አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ቅድመ-ክስ
******
የቅድመ - ክስ እስራት አስመልክቶ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ፕወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የማጠቃለያ ንግግር አድርገዋል፡፡
የንግግሩን ሙሉ ቃል ከፍርድ ቤቱ ድረ-ገጽ ከዚህ በታች በተገለጸ መስፈንጠሪያ ያገኙታል፡፡

https://www.fsc.gov.et/News-Media/Services-for-Media-/Speeches/%e1%8b%a8%e1%89%85%e1%8b%b5%e1%88%98-%e1%8a%ad%e1%88%b5-%e1%8a%a5%e1%88%b5%e1%88%ab%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%88%98%e1%88%8d%e1%8a%ad%e1%89%b6-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8b%b0%e1%88%a8%e1%8c%88-%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%8c%8d%e1%88%ad
Urgent press statement by AHRE
የወንጀል አፈጻጸም ደረጃ
#አለ_ህግ
መግቢያ

የወንጀል አፈጻጸም ደረጃን ስናነሳ ወንጀልን ለማቋቋም ከሚያስፈልጉት ሶስቱ ፍሬ ነገሮች አንዱ የሆነውን ግዙፋዊ ፍሬ ነገርን እናነሳለን፡፡ በመሆኑም አንድን ስው በወንጀል ጥፋተኛ ነው ለማለት አንድ የፈጸመው ማድረግ ወይም አለማድረግ (ድርጊት) መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ወደ ወንጀል አፈጻጸም ደረጃዎች ስንምጣ በቀጥታ እያነሳን ያለነው ይህ ያማድረግ ወይም ያለማድረግ ድርጊት በምን ያህል ደረጃ ተፈጽሟል የሚለው ጉዳይ ነው፡፡አንድ ወንጀል ፈጻሚ አንድ ውጤት ለማግኘት ሊፈጽመው የሚችለው ማድረግ ወይም አለማድረግ ይኖራል፡፡በተለያዩ ምክንያቶች ወንጀል አድርጊው ድርጊቱን ጀምሮ ሳይጨርስ መቅረቱ የሚፈልገውን ውጤት ላያገኝ ይችላል፡፡ይህም የሚያሳያው የወንጀል ድርጊቱ የተለያዩ የአፈጻጸም ደረጃዎች እንዳሉት ነው፡፡ሆኖም በሕግ አስተምሮች አንድ የወንጀል ድርጊት ግዙፋዊ ፍሬ ነገሩ ተሟልቷል ፤ሰለሆነም ወንጀል ተፈጽሟል የምንልበት የድርጊት አፈጻጸም ምን ደረጃ ላይ ሲደርስ ነው የሚለው ቡዙ ጊዜ አከራካሪ ጉዳይ ነው፡፡በመሆኑም በተለይም ባልተጠናቀቁ ድርጊቶች ወንጀል አድራጊው ይህን በማድረጉ ወንጀሉን ለመፈጸም መወሰኑን ያሳያል፡ይህንን ማድረጉ ወንጀል ለማድረግ መወሰኑን አያሳይም ለማለት የሚቻልበት ድንበርን ለማስቀመጥ ያስቸግራል፡፡ምክንያታዊ በሆነ ሰው እይታ እንደ ወንጀሉ አፈጻጻም በህሪ ተጠርጣሪው ያደረገው ድርጊት ወንጀል ለመፈጸም መወሰኑን ማረጋገጥ የሚቻልበት ደረጃ የደረሰ ከሆነ ግዙፋዊ ፍሬ ነገሩ እንደተሟላ ለመቁጠር እና ፋጻሚውንም ጥፋተኛ ለማለት ይቻላል፡፡በኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ የታወቁት ወንጀል አፈጻጸም ደረጃዎችን እንደሚከተለው ለማየት ተሞክሯል፡፡

