዋዮች በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤
. የተዋዋዮች የጋብቻ ማስረጃ ወይም የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፤
. ተበዳሪው የንግድ ማህበር ከሆነ መመስረቻ ጽሑፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ የንግድ ዋና ምዝገባ እና እንደ አስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባኤ፤
. ገንዘቡ የተላለፈበት (የባንክ ስቴትመንት ስሊፕ) እና የባንክ ደብዳቤ፤
. በተቋማችን ተገልጋዮች ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ ለአገልግሎቱ የሚወስደው ጊዜ 30 ደቂቃ ነው፡፡
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ( share ) በማድረግ ብልሹ አሰራር እና ሙስናን ይከላከሉ፡፡

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
#የሚንቀሳቀስ ወይንም የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውል

“የመያዣ ውል ማለት አንድ ባለዕዳ በባለገንዘቡ በኩል የሚገባውን ግዴታ ለመፈጸም መቻሉን ለማረጋገጥ መያዣ ተብሎ የሚጠራውን ዕቃ ለመስጠት የሚገደድበት ውል ነው፡፡” በማለት በፍ/ብ ቁ. 2825 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

“ዋስትና የተሰጠበት ግዴታ ከፍተኛው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ በማንኛቸውም ሁኔታ ቢሆን በግልጽ ተጠንቅቆ በመያዣው ውል ውስጥ መመልከት ይገባዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ውሉ ፈራሽ ይሆናል” በማለት በፍ/ብ. ቁ 2828(1) ተጠቅሷል፡፡

“የመያዣው ውል ከ500 ብር በላይ የሆነ እንደሆነ ውሉ በጽሁፍ ካልተደረገና ይኸውም ጽሁፍ እርግጠኛ ቀን ካገኘበት ዘመን ጀምሮ ካልሆነ በቀር አይጸናም፡፡ ይላል፡፡” በፍ/ብ. ቁ 2828 (2)፡፡

“የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣን የሚያቋቁም ውል ወይም ህጋዊ ሰነድ በጽሁፍ ካልተደረገ በቀር ዋጋ የለውም፡፡ በማለት በፍ/ብ.ቁ 3045 (1) ላይ ተጠቅሷል፡፡
በፍ/ብ. ቁ 3045 (2) መሰረት መያዣ የተሰጠበት ገንዘብ ልክ በኢትዮጵያ ገንዘብ ካልተመለከተ በቀር ፈራሽ ነው ::

የመያዣ ውል ለመዋዋል ወደ መስሪያ ቤታችን ሲመጡ ተገልጋዮች ማሟላት ያለባቸው ጉዳዮች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
.በተቋሙ የDARIS ስርዓት የተዘጋጀ የአገልግሎት ቁጥር

.የተዋዋዮ በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤

.የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሆነ ሁለት የሰው ምስክሮችና መታወቂያ፤
.ተዋዋዮች ከህግ / ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጫ ሰነድ፤
.የተዋዋዮች የጋብቻ ማስረጃ ወይም የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፤

.በመያዣነት የቀረበው ንብረት የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ፤
.የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፤ መተዳደሪያ ደንብ እና ቃለጉባኤ እንደአስፈላጊነቱ ዋና የንግድ ምዝገባ፡፡
#አለ_ህግ
የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 - መንግሥት በፉጨት የጠራውን በጅራፍ የገረፈበት ሕግ

“The execution of the laws is more important than the making of them” Thomas Jefferson

“የሕጎች አተገባበር ሕጎቹን ከመደንገግ በላይ አጅግ አስፈላጊ ነው”

“ይህ ጽሑፍ በሕግ ትምህርት ዘርፍ በተለይም በውል ሕግ ዙሪያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉት ዛሬም በሕግ ሥርዓቱ መሻሻል ላይ አሻራቸውን እያኖሩ ላሉት ለፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ ትንሽ ምስጋና ትሁንልኝ”