የማሰናዳት ተግባሮች

በወንጅል አፈጻጻም ደራጃዎች መካከል የማሰናዳት ተግናር አንዱ ሲሆን በዚህ ራገድ ሚነሳው ጥያቄ አንድ ሰው ወንጅል ለመፈጸም መሰናዳቱ በወንጅል ያስቀጣዋል ወይንስ አያስቀጣውም የሚል ነው፡፡ የወንጅል ህጉ አንቀጽ 26 ስር የወንጀልን ድርጊት ለማሰናዳት ወይም ለማመቻቸት በተለይም መሳራዎችን በማሰባበሰብ ወይም ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የተደረጉ ድርጊቶች አያስቀጡም በማለት ደንግጎ ይገኛል፡፡ ምክንያቱም የወንጀል ህጉ የሚቀጣው የሰውን ሀሳብ እና ድረጊትን በመሆኑ ሀሳብ በድርጊት እስካልተገለጸ የፈጻሚውን የሀሳብ ክፍል ለማወቅ አይቻልም፡፡ ሀሳቡ ምን እንደነበረ ማወቅ የሚቻል ቢሆንም በተግባር እስካልተገለጸ ድረስ በመሐበረሰቡ ዘንድ ሊፈጥረው ያሚችል አንድም ችግር ሊኖር ስለማይችል ፤ በድርጊቱ ጥፋት ሲያስከትል እንጂ ሀሳብን ብቻውን መቅጣት አይቻልም፡፡በአጠቃላይ ሰዎች ምን እያሰቡ እንደሆነ ባለመታወቁ ብች ሳይሆን ቢታወቅም እንኳን ይህንኑ ሀሳባቸውን ወደ ተግባር ሚይቀይሩት መሆኑን እርገጠኛ ለመሆን አይቻልም፡፡

በመሆኑም የማሰናዳት ትግበሮች በወንጅል አያስቀጡም ነገር ግን ፡-

1ኛ ራሳቸው ወንጀል ሆነው ሚያስቀጡ መሆናቸው በህግ የተደነገገ እንደሆነ

ለምሳሌ አንድ ሰው ሰውን ለመግደል በማስብ በህግ ወጥ መንገድ መሳሪያ ገዝቶ የመሰነዳት ተግበር ሲፈጸም ቢገኝ ይህ ሰው ምንም እንኳን መሳሪውን የገዛው ሰውን ለመግደል ቢሆንም ሰውን ለመግደል በመሰናደት ተግበር ሳይሆን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ያሚጠየቅ ይሆናል፡፡

2ኛ ከወንጀሎቹ ከባድነት እና በአጠቃላይ ከሚያደርሱት አደጋ መጠን የተነሳ ልዩ ወንጀል መሆናቸው በህግ በግልጽ የተደነገገ እንደሆነ

አንዳንድ ወንጀሎች ቢፈጸሙ ከፍተኛ ጉዳት በሰው እና በንብረት ላይ ሊያደርሱ ያሚችሉ በመሆናቸው እኝህን ወንጀሎች ለመፈጸም መሰናደት በረሱ ያሚያስቀጡ ሲሆን፤ ይህም እንዚህን ወንጀሎች ለመደንግግ በወጣው ህግ ላይ እኝህን ወንጀሎች ለመፈጸም መሰናደት በራሱ እንደሚያሰቀጡ በህጉ ላይ ተደንግጎ በሚገኝበት ጊዜ ነው፡፡ በአገራችን ህጎች የሽብር ወንጅል ለመፈጸም መሰናዳት ፤ በአገር እና በህግ መንግስታዊ ስረዓቱ ላይ ፤በአገር መከላከያ ላይ ወንጀል ለመፈጸም መሰናዳት በወንጀል የሚያስቀጣ ናቸው በማለት በህጉ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ሙከራ

ሙከራ አንድን ወንጀል ለመፈጸም የወንጀል ድርጊቱ በቀጥታ የተጀመረ እና ለወንጀሉ ውጤትም የተጠጋ ተግባር ነው፡፡ በወንጀል ህግ አንቀጽ 27 /1 መሰረት ማናም ሰው አሰቦ ወንጀልን ለማድረግ ጀምሮ የወንጀሉን ድርጊት እስከ መጨረሻ ያልተከተለ ወይም ለመከተል ያልቻለ ወይም የወንጀል ድርጊት እንዲፈጸም እስከ መጨረሻው ተከትሎ አስፈላጊ የሆነውን ውጤት ያላገኘ ቢሆንም በመሞከሩ ብቻ ጥፋተኛ ይሆናል በማለት በህጉ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ከህጉ ድንጋጌ እንደምንረደው

 ሙከራ በሙሉ ሀሳብ የሚፈጸም መሆኑ ፡-ከድንጋጌው ይዘት እንደምንረዳው ምንግዜም ቢሆን ሙከራ ተደርጓል ለማለት የድርጊቱ አድራጊ ወንጀሉን ያደረገው ይህንኑ ድርጊት አስቀድሞ ለመፈጸም በማሰብ እንደሆነ ለመረዳት ይቻላል፡፡
 የወንጀል ድርጊቱ መጀመር ያለበት መሆኑ ፡- አንድ ሰው ወንጀል ለመፈጸም መሰናዶ ከደረገ በኋላ ወንጀሉን የሚፈጽምበት ሁኔታ ሲሆን የወንጀል ድርጊቱ ምንም እንኳን በተለያዩ ምክንያቶችን ፍጻሜውን ባያገኝም ነገር ግን ያወንጀል ድርጊቱን መፈጸም መጀመር ያሙከራ ወንጀል መፈጸሙን ያሚያሰይ እና እንዲሁም ያሚያስቀጣ መሆኑን ያመለክታል ፡፡
 እስከ መጨረሻው ለመከታተል ያለመቻል ፡- አንድ ወንጀል ፈጻሚ ያወንጀል ድርጊቱን ጀምሮ ነግር ግን ያሰበውን ውጤት ለመግኘት እስከ መጨረሻው ለመከተል በውስጣዊ እና በውጫዊ ምክንያቶች ያልቻለ ሰሆን ፡፡
ውጫዊ ምክንያቶች-ከፈጻሚው ቁጥጥር ውጪ በሆኑ ምክንያቶች የወንጀል ድርጊቱን እሰከ መጨረሻው መከተል ሳይችል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ፈጻሚው ወንጀሉን ሊፈጽምበት የተጠቀመው መሳሪያ እምቢ ሲለው ፤ተጎጂው እራሱን ቢከላክል ፤ቢያመልጥ ወይም ፖሊስ ደርሶ ፈጻሚውን ቢይዘው የወንጀል ድርጊቱን እሰከ መጨረሻው መከተል እንዳይችል ያሚያረጉት ውጫዊ ምክንያቶች ናቸው፡፡
ውስጣዊ ምክንያቶች-ፈጻሚው የወንጀል ድርጊቱን ለመፈጸም የጀመረውን ድርጊት በራሱ ውስጣዊ ምክንያት ወንጀል መፈጸሙን ሲተው ነው፡፡ይም በመጸጸት ፤በመፍራት ፤ወይም በማዘን ድርጊቱን ሳይፈጸም ቢቀር ሊሆን ይችላል፡፡
 የታሰበው ውጤት ያለመገኘት ፡-በወንጅል ህጉ አንቀጽ 27 መሰረት የሙከራ ወንጀል ታሰበው ውጤት ያልተገኘ መሆን አለበት፡፡በመሆኑ የግዙፋዊነት ፍሬ (ድርጊቱን መፈጸም ያለመፈጸም ) ነገሩ መሟላቱን አስፈላጊ አይሆንም፡፡ይልቁንም ፈጻሚው እስከ ቻለው ድረስ የሰራቸው ድርጊቶች ግዙፍነት ያላቸው ፍሬ ነገሮች እንደሆኑ ያሚቆጠሩ ናቸው፡፡ታስቦ ያሚፈጸም ድርጊት አለ፡፡ድርጊቱ ውጤት ፋጻሚው ባሰበው መልኩ እስካል ሆነ ድረስ ወንጀሉ እንደተፈጸመ የሚቆጠረው በሙከራ ደረጃ ነው፡፡ሆኖም የወንጀል ድርጊቱ የታሰበውን ውጤት ያስገኘ ሲሆን ሙከራነቱ ይቀራል፡፡
 ሙከራ ሁል ጊዜ የሚያስቀጣ ስለመሆኑ