ዛሬም ያልተላቀቅነው እርግማን ነው፡፡ ትውልድ ቢቀያየርም፤ መሪ ቢለዋወጥም፤ ዓለም ብትሰለጥንም፤ ዕውቀት ቢገባንም፤---ትላንት ታሪካችን ነበር፡፡ “የኢትዮጵያ ታሪክ” ብለው በልጅ አዕምሮ ያስተማሩንም ይህንኑ ነው….‘የእርስ በእርስ ጦርነት’፡፡ዛሬም ይህ ትውልድም ይህን እርግማን ዕውቀት አድርጎት እርስ በእርሱ እየተገዳደለ የራሱን ታሪክን በመጻፍ ላይ ነው፡፡ የኢፌዲሪ መንግሥትም “የሕግ ማስከበር ዘመቻ” ብሎ ለጠራው ለዚህ ጦርነት “ወንዱን ትጥቅ ሴቷን ስንቅ” ይዛችሁ ውጡ ብሎ አስቸኳይ አዋጅ በነጋሪት ጎስሞ ከድሉ መልስ በጦርነቱ ጊዜ ለተጠቀምብክበት ትጥቅ ፍቃድ የለህም ብሎ ታህሳስ 30 ቀን 2012ዓ.ም ባወጣው የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በሕግ ጅራፍ ህዝቡን ዛሬም እየገረፈ ነው ብልህ---ምላሽህ እንደ ገብረሕይወት ባይከዳኝ “ጃንሆይ ይህን ህዝብ ግን እንደራስዎ ህዝብ ያዩታል?” የሚለው ጥያቄ አይሆንም ወዳጄ? ተከተለኝማ ነገሩን ልዝለቅህ…



1. መነሻ ምክንያት

አንድ

የፌደራል ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ ላይ በጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም የጦር መሣሪያ ፍቃድ ሳይኖረው 16 ጥይትና 01 ካርታ ይዞ በመገኘቱ የጦር መሣሪያ አስተዳደር ቁጥጥር አዎጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 4/1/ እና 22/3/ ተላልፎል የሚል በማቅረቡ ነው፡፡ ተከሳሹ የተከሰሱባቸው መሣሪያዎች አስቀድመው ከያዙትና ፍቃድ ካላቸው መሣሪያዎች በተጨማሪ ነው፡፡

ሁለት

መንግሥት በህልውናው ዘመቻ ጊዜ ያወጣሁን ልዩ መመሪያ ተከትሎ የያዘውን ሽጉጥና 1 ጥይት አስመዝገቦ በዘመቻው ከተሳተፈ በኃላ ዘመቻው ሲጠናቀቅ ግለሰቡን ተከሳሽ በማድረግ ከሳሽ በየካቲት 7 ቀን 2014ዓ.ም የጦር መሣሪያ ፍቃድ ሳይኖረው 1 ጥይትና አንድ ሽጉጥ ይዞ በመገኘቱ የጦር መሣሪያ አስተዳደር ቁጥጥር አዎጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 4/1/ እና 22/3/ ተላልፎል የሚል ክስ በፌደራል ዐቃቤ-ሕግ የቀረበባቸው መሆኑ ነው፡፡