በወንጅል ህግ አንቀጽ 27/2 መሰራት ሙከራ ያሚያስቀጣ ሲሆን የህጉ ድንጋጌም ፡-

በህጉ ላይ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር የወንጀል ሙከራ ሁልግዜም የሚያስቀጣ ነው፡፡ለወንጀል ድርጊት የማነሳሳት ወይም የአባሪነት ሙከራ በህግ ተገልጾ ያስቀጣል ተብሎ ካልተደነገገ በቀር አያስቀጣም በማለት በህጉ ተደንግጎ ይገኛል ፡፡
ከዚህ የህግ ድንጋጌ እንደምንረዳው ወንጀል አድርጊው የወንጀል ድርጊቱን ውጤት በተፈለገው ሙከራ ባያገኝም እንኳን በመሞከሩ በራሱ ያሚቀጣ ይሆናል፡፡የተሳበውን ውጤት ስላልተገኘ በወንጀል ልቀጣ አልችልም በማለት እንደ መቃወሚያ ሊያነሳ እንደማይችል ለመገናዘብ ይቻላል፡፡ይህ ሁኔታ የሚያሳየው የወንጀል ህግ ግብ የወንጀለኛውን ሀሳብ መቅጣት እንጂ ድርጊቱን የመቅጣት አለማ እንዳሌለው ለመረዳት ይቻላል፡፡በአጠቃላይ ሙከራ ያሚያስቀጣው በሙከራ ድርጊቱ ጥፋት በመድረሱ ምክንያት ይህንኑ ለመከላከል ብቻ ሳይሆን የፈጻሚውን አደገኛ አስተሳስብ ለመከላከል መሆኑን ለመረዳት ይቻላል፡፡

ሙከራና ቅጣት

በወንጀል ህጉ አንቀጽ 27/3 ስር የወንጀል ድርጊት በመሞከሩ አድራጊው በመደቡ ለመፈጸም በፈለገው ቅጣት ይቀጣል በማለት ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ከህጉ ድንጋጌ እንደምንረዳው የወንጀል ድርጊት መሞከርም ሆነ ወንጀሉን አጠናቆ በፈጸመው ሰው መካከል የሚደረግ የቅጣት ልዩነት አለመኖሩን ነው፡፡

ነገር ግን ፍርድ ቤት ቅጣት ሲወስን እንኚህን ሶስት ጉዳዮች ማየት ይገባዋል

1ኛ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 117 እንደተደነገገው የወንጀል ድርጊቱ እጅግ ከባድ በመሆኑ በሞት የሚያስቀጣ እንደ ሆነ ይህ የወንጀል ድርጊት ፍጻሜ ያገኘ ሙሉ ውጤት የተገኘበት ወንጀል ድርጊት መሆን አለበት፡፡ ማንኛውም የወንጀል ሙከራ በሞት ቅጣት እንደማያስቀጣ ከህጉ ድንጋጌ ለመረዳት ያስችላል፡፡

2ኛ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 28 ላይ እንደተደነገገው በሙከራ ወንጀል የወንጀል ድርጊት ቅጣትን ከሚያቀሉ ምክንያቶች አንዱ መተው እና መጸጸት ነው፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት አድራጊው የነበረውን የወንጀል ድርጊት በገዛ ፍቃዱ የተወ እንደሆነ ፤ የነገሩ ሁኔታዎች የሚገቡ ምክንያቶች ሲያገኝ ፍርድ ቤት በህግ በተፈቀደለት ወሰን መሰረት ቅጣቱን ሊያቀል እንደሚችል በህጉ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