2. የጦር መሣሪያ አስተዳደር ቁጥጥር አዎጅ ቁጥር 1177/2012 የአተገባበር አድማስ

ይህ የጦር መሣሪያ አስተዳደር ቁጥጥር አዎጅ በአንቀጽ ቁጥር 29 ላይ ከታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆንና የደነገገ ቢሆንም በመሸጋገሪያው ድንጋጌ በሆነው አንቀጽ ቁጥር 23(1) ላይ ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት መሣሪያ የያዙና ለያዙት የጦር መሣሪያ ፍቃድ የመያዝና የመጠቀም ፍቃድ ያላቸው ሰዎች በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ተቆጣጣሪው ተቋም በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ ቀርበው ፍቃድ የመጠየቅና በአዎጁ የተመለከቱትን መስፈርቶችን አሟልተው ከተቆጣጣሪው ተቋም ፍቃድ መውሰድ እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡
እንደዚሁም ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት ፍቃድ ሳይሰጣቸው ግን ደግሞ የጦር መሣሪያ የያዙ ሰዎች ደግሞ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተቆጣጣሪው ተቋም በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ ቀርበው ፍቃድ የመጠየቅና በአዎጁ የተመለከቱትን መስፈርቶችን አሟልተው ከተቆጣጣሪው ተቋም ፍቃድ መውሰድ እንዳለባቸው በአንቀጽ ቁጥር 23(2) ላይ ተደንግጓል፡፡
በመሆኑም አስቀድሞ በነበረው የሕግ አሰራር የጸና ፍቃድ ያላቸው ግለሰቦች በአንቀጽ 23(1) መሰረት ቀርበው አዲስ ፍቃድ ለማውጣት የሁለት ዓመታት ማለትም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2014ዓ.ም ጊዜ ድረስ አላቸው፡፡
እንደዚሁም አስቀድሞ በነበረው አሰራር ፍቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሣሪያ የያዙ ሰዎች ደግሞ የአንድ ዓመት ማለትም እስከ ታኀሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ፍቃድ የማውጣት መብት በሕጉ ተሰጥቷቸዋል፡፡
በተለይም የጦር መሣሪያ የያዙ ግለሰቦች ከላይ የተመለከተውን ግዴታቸውን እንዲወጡ አዲስ ፍቃድ እንዲያወጡ የጊዜ ሰሌዳ የማስቀመጥ ግዴታ በተቆጣጣሪው ተቋም ላይ ተጥሏል። ዳሩ ግን ተቋጣጣሪ ተቋሙ የጊዜ ሰሌዳ አላወጣም። በዚህም ተቋሙ ይህን መንግሥታዊ ግዴታውን አልተወጣም። ስለዚህ የማስመዝገቢያ ጊዜ ባላለፈበት፣ መመሪያና የጊዜ ሠሌዳ ባልወጠዓበት ሁኔታ ግለሰቦችን ተፈጻሚ ሊደረግ የማይገባባቸውን የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2012ን መሠረት በማድረግ ምንም ዓይነት ክስ ሊቀርብ አይገባም።
ነገር ግን ዛሬም እራሱ መንግሥት ላልተወጣው ግዴታ ግለሰቦችን እየቀጣ ነው፡፡ ፍ/ቤቶችም እንደ ሦስተኛ የመንግሥት አካልነታቸውና ሌሎች የመንግሥት አካል የሆኑትን ሕግ አውጪና ሕግ አስፈጻሚ በcheck & balance ስልጣናቸው መቆጣጠርና ይህ አለመተግበሩን በመከታተል ግለሰቦችን ነጻ ሊያደርግ ሲገባው ሕጉን እንደ ወረደ በመተግበር የአስፈጻሚው አካል ጅራፍ የሚጮህበት ሜዳ መሆናቸው ሊቀር ይገባል፡፡
3. ልዩ ሁኔታ

የጸና ፍቃድ የሌላቸው የጦር መሣሪያዎችን ሁሉ በአዲስ ምዝገባ ህጋዊ ለማድረግ መመሪያ የወጣ ስለመሆኑ

ሀገራችን የነበረችበትን ህልውና የማስከበር የጦርነት ዘመቻን ተከትሎ መንግሥት ማንኛውም ሰው የጸና ፍቃድ ባይኖረውም የጦር መሣሪያ የያዘ በሙሉ ይህን የጦር መሣሪያ እንዲያስመዘግብና አስቀድሞ ያለፍቃድ በመያዙም የወንጀል ተግባር ተደርጎ እንደማይቆጠር የሚገልጽ መምሪያ ወጥቶ ተግባራዊ ሲደደረግ ነበር፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም የወንጀል ሕግን አስመልክቶ የሚወጣ ሕግና መመሪያ ለተከሳሹ ጥቅም የሚሰጥ ከሆነ ወደኃላ በመሄድ ተፈጻሚ ሊሆን የሚገባው ስለመሆኑ የሚደነግግው የወንጀል ሕጉ አንቀጽ ቁጥር 5(3) እና ኢትዮጵያ ያጸደቀችሁ ዓለምአቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብት የቃልኪዳን ሰነድ አንቀጽ ቁጥር 9(4) አንዱና ዋናው የሕጉ መርህ ነው፡፡
በመሆኑም ይህ ልዩ የመንግሥት የዘመቻ ጥሪና መመሪያ ያለፍቃድ የጦር መሣሪያ መያዝን አስመልክቶ በጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2012 መሰረት ክስ የቀረበባቸውን እና ጉዳያቸው በፖሊስ በምርመራ ላይ ያሉ ጉዳዮችን ሁሉ ወንጀልነታቸውን ያስቀረ በመሆኑ ይህ ልዩ መመሪያ በስራ ላይ በነበረ ጊዜና ከዚያ በፊት በነበሩ ጉዳዮች ላይ አዎጅ ቁጥር 1177/2012 ተፈጻሚነት የለውም፡፡
4. ትግበራ

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆኑኝን ምክንያቶች በግል የገጠሙኝ ጉዳዮች ሲሆኑ በትግበራ ላይ ያለውን ሂደት ለመጠቆም የሚረዱ ከመሆኑ ባሻገር አጠቃላይ ስለአተገባሩ መደምደሚያ ላይ ልንደርስባቸው የሚገቡ አይደሉም፡፡ በመሆኑም እናንተም የገጠማችሀን ጨምራችሁበት በዕውቀት ብርህን ይበልጥ እንድንቀራረብና ወጥ እና ታማኝ የሆነ የፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ የበኩላችንን እንድናዋጣ አደራ እላለሁ፡፡