3ኛ ሊፈጸም የማይቻል ወንጀል በሙከራ ደረጃ ከቀረ ቅጣቱን የሚያቀል ይሆናል፡፡ በማንኛውም ዘዴና መሳሪያ ወይም በማንኛውም ነገር ላይ ምንም ቢሆን ሊፈጸም የማይችል ወንጀልን ለማድርግ ለሞከረ ሰው ፍርድ ቤቱ እንደመሰለው ቅጣቱን ያቀልለታል፡፡በወንጀል ህጉ አንቀጽ 29 ላይ እንደተደነገገው አድራጊው ጉዳት ለማድረስ በማንኛውም ዘዴ ወይም መሳሪያ፤ በአምልኮ ስራ፤ በሞኝነት ወይም በመንፈስ ልልነት የወንጀል ድርጊት ሙከራ ባደረገ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ከቅጣት ነጻ ያደርገዋል በማለት በህጉ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳ/ት
በተጨማሪም ድረ-ገጻችንን www.eag.gov.et/am-et/ ይጎብኙ/ይከታተሉ
አዲስ መታወቂያ መስጠት ተቋረጠ
.
የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ላልተወሰነ ጊዜ " አዲስ መታወቂያ " የመስጠት አገልግሎት ማቆሙን አስታውቋል።

ኤጀንሲው የመታወቂያ ፣ የልደት ፣ የጋብቻና የሞት ማስረጃዎችን ይመዘግባል ፤ ዜጎች በሚፈልጉበት ወቅትም አገልግሎቱን ይሰጣል፡፡

በአገልግሎት አሰጣቱ ውስጥ በተለይ የመታወቂያ አገልግሎቱ ላይ በተቋሙ ውስጥ እና ከተቋሙ ውጭ ባሉ ሃሰተኛ ማስረጃን በሚያድሉ ግለሰቦች የተነሳ ለማይገባቸው ሰዎች መታወቂያ አላግባብ እየተሰጠ መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል።

ይህን ህገ ወጥ የሆነ ድርጊት ሲፈጽሙ የተያዙ ግለሰቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን አሳውቋል።

የነዋሪነት መታወቂያ ለማግኘት ሲባል ህገወጥነት እየተባባሰ በመምጣቱ ችግሩን በሚገባ ለማጥራት እንዲቻል በከተማ አስተዳደሩ ደረጃ በተላለፈ ውሳኔ መሰረት አዲስ መታወቂያ እንዳይሰጥ ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱን ኤጀንሲው ገልጿል።

የመታወቂያ እድሳትም ሆነ ሌሎች የወሳኝ ኩነት አገልግሎቶች ባሉበት ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡
አዲስ ቲቪ
አለ_ህግ ✳️ Law Societies✳️
@lawsocieties
#አለ_ህግ#Ale_Hig, ነፃ የህግ የማማከር አገልግሎት፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ክሶች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች 🔴ሁሉንም ሕጎችና ባለሙያዎች እዚሁ ያገኛሉ🔴 All in one, for All. መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው። contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.com
#Share

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #አለ_ስራ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
@lawsocieties
@lawsocieties
እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ! 

የዒድ አልፈጥር በዓል ሰኞ ይውላል።

ዛሬ ጨረቃ ባለመታየቷ ነገ ረመዷን 30 ሆኖ ዒድ አልፈጥር በዓል ሰኞ ሚያዝያ 24 ይሆናል። ኢትዮመረጃ
#አለ_ህግ #Ale_Hig
Join and Share❗️❗️
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
#Wagagen Bank#7 - Position

▪️1 -Archive library
▪️2 -Attorney I❤️
▪️3 -Trade service officer I
▪️4 -District Hr business partner I
▪️5 -Sr Foreign banking & Remmittance Officer
▪️6 - Sr trade service officer
▪️7 - Manager, foreclosure & debt Litigation
▪️Find More Details Here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3vVJy8Y

▪️Deadline - May 07/2022
#Bank of Abyssinia#

▪️1 - Legal Credit.Attorney
▪️2 - Legal Credit.Senior Attorney
▪️3 - Grade I Branch Operation Manager
▪️Find More Details Here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3F7Ibbl

▪️Deadline - May 05/2022
ከደረሰኝ ጋር የተገናኙ ወንጀሎች እና ቅጣታቸው።።።።።።።።።።።።።።።።
#አለ_ህግ #Ale_Hig
I. ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ያለደረሰኝ ግብይት ያከናወነ እንደሆነ ከብር 25ሺ (ሃያ አምስት ሺ ብር) እስከ ብር 50ሺ (ሃምሳ ሺ ብር) የገንዘብ መቀጫ እና ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
II. በአንድ ግብይት በተሰጡ ተመሳሳይ የደረሰኝ ኮፒዎች ላይ የተለያዩ ዋጋዎችን በመመዝገብ የሽያጭ ዋጋን ያሳነሰ ማንኛውም ሰው ብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ከአምስት ዓመት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
III. የሽያጩ ትክክለኛ ዋጋ ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ ከሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (||) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኞቹ ላይ ከተመለከቱት ከፍተኛው የገንዘብ መጠን እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት የሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
IV. ግብይት ሳይፈጸም ደረሰኝ የሰጠ ወይም የተቀበለ ሰው ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
V. በዚህ ተራ ቁጥር (IV) የተመለከተው ደረሰኝ ከብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ የገንዘብ መጠን የያዘ እንደሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (|) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኙ ከተገለጸው የገንዘብ መጠን ጋር እኩል በሆነ የገንዘብ ቅጣት እና ከአስር ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደረስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VI. ባለሥልጣኑ ሳይፈቅድለት የታክስ ደረሰኝ ያተመ ሰው ከብር 300ሺ (ሦስት መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 500ሺ (አምስት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሁለት ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VII. በዚህ ተራ ቁጥር (VI) መሠረት ጥፋተኛ የተባለ ሰው ወንጀሉን ለሁለተኛ ጊዜ ፈጽሞ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ የህትመት መሣሪያው እና የማተሚያ ድርጅቱ ይወረሳል፣ የንግድ ፈቃዱም ይሰረዛል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig
Cost Sharing Directive .pdf
85.8 KB
#አለ_ህግ #Ale_Hig
የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት ክፍያ አሰባሰብ አፈፃፀም መመሪያ
@Lawsocieties
የአሰሪና ሰራተኛ ውል.docx
20.6 KB
የቤተሰብ ውክልና #አለ_ህግ #Ale_Hig

የቤተሰብ ውክልና ፡- መሰረቱ የፍትሃብሔር ህግ አንቀጽ 2203 እና /ወይም 2205 ድንጋጌዎች ሆኖ በፍትሃብሄር ስነ-ስርዓት ህግ አንቀጽ 58 መሰረት ለቅርብ ዘመድ ማለትም ባለቤት፣ወንድም፣እህት፣ልጅ፣አባት፣አያት፣ እናት ለሆኑ ሰዎች የሚሰጥ የውክልና ዓይነት ነው፡፡

ውስን ውክልና

ውስን ውክልና፡- ተወካይ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ንብረቱን በስም እና ዝርዝር መረጃውን በመጥቀስ የውክልና ስልጣን የሚሰጥበት ነው ፡፡
ሙሉ ውክልና

ሙሉ ውክልና፡- ተወካይ አጠቃላይ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረቱን በሚመለከት ዝርዝር መረጃ መስጠት ሳያስፈልገው በጥቅሉ ውክልና የሚሰጥበት ነው፡፡
#አለ_ህግ @Lawsocieties
አዲሱ-የንግድ-ሕግ 55932.pdf
3.4 MB
Share 'አዲሱ-የንግድ-ሕግ 55932.pdf'
በህግ አምላክ ምን ማለት ነው❗️
ቀድሞ በጥሩ ማብራሪያ የመለሰ ሽልማት አለው።
#አለ_ህግ #Ale_Hig