አመሰግናለሁ! Dagim Assefa source Abyssinia Law blog , Apr 20 2022
የድምፅ ብክለት
#አለ_ህግ
የድምፅ ብክለት ክልከላ ባለቤቱ ስራውን የሚፈፅመው በራሱ ንብረት ወይም ቤት ውስጥ ቢሆንም ድርጊቱ ሌላውን ጎረቤት እንዳይረብሽ፣ እንዳያውክ፣ ወይም ችግር እንዳያስከትል በማድረግ መብቱን ይጠቀም ዘንድ ህጉ ያበጀው የባለቤትነት መብት አጠቃቀምን አድማስ የሚወስን ስርዓት መሆኑን ከአንቀፅ 1226 እና ተከታዬቹ ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።
ይህን ችግር ለማስወገድ የሚቀርበው አቤቱታ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1149 ስር ከተመለከተው በይዞታ ላይ ሁከት መፍጠር ተግባር የሚለይ ሲሆን አንዴ የተፈጠረ የድምፅ ብክለት እንዲቀጥል የሚደረግበት አግባብ ስለሌለ በይርጋ የሚታገድ አይደለም።
ANRS justice professional trainings and Legal research institute.
Safaricom Telecommunications Ethiopia PLC ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Position :Liaison Officer (Dire Dawa)

የትምህርትዓይነትእናደረጃ:-
Bachelor’s Degree in Political Science/ Law/👍👇

🇪🇹 የስራ ቦታ፡ ድሬደዋ

🧭የምዝገባ ጊዜ /Deadline/: እስከ ሚያዚያ 29 /2014 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://jobs.amazonethiopia.com/job/liaison-officer-dire-dawa/
#አለ_ህግ #አለ_ስራ
የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዎጅ ቁጥር 1177/2012፡ መንግስት በፉጨት የጠራውን በጅራፍ የገረፈበት ሕግ

በ፡ ዳግም አሠፋ

ይህ ጽሑፍ የጦር መሣሪያ አስተዳደር ቁጥጥር አዎጅ ቁጥር 1177/2012 የአተገባበር አድማስን ከሁኔታዎች ጋር ያገናዝባል።
መልካም ንባብ!

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2030-firearm-administration-and-control-proclamation-of-ethiopia
#የሚንቀሳቀስ ወይንም የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውል

“የመያዣ ውል ማለት አንድ ባለዕዳ በባለገንዘቡ በኩል የሚገባውን ግዴታ ለመፈጸም መቻሉን ለማረጋገጥ መያዣ ተብሎ የሚጠራውን ዕቃ ለመስጠት የሚገደድበት ውል ነው፡፡” በማለት በፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2825 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

“ዋስትና የተሰጠበት ግዴታ ከፍተኛው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ በማንኛቸውም ሁኔታ ቢሆን በግልጽ ተጠንቅቆ በመያዣው ውል ውስጥ መመልከት ይገባዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ውሉ ፈራሽ ይሆናል” በማለት በፍ/ብ. ቁ 2828(1) ተጠቅሷል፡፡

“የመያዣው ውል ከ500 የኢትዮጵያ ብር በላይ የሆነ እንደሆነ ውሉ በጽሁፍ ካልተደረገና ይኸውም ጽሁፍ እርግጠኛ ቀን ካገኘበት ዘመን ጀምሮ ካልሆነ በቀር አይጸናም፡፡ ይላል፡፡” በፍ/ብ. ቁ 2828 (2)፡፡

“የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣን የሚያቋቁም ውል ወይም ህጋዊ ሰነድ በጽሁፍ ካልተደረገ በቀር ዋጋ የለውም፡፡ በማለት በፍ/ብ.ቁ 3045 (1) ላይ ተጠቅሷል፡፡

በፍ/ብ. ቁ 3045 (2) መሰረት መያዣ የተሰጠበት ገንዘብ ልክ በኢትዮጵያ ገንዘብ ካልተመለከተ በቀር ፈራሽ ነው ::

በዚህም መሰረት በፍ/ብ. ቁ 2825 እና 3041 መሠረት የመያዣ ውል ለመዋዋል ወደ መስሪያ ቤታችን ሲመጡ ተገልጋዮች ማሟላት ያለባቸው ጉዳዮች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡

.በተቋሙ የDARIS ስርዓት የተዘጋጀ ሰነድና የአገልግሎት ቁጥር

.የተዋዋዮ በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤

.የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሆነ ሁለት የሰው ምስክሮችና መታወቂያ፤

.ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጫ ሰነድ፤

.የተዋዋዮች የጋብቻ ማስረጃ ወይም የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፤

.በመያዣነት የቀረበው ንብረት የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ፤

.የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፤ መተዳደሪያ ደንብ እና ቃለጉባኤ እንደአስፈላጊነቱ ዋና የንግድ ምዝገባ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተገልጋዮች የተባሉትን ነገሮች አሟልተው ሲቀርቡ ለዚህ አገልግሎት የሚወስደው ጊዜ 25 ደቂቃ ነው፡፡

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
Organization for the Development of Women And Children in Ethiopia ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Position:- Invitation for Consultancy

📚ትምህርትዓይነትእናደረጃ:- SRH and national level AY SRH strategy and related policies and laws and manage the tasks detailed in the TOR.

🇪🇹 የስራ ቦታ ፡- AddisAbaba

🧭የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ ሚያዚያ 28/2014 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://bit.ly/37PaLCg
------------------------------------------------
#Mekdela Amba Univeristy#

▪️Required No - 72 positions 0 EXP
▪️Professions - Accounting, Agro forestry, Anthropology,Basketball, Biology Teacher,Biotechnology,ChemistryTeacher,Civics,Computer Science,software engineering,Economics,English Teacher,Environmental-Science,finance management,Forest science,Forestry,Geography,Geology,Handball,Inform- Technology,International-relations, language and literature,
law, management,marketing, mathenatics, microbiology,natural resource management,physics teacher,political science,psychology,sport medicine,sport-science,surveying, volleyball
▪️Find More Details Here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3vJIu7Y

▪️ Deadline: May 06 /2022
Ethiopian Women Lawyers Association(EWLA) ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Position :- Legal Officer

የትምህርት ዓይነት እና ደረጃ:-
BA/MA Degree in Law and Human Right/optional

🇪🇹 የስራ ቦታ ፡ አፋር

🧭የምዝገባ ጊዜ /Deadline/: እስከ ሚያዚያ 28 /2014 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://jobs.amazonethiopia.com/job/legal-officer-3/

🔰ወደፊት የምናወጣቸው የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎች በፍጥነት እንዲደርስዎ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ይወዳጁ!
ቴሌግራም: https://t.me/Lawsocieties
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
#የውል ማሻሻያ

ተዋዋይ ወገኖች በተለያየ ጊዜና በተለያዩ ምክንያቶች ለህግና ለሞራል ተቃራኒ ካልሆነ፣ ሊተገበር የሚችል ከሆነ እና ተያያዥ ምክንያቶች ቀድሞ የነበረው ውል በመለወጥ ማሻሻል ይችላሉ፡፡
መረጃውን ለሌሎች እንዲደርስ በማድረግ ተቋሙ አላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት እንዲሁም ብልሹ አሰራር ለማስቀረት እያደረገ ያለውን ጥረት ያግዙ ፡፡
በመሆኑም ተዋዋይ ወገኖች ውል ለማሻሻል ወደመስሪያቤታችን ሲመጡ ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡


. በተቋሙ የDARIS ስርዓት የተዘጋጀ እና የሚሞላ ሰነድ ወይም የአገልግሎት ቁጥር፤
• ቀደም ሲል የተመዘገበው ወይም የሚሻሻለው የውል ሰነድ፤
• ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን(ውክልና) ፤
• የተዋዋዮች ጊዜው ያላለፈበት ወይም በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤
• ውሉ የሚሻሻለው የማይንቀሳቀስ ንብረት ማስተላለፍ ውልን በሚመለከት ሲሆን ሁለት ምስክሮች ፤
• የተዋዋዮች ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፣
• የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ እና ቀደም ሲል የተመዘገበው ወይም የሚሻሻለው ቃለ-ጉባኤ ወይም የውል ሰነድ፤
ተገልጋዮች ከላይ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች(መረጃዎች) ሙሉ በሙሉ አሟልተው ሲመጡ ውሉን ለማጠናቀቅ 25 ደቂቃ ብቻ ነው፡፡
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
#Abyssinia Bank#🚩For Fresh Graduates

▪️1 -Trainee Legal
▪️2 - Trainee Agricultural Engineer
▪️Find More Details Here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3rJXYYn

▪️ Deadline: April 29 /2022

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